ልጥፎች

ጥያቄው የብትን አፈር የነፍስ ጉዳይ ነው!

ምስል
ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም። ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንደምን አላችሁልኝ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ። በነገረ ጣይቱ ላይ ዛሬ ጥዋት እጅግ ከማከብረው ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት በላይ በግሉ ስለ ኢትዮጵያኒዝም የተጋ እና ያታገለ የአክቲቢስት አቶ መስፍን ፈይሳን ምልከታ አዳመጥኩኝ። ባለፈው ሳምንትም የርዕዮት ሚዲያን ምልከታ ተከታትያለሁኝ።  የወዳጄን የመስፍኔን ከቅንነት ስለሆነም በትርጉም ባቃናው፤ ትንሽ ዘለግ አድርጌ እንደ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ምልከታየን በሚል ነው እንዲህ ማለት ፈልግሁኝ።  እሱ ቅን ኢትዮጵያዊ ስለሆነ በሃሳብ ልዩነቱ ልናዝንበት የሚገባ አይሆንም። ምንግዜም በአንደኛው ሃሳብ ባንግባባ በሌላው ደግሞ እንስማማለን ወይንም በድምጽ ተዕቅቦ እንለያለን። ይህ የእውነተኛ ዴሞክራሲ ፈላጊው እውነት ነው። ግራው ዘመም መንፈስ ያደረበት ብቻ ነው ሞጋች ሃሳቦችን ወይንም ፈንጋጣ ሃሳቦችን የሚፈራው። ያው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አምላኩ ስለሆነ።  ·        የሆድ የሆድን።   ኢትዮጵያ የክት እና የዘወትር ልጅ የላትም። ኢትዮጵያ ስለ ልጆቿ ክፍልፋይ አሰናድታ አታውቅም። ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም ። ኢትዮጵያ ላይ ያለው ንጹህ አዬር ኦክስጅን አንተ / አንቺ የእኔ አይደለህም /ሽም ብሎ ገድቦ አይዋቅም፤ ለይቶም አያውቅም። አንድ ተራራ ላይ ያለው ነፋሻ አየር እኩል ነው ለሁሉ ፍቅሩን የሚያዳርሰው፤ ዝናቡም ሲመጣ እንዲሁም መቻቻልን በእግሩ አንዲሄድ ያደርገዋል፤ የኢትዮጵያ ጸሐይም ስትመጣ ለሁሉም ብርሃነኗን በሐሤት ትለግሳለች። ስታኮርፍም ስትስቅም እኩል ነው።  ...

መቼ ይሆን አሉታዊ ቁርቁሱ የሚያበቃው? ይንፍቀኛል ...

ምስል
„አማራነት መንፈስ ነው።“ „ብዙ ነገርን እንናገራለን፤ የነገሩ መጨረሻ እሱ ብቻ ነው፤ እንጂ ነገር ግን መጨረስ አንችልም።“ „መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፫ ቁጥር ፳፯“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.09.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ·        ግ ራሞተ ተሰሞናተ። የሰሞናቱ ትርምስ ግርም ይለኛል። አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ መድረኩን እስቲ እንዳሻችሁ ሁኑበት ያሉ ይመስለኛል። ምክንያቱም የስሜን አሜሪካ የነበረው የመሰናዶ ውጣ ውረድ ብዙ እንዳሰተማራቸው አስባለሁኝ። በዝርዝር ሥም አቀማማጥ ሁሉ ቦክስ እንደነበር የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሪፖርት አስረድቶኛል። የሆነ ሆኖ በቤተመንግሥትም ደረጃ የአደባባይ ሥራ እንብዛም ኑሯቸው የማያውቀው ዶር ሙሉቱ ተሾም ሳይቀር ብዙ ጊዜ ብቅ እያሉ በቴሌቪዥን መስኮቶች እያዬናቸው ነው - አሁን አሁን። እንኳን ለዚህ አበቃቸው ያሰኛል። መቼስ መነቃነቅን የመሰለ ነገር ስሌለ …. ተነቃነቅ ስንፍናን ነቅንቅ ሞራልን አድምቅ ኢትዮጵያን አልቅ>>  አማራ ተጋድሎ እና ቄሮ ነፃ አውጥቷቸዋል ፕ/ ዶር ሙላቱ ተሾመን። የቀድሞውን ጠ/ ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝንም ታጋድሎው ገላግሏቸዋል። ግንቦት ሰባቶችንም „የት ናችሁ? የት ደረሳችሁ? ምን ያዛችሁ“ ከሚለው ፈተና ገላግሏቸዋል። ተመሰገንም ሊሉት ይጋባል። ማጣፊያው ያጠረ መከራ ነበረ እና በዬጊዜው የመልስ ቀዳዳ ማጮለቅ…  በሌላ በኩል የአንዱ ሥም ላይ ለልዕለና የሌላው ደግሞ ታች ወድቆ ሲፈጠፈጥ፤ የሌላው ደግሞ „የእኔ የእኔ“ እዬተባለ ሽሚያ ላይ - ለወረት ከፍ እና ዝቅም ሲባልለት ይታያል። ሌላው ደግሞ ግራው እና ቀኙ ማህል ላይ ሰቅዘው...