"እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱልን!" አናባቢም ተነባቢም አምክንዮ!
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
"እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱልን!"
„ከግፍ ብዛት የተነሳ ሰዎች ይጮኃሉ፤
ከኃያልን ክንድ የተነሳ ለእርዳታ ይጣራሉ።“
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
Sergute©Selassie
26.01.2020
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ይህን ዘመን እናልፈው ይሆን? ለካንስ ፌስ ቡክ እንዲህ
ህይወት ነው። እንዴት ፈርቼው እኖር መሰላችሁ ውዶቼ። "
እኛን ውሰዱና እህቶቻችን መልሱ!" ዘመንን አናጋሪ፤ ዘመንን
መካሪ፤ ዘመንን ገሳጭ፤ ዘመንን መርማሪ፤ ዘመንን ተርጓሚ፤ ዘመንን አናባቢ፤ ዘመንን ተነባቢ ያደረገ ጉልበታም አመክንዮ ነው።
ሰለዚህም ነው ወደ ሌላውን የጹሑፍ እርማቴ መሄዱን ትቼ ይህን
ከቶውንም የማይገኝ የውስጥነት ቅኔ ላጋራችሁ ብዬ የወሰንኩት። የትውልድ የርህርህና ሥጦታ እንዲህ ባለ የመሆን ውስጥነት ነው ሃዲዱ
መዘርጋት አለበት። ብዬ አምናለሁኝ። እራስን ፈቅዶ መስጠት። እራስን ወዶ ለስቃይ አሳልፎ ማስረከብ። እንደምን ያለ ድንቅነት ነው?
ዕውነት እንዲህ በፍጡራን ሲገኝ እንዴትስ አያጽናና። ብሩክ የሆነ መልዕክት። አደራንም ያወጣ። ትውፊትም መሆን የሚችል። የበቃ!
ለክርስትና እምነት ተከታዮች የጌታችን መዳህኒታችን የእዬሱስ
ክርስቶስን ጽዋ የተቀበለ መልዕክት ነው። ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሃጢያት ሲል ነው ሞትን የቀመሰው፤ የተገረፈው፤
የተሰቀለው፤ የተንገላታው። እህቶቻችን ሆይ! ስቃያችሁን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ነው መልዕክቱ። ውስጥን እንዴት የሚመረምር ነው።
በፍጽምና ሩህን የሚፈትሽ ኃያል መልዕክት አለው። እንዲህ ዓይነት ሰብዕናም አለ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ። ይህ መልዕክት
ለየኢትዮጵያዊነት ልዩ ማህደረ - ማዕረጉ ነው።
እንደምንስ ያለ
ልብ
የሚነካ፣ የሚፈትን፣ ውስጥን የሚጠይቅ እኛዊነት ነው። የእርህራሄው መጠን አጥንት ድረስ ይሰማል። እናት አንጀት የሚባሉ ተባእትን ሁሉ እነኝህ ወጣቶች ይወክላሉ። እንደምንስ አይነት ከተባረከ ማህፀን ነው የወጣችሁት? ከእንደምንስ ያለ አብራክ
ይሆን የተገኛችሁት። ብሩክ ቅዱስ ሁኑ። አሜን! መቼም ዘንድሮ በሁሉም ነገር ሆድ ብሶኛል፤ እያነበብኩኝም እዬጻፍኩም ዕንባዬን መቆጣጠር በፍጹም አልቻልኩም። የመልዕክቱ ትህትና ቃለ ወንጌል
ነው። ህይወት።
