ልጥፎች

ዕውቅና የሌው ችግር ከመፍትሄ ማን አስደርሶት?!

ምስል
እንዴት? መቼ? በምን ሁኔታ? ስለምንስ? ዕውቅና የሌለው ችግር  ከመፍትሄ ማን አስድርሶት? "ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል፤ መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል።"  መጸሐፈ ምሳሌ ፳፱ ቁጥር ፬ ·        መ ራራ መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=v1-4DqsofQw የራያ አማሮች በትግራይ ቅኝ ገዢ ወራሪዎች የሚደርስባቸው እንግልት ግድያና የማንንት ነጠቃ። https://www.youtube.com/watch?v=cUE6uDsTPW4 Ethiopia Special News የወልቃይ ስቃይ እየበረታ መቶዋል October/5/2018 https://www.youtube.com/watch?v=szp63jqOiXs ራያ አላማጣ ከትግራይ ጨፍጫፊ ሰራዊት ጋር ፍጥጫ 7 አማሮች ተገድለዋል ·        እ ምታን በዕድምታ፤ ኡኡታን ለሰርክ … አሁንም ጩኸት ሆነ። አሁንም እሪታ አለ። አሁንም ስጋት አለ። አሁንም መከራ አለ። ህፃናት ያለቅሳሉ፤ እናቶች ያነባሉ፤ አዛውንቶች ኡኡ ይላሉ። ማን አላቸው እና ያልቅሱ ... ፈጣሪ ከሰማቸው። አሁንም የታቀደ ጥቃት አለ። አሁንም ለቅሶ አለ። አሁንም መሰደድ አለ። አሁንም ተስፋ ማጣት አለ ለአማራ። አሁንም መኖር ተከልክሏል። አሁንም መተንፈስ አያቻልም - አማራ። አሁንም ችግሮች በአይነት ተደርድረዋል በተለይ ለአማራ። አሁንም አሳሩ ውጧታል አማራን። እንዴት ይፈታ? መቼስ ይፈታ? በምን ሁኔታስ ይፈታ? ስለምንስ ችግሩ አዬለ? መቼ ይፈታ ቢባል ችግሮችን ለመፍታት ለችግሩ ዕውቅና መስጠትን ይጠይ...

ልዕልት ርዕዮት አለሙን እስኪ እንዴት ባጀሽ ልበላት።

ምስል
ትናንትን ዛሬ በምልስት እስኪ ይቀፈው? ወርዱ ከቻለው?   „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡ ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ው ፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥ ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም።“ ( ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫ )  ከሥርጉተ© ሥላሴ 21.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        ማሰብ እና ማግኘት ጋዳ ናቸው። ልዕልት ርዕዮት አለሙን ዓይኔን በዓይኔ የማዬት ያህል ነበር የማስባት። እጅግም እሳሳላት ነበር የዛሬውን አያድርገው እና። ከእስር መፈታቷን ብቻ ሳይሆን የብርታትን እኩልነት ብርሃን ትሆናለች ብዬም በጽኑ አስባት ነበር። መመኘት ከልካይ ስሌለበት የውስጤ ሐሴት ትሆናለች የሚል ብሩህ ተስፋ ሰንቄ ነበር መፈታቷን የጠበቅኩት። የሚገርመው የእሷም የእህቷም መጠሪያ ሥም የእኔም  የእህቶቼም ነው። ሥምም ትርጉም ይሰጣል የውስጥ ሲሆን። እናም እጅግ አቅርቤ አያትም ነበር። በመጨረሻ ግን አሜሪካ ከገባች በኋ ዋላ ለእነዛ ካቴና ላይ ላሉ ነፍሶች ብጣቂ አዘኔታ ስታጣ ነፍሴን ጨነቃት፤ እጅግ ካዘንኩባቸው ጥቂት ነፍሶች አንዷ እሷው ሆነች። አሁን በቅርቡ በጀግኒት እማዋይሽ አለሙ ጉዳይ ታታሪ አቶ ተሎ...