የኢትዮጵያ ሴቶች ለዕንቋማ ዘመናቸው ጥበቃ ሊያደርጉለት ይገባል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ለዕንቋማ ዘመናቸው ጥበቃ ሊያደርጉለት ይገባል። „እግዚአብሄር አምላክ በአዳም ከባድ እንቅልፍ ጣለበት አንቀላፋም፣ ከጎኑም አንዲት አጥነትን ወስዶ ሥፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሄር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት።“ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፳፩ እስከ ፳፫። ) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 16.12.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። · ከጠ ቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የመንፈስ ፍልቅ በጥቂቱ። „ ወንድ እና ሴት በሚያስደንቅ ሁኔታ የተፈጥሮ ልዩነት አላቸው። ወንዶች በደንብ እንድትሰሙኝ እፈልጋለሁ። ሴቶች በሚያስደንቅ ሁኔታ ከወንዶች የተሻለ ብቃት አላቸው። “ /ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/ https://www.youtube.com/watch?v=NHhWHrJOuHU Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል ሁለት https://www.youtube.com/watch?v=AHyuaT4mqz4 Ethiopia Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል አንድ „ ወንዶች በሴቶች ላይ የበላይነታቸውን ያረጋገጡ ጊዜ ግማሽ አካላቸውን አይደለም ቆርጠው የጣሉት። ትልቁን ዕወቀታቸውን ቀበሩት፤ ዕወቀታቸውን ቀብረው ሆነ ጨዋታው።“ ከባለቅኔው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የተወሰደ/ „ ክርስትና ማለት ትንሳ...