ልጥፎች

አዲስ ቅዱስ ጸበል ከመንፈስ ሲፈልቅ የተዋህዶ ተጋድሎው ሊጋፋው አይገባም።

ምስል
መታመንን መቀበል ግማድ ነው? ግማድ ግን ሃይል ጽናት  መድህን ነው? ቀራንዮ ግማድ ነው ግን ፍቅርን ወለደ።      በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤ አሜን! „ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋዋላ ስለ እኔ እንደ ገና ልታስቡ ጀመራችሁ፣ በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፤  ጊዜ አጣችሁ እንጂ ማሰብ ታስቡ ነበር። ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበትን ኑሮ  ይበቃኛል ማለትን ተምሬያለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ፤ መብዛትንም አውቃለሁ፤   በእያንድንዱ ነገርም በነገር ሁሉ መጥገብን መራብንም መብዛትንና መጉደልን  ተምሬአለሁ፤ ኃይል በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።“ (የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆላስያስ ምእራፍ ፲ ቁጥር ፲፫) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 29.07.2018 ( ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·         አ ቦው ከአብዩ መንፈስ ጋር አገር ቤት ለመግባት ቅድመ ሁኔታ አያስፈልጋቸውም። ደፋር እርምጃ መራራ ነው። ሞትን ለመድፈር ሰምዕትነትን ለመፈቀድ የልብ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። ነገ ለመሄድ ከወስን ስለምን ለነገ ሌላ ቀን ይቀጠርለታል። በዚያች ቅጽበት የፈጠሪ ውሳኔ ካለበት የትም አይቀርም ሞትም ድልም ታሪክም።  ይህ መዋል ገድለ ስለሆነ አድሉን ቅድስት ተዋህዶ ልታጣው አይገባም ባይ ነኝ ይህን የልዩ ትውፊት አዲስ የፊደል ገባታ። ስንዱ የቀደመ መንፈስ ዝግጅቱን አጠናቆ ነው የጠዬቃችሁ፤ ልጃችሁ ይህን ያህል ማይል አቋርጦ ከደጀ ሰላማችሁ ድረስ መጥቶ፤ ወደ አገር ቤት እንደ ታቦት ከብክቦ ሊወስዷችሁ ሲፈቅድ ቅብዕና ነው፤ ቅብዕ ደግሞ ሊገፋ አይገባም፤  ምርቃቱ ከነፈሰበት ...

... ወጣትነት እና እኔ ሳንገናኝ ተላለፍን …

ምስል
ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባቡ ይፈተሽ። (ከስምንት ዓመት በፊት የተፃፈ ለህትምትም የበቃ።) “ አቤቱ፣ በልቤ ውስጥ አመሰግንሃለሁ፣ ታአምራትህንም፡ ሁሉ እናገራለሁ። በአንተ፣ ደስ፡ ይለኛል፣ ሐሤትንም አደርጋለሁ።“ ( መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፱ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) የኔዎቹ ይህ እ.ኢአ. በ2002 ከታተምው “መክሊት” የግጥም መድ ብ ል ላይ ያለነው። ዛሬ ላይ ሳነበው ግርም ብሎኝ ገጹንም ቁጥሩን ከነተፈጥሮ ሳላዛባ ነፃነቱንም ሳልነፍግ፤ ሳድስ ላይ ግድፍት ሁልጊዜ አለብኝ እና እሱን ብቻ አርሜ ለዛሬ ብያለሁኝ። ግጥሞቼን ስከውን ማሳሪጊያ ያደርኩት የወግ ገበታ ነው። እርእሱ  “ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባባቡ” ይፈተሽ ይላል። ይሄ ዛሬም ለጠ/ አብይ አህመድ ካቢኔ የሚያግዝ ዕይታ ጭምር ነው። ያግኙት አያግኙት ጹሁፌን አላውቅም። የወንጌል ጥቅሱም መጸሐፍቴ ሲጀመሩ ሁልጊዜ ወንጌል ስላለበት መግቢያውን እሱን እንዳለ ወስጄዋለሁኝ። በተረፈ መልካም ቆይታ ከ2002 ዕይታዬ ጋር። ያ ዕይታ እና ዛሬ ሃዲድ የመስራት የእናንተው የ እኔዎቹ የውዴቼ ተግባር ይሆናል። ስሜቴን ሰብስቤ ለመጻፍ አቅም አጣሁኝ። ዜግነት በተማላ እንደላ ብቻውን ዘነዘናውነን ቁሞ ይታዬኛል። ዜግነቴ አረፈ ስል በመዲና ላይ በጠራራ ጸሐይ ካለ ጠበቂ፤ ካ ለ አንዳች ጠያቂ እንዲህ ሲሆን ለእኔ መራራ ሃዘን ነው። እኔ መጻፍ አቅቶኝ አያውቅም፤ ልክ ባንቧ ውሃ የመክፈት ያህል ነው። አሁን ግን አልቻልኩም ስለዚህ ነው ወደ ቀደሙት መሄድ ግድ ያለኝ። እንደ ማሰረጊያ …  መክሊተ መጸሐፈ የግጥም ስብሰብን ዕሴት።        ...