ልጥፎች

የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ መሰላም መጡ። ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝማራ ለራህብ የሚራራ „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ·         የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት። የእኔ ሃሳብ ከሌላው የተለዬ ነው። በጦርነቱም፤ ጦርነቱን ለማስነሳት የነበሩ ቅድመ ጉዝጓዝ ሁኔታዎችን አስመልክቶም ለዬት ያሉ ሃሳብ ነው የነበረኝ። እራሱ አቶ ሴኩትሬ የማን ነበሩ የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። በ ኦነጋዊው ኦህዴድ ሰበር ሳይዋጡ እርጋታን ይጠይቅ ነበር ሁሉም ነገር። ከመቀደም ለመቅደም። ጦርነቱን አስመልክቶ ከብዙ ወዳጆቼ ጋር ተለያይተናል። አንዳንዶቹ የኦህዴድ ጥጋብ ፕሮፓጋንዲስት እንድሆንም ጠይቀውኝ ነበር። ድፍረቱ ቢገርመኝም። በምን ታምር? በምን ቀመር ሥርጉተ ሥላሴ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ቅራሪ ልቅላቂ ፕሮፖጋንዲስት እንድትሆን እንደታሰበ አሁንም ይገርመኛል። ወይ ልክን አለማወቅ። ይህም ሆኖ መዳን አለ ብለን „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ“ ሲባል እኮ ዕድሉን ሰጥተን አይተነዋል። የሆነ ሆኖ ከጦርነቱ ዋዜማ ጀምሮ ዞር ብላችሁ ፕሮፋዬሌ ላይ ብትበረብሩ ታገኙታላችሁ። ከጦርነት አመድ እና በቀል ብቻ ነው የሚተርፈው። በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም። የሰሜን ፖለቲካ ድቅትም ነው። በጦርነት በዓይኔ ያዬሁትን ሁሉ በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ከሁሉ በላይ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይን ያመነ ጉም የዘገና ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ለውጩ ዓለም እኮ የአማራን ሊቃናት ፈጅተው አማራ ሥልጣን ሊገለብጥ ነበር ብለው ሪፖርት አድርገዋል። ለጎረቤት አገሮችም እንርዳችሁ ተብለን ተጠይቀን በቁጥጥር...

ሕይወት የጥያቄ እና የመልስ ጭማቂ ናት። (24.03.2021)

ምስል

አቅም።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   " ዝም ብዬ የመከራዬን ቀን እጠብቃለሁ። " ( ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ )     አ ቅም። አቅም በግል ህይወት፣ በማህበራዊ ህይወት፣ በፖለቲካ ህይወት፣ በቤተሰባዊ ህይወት፣ በኃይማኖታዊ ህይወት ደሙ ነው። አቅም አልባ መኖርም፣ ህይወትም፣ ዓላማም ግብም ፍቅርም የለም። አቅም በተለያዬ እርከን፣ በተለያዬ ሁነት ሊሰጥ፣ ሊከፋፈል ይችላል። አቅም ነው ማሸነፍ። አቅም ነው ድልአድራጊነትም። አቅም በሁለት ልንከፍለው ብንችልም እንደ ፈንጋጣው ሥርጉትሻ ዕሳቤ ሦስተኛም አቅም አለ ብላ ታስባለች።   1) የሰለጠነ። 2) ያልሰለጠነ። 3) ቅብዓ። የሰለጠነው ክህሎት የምንለው፣ ክህሎት ግን ምንድን ነው ? ጭብጡን ላዘግይ እና ለወል ውል የሚሆኑ ሃሳቦችን ላንሳ። ራስን መግዛት፣ አዙሮ የማዬት ብቃትንና ጠንካራ ህሊናን ይጠይቃል። አንድ ኃይማኖተኛ ውጪያዊ ረቂቅ ኃይልን እንደሚፈራ ሁሉ፣ የህሊና ጥንካሬ ያለው ሰውም ደግሞ ህሊናው የሚያወግዘውን ተግባር # በመፆም ከራሱ ጋር # መጣላትን በህሊና ቁስል ማሰቃዬት አይፈልግም። 1) የ ሰለጠነ አቅም። ፕሮፌሽናሊዝም እንደ ማለት ነው። ከዲስፕሊን፣ ከትምህርት፣ ከተወሰኑ ዓመታቶች ጋር በረጅም ጊዜ ሰልጥኖ ሥራ ላይ ሲውል አቅሙ ሥልጡን ...