ልጥፎች

ዴሞክራሲ ሲቀርጡበት። ሳይቀጥሩበት ሳይቆርጡበት።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዴሞክራሲ ሲ ቀ ርጡበት። ሳይ ቀ ጥሩበት ሳይ ቆ ርጡበት። „ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ በመከራቸውጊዜ ግን ተነስተህ አድነን ይላሉ።“   ትንቢተ ኤርምያስ ፪ ቁጥር ፳፯ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie 20.02.2019 ከእም ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ዴሞክራሲ ነጭ ከረሚሎ ነው። ሁሉ ይወደዋል። ሁሉም ይሳሳለታል። ሁለም ሰፍ ብሎ  የትናጋው ማሟሻ  ያደረገዋል። እስታሁን ባለው ዘመን ስልጣንን ፈቅዶ በማስረከብ ኮ/ጎሹ ወልዴን አይተናል። የራስን ክብር ዝቅ አድርጎ ሌላውን ከፍ በማድረግ በዶር ለማ መገርሳ አይተናል።  እንዲሁም ሲነሪቲውም የመሆን መቻል አቅሙም እያለ እሱን እለፈኝ ብሎ ለኢትዮጵያ ሲባል እራስን ገርቶ በመገኘት ደግሞ በአቶ ደመቀ መኮነን አይተናል፤ የህውሃት የቆይልን ተማህጽኖ እያለም ግን በቃኝ ብሎ ሥልጣንን በፍሰሃ በማሰረከብም በአቶ ሃይለማርያም ደስአለኝም አይተናል። እንደ ድርጅትም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ታሪኩን አሳልፎ በመሸለም እረገድ ብዴን አንደኛ ነው ዲከርድም በጣሽ ነው። ባይሆን ...  ሌላው የተወካዮች ምክር ቤት አብዛኛው እጅ የ108 ድምጽ ተቀብሎ ጠ/ሚሩ በሚሰጡት መመሪያ ሥር ራሱን አስገዝቶም አይተናል ከኮንፌድሬሽኗ ትግራይ በስተቀር። ዴሞክራሲ መራራ መሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ ህውሃት በአካል ያዬታዬበት ዘመን ይህ ነው። ፈተናውን ድርጅቱ ማለፍ አልቻልም።  ወደቀ ። ስለምን በፊትም አልነበረበትምና። 33ቱ አባላቱ የተቃወሙትን፤ በአብዛኛው ድምጽ የጸደቀውን የተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ አሻም ብሎ በድጋሚ ውይይት በማድረግ የበላይ አካሉን ውሳኔ አልቀበልም ሲል ዴሞክራሲ ቀድ...

ውሃ በቀጠነ ቁጥር መበርገግ አያስፈልግም።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ውሃ በቀጠነ ቁጥር መበርገግ አያስፈልግም ። „ፈራህ አትፍራቸው።“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie 20.02.2019 ከእም ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        መንፈቀ ሌሊት - አንድ። እንዴት አላችሁልኝ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ አንድ ህልም አዬሁኝ። አንድ የተዘጋ በር ተከፈተ። ከዛ የተዘጋ በር ሲከፍት ሜዳ አለው። ሜዳው ላይ ትንሽ ሳር በቅሎበታል። አንድ ሰው ከአቶ ሃይለማርያም ደስለኝ ጋር አለ። ያ ሰው ግን ግርዶሽ ጥሎበታል።  እናም አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳሩን ገፋ ገፋ አድርገው ከሉት። አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ሳሩን ገለጥለጥ ሲያደርጉት በሰው ቁም ልክ የሆነ ጉድጓድ ተከፈተ። ከዛም አንድ ብረት በብረት የሆነ የተቆለፈ ትልቅ የብረት ሳጥን ወጣ። እንደወጣ ቀረብ ብዬ ላይ ስፈልግ በሌላ አቅጣጫ ከአንገቱ ላይ ራፊ ያደረገ አንድ እርቃነ ነፍስ የሆነ ከ9 እስከ 11 ዓመት ዕድሜ የሚሆን ታዳጊ ወጣት መለመላውን መጣ። ታዳጊ ወጣቱ ያልተገረዘ ነው። ታዳጊ ወጣቱ ዕብድ ነው።  እሱ ሲመጣ እኔ ፈርቼ ቦታውን ለቅቄ ወጣሁኝ። ስወጣ ያ ሳጥን ሳይከፈት ነበር ... ህልሙ የውነት ነው። ፍቱት… ኢትዮጵያ መንፈቀ ሌሊት ላይ ነው ያለችው። ·        መ ንፈቀ ሌሊት - ሁለት። ያው የማለዳ ቁርሴ የሳተናው ድህረ ገጽ ነው። በርከት ያሉ ጹሑፎች አዬሁኝ። ትንሽ አነበብኩኝ። ስለ ጠ/ሚር አብይ አህመድ „ካህዲነት“ ጠንከር ያለ ጹሑፍ ወጥቷል። ሰለ ወዮልሽ አዲስ አባባም እንዲሁ። አሁን መፈናቀሉ...