ህግ በራስ ላይ እንዲህ ተፈጻሚ ሲሆን ተስፋ ማደሪያ ይኖረዋል።
እንኳን ደህና መጡልኝ። ህግ በራስ ላይ እንዲህ ተፈጻሚ ሲሆን ተስፋ ማደሪያ ይኖራዋል። „ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።“ ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.02.2019 ከእመ ዝምታ ከሲዊዝሻ። „ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=yIzEROYdwoE #EBC ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የጉዲፈቻ ልጃቸውን ህጋዊ አደረጉ፡፡ „ለተባረከች አገር የተባረከ ትውልድ“ ዓላማው አድርጎ የተነሳው እሸቱ መንፈስ እንሆ እንደ ማንኛውም ዜጋ በፍርድ ቤት ተገኝተው ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እና ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከ5 ወራት በፊት በጉድፊቻ የተረከቡትን ልጃቸውን በህጋዊ ውሳኔ መቀበላቸው ኢቢሲ ዘግቧል። ህግን እንዲህ በሁሉ ዘንድ እኩል ተፈጻሚ ሲሆኑበት ተስፋ ማደሪያ ይኖረዋል። ተስፋም መብቀያ ይኖረዋል። ተስፋም ጥግ ይኖረዋል። ተስፋም ትውልድ ይሆናል። የትውልድ የመንፈስ ብክነትም በዚህ መልክ መልክ ቅጥ ለማስያዝ ተግባሩ ትራስ ይሆነዋል። ትውልድም ከሚሰማው ይልቅ የሚያየውን ስለሚያምነው በሚያምነው ልክ ትውልዳዊ ድርሻውን ለማሳ...