የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ መሰላም መጡ።

ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ

በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝማራ

ለራህብ የሚራራ

„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ“

(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)

·     



  የወሌሌ ገበታ እና ጠቅላይ ሚኒስትርነት።

የእኔ ሃሳብ ከሌላው የተለዬ ነው። በጦርነቱም፤ ጦርነቱን ለማስነሳት የነበሩ ቅድመ ጉዝጓዝ ሁኔታዎችን አስመልክቶም ለዬት ያሉ ሃሳብ ነው የነበረኝ። እራሱ አቶ ሴኩትሬ የማን ነበሩ የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው። በ ኦነጋዊው ኦህዴድ ሰበር ሳይዋጡ እርጋታን ይጠይቅ ነበር ሁሉም ነገር። ከመቀደም ለመቅደም።

ጦርነቱን አስመልክቶ ከብዙ ወዳጆቼ ጋር ተለያይተናል። አንዳንዶቹ የኦህዴድ ጥጋብ ፕሮፓጋንዲስት እንድሆንም ጠይቀውኝ ነበር። ድፍረቱ ቢገርመኝም። በምን ታምር? በምን ቀመር ሥርጉተ ሥላሴ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ቅራሪ ልቅላቂ ፕሮፖጋንዲስት እንድትሆን እንደታሰበ አሁንም ይገርመኛል። ወይ ልክን አለማወቅ። ይህም ሆኖ መዳን አለ ብለን „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ“ ሲባል እኮ ዕድሉን ሰጥተን አይተነዋል።

የሆነ ሆኖ ከጦርነቱ ዋዜማ ጀምሮ ዞር ብላችሁ ፕሮፋዬሌ ላይ ብትበረብሩ ታገኙታላችሁ። ከጦርነት አመድ እና በቀል ብቻ ነው የሚተርፈው። በጦርነት አሸናፊም ተሸናፊም የለም። የሰሜን ፖለቲካ ድቅትም ነው። በጦርነት በዓይኔ ያዬሁትን ሁሉ በዝርዝር ጽፌያለሁኝ። ከሁሉ በላይ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይን ያመነ ጉም የዘገና ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ።

ለውጩ ዓለም እኮ የአማራን ሊቃናት ፈጅተው አማራ ሥልጣን ሊገለብጥ ነበር ብለው ሪፖርት አድርገዋል። ለጎረቤት አገሮችም እንርዳችሁ ተብለን ተጠይቀን በቁጥጥር ሥር አውለናዋል አልናቸው ብለው ነግረውናል። ያን ጊዜ እኮ አማራ ክልል ላይ ቀዝቃዛ ጦርነት ነበር ያካሄዱት።

በብስጭት ባህርዳር ውድም እንድትል ሁሉ ህልማቸው ነበር። አሁን ጉርጎራ ላይ ስለመሆናቸው ስለ ነገረ ቤዛዊት ትናንት ሲተርኩልን ነበር። ያን ጊዜ ስንቱ አቅም ነው ከሁለት ተተርትሮ የባከነው። ዛሬ ላይ ስታዩት የሰኔ 15/20211 ምን እና ምን ይላል ጣዕሙ?

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን አምኖ ለሰከንድ አምኖ መደገፍ፤ አምኖ ቀዳዳ እሞላለሁ ማለት፤ ሰባራ ጠጋኝ ወጌሻ መሆን ዕብደት ነው። አሁን ከእኛ ይልቅ ደጋፊዎቻቸው፤ በስውር ሽፋን ሲሰጥ የባጀው የኦህዴድ ካድሬ ሁሉ መውጫ ቀዳዳ እዬጠፋው ነው። 

·       እንደ ገና ደግሞ እንደ ገና ነው ሁሉም ነገር ከዜሮ።

እኔ እንደማስበው አሁን በፓርላማ ስለሆነው ነገር ከግርባው ብአዴን ጋር ስምምነት ሳይኖር ተፈጽሟል ብዬ አላስብም። ግርባው ብአዴን አብን እንደ ጦር ነው የሚፈራው። እሱም ሲወቀስለት ፌስታው ነው። በሌላ በኩል የአማራ ልዩ ኃይል ከወልቃይት፤ ከጠገዴ፤ ከራያ ይውጣ የሚባለውን ውሳኔ ግርባው ብአዴን የሚፈራው የአማራን ህዝብ እንጂ ውሳኔው ይመቸዋል። ስለዚህ  ኦህዴድ ሥርዕወ መንግሥት ጫና እንዲኖር ይፈልገዋል ብዬ አስባለሁኝ። ስምምነቱ አይኖርም ብዬ ፈጽሞ አላስብም። እኛን ክሰሱ ተብለው ሁሉ ሊበረታቱ ይችላሉ ኦህዴዶች። የአሜሪካን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለመዳን። ገደላችሁልኝ ተብለው አይደለም የቤንሻንጉል እና የጉምዝ ገዳይ ፕሬዚዳንቶች የተሸለሙት። በቅርቡስ ጠቅለዩ ተሸላሚ አልነበሩንም?  በዛ ማግሥት አይደለም ወይ ማህበረ ሌንጮ አማራ ክልል ላይ ጉባኤ ያካሄዱት? 

የሆነ ሆኖ የሰሞናቱ የኦህዴድ እና አቶ ጃል ማሮ አብረው ስለመስራታቸው ማረጋጋጨዋ አቶ ጃል ማሮ ከቢኦኤ ጋር በነበራቸው ቆይታ የከሰሱት የአማራን ልዩ ኃይል ነበር። እራሱ አቶ ጃል ማሮ ቃለምልልስ እንዲደረግላቸው የተደረገው በኦህዴድ ድርጅታዊ ሥራ ነው ብዬ ነው እማምነው። ውስጥ ለውስጥ የህወሃት እና የ ኦህዴድ መስመር አልተዘረጋም ብዬ ማሰብ አልችልም። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ  ኢማጅኔሻናቸው የሴት ቀሚስ ይልበሱ ቢባሉ ይለብሳሉ። ሴት ነኝ ብለው ሁሉ ሊያውጁ ይችላሉ። የሆነ ሆኖ ኦህዴድም ያወጣው መግለጫ ያንኑ ነው የጃል ማሮን። ፓርላማው የፈጸመውም ያንኑ ነው። ጠቅላዩ ወደ ጁቪተር መጥቀው ነበር ብለን እናስብ ይሆን? ወይንስ መንፈስ ስለሆኑ ተሰወሩ? ክክክ። ያው በተሰካላቸው ያማጅኔሽን አክናፋት ወደ ሰማዬ ሰማያት አረገው ቢሆንስ? ክክክ።

·       ይህ ለምን ሆነ? በስሱ።

እኔ እንደማስበው የአሜሪካ መንግሥት በቅርቡ ልዑክ ልኳለኝ። ስምምነት ተደርሷል ብዬ ልሰብ። ያን ስምምነት ለማስፈጸም ኬሚሴ፤ አጣዬ፤ ማጀቴ፤ ኤፍራታ፤ ወለጋ ላይ መሰል ግጭቶችን ቀድሞ ማሰናዳት እና መፈጸም አንዱ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የተለመደ ኦፕሬሽን ነበር። ከዛ ወንጀሉን ለአማራ ክልል ማሸከም። ከአማራ ክልል ደግሞ ልዩ ