በለው! አቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ምን እያሉን ነው?
የመፍንቅል መንፈስ ማህበርተኞች የመንትዮሹ መልዕከታት ውጥረት። „እኔም ተመለስሁ፣ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዬሁ፤ እንሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፏአቸው እጅ ሃይል ነበር፤ እንርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።" መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። · ቁጥር አንድ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/93457 ምርቱን ከግርዱ እንለይ ! ኦቦ አዲሱ ረጋሳ August 9, 2018 | „ነፃነት፣ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ !“ ለቁጥር አንድ መልስ በዚህ ሰጥቻለሁኝ። እርግጥ ነው እንደ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ባንዴራ ጨርቅ ነው ዓይነት አገላለጹን በሚመለከት አልነካካሁትም። ሌላውን ጭብጥ ግን ትንሽ ሄጀባታለሁኝ። ለማያያዝ ነው ሊንኩን የለጥፈኩት የሁለቱ መንትዮሽ ፍንገጣ እና ጥሪያቸው መከተታል እኔ ቀደም ብዬ ስገልጻቸው ከቆዬሁት ይሁን አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት እንዲመጡ የነበረውን ምኞቱ ጋር ሃዲዱን እንድታገነዝቡት ነው። በዚህ ሊንክ ለሁለቱ መንፈሶቹ ያለውን ዕይታ የገለጸበት ነው አቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/88248 „ ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም ? – ጀዋር መሐመድ ያብራራል |...