የአላዛሯ ኢትዮጵያ ድንብልብል መከራ፡
ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ። „ታላቅ ክንፍ እና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበር፤ እነሆም ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ።“ ትንቢት ህዝቅኤል ፲፯ ቁጥር ፯ እስከ ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 01.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። · የገማናችን ብርከታው። ይግርም ነው። አቶ ጌታቸው አሳፋ ሱዳን ሄዱ የሚለው ነገር አያሳምነኝም እዛው ትግራይ ውስጥ ነው ያሉት ብዬ ጽፌ ነበር፤ አይደለምን? አሁን ይድነቃችሁ ብለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የምክር ቤት አባል ሆነው መመረጣቸው ብቻ ሳይሆን በቀጣዩ የኢህአዴግ ጉባኤም እንደሚታደሙም ተገልጧል። የማስፈራሪያ ትልቁ ዘንግ፤ የማንአለብኝነትም ተጋድሎ … ለዚህም ነበር እኔ ችግሩ ሌቦች ተፈቱ ሳይሆን ለውጡ ሊቀለበስ ይችላል ብላችሁ እሰቡ ያልኩት" ጭንቁ ሌቦች አቅም አገኙ ነው " ፤ አቅማቸውን አጠናከረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይንም ሞት ብለው ተነስተዋል። እኛም ጉዝጓዝ ሆነን መባጀታችን መርሳት የለብንም። ኦዴፓ ውስጥም ማን ማንን እንደሚደግፍ አዲስ እጩ ያቅርቡ አያቅርቡ ገና ሰው ልብ ያላለው ጉዳይ ነው። ኦዴፓ ሙሉ ድምጹን ይዞ ይጋባል የሚል ዕድምታ አነባለሁኝ። ከሆነ ጥሩ ነው። ነገር ግን የአቶ ጃዋር መንፈስ ሌላ መሰናዶ የለውም ብሎ ማሰብ እራስን መርሳት ይመስለኛል። ሌላ ድልድይ ፈላጊዎች ናቸው። አፈንግጦ ለመውጣትም የተሰናዱበትን አመክንዮ ሊኖር ስለ መቻሉም ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። ያ ባይሆን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይህን ያህል የልብ ልብ አያገኝም ነ...