ልጥፎች

የልጆች የህይወት ዳገታዊ ግማድ። እስጨናቂው ዕጣም።

ምስል
ወላጃዊ ግዴታን በመወጣት እረገድ የትውልዱ ዕጣ መለጣ እንዳይሆን ቢታሰብበት መልካም ነው። አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳን ከጩኸት ቃል ሩቅ ነህ? (መዝሙር ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ © ሥላሴ 04.08.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) ·        የመጓጓዣ ሃሳብ። ይህ ርዕሰ ጉዳዬ ዛሬ ባለሁበት ዕድሜዬ ያሳብኩት አልነበረም። ይህን ገና ታዳጊ ወጣት እዬለሁኝ ከውስጤ የነበረ አብሮኝ ያደገ ደሜ ነው። አብሮኝ እንዲያድግ የሆነበት ምክንያትም እብዬ እና አቨይ ሲለያዬ የማወቀው ታሪክ ስላልነበረኝ አድጌ ነፍስ ሳውቅ እኔ ከእናቴ ጋር መሆኔን ሳረጋግጥ በራሱ ጊዜ በመንፈሴ የተጸነሰ ይመስለኛል። መራራ የደም ቅምረት ላረሳው ላይረሳኝ ተዋደን በአንድ ማዕድ አብረን የኖርን ግማድ። ከዚህ በተጨማሪ ከወላጆቻቸው ጋር በጋራ ከሚያድጉት ይልቅ እንደ እኔ ከእናታቸው ጋር የሚያድጉት ዕድል ያሸለበችባቸው እጅግ በርካታ ህፃናት የመንፈስ ምሾም ህሊናዬን እንዳይተኛ አድርጎ ኮትኩቶ ስላሳደገውም ጭምር ነው። ከአደግኩ በኋዋላ እንደተረዳሁት ማግባትም መፍታትም ገብያ ሄዶ እቃ እንደ መግዛት እጅግ ቀላሉ የህይወት ክፍለ አካል መሆኑንም ተገንዝቢያለሁኝ። በህይወቴ ከሚያሥፈሩኝ ነገሮች ትልቁ ትዳር ሆኖ በልቤ ጽላት የተከተበውም በዚኸው የመከራ ጠመኔ መሆኑ ዛሬ ዛሬ ይረዳኛል። ላም ጣም ለሌለው ሕይወት ስለምን የሰው ልጅ ጉልቻን አህዱ ይለዋል?  አሳዛኙ ነገር በእኔ አልበቃ ብሎ እህቶቼም በዚህ ውስጥ ኑሯቸውን መወሰናቸው ዛሬ ላይ ውስጤን ያርመጠምጠዋል። ከማህበረሰቡም፤ ከቤተሰብም ያዬነው የትዳር ናሙና ባለመኖሩ ታላቁን እዮራዊ ጸጋ ሸሽተነው እንድንኖር ተገደናል። ...

ቆሞሳት እና ቅናዊ ምዕራፍት!

ምስል
የቆመሱ ፈቃደ ተክለማርያም „ስንብት“ በፈቃዱ  የሰላም ሐዋርያነት   ነው። „የቀደሙት ነብያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፣ --- የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፣ --- ከክፉ መንገዳችሁ እና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ ይላል እግዚአብሄር።“ (ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ©ሥላሴ 02.08.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)    v     ልመና። እጅግ የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ትንሽ ለዬት ያለ እድምታ ስለሆነ በጽሞና ትከታተሉት ዘንድ በዘንካት ትሁት መንፈስ እጠይቃችሁ አለሁኝ፤ እኔ ሎሌያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ።   v   መካሄጃ። ዛሬ ደግሞ የቀብር ሥርዓት አለ። ማልቀስ ግን አይገባም። ማንባትም አይገባም። ይህን ሳለደርግ፤ ይህ ሳይሆን ሊባልም አይገባም። ይህ ሊሆን ግድ ያለበት እዮራዊ የሚስጢር ዕድምታ ስላለው። የመጨረሻም ቢሆን ስንብቱ ግን እዬራዊ ሥራ አለበት ስለሆነም እባካችሁን ሃዘኑን በልክ አድርጉት። ታላቅ መነኩሴ ነበር። ቆምሶ ኖሮ ነው፤ ቆምሶ ነውም ያለፈው።  የኔዎቹ ግራ አይገባችሁ እገልጠዋለሁኝ የሚሰማኝን። ሰማዕትነትን ዘመኑ ፈቅዶታል። ሁለት ሰማዕታት ሰኔ 16 ቀን፤ በወሩ ሀምሌ 19 ሌላ ሰማዕት፤ የተክልዬ ጊዮርጊስ ለተክልዬ ሌላ የሰማዕትነት ዜና አዲስ አበባ አስተናገደች። ጸጥ ረጭ ብላ የባጀቸው አዲስ አበባ ሁሉንም በዓይነት እያስተናገደች ነው። ተደሞን ለተደሞ ጊዜ ከተሰጠው።   v   ትውስታ። ታስታውሱ ከሆነ ማን ጠ/ ሚር ይሁን በሚለው ላይ የዶ...