የሳጅን በረከት ስምዖን እና የሳጅን ታደሰ ካሳ የዋስ መብት ጥየቃ እና የቦታ ምርጫ ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው ተደመጠ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። ብራቦ ! የባህርዳር እና የአካባቢው ፍርድ ቤት። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ 25.01.2018 · መነሻ። አሁን የዋልታ ቴሌቪዢን እንደዘገበው የሳጅን በረከት ስምዖን እና የሳጅን ታደሰ ካሳ የዋስ መብት ጥያቃ እና የቦታ ምርጫ ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው ተደመጠ። እኛም እልል አለን። ሐሤትም አደረግን። ቀልዱ መቆም እንዳለበተም አበክረን እንገልጻለን! https://www.youtube.com/watch?v=wOycDRy-8eM ዋልታ ቲቪ 17/05/2011 ዓ . ም የቀን 6 ፡ 30 ዜና | Walta TV News 12:30 PM 1/25/2019 · ዕይታ። ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ አዲስ የብሥራት ሌላ ዜና ደግሞ አለን። ተመስገን ብለን ቀኑን አህዱ እንል ዘንድ የሰማዩ ዳኛ ፈቅዶልናልና። ከፍተኛ ስጋት ነበር በህመም ምክንያት በዋስ የሴራ ቸረቸራ ዋሻው፤ የጥፋት ሥራአስኪአጁ ሳጅን በረከት ስምዖን እና ዋርሳቸው ክንዳቸው - ደጀናቸው አቶ ታደሰ ካሳ /ጥንቅሹ/ ይለቃቃሉ በሚል። ይህ የስጋት ጥያቄ በመጀመሪያው ቀን የተነሳ ነበር። መቼም የአማራ መንግሥት ጅል ካልሆነ በስተቀር አምሱኝ፤ ቅበሩኝ፤ አቃጥሉኝ ካሰኛችሁም ዘልዝሉኝ ካለለ በስተቀር የነቀርሳውን ጭንቅላት ለቆ እንደ ገና በሴራ መርብ እንደ አሳ ለመጠመድ ይወስናል ብዬ አላስብም። ልቡን አውልቆ...