የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለሰላም ዘብ መቆም ነው!
የአማራ ተጋድሎ ቀዳሚ ተግባር ለክልሉ ህዝብ ሰላም ዘብ መቆም ነው። „አግዚአብሄርን የሚፈለግ ልብ ደስ ይበለው።“ መጽሐፈ መዋዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲ 03.11.2-18 ከሥርጉተ©ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አማራ ከዚህ መሪው ጎን መቆም ግድ ይለዋል። ጦርነት አውዳሚ ነው። ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ ቢኖር አመድ እና ቂም በቀል ብቻ ነው። ቂም እና በቀል ደግሞ ለቀጣዩ ትውልድ ጸር ነው። ጥቂት ሰዎች ለውጥ አልመጣም ይላሉ። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በቀና የሚዩት አንዳችም ነገር አለመኖሩ ሰው ከምን ተሠራ እስከማለት እደርሳለሁኝ። ፍጹምነት ከሰው መጠበቅ ዓይነት ነው። ግድፈት የለም ማለቴ አይደለም። ግድፈት ራሱ ሰውኛ እንጂ ሮበትኛ አይደለም። ብቻ ሁሉንም ድፍጥጥ ሲያደርጉት የትኛው ፕላኔት እንዳሉ ይገርመኛል። እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ግን የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ለውጤት የበቃ ነው ባይ ነኝ። ኮሽታ የማያሳማ፤ ዕወጁልኝ የማይል ለውጥ አለ። ቀውስ የለም ማለቴ ግን አይደለም። የግርግር ሙሽሮች በእጃቸው የሰሩት ቀውስ አለ። ያው ሁሉ የሥልጣን ጥመኛ አይደለ። ያ ያው ሁሉ የቤተመንግሥት ቀይ ምንጣፍ ምኞተኛ አይደለምን? የአማራ የማንነት ህልውና ተጋድሎው መሰረታዊ ጥያቄዎች መፈታት ለመቻል የሥርዓቱ አዋራሪሶች ከሥልጣነ ገብታቸው በስልት ማስነሳት ነበር የመጀመሪያው ረድፈኛ ተግባር። ይህ በሚደንቅ ሁኔታ ተከናውኗል። ርዕዮቱም ቢሆን ሞራው ነው ያለው። ይህ ስለተከናወነም በሁለቱ የአገር መሰረት ሃይማ...