ርህርህና ተሰደደ። እግዚአብሄርም አለቀሰ።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። እርህርህና ተሰደደ። እግዚአብሄርም አለቀሰ ። „በምድር ላይ የሰው ህይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?“ (መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 7 ቁጥር 1) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ©ሲዊዘርላንድ 10.01.2020 እንዴት ናችሁ ቅኔዎቹ የአገሬ ልጆች ? ደህና ናችሁ ወይ? የኢትዮጵያ ፖለቲካ የከረባት እና የገበርዲን ብቻ በመሆኑ ስሞግት ኖርኩኝ። ደጉ ዘሃበሻም፤ ደጉ ሳተናውም ፈቃዳቸውን አልነሱኝም። በራሴ ግራቀኝ ሚዲያም በጸጋዬ ድህረ ገጽ እና ጸጋዬ ራዲዮም በኽረ አጀንዳ ነበር። በሌላ በኩልም በአገረ ኢትዮጵያ ዕንባ ሲበረታ፤ የዕንባ ቅልቅል ሲ ገ ን የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ አድምጡልን፤ እባካችሁ እርዱን እያልኩ በዬደጁ ስባትልም ምክንያት አድርጌ አቀረብ የነበረው የሴቶች አቅም ዕውቅና አለመሰጠቱ ነው የኢትዮጵያን ችግሩን ያበራከተው፤ ሴቶችም ባለቤት ያጡበት መሰረታዊ አመክንዮ ሴት ወሳኝ ሊሂቃን ወደፊት ባለመምጣቸው ነው እል ነበር። ሴቶች በክህሎታቸው ብቃት ሥርዓቱን የመ ግ ራት፣ የመለወጥ አቅም አላቸው፤ ዕድሉን ካገኙ ሴቶች በጸጋቸው ጸጋ አትራፊ የርህርህና ማህንዲስ የመሆን ተስፋ ይኖራዋል ነበር ሙግቴ። ጠሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ሴቶችን ወደፊት አመጡ ብዬ ደስ አለኝ። ከቀደመው ሰብዕናቸው ተነስቼም ተስፋ ነበረኝ። ብዙም ጽፌበት ነበር። ያን ስለምን እንዳደረጉት አሁን አሁን የራሱ ዕድምታ እንዳለው እዬገባኝም ነው፤ ያው የወደቀውን ኢህዴግ የግንባራቸውን ሥም ለማደስ ነው የተጠቀሙበት። አሁን ሙሽራው ኢህዲግ ነው ያለው። የሆነ ሆኖ በዛን ጊዜ እኔ ብቻ ሳልሆን ዓለም...