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የማያቸው ንጹህ ተሳትፎዎች ስድብ
የለባቸውም፤ ቂም የለባቸው፤ ጥላቻ የለባቸው፤ መተላለፍ ብዙም የለባቸውም። ሰዋዊነት ባመዛኙ ጎልቶ እና ጎምርቶ በጉልበታም
መልዕክቶች፤ በጠንካር የኪነ ጥበብ ብቃት የተቀመሩ ፖስተሮች ናቸው እኛና እኛን እትብታዊነት በአንድ የዕንባ ማዕዶት ላይ ያገናኜን።
መከራችን መገናኛ ሰራ። ከዚህ የዕንባ ማዕድ ያፈነገጡ ሊኖሩ ቢችሉም ነገር ግን ያለው ተሳትፎ እጅግ የሚደንቅም የሚገርም ብቁ
ነው። ከልጅ እስከ አዋቂ ድረስ ሁሉም ውስጡን እያስጎበኜ ነው።
በሁሉም ብመሰጥም የእናት ጋዜጠኛ እዬሩሳሌም ተ/ፃድቅ
ፕሮግራም እዬመራች ዕንባዋን መቆጣጠር አለመቻል፤ የልጆች ተሳትፎ እና የእነዚህ ሦስት ወጣቶች ውስጥነት እጅግ ነፍሴን የገዛው ሁኔታ ነው። በሌላ
በኩል የውጭ ዜጎችም ዕንባችን መጋራታቸው ብሩክ ዜና፤
ልልፈውም፤ ልተውውም፤ ቸል ልበለውም ሊባል የማይችል ነገር
ነው። በዚህ ማህል ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ደግሞ ወደ ኤርትራ እንዳቀኑ እዬተደመጠ ነው። ምን ነካቸው ያሰኛል። በቃ
እንዲህ ዓይነት የጭንቅ ቀን ሲመጣ ሹልክ ይላሉ። እንግዲህ መግለጫው ሊሰጥ ከታሰብ እሳቸው በሌሉበት የተፈጸመ እንዲባልላቸው
ይሆን?
የሆነ ሆኖ ልዑል እግዚአብሄር እረኛ ለዚህ ዕንባ ይስጥ።
ልዑል እግዚአብሄር ካዘኑት ጋር የሚዝን እረኛ ይስጥ። ልዑል እግዚአብሄር ከተጨነቁት ጋር የሚጨነቅ ሙሴ ይስጥ። ልዑል
እግዚአብሄር ከተሰቃዩት ህዝቦቹ ጋር አብሮ የሚሰቃይ የእኛነት አለቃ ይስጥ። አሜን! ሁሉም ነገር ሆድ ያስብሳል። ሁሉ ነገር
ያባባል። ሁሉ ነገር ይጨንቃል። ዘመኑም ከጨለማ በላይ ይጨልማል። ዘመነ
የመቃብር ሥፍራ!
ክፉነት ነግሶ ርህርህና ተሳደድ። ጭካኔ ነግሶ ደግነት
ተገለለ። አረመኔነት ገዝፎ ሰዋዊነት መጠጊያ አጣ። ህዝብ ባለቤት አጣ። ግርባው ብአዴን የተጎጂ ቤተሰቦች ሄደው ሲያነጋግራቸው
እንክብካቤ ማድረግ ሲገባው „የፖለቲካ መጠቀሚያ አደረጋችሁት“ ብሎ እንዳሰናበታቸው አዳምጫለሁኝ። አርዮሳዊነት! ከቶ ከሰው ዘር ይሆን የተፈጠሩትን?
የልጅ አድራሻ በምን ሁኔታ ላላወቀ ወላጅ ይህ መልስ ነውን?
አደራ የተሰጠው እኮ ለመንግሥት ነው። መንግሥት የሚያስጨንቀው እሱ ዝብርቅ፤ ብርቅርቅ አመራር ወይንስ የእነዚያ ተስፋቸው የጨለመ ስቃይ
ውስጥ ያሉ ልጆች? የትኛው ነው የሚቀድመው? የታመመ በሽተኛ ዕሳቤ። ሁለመናው ድውይ ሆነ። የዳነ የተረፈ ነገር ጠፋ።
· ክውና።
ሁሉን አይደለም ያቀርብኩት ጥቂቱን ነው። ይህን ንጽህና
አማላካችን ይጠብቅልን። ይህን ርህርህና ያለምልምን። እንዲህ የምንተዛዝንበት የድንግልና ዘመን ያምጣልን። አሜን!
ቸር ወሬ ያሰማን አምላካችን። አሜን።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