የሳጅን በረከት ስምዖን እና የሳጅን ታደሰ ካሳ የዋስ መብት ጥየቃ እና የቦታ ምርጫ ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው ተደመጠ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

ብራቦ! የባህርዳር
እና
የአካባቢው ፍርድ ቤት።

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ
25.01.2018

·       መነሻ።

አሁን የዋልታ ቴሌቪዢን እንደዘገበው የሳጅን በረከት ስምዖን እና የሳጅን ታደሰ ካሳ የዋስ መብት ጥያቃ እና የቦታ ምርጫ ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው ተደመጠ። እኛም እልል አለን። ሐሤትም አደረግን። ቀልዱ መቆም እንዳለበተም አበክረን እንገልጻለን!

ዋልታ ቲቪ 17/05/2011 . የቀን 630 ዜና | Walta TV News 12:30 PM 1/25/2019

·       ዕይታ።

ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ አዲስ የብሥራት ሌላ ዜና ደግሞ አለን። ተመስገን ብለን ቀኑን አህዱ እንል ዘንድ የሰማዩ ዳኛ ፈቅዶልናልና።

ከፍተኛ ስጋት ነበር በህመም ምክንያት በዋስ የሴራ ቸረቸራ ዋሻው፤ የጥፋት ሥራአስኪአጁ ሳጅን በረከት ስምዖን እና ዋርሳቸው ክንዳቸው - ደጀናቸው አቶ ታደሰ ካሳ /ጥንቅሹ/ ይለቃቃሉ በሚል። ይህ የስጋት ጥያቄ በመጀመሪያው ቀን የተነሳ ነበር።

መቼም የአማራ መንግሥት ጅል ካልሆነ በስተቀር አምሱኝ፤ ቅበሩኝ፤ አቃጥሉኝ ካሰኛችሁም ዘልዝሉኝ ካለለ በስተቀር የነቀርሳውን ጭንቅላት ለቆ እንደ ገና በሴራ መርብ እንደ አሳ ለመጠመድ ይወስናል ብዬ አላስብም። ልቡን አውልቆ ልብ አልባ የመኖር ያህል ይሆናል እንዲህ መሰል ኮረኮንቻዊ ዳጣዊ ውሳኔ ከተወሰነ።

ቃላትም - ሐረግም - ፊደልም- ቋንቋም አይገልጸውም ሳጅን በረከት ስምዖን ማለትን። ዲያቢሎስን በአምሳሉ በምደረ ኢትዮጵያ በአካል እንዲኖር ማድረጉን ራሱ መዳህኒዓለም አባቴን ባገኘው የምጠይቀው ይህን ነበር። ፈጣሪን ከሰቀለው ሳጥንኤል፤ ከፈረደበት ጲላጦስ አንዳችም ቅንጣት ነገር ልዩንት የለውም የእኒህ  ሰው ጃርታዊ ተፈጥሮ። ፍልፈል!

የኢ-ሰብዐዊነት ሶፍቱ ዌሩም ሃርድ ዌሮም ሁሉቱንም አጣምሮ የተፈጠረ ፍጡር ቢኖሩ አቶ በረከት ስምኦን ናቸው። ተፈጥሯቸው ንጋት የማያውቅ ጨለማ ነው።

በህይወታቸው ለማንም ለምንም ቅን አስበው የማያውቁ ቅንነት ስለመፈጠሩም የማያውቁ እኩያ ነገሮችን በመደርደር፤ በእኩይ ነገሮች ላይ የምርምር ተግባር በመከውን መዋለ ዕድሚያቸውን ሁሉ ያቃጠሉ ከንቱ ሰው ናቸው።

እንደ ሰው ለማዬት እኔ እራሱ ይቸግረኛል። ከሳቸው ጋር በምን አግባብ ኢትዮጵያዊው ሰው ጓደኝነትም - ጉርብትናም - የሥራ ባልደረባነትም ፈጥሮ እንደኖረ ራሱ ሳስበው ይገርመኛል። በሰው አምሳል የተፈጠረ ሳጥናኤል ጋር ራሱ የመግባቢያ ቋንቋው መኖሩ ራሱ ሳወጣው ሳወርደው መልስ አጣለታለሁኝ። ከሳቸው ጋር በዬትኛው ቋንቋ ይሆን መግባባት የሚቻለው? እኔ ቀደም ባለው ጊዜ የሚሰጡት መግለጫ ራሱ አይገባኝም ነበር። እንዳንግባባ ያደረገን ደግሞ የተፈጥሯቸው አገነባብ ሰውኛ ባለመሆኑ ይመስለኛል።




 ውዶቼ - ጭንቅላተቸውን እስኪ እዩት እንዴት እንደተፈጠረ። ቅሉን ራሱን ተመልከቱት። ቀና ነገርን፤ መልካም ነገርን፤ ደግነትን፤ ርህርህናን፤ ሰላምን፤ ፍሰሃን ለማናድ - ለማፍረስ - ለማቃጠል አቅዶ የተፈጠረ ስለመሆኑ ይነግራችሁዋል። እፉኝት!

እፉኝት ሲረገዝ አባቱን ሲወለድ እናቱን እየገደለ እያስገደለ ሞትን በሞት እያጣፋ መኖርን በሞት የቀመረ ተፈጥሮ። ፈጣሪ በአምሳሉ የፈጠረውን ሰው አሰቃይቶ ደስታ እንዴት ይገኛል? መኖርስ እንዴት ይመቻል?

ሳጅን በረከት ስምዖን ሲፈጠሩ ሰው ጠል ሆነው ነው የተፈጠሩት። ሲፈጠሩ ተፈጥሮ ጠል ሆናው ነው የተፈጠሩት። ሲፈጠሩ የትኛውም አቅም ጠል ሆነው የተፈጠሩት። ራሳቸውን ዋሽተውን ክደውም ነው የነሩት። መጸሐፈ ሄኖክ ላይ ያሉ የጸላዬ ሰናይ ልጆች፤ የልጅ ልጆች አፈጣጠሮች ሳነባቸው እማስባቸው እሳቸውን ነው።

አሁን ስለ እሳቸው ሰው ለመተርጉም ሲጣጣር አያለሁኝ። ድንጋይ ምኑ ይተረጎማል? ዲያቢሎስ ምኑ ይተረጎማል? በሰው አምሳል የተሰሩ የምድር ሲኦል ናቸው። በ27 ዓመቱ የመከራ ዘመን ከጫፍ እስከ ጫፍ ለተፈጠረው ተፈጥሮ ጠል ጉዳይ መሰረቱ እኒህ እሾህ ነበሩ። ሰው አቅልሎ ያዬዋል ወይንም ከሆነ ከሆነ ነገር ጋር ያነካካዋል፤ የሳቸው ተፈጥሮ በወል እንቀጣበት የተጣለብን መርገምት ነበር። ራሱ ማዘናችን ዕንባችን ጤና ማጣታችን ሁሉ እኮ እሳቸው በሚፈበርኩት ኢ - ሰባዕዊ የሆነ ቅምረት ነው። 

አሁን ተመስገን የሚያሰኛው ያ መርገምት በአቤል ዕንባ እዩርን አንኳኩቶ በሰው እጅ እሱም ወድቆ አሳያን። የመጀመሪያው ቅጽበትን የምሥራች አያክለውም። 

እሳቸው የተፈጥሮ ጠልነታቸው ራሱ የሰላም አዬር ንፋስ ሲነፍስ ያውካቸዋል፤ ዝናብ ሲጥል ይበሳጫሉ፤ ተክሎች አዝርት እጸዋት ሲበቅሉ፤ ሲያድጉ ሲያሰብሎ ይተማማሉ። የበቀለ የጸደቀ የፋፋ ነገር ያማቸዋል።

 ወፎች በሰማይ በሰላም ሲበሩ ይበጠብጣቸዋል፤ ሰዎች ሲሳሳቁ ውስጣቸው ያለቅሳል፤ ሰዎች ተስፋ ሲኖራቸው ያሳብድቸዋል፤ ሰዎች ሲወደዱ ይገረጨረጫሉ። እኔ ሰኔ 16 ቀን 2016 እንዴት እንዳሳለፉ ያዬቸው ስል ነበር። 

