ልጥፎች

„ጋዜጠኝነትን እንደ መንገድ እንጂ እንደ ግብ አላዬውም።“ (ጋዜጠኛ ሙኒራ አብደልመናን አውል)

ምስል
    „አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል፤ በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል? በቅንነት የሚሄድ ጽድቅንም የሚያደርግ በልቡም ዕውነት የሚናገር“ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 14 ቁጥር 1 )   ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና የሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ   የሚራራ።   „ ጋዜጠኝነትን እንደ መንገድ እንጂ እንደ ግብ አላዬውም።“          (ጋዜጠኛ ሙኒራ አብደልመናን አውል) ·        መነሻ ምርኩዜ። https://www.youtube.com/watch?v=mm3mFckIO_8&t=68s Ethiopia: EthioTube አፈርሳታ - Lidetu Ayalew : ልደቱ አያሌው | February, 2021 104,436 views • Premiered Feb 13, 2021 ·        ምክሬ። እናት የመጀመሪያዋ ትምህርት ቤት ናት እላለሁኝ። እናትም የመኖር መቅድመ የፊደል ገበታ ናት እላለሁም። እናት የመጀመሪያዋ ዬህይወት ጎዳና ናት እላለሁኝ። እናት የመጀመሪያዋ ሉዓላዊ መምህር ናት የሚል ፍልስፍናም አለኝ። ትክክለኝነቱን ሁሉም ከእናት ማህጸን ስለተፈጠረ መመዘን እና መወሰን የእያንዳንዱ የሥርጉትሻ ብራና ቅን ታዳሚ መብት ይሆናል። እናቴ እብዬ ሆዴ በማህበራዊ ግንኙነቴ ውስጥ ከምትለግሰኝ ምክር አንዱን ላጋራ። „መጀመሪያ ስታይው የምትደነግጭለት፤ ከራስ ጸጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ውርር ካደረገሽ ያ ሰው፤ ያቺ ሴት የአንቺ የውስጥሽ የምትሆን ናት እና አትለፊው፤ አትለፊያት“ ትለኝ ነበር...

የለወጥ ሃሳብ እና ዘመነ ኦሮሙማ ...

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ማክሰኞ ዕለተ ተናኜ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   የለውጥ ሃሳብ።           የለውጥ ሃሳብ ሂደትን                 ማዕቀብ በመጣል ማስቆም                ወይንም የታቆረ ማድረግ                 አይቻልም። በፍጹም።                 ተፈጥሯዊ ነውና!   „በታካች ሰው እርሻ፤ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን   ቦታ አለፍሁ። እነሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፤ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል። የድጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“    (መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴፩) ·        በር።   ለእኔ በማሰብ ልቅና የአስተሳሰብ ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ። የነቃው የህሊና ክፍል አዲስ ሃሳብ ሲያፈልቅ ሃሳቡን የሚቀበል ህሊና፤ አዕምሮ ሊኖረው ይገባል። ይህ አዕምሮ ያፈለቀውን አዲስ ሃሳብ የሚመጥን የሰብዕና አቅም የሚኖረው ከአቅሙ ከራሱ በመመንጨቱ ነው።   አዲሱ ልቅና ያለው አስተሳሰብ/ ሃሳብ የትውስት ወይንም የብድር አይደለም። ስለምን? አዲሱ ዬአስተሳሰብ ልቅና ካለው ከራሱ ህሊና፤ የአዕምሮ የአቅም ፏፏቴ የመነጨ ስለሆነ ዲስፕሊኑን የመሸ...