ለምን ሲሰላ።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „እግዚአብሄርን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች። የኃጣኣን ዕድሜ ግን ታሳጥራለች።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 10 ቁጥር 27 ለምን ሲ ሰ ላ። ሥርጉተ © ሥላሴ Sergute © Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። 04.01.2020 በኢትዮጵያ ተሰምተው የማይታወቁ የጭካኔ ድግግሞሽ በዙር እያዬን ነው። የኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ የጭካኔ ፋክክርም አያለሁ። ሥልጣን ጠቅልሎ መያዝ ብቻ ሳይሆን አማራ ክልል አቅም ብቅ እንዳይል በባሩድም በካቴናም ቅጣቱ ድንበር የለሽ ነው። ይህም ሆኖ የአማራ ክልል በባዶ እጁ ሆኖ ይቀናበታል። ስለዚህም አቻዊ ጭካኔ ተከስቶ ክልሉ ይወገዛል። ኦሮምያ ላይ የሰው ልጅ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ አማራ ክልል ላይ ለጥናት የሄዱ ንፁኃን በድንጋይ ተቀጥቅጠው ተገደሉ። ኦሮሚያ ክልል ላይ ቤተክርስትያን ሲቃጠል አማራ ክልል ላይ መስጊድ ይቃጠላል። ኦሮምያ ላይ መፈናቀል ሲኖር አማራ ክልልም ላይ መፈናቀል ይከሰታል። ኦሮምያ ላይ የፓርክ ቃጠሎ ሲኖር አማራ ክልልም ላይ ይኽው መሰሉ ይከሰታል። በኦሮሚያ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ታግተው የደረሱበት ሁኔታ አይታወቅም ሲባል አማራ ክልል ህፃናት ታግተው ይረሸናሉ። በዚህ ውስጥ ኦሮምያ ለሚፈጠረው ቀውስ የኦዳ መንግሥት ዝምታን ይመርጣል፣ አማራ ክልል ሲሆን ደግሞ ግሎባሉ ዓለም እንዲያውቀው ከጠሚር ጀምሮ ልብ የተገጠመላቸው ወጥተው ሲያወግዙ ይደመጣል። · ...