ልጥፎች

"እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱልን!" አናባቢም ተነባቢም አምክንዮ!

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። " እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱልን !" „ከግፍ ብዛት የተነሳ ሰዎች ይጮኃሉ፤   ከኃያልን ክንድ የተነሳ ለእርዳታ ይጣራሉ።“ ሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 26.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ይህን ዘመን እናልፈው ይሆን? ለካንስ ፌስ ቡክ እንዲህ ህይወት ነው። እንዴት ፈርቼው እኖር መሰላችሁ ውዶቼ። " እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱ !" ዘመንን አናጋሪ፤ ዘመንን መካሪ፤ ዘመንን ገሳጭ፤ ዘመንን መርማሪ፤ ዘመንን ተርጓሚ፤ ዘመንን አናባቢ፤ ዘመንን ተነባቢ ያደረገ ጉልበታም አመክንዮ ነው። ሰለዚህም ነው ወደ ሌላውን የጹሑፍ እርማቴ መሄዱን ትቼ ይህን ከቶውንም የማይገኝ የውስጥነት ቅኔ ላጋራችሁ ብዬ የወሰንኩት። የትውልድ የርህርህና ሥጦታ እንዲህ ባለ የመሆን ውስጥነት ነው ሃዲዱ መዘርጋት አለበት። ብዬ አምናለሁኝ። እራስን ፈቅዶ መስጠት። እራስን ወዶ ለስቃይ አሳልፎ ማስረከብ። እንደምን ያለ ድንቅነት ነው? ዕውነት እንዲህ በፍጡራን ሲገኝ እንዴትስ አያጽናና። ብሩክ የሆነ መልዕክት። አደራንም ያወጣ። ትውፊትም መሆን የሚችል። የበቃ!   ለክርስትና እምነት ተከታዮች የጌታችን መዳህኒታችን የእዬሱስ ክርስቶስን ጽዋ የተቀበለ መልዕክት ነው። ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሃጢያት ሲል ነው ሞትን የቀመሰው፤ የተገረፈው፤ የተሰቀለው፤ የተንገላታው። እህቶቻችን ሆይ! ስቃያችሁን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ነው መልዕክቱ። ውስጥን እንዴት የሚመረምር ነው። በፍጽምና ሩህን የሚፈትሽ ኃያል መልዕክት አለው። እንዲህ ዓይነት ሰብዕናም አለ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ። ይህ መልዕክት ለየኢትዮጵያዊነት ልዩ ማ...

ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች /ከቢቢሲ የተጋራ/

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „አቤቱ ሰውነቶቼን አሁንም ለአንተ ሰጠሁኝ።“ (መጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 4 ቁጥር 12) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ስለአዲሱ ኮሮና ቫይረስ ማወቅ የሚገባዎ ነጥቦች   እንዴት ናችሁ ቅኔዎቹ የአገሬ ልጆች ደህና ናችሁ ወይ? እኔ ደህና ነኝ። ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ዛሬ ወሳኝ ነጥብ አንስቷል። ስለ አዲሱ ኮሮና በሽታ። ጤናችሁም፤ ደህንነታችሁም አጀንዳዬ ስለሆነ እነሆ ሼር አድርጌያለሁኝ። እናንተምስ ሳትደክሙ መልዕክቱን ሼር አድርጉት።   „በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተከሰው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ ወደ በርካታ አገራት እየተዛመተ ይገኛል። አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን፣ አውስትራሊያ በሽታው መታየቱን ሪፖርት ካደረጉ አገራት መካከል ይገኙበታል። የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይዛመት እየወሰደ ስላለው እርምጃ እና ስለ ቫይረሱ የሚከተለውን መረጃ አስተላልፏል። ·        ኮሮና ቫይረስ ምንድነው ? የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው። የቫይረሱ   መተላለፊያ መንገዶች በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ። ·        የበሽታው ምልክቶች...