እሳቸው እራሳቸውን እራሳቸውን አያውቁቱም። ከሰው ዘር አለመሆናቸውንም አልተረዱም። ቡርቡዳ ትርያንግል ናቸው። እሳቸው ለርግማን መፈጠራቸውን አንድም ቀን ሳይረዱት ለዚህ ፍፃሜ በቁ። ክፉ ምናባቸው እሳቸውን ይተረጎማል? የሚያስቡትን ሆነ የሚወስነቱት እራሱ እራሳቸው አያውቁትም። 

ክፋትን ሰው ለመተርጎም ይቻለዋለን? ግን ክፋት ቅርጽስ- መልክስ - ቁጥርስ - ፎርምስ አለውን? የለውም። ሴራ ከራስ ተሰማ ናደው ቀጥሎ ተፈጠረ ቢባል በእኒህ ርኩም ተፈጥሮ ውስጥ ነው።

እኔ እነዛን ደግ ወላጆቻቸውም አዋቃቸዋለሁኝ፤ እማማ ብሬን እና አቦይ ገ/ህይወትን አሁን ከእነሱ ይህ ጃርት የሆነ ተፈጥሮ ተገኜ ለማለት ራሱ ይቸግርኛል። ለእነሱም በውነቱ ዕዳ ነው የተጠላባቸው። መርገምት።

የፈለገ ሴረኛ፤ የፈለገ ተንኮለኛ፤ የፈለገ ሸረኛ፤ የፈለገ አድመኛ በእኔ ዕድሜ አቅርቢ ብባል ከሳጅን በረከት በላይ እማቀርበው አይኖረኛም። የሳቸው ማህበርተኞች አሉ እንደ ድርጅት ህወሃትንም መውሰድ ይቻላል። የሳቸውን ተፈጥሮ ወራሾች ናቸው ብል ይቀለኛል። 

የሴራም የሸርም የአድማም የክፋትም የመጨረሻው የተፈጥሮ ደረጃ ያለው በእኒህ እኩይ ተፈጥሮ ነው። የመጨረሻው የትምህርት ደረጃ ፕሮፌሰርነት ሳይንቲስትነት ነው አይደለም? ክፋትም ሴራም፤ ሸርም የምርምር ማዕከሉ በሳቸው ጭንቅላት ውስጥ ነው ያለው

በነገራችን ላይ ሳቅ የሚባለውን አያውቁትም፤ አይደለም ሳቅን ሰው የሚበላውን ታላቅ ፍጡር ስለምን እንደ ተፈጠረም አያውቁትም። እራሳቸው የሰው ምስል ያላቸው በተፈጥሮ ግን በእኩይ የተዋቀሩ መሆኑም አያውቁትም። በብዙ ስብርባሪ የእሾኽ፤ የባልጩት፤ የአሜኬላ፤ የአሽዋ ድቃቂዎች የተቀመሙ እንደሆኖ ነው የሚገባኝ። በተቃጠለ ነፍስ ውስጥ ያለ ጨለማዊ ሰብዕና።

ጎለያድን ያሸነፈው ቅንነት ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሲሆኑ እብድ ነበር የሆኑት። ለእብደት ብዙዎችም አብደዋል። የብዙዎች እብደት የማንፌስቶ ፍቅርኛነታቸው ይህን ዕድል ማንፌስቷችን ቢኖረው ብለው ያስቡ ይመኙ ስለነበር ነው። ይህ ደግሞ ሰውኛ ነው።

የአቶ በረከት ስምዖን ግን ይህ ብሩኽ ዘመን እንደሚመጣ ስለሚያውቁ ሳቃችን ለመቃማት ነበር የተሰናዱት። ሰላማችን ለመንጠቅ ነበር አና ብለው አደበባይ ወጥተው ለመውረር የተነሱት። አፈጣጠራቸው ሰውኛ ስላልሆነ መንገዳቸው፤ የሚያልሙት፤ የሚተልሙት ሁሉ አመድማ ጥመት እና ጥነት ነው። የቀትር እባብነት።

ከዛ በፊት እኮ አብይ ስለሚባል አንድ ቅን ነፍስ ትዝ ብሏቸው አያውቅም፤ ማግስትን አብርቶ እንደሚቀጥል ሲታሰብ ግን ክፉ አውሎ ሞገድ ለማስነሳት ማሰኑ። ያን ጊዜ ይህን እኔ ጻፍኩኝ።

ግብዕቱ አይቀሬ!

