ልጥፎች

ዕንባና የማስቲካ የፕሬስ ሴክራትርያት ውሎ። /ቅኝት/

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዕንባና የማስቲካ የፕሬስ ሴክራትርያት ውሎ። „ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው  በደጆችዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ ልብሳቸውን  የሚያጥቡ ብፁዕን ናቸው።“ የዮሖንስ ራዕይ ምዕራፍ ቁጥር ፳፪ ቁጥር ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        እንደ ቅድምያ … ጤና ይስጥልኝ አዱኛዎቼ? እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያስ እንዴት ይዞሻል ቋዬ ቀመስ ወጀቡ ገጀራና ሜጫውስ? ከዛሬው ጉዳዬ በፊት ግን እንዴት ነው አቶ አህመድ ሼዴ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሆኑን? ይህ እንቆቅልሽ የዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ፖለቲካዊ ውሳኔ መፍቻ ሹክ የሚለው ይኖራል … ዕለቱን ተወራራሽ የሆኑ የሀዘን ድባቦችን እኛ እኛን ይፈታተሻሉ … ·        የጃዋርውያኑ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ልቦና በማስቲካ ተውኔት … https://www.youtube.com/watch?v=i-r7ACaC8Wk #EBC   ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ጐበኙ፡፡   የገጀራ እና የሜንጫ ቤተኛ የሆኑት አቶ ንጉሡ ጥላሁን አለቃቸው አቶ አባ ዱላ ገመዳ በአዬር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢነታቸው የዛን የበረራ ነገር ስንብት ለማድረግ በማይፈልጉት ከቶውንም አጥብቅው በሚጸይፉት፤ በሚሳለቁበት ቤተ ቅዱሳና ቦታ ተገኝተው  የእነዛን ሰማዕታት እዬቀፈፋቸውም ቢሆን ስንብት   https://www.youtube.co...

ውድ የአገሬ ልጆች አትጨነቁ፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና፤

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ውድ የአገሬ ልጆች አትጨነቁ አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና። „ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆቿዋም ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ፤ ልብሳቸውን የሚያጥቡ፤ ብፁዕን ናቸው፤ አምስቱ ውሾች ግን ከዚያች አገር ወጥተው ይሄዳሉ።“ የዮሖንስ ወንጌል ፳፪ ቁጥር ፲፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                           አምላክ አለው! ቅኖቹ የጹሑፌ ታዳሚዎች እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ እዚህ ደመንመን ብሏለኝ። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? ያን ግዙፍ መከራ ካስተናገድን ጉዳያችን ቅርባችን ላደርግን ወገኖች ዛሬ 8ኛ ቀኑ ነው። የሰውም ግፍ ስላለው ስለገጠመው መከራ ለመርሳት ጊዜው ገና ልጅ ነው። ምልክቱ ግን እዮራዊ ነው።   በአላዛሯ ኢትዮጵያ ብዙ ቃለ ምልልሶችን ሌሉትን ሙሉ አዳመጥኩኝ። ያው ይህ የበራራ አደጋ በመንፈሴ ውስጥ ትንሽ ተገስ እስኪል ድርስ እንዲህ ነኝ - እንቅልፍ አጣለሁኝ። አንድ ጊዜ አውሮፕላን አደጋ ከደረሰ በኋዋላም ተከታይ ይኖራል ብዬ ስለማስብ ይጨንቀኛል። ሌላው ደግሞ እዛው ኢትዮጵያ መሬት ላይ ተፈጽሞ እንኳን ምንም አይመስለውም። ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ብዙ ሰው መስጋት ብቻ ሳይሆን ልክ በቅንጅት ጊዜ የተሰማው ዓይነት በመንፈስ፤ በተስፋ መሟሸሽ አያለሁኝ። አገር እኮ ...