ልጥፎች

ዘመነ - የመቃብር ሥፍራ፤

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡ። ዘመነ - የመቃብር ሥፍራ፤ እዬሞትክ ጠብቀኝ/ ጠብቂኝ የአብይዝም 50በ60 ያረጠ ፖለቲካ። „እኛ ከጨለማ የተነሳ በሥርዓት መናገር   አንችልምና፤ የምንለውን አስታውቁን።“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 37 ቁጥር 19) ሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie 24.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ መኖርን የነጠቀው የመቃብር ሥፍራ ዘመን ይሁነኝ ተብሎ በቀኝ በግራ ገመናው እንዳይጋለጥ እንክብካቤ እዬተደረገለት ነው። አራስ ቤት ወይንስ ጫጉላ ጊዜ እንበለው ይሆን? በቀዳዳው ሁሉ እንደፍናለን ብለው ተደማሪ ነፍሶች ታከቱ። ብዕሩም ብራናውም፤ ማይኩም መድረኩም „ተስፋ አለን“ እያሉ እልልታውን ያስከንዱታል። ፍልሰፍናውንም ቅብጥ እና ቅልጥ ያደርጉታል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ሠርግ ላይ ወይንም ቅልቅል ላይ ወይንም መልስ ላይ ወይንም ግጥግጥ ላይ ያለች ይመስላቸዋል። ከንቱነት! ግን ህሊና እግር ወይንስ እግር ህሊና ቦታ ተለዋውጡ ይሆን? የእኔ እህት ብትሆን? የእኔ ወንድም ቢሆን? የእኔ ልጅ ብትሆን? የእኔ ልጅ ቢሆን ተብሎ እንዴት አይታሰብም? እንደ እኔ ይህ ሰሞን አኮ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ የሚወለበለብበት ጊዜ ነበር። ሌሎችም የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መኖር ነበረበት ይላሉ። እነዛ ቀንበጥ እና ሸባላ ልጆቻችን የት እንደ ደረሱ? ምንስ እንደሆኑ እኛ እማናውቀው ነገር የለም። ምን እንደሆኑ ቤተሰብ የሚያውቀው ነገር የለም። ምን ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ወላጆች አያውቁም። ወላጆች ልጆቻቸውን ማጣታቸው አልበቃ ብለው ህሊናቸው ደግሞ ይቀጣል፤ ይቀጠቀጣል። አማራነት ግማድ ነው! ዘመዶች ሆኑ እንደ ትውፊታችን ጎረቤቶች፤ ህሊና ያላቸው መምህራን...

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዲስክርምኔሽን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዲስክርምኔሽን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት። „ኃጢያት ብተሰሠራ ምን ትጎዳዋለህ? መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ?“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 35 ቁጥር 6) ሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie 21.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ይድረስ ለኢትዮጵያዊው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፤ አዲስ አበባ። ግልባጭ ለ ዶ / ር ዳንኤል በቀለ  - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን - ኮሚሽነር፤ አዲስ አበባ። ·         ልዑል እግዚአብሄር ለጥያቄዬ ተደማጭነትን ይሰጠው ዘንድ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ጥቅስ ላጠይቅለት። „ከግፍ ብዛት የተነሳ ሰዎች ይጮኃሉ፣ ከኃያላን ክንድ የተነሳ ለእርዳታ ይጠራሉ።“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 35 ቁጥር 9) እንሆ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ የቅድሰት ድንግል ማርያም ፍቅር በጭነት ዚታ መኪና በድፍጠጣ በበላዩ ላይ ተሄደበት። እግዚኦ! ማህከነ! ተሳህለነ! ·         በ ር። እንዴት ናችሁ የአገሬ ቅኖች - ቅኔዎች? ደህና ናችሁ ወይ? ትንሽ የንፋስ ሽውታ በቀዝቃዛ ርጥበታማ አዬር፤ ጭሮሮ ሆነው መለመላቸውን የቆሙቱን እጽዋት ባልስ መሰል ዳንስ ያሠለጥኑታል። ግራጫማ ጭስ መሰል የሰማይ ትንፋሽ የአዬሩን ውቅያኖስ በስሱ ይቀዝፈዋል። ልዕልት ጠሐይም በልግመት ብቅ ብላለች - እንደ ነገሩ። ለ ብ ታን እንኳን ነስታ። በዚህ ማህል ጉርብጥብጥ ብሎኝ ስለሰነባበተው እስካንዳንብያ አገር ያለ የሚመስለው የኢትዮጵያዊ ብሄራዊ   የምርጫ ...