ልጥፎች
መጸሐፍቶቼ ልጆቼም ነፃነቶቼም ናቸው!
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል" መጽሐፈ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር፱ ተስፋ ይመጣል ተስፋም ይሄዳል ተስፋም ያነጉዳል ተስፋም ይክሳል ... አንድ ቀን ... ይጠበቃል! እንኳን በደህና መጡልኝ መጸሐፍቶቼ ልጆቼም ነፃነቶቼም ናቸው! ልጆችን መንከባከብ ደግሞ የማህበረሰቡ ተግባር ነው። ተስፋችንም በፖለቲካ ሊሂቃኑ ሳይሆን በማህበረሰባችን ብቻ ነው! v እፍታ። የኔዎቹ የኔታዎቼ እንዴት ናችሁ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? ማህበረሰባችን በዬአካባቢው በመንፈስ የታሠሩትን ልጆቹን ማስፈታት ይኖርበታል። ስደት የምንኖረው ባለመክሊት ልጆቹም በስውር ካቴና ነው የባጀነው ውጭ አገር። አብሶ አማራነት ቀራንዮ ነው ። ማህበረሰባችንም እራሱን በሽንገላ ሳይስከበብ ነጥሮ መውጣት ይኖርበታል። ስለሆነም ለድጋሚ ዕስርም ራሱን ማሰናዳት እንደሌለበት አበክሬ አስገነዝባለሁኝ። ታገሽነቱ በተግባር ይመሳጠር። አሁን ያለው የአገር ውስጥም የውጭ ጭቆና ዓይነት እና ስልትና የጭካኔ ተመክሮ የጫጉላ ሽርሽር እንዴት ሁለቱን አቀናጅቶ ጭቆናን ሉላዊ በማድረግ ንቁ፤ ትጉህ ኢትዮጵውያንን በሁሉም አቅጣጫ ማፈን እና ሰላ ማቸውን ማስጣት ይቻላል ነው ምክክሩ። ይህ ስለላ እሰከ አውሮፓ ህብረትም ይዘልቃል። ውሉም ጋብቻውም ይኼው ነው። ሞጋች ማህበረሰብ አይፈለግም። ግን ስንቱን አግልለው፤ ስንቱን ከጫዋታ ውጭ አድርገው እንደሚዘልቁት ወፊቱ ትጠዬቅ። ግሎባላይዜሽኑን በኢጎ አፍነው ማስቀረት ከቻሉ ይሞክሩት። ጥቂት ሰዎች ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ... ግን እልፎችን ያፈራሉ ... ስለሆነም የአፈና...
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ እና የሚኒስትሪ ቀጣይ ዕጣን በሚመለከት የት/ሚር የወሰደው ደፋር እርምጃ ጥሩ ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የት/ሚር ደፋር እርምጃ ጥሩ ነው። „ወርቅና ብዙ ቀይ አንቚ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት። መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭“ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እፍታ በመሆን ውስጥ ያለ መኖር ሥነ - መኖሩ ዕውቅና ያለው ነው። በመኖር ውስጥ ያለ አለመኖር ደግሞ ሥነ - መኖሩ ስሩዝ ነው። በመሆን ውስጥ ያለ መኖርም ሥነ - ሰውነቱ ህልው ነው። በመሆን ውስጥ የሌለ መኖር ደግሞ ሥነ - ህይወቱ ተደፍሯል። በ መደፈር እና በማስ ደፈር ያለው ድልድይ ደግሞ እንደዬሰብዕናው ኩሰት ወይንም ጥንዙልነት ፤ ወይንም ቀጥነት ፤ ወይንም ዝልቅነት ይወሰናል። ድልድዮ ደግሞ እውነት ከሆነ ከቀጥነት ከዝልቅነት ጋር ሲዋደድ፤ ዕብለት ከሆነ ግን ጥንዙልነት እና ኩሰት ይገጥማዋል። በዚህ ማህል አዲስ ትውልድ፤ ተተኪ ትውልድ፤ መጪ ትውልድ ደግሞ አለ። ይህ የትውልድ ሂደት ባለማቋረጥ ሲከታታል ቁጬታው በቁጭታ መዳህነት ከተባዛ ወይንም ከተደማመረ ትውልድ ተከታይም፤ ተተኪም፤ መጪም ትውልድ የብክነት አንፓዬር ሥጦታ ይቀርብለታል። በዚህ ስምጠት ባናወዘው የብከነት ኢንፓዬር ውስጥ ማግሥትን ማሰብ ይከብዳል። መሰረታዊ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው በቀጣይ ትውልድ ላይ ልብ ያለው ተግባር ለመከወን ከብክነት የሚታዳግ፤ ጭምት ፤ ምራቁን የዋጠ እስተውሎት ይሻል። የወግ ገበታ። የሰሞኑ የት/ሚር ከግልቦ ንድፍ ወጥቶ እንደ ቀደመው የ8ኛ እና የ6ኛ የሚኒስትሪ ፈተናን አሰጣጥን፤ የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የደረጃ ልክን ጨምሮ፤ የማትሪክ ፈተና አሰጣጥን ለማሻሻል ወይንም በምልሰት ራሱን ወቅሶና፤ ራሱ...