የበረከት የሸር ሸጎሬ፤ ግብዕቱ አይቀሬ!
ከሥርጉተ - ሥላሴ 14.03.2018

የአንቡላ ቃርምያ!

የአንቡላ ቃርምያ!
ከሥርጉተ ሥላሴ(Sergute©Sselassie)
 26.02.2018 (
ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ብዙ የማንፌሰቶ ማህበርተኛ አባላት ብዙም አልተረዱትም። ምክንያቱም መጪውን ዘመን አሻግሮ ለማዬት ከዛቸው ከወረቀት አምላኪነት ጥብቆ ራቅ አድርጎ ማሰብ ስላላስቻላቸው። „እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም፡“ ይፈጸም ዘንድ ነው የሆነው ሁሉ ነገር።

ያ ሞገዳማ የሳጅን በረከት ወጥቶ ታሪካቸውን የዶር አብይ አህመድን የማብጠልጠል፤ የማጣጣል ተግባር የለውጡን አከርክሪ ጠልፎ ለመጣል ላለመው ሁሉ የማስታገሻ ክኒን ነበር። ነገር ግን ያ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አገር ገብቶ ማስጨብጨብ ባልተገኜ ነበር።

የሰሞኑ የዲያቢሎስ የሰንሰለት ገመድም እንዲህ ሆኖ ለማዬት ባልታደልን ነበር። የሳጅን በረከት መታሰር አይደለም ለኢትዮጵያ ለመካከለኛው አፍሪካም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ታላቅ የሰላም የብሥራት ቀን ነው። 

ክፉዎች ቦታ አይበቃቸውም። ይጠባቸዋል። በሉላዊ ደረጃ ዕድሉን ቢያገኝ ይህ ጃርታዊ ተፈጥሮ ሉላዊውን ዓለም ለማፍረሰም አያመናታም። ትግሉ ከሰው ተፈጥሮ ጋር ነውና።

ሳጅን በረከት ሰው ያላወቀላቸው ትልቁ ህመማቸው የሐገር መሪ የመሆን ህልመኛ መሆናቸው ጉዳይ ነው። ይህን ጭንቅላታቸው ሄሮድስ መለስ ዜናዊም ያወቁላቸው አይመስለኝም። ምሽጋቸው ህወሃትም እስከ ዛሬዋ ቀን አያውቁትም። አሁን የሴራ ደቀመዙራቸው አቶ ጌታቸው ረዳም አልተረዱትም። ሳጅን በረከት ጉልላቷን እንዳ አለሙ፤ ከዛ ለምደርስም እንደቧጣጡ እንዲህ በከንቱነት የተወራረዱ ሰው ቢኖሩ እሳቸው ናቸው።

የናዚ ተፈጥሮ የሰፋ ህልመኝነት በሳቸው ዘንድ አለ። እድሉን ቢያገኙ የሚገደባቸው አንዳችም ሃይል አይኖርም ነበር። ማጥፋት - ማክሰል። ካልቻሉም መፋደስ ይህን ባይችሉም መፈግፈግ ነው ተፈጥሯቸው። ከሁሉ በላይ ኮንፕሌክሳም ናቸው። ማይክራፎን እስትንፋሳቸው ነው ነጮቹ አቲንሽን ሲከር እንደሚሉት።

ይህ የበታችነት ስሜት ብሎናቸውን ስላወለቀው ከደግነት ጋር ሳይገናኙ መዋለ ዕድሚአቸውን በሙሉ በተንኮል እርሾ ተቦክተው፤ በሴራ ውሃ ተቀጥነው ጥፋትን ጋግረው ዕድሚያቸው በአክትሞት እንዲጠናቀቅ አድርጎታል። 

