ልጥፎች

በሴቶች እና በአብይ ዙሪያ ሥርጉተ በታህሳስ 26/2017 ምን ብላ ነበር?

ምስል
        አብይ ኬኛ!  ክፍል ሦስት -  ለቅኖች ብቻ።            አብይ ለእኛም  ለሴቶች አናባቢያችን                         Vowels ነው። „ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሳ ጊዜ፤ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግድላዊት ማርያም ታዬ።  እርስዋ ሄዳ  ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት፤ ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው። እነርሱም ህያው እንደሆነ  ለእርስዋም አንደታዬ ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህ በኋዋላ ከእነርሱ ለሁለት ወደ ባላገር ሴሄዱ፤ በመንገድ በሌላ  መላዐክ ተገለጠ። እንርሱም ሄደው ለሌሎች ሄደው አወሩ፤ እነዚያን ደግሞ አለመኗቸውም። ኋላም በማዕድ  ሳሉ ለአስራአንዱ /ሐዋርያት/ ተገለጠ። ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኗቸው፤ አለማመናቸውን የልባቸውን  ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው፤ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።  ያመነንም፤ የተጠመቀም፤ ይድናል። ያለመነ ግን ይፈረድበታል“    (የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ  ፲፮ ከቁጥር ፱ አስከ ፲፯። ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፳ ከቁጥር ፩ ጀምሮ … )  የበለጠ ሚስጢሩን ለማዬት የዬሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ ጀምሮ ያለውንም በጥልቀት መመልከት ይቻላል። በመንፈሳዊ ህያዊነት ቃለ ህይወቱ መረቡን በረቂቅነት በውስጣችን ይዘራል። ይሄም ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሚስጢር። የክርስትናም። ዶር አብይ አህመድ አኮ የቅኔ ማዕዛ ናቸው። እሳ...

ዋው! ሴት ርዕሰ ብሄር!

ምስል
የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ 4 ኛው የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆኑ። „አቤቱ ጸሎቴን አድምጥ ልመናዬንም ቸል አትበል።“ መዝመረ ዳዊት ፶፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 25.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ሰሞኑን ሲያወዛግብ በባጀው የፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ ክብርት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ-ኢትዮጵያ ሴት ርዕሰ ብሔር መሾማቸውን ቢቢሲ ዘገበ። https://www.bbc.com/amharic/news-45974821 አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ - ኢትዮጵያ ሴት ርዕሰ ብሔር አገኘች ይህ እንግዲህ ቦታው ብዙም የረባ ፓለቲካዊ ድርሻ ባይኖረውም ሴቶችን ወደ ፊት ለማምጣት መደፈሩ ግን ለእኔ መልካም እና ወርቅም እርምጃ ነው። ነገ ደግሞ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንታዊ ይሁን በጠ/ሚስትራዊ ትመራ ብቻ ሴት ሙሉ የፖለቲካ አንኳር መሪ ልትሆን የምትችልበት መሰመር ጠራጊ ነው ብዬ አስባለሁኝ። አንድ ጊዜ የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ሴት ጠ/ሚር ስትሆን ነው ብዬ ጽፌ ሃሳቤ እንደተንጠለጠለ ወዲያው ነበር ጉልበተኞች ያስነሱብኝ። ከዛም በመነሳት ሴቶች ብልህ አመከንዮ አላቸው ጊዜ እስኪሰጣቸው ድረስ ጠብቅው ያቆዩት ዘንድ እምከራለሁም ብዬ ምላሹን ጽፌ ነበር። በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ያለዋለው ድንግል ሃብት የሴቶች ብልሃት ነው። በ እኛ ውስጥ ተነገረው ያማይልቁ ጥበባዊ ብቃቶች አሉን። ይህን በድፍረት ነው እኔ እማናገረው።  ስለሆነም ለክብርት ርዕሰ ብሄሯ  ሳህለወርቅ ዘውዴ-ኢትዮጵያ ከውስጤ ከትንፋሼ ከነፍሴም  እንኳን ደስ አለዎት እላለሁኝ። ለመላ የኢትዮጵያ ሴቶችም እንኳን ደስ አለን እላለሁኝ። ምንም ይሁን ምን ሴቶች ስማቸው ጎልቶ ሲጣራ ለእኔ ደስታዬ ...