ልጥፎች

ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውድቀት እንጂ የዴሞክራሲ ተስፋ የልቅና ምህንድስና አይደለም።

ምስል

ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውደቀት እንጂ የተሰፋ ልቅና አይደለም። {ክፍል አንድ}

ምስል
ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውደቀት እንጂ  የተስፋ ልቀና አይደለም ። ክፍል አንድ። „የደከሙት ን እጆች አበርቱ፤   የላሉትን ም ጒልበቶች አጽኑ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፴፭ ቁጥር ፫ ዝግጅት ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 06.06.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። v ተስፋ ይ ራመዳል። v ተስፋ ያ ራምዳል። v ተስፋ ያ ጓጉዛል።   v ምን ያህል እንደተጓዝኩኝ አላውቀውም? v ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም? v አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸልኝ። v ተስፋን እጠብቃለሁኝ { የመጀመሪያው ተስፋ መጸሐፌ ላይ የመጨረሻ ሽፋኑ ላይ ላይ የጻፍኩት ነው} የትውስት አይደለም እንደማለት። ·        እ ፍታ እጅግ የምትናፍቁኝ የአገሬ ልጆች፣ የኔታዎቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? የአብይወለማ መንግሥት ስለ ዴሞክራሲ በቀን የሚናገርበት ዝክረ ቋት ቢሰናዳ ሞልቶ ይፋሳል። ዴሞክራሲ በዚህ በቀን ስንት ጊዜ የመግለጫ አክሮባት በሚሰራበት፣ እንዲሁም ዴሞግራፊ አውራ መርህ በሆነበት ድርጅት ፍትልክ ሊል ከቶውንም አይችልም። አለበደምና@ፈጽሞ። መሬት ያለካስማ አይቆም፤ ዴሞክራሲም በዴሞግራፊ ፍልስፍና አይቆምም ። ሁለቱ የተለያዩ መነገደች ናቸውና። ጨላማ ከብርሃን ጋር ግጥም የለውም። ዴሞግራፊ ለዴሞክራሲ ፍልስፍና ቀራንዮ ነው። ·        የ አገር ጭንቅላት። ዴሞክራሲ የመሰረቱ አገሮች ስከነቱ ያለው ከሥርዓቱ ጭንቅላት ነው። አውቆ - አበድም፤ እብድም፤ መንፈሱ ያልተረጋጋም፤ የኢጎ አርበኛም፤ የዝና ዘመናይም፤ ...

በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ቃሬዛ ላይ ነው። (የወግ ገበታ 05.06.2019)

ምስል

በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  በ መሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።   ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱“ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie 05.06.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። በ መሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። ውስጥህን እዬበወዘ ውስጥነት ሰጠሁኽ ምን አልባት ገና ፅንስ ላይ በእናታቸው ማህጸን ላሉት ላይገለጥ ይችል ይሆናል። ሰ ው ለሆነ ሁሉ ግን ይህ የአለመኖር ዕጣ ፈንታ ወይንም እያሉ ቀፎ ለመሆን መፍቀድ ከጽንስነት የማይሻል ተፈጥሮ ነው ላርባ ላይ ለላ ቢገልጹት መሃንዲሶቹ መልካም ነው። የ ሚገርመው እነሱ የሚያስቡት ኢትዮጵያዊ ዜጋን እንደ ፑፓ ነው። ድፍረት ነው ይህ በራሱ። በግርዶሽ ትዕይንት እያዛሉ የልባቸውን ይከውናሉ። ለ ሰው ልጅ አንገት ነው ወይንስ ሃብል ነው የሚያስፈልገው? ይህን ጥያቄ መመለስ ያለበት ሁሉም መሆን አለበት። 100ሚሊዮን ህዝን ላርባ ነህ ማቹሪቲ ይጎድልሃል የማለትም ያህል ነው ዴሞግራፊ ለእኔ። ዴሞግራፊ ፍልስፍና እያራመድክ በምርጫ ተወዳድረህ ታሸንፋለህ ብሎ ነገር ከቧልትም ያለፈ ሃጢያትም ነው። ዛ ሬ የማከብራትን ብዙም ፈተና የተቀበልኩባትን የክብርት ወ/ት ዳኛ ብርቱካን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ቃለ ምልልሱ ራሱ የተደረገበት ቦታ   የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ነው። የ ጠ/ሚሩ ቢሮ በሚሰጠው አመራር የሚሰጥ ሁለተኛ የከፍተኛ ዜጎች ቃለ ምልልስ መሆኑ ነው። ይህ የቤተመንግሥት ደረጃ ለOBN መሰጠቱንም በይበልጥ ያረጋገጥ...