ሞታቸውን እምጠብቀው አንድ ጊዜም እንደጻፍኩት ሬሳቸው ወደ መሬት ሲላክ ሰው እዬሰማ እያዬ እንጦርጦስ እንደሚወርድ ነው።  እድሜ የሰጣቸው ቅን ዜጎች ሁሉ የእውነት መኖርን የታዱሉ ሁሉ ቢጠብቁት እሚፈጸም ይመስለኛል። መቃብር ራሷ አትችላቸውም። ብዙ ግራጫማ ሰብዕናዎች አሉ። የሳቸው ግን የጨለማው ነው። 

ስለሆነም እግዚአብሄር ምክንያት አለው ለሁሉም ነገር። ይህ ይሆን ዘንድ ቀን ጠብቆ ወስኗል። ጠንቅነቱ ለአፍሪካም ለዓለምም ጭምር ነው። አንድ አዶልፍ ሂትለር ምን ያህል ዓለምን እንዳመሳቀለ ይታወቃል። 

ለሳቸው እንደ ቤተ እስራኤል ማጥፋት የሚለፍጉት ዘር አማራን ነው። አንድ ተረብ አቶ ወንድም ልጅ ፋሲል የኔ ዓለም ጥፏል /ጋዜጠኛ/። „ሳጅን በረከት አማራ ብሄርተኝነት አመጣ“ ብሎ እንደ ተለመደው ጋዜጠኛው የፍልስፍና ችግር አለበት። ስለምን? ወስዶ ከአማራ ብሄርተኝነት ጋር እንደ ሸነቆረው በሌላ ጹሑፍ እምለሰብተለሁኝ … ዝም ብዬ ላልፈው አልችልም። 

የሆነ ሆኖ ለአማራ ክልል መስተዳድርም ለዳዊት የሰጠውን አቅም ፈጣሪ ይሰጠው ዘንድ በጸሎት መርዳት ያስፈልጋል።

ይህን ታምር እናይ ዘንድ አማራ መሬት ይህን የዳግሚያ ትንሳኤ ማስተናገዱ ፈጣሪ ሊነግረን፤ ሊያስተምረን የፈለገ ታላቅ ቁምነገር አለ። መከራችን ጥሰን እንወጣ ዘንድ ታላቅ በር ተከፍቷል። ትናንትም ታላቁ በር የተከፈተው „በጣና ኬኛ“ ነው። ዛሬም „ጣና ኬኛ“ ዓመት ድገሙ እያለን ነው - በጣና ዘገሊላ።

ይህን ለመተርጎም የተሰጠው ብቻ ነው ብልህነቱን የሚያገኘው። ይህን በአንድም በሌላም የሚያወላግዱ፤ የሚያጣሙ፤ ከሌላ ነገር ጋር ሊያይዙ - ሊያነካኩ፤ የትርጉም ዝበት ለመፍጠር የሚፈልጉ አሳዛኝ ፍጡራን ይኖራሉ።

 እግዚአብሄር ሃይል አምላክ ነው። ደከመ ሲባል የሚያጠነክር፤ አለቀ ሲባል የሚሞላ፤ የለም ሲባል የሚያኖር ታላቅ አምላክ አለን። ሰሞናቱ አስተረዬ ነው። የዛሬ ዓመቱን አስተርዬ አማራ በምን መልክ እንዳሳለፈ ቅኖቹ ያውቁታል። አስተረዬ የጣና ዘገሊላ ሚስጢር የተገለጠበት ዘመን ነው። ባዶ እንስራን በወይን የሞላ አምላክ ይኸው ታምሩን አማራ መሬት ላይ ቀጥሏል። „ልብ ያለው ሸብ“ እንደ ጎንደሮች። ቅንነት ራሱ ይገልጣል። ሴራን - አድማን - ሸርን - ጥሶ የሚወጣው ፈጣሪ የሰጠን ቅንነት ብቻ ነው። አማራ ቅን ዜጋ ነው።

በተረፈ የሰው ተፈጥሮ ያለው ሁሉ ይህን እርምጃ ተከትሎ ብአዴን ብርታት እና ጥንካሬ እንዲአገኝ፤ ፍትህ የጎበጠው ቀን እንዲቃናለት የበኩሉን ማድረግ ይጠበቅበታል።

የባህርዳር እና የአካባቢው ፍ/ቤት ትክክለኛ ውሳኔ ነው የሰጠው፤ ምንም የዋስ መብት፤ ምንም የቦታ ለውጥ አያስፈልግም ብሏል። 

ጥበቃው በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበትም ገልፆል። ህወሃት ብቻ ሳይሆን የሳጅን በረከት መረብ የትም ቦታ፤ በዬትም ሁኔታ ስላለ የአማራ ክልል መንግሥት ታማኝ ጠባቂዎችን ወልዶም ቢሆን ቦታውን ማስጠበቅ ይኖርበታል። የቤተሰብ ግንኙነቱንም በልክ እና በመጠን ማድረግ ይኖርበታል። 

አብሶ የተጎዱ የአማራ ልጆች በጥበቃ ተግባር ቢመደቡ ይመረጣል። አማራ በዘመነ በረከት አሯል - ከስሏል። ሳጅን በረከት ስምዖን አምልጠው ትግራይ ቢገቡ መይሳውም፤ በላይም፤ ገብርዬም፤ ገልሞም ዳግሚያ እንደሞቱ ብቻ ሳይሆን ቀበቶውም መቀነቱም በቁም እንደ ተቀበረ ይቁጠረው ብአዴን። የሞት የሽረቱ ትግል ነው። 

ከዚህ ጋር ሌላም የተደራጀ ትንኩሳ፤ ሌላም ህውከት ለመፍጠር የሚጠሩ ማናቸውም ነገሮች ሁሉ ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል የአማራ ህዝብ። 

የአማራ ህዝብ ይህን የነፃነት አዬር በችሮታ - በጥገኝነት - ተጠምኖ ወይንም ሌላውን ተጥልሎ አይደለም ይህን ድል ያገኘው። ስለዚህ በደሙ ያገኘውን ድል የመጠበቅ፤ የመንከባከብ፤ የማድነቅእውቅና የመስጠት ግዴታ ይኖርበታል። ከብአዴንም ጎን የመሰለፍ ግዴታም አለበት።

ይህን ለውጥ የአማራ ህዝብ እንደ ልጁ፤ እንደ ትዳሩ፤ እንደ ሥራው ሳይሆን ከዛም በበለጠ ፈጣሪ/ አላህ ታምራቱን የገለጸበት የምርቃት ዘመን መሆኑን አውቆ በጥንቃቄ የመያዝ፤ በዝግታ የመያዝ በእርጋታ ሁሉንም ነገር የመከታታል ግዴታ አለበት።  

አሁን ማን ያስባል ያን ያህል ጠ/ሚር አብይ አህመድ ብቁ አይደሉም ለጠ/ሚኒስተርነት አይወዳደሩም፤ ባህላችንም አይፈቅድላውም ያለ ነፍስ ከርቼሌ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ደግሞ በአውሮፓ ህብረት በዓለም የኤኮኖሚ ፎረም በከፍተኛ ክብር ግርማ እና ሞገስ መስተናገድ። ልዩ ዘመን ነው!

አውሮፓ ህብረተ ሲታሰብ የትኛው ድርጅት እና ማን ነበር እምናሰበው? ዛሬ ደግሞ ያ ቀርቶ ሌላ አዲስ ታሪክ ፈጣሪ በጥበቡ - በትንግርቱ - በታምራቱ ኤልሻዳይ አምላክ እያሳዬ ነው እርዳታው እራሱ እኮ ዛቅ ያለ ነው … 

„የመደመርን ሉላዊ“ ትንታንም ሰምተናል፤ „መደመር“ ቃሉ ተፈጥሮውን ክብሩን ልዕልናውን በጠበቀ መልኩ ሳይተረጎም ነው እንዳለ ነው የቀረበው። አዲስ አባባን እንደ ሥሟ አበባ ስለማድረግ? አዳምጠናል። የምጽዋ አዲስ አባባ መንገድ ጉዳይስ?የሆነው ሁሉ ሰው ባሰበው መንገድ አይደለም።

ዘመኑ የታምር፤ ዘመኑ የምርቃት ነው።የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቀናለታል።“ ያሰብነውም፤ ያለመነውም፤ ቀልባችንም፤ መንፈሳችንም ተስፋችንም እንዲያርፍ ከለመነው ቦታ ፈጣሪ ቀብቶልናል። ተመስገን!

የፈጣሪ ሥራ እንዲህ ነው። ጎልያንድን የረታው በራሱ ፈቃድ በቀባው ጥንካሬ እና ብርታት ነው። እነሆ የህወሃት ጎልያድም ምን ቀኑ ቢረዝምም ተረታ! ሽንኩ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ የሙት መንፈስም ሁለተኛ ሞቱን ሞተ።  


ወደፊትም ዬዬትኛውንም የማህበረ ደራጎን ሴራ የሚያከሽፈው እዮር ይሆናል። የመመረጡ መክሊት ቅባዕው ራሱ ተጋድሎውን ፈጽሞ ትንቢት እንደተነገረላት የፈጣሪ ጥበብ የሰራው ቅድስና ዕውን ይሆናል። ኢትዮጵያ ሰላም ትሆናለች። በዬአቅጣጫው ቱኩ ቱኩ የሚለው ጎርፋማ አረፋትም በፈጣሪ ሃይል ይሰክናል። በደቦ የመታመሱም ብክነት በፈጣሪ ታምራት ድራሹ ይጠፋል።

እዮባዊነትን ከተሰነቀ፤ አደብ ከተዋጠ ማግስት አምሮና ተውቦ ያብባል - ያሰብባል። የሰው ልጅ ከህግ በላይ መሆኑን ወቅት ሊፈቅደለት ቢችልም ፈጣሪ ሲፈቅድ ግን ከመንበሩ አውርዶ እንደማንኛውም ተርታ ዜጋ ደረጃውን ያሳውቀዋል።

ይህ ታምረኛ ዘመን ያሳዬን ይህን ነው። በራሳቸው ፈቃድ ከፍ ክፍ ያሉትን ዝቅ አድርጎ፤ በራሱ ፈቃድ ከፍ ያደረገውም መንበሩን አደላድሎ አሳይቶናል። ታናሾች በብዕራቸው ቀለም ብቻ ሲያሸንፉ ነገሩ የፈጣሪ ስለመሆነ ልብ ያለው የለም። በቅኖች መንፈስ እሱ ምንጊዜም ህያው ነው። ቅኖች አዳፋ ቢለብሱም፤ ትቢያ ላይ ቢገኙም፤ እሱ የሚያረብላቸው የሚያበራላቸው መልካም ነገር ግን ማንም አይወስድባቸውም - አለ። 

በሳጅን በረከት ስምዖን በቁጥጥር ስር መዋል የሚሊዮን እናቶች ወህ ብለው እንቅልፍ ተኝተው ያድራሉ። የክንፈ የደህንነት ማሰጥልጠኛ የበቀል መወጣጫ እስር ቤቶችም አረፈዋል። 

ትውልድን በተንኮል፤ በሸር፤ እና በሴራ የማደረጃት፤ የመምራት ትልምም እንሆ እንኩት ብሎ ደቋል። አንድ ጋኔል ብቻ ሳይሆን ሰባት ጋኔል ነው በቁጥጥር ሥር የዋለው ከእነ ግብረ አበሩ። 



የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ስንበት ከማን ጋር እንደሆነ ፈጣሪ ነግሮናል፤ አሳይቶናል፤ አሁን ደግሞ ዋናው ዲያቢሎስ ከክናዱ ጋር ወደ ክነቱነት ወርዷል። ተመስገን! ከህግ በላይ ማንም የለም። 
https://www.youtube.com/watch?v=76IFoT-5yrg&t=582s


አፈሬ ነው መስመሬ(23 06 2018)


ቅንነት ያሸንፋል!

የኔዎቹ ኑሩልኝ

መሸቢያ ጊዘ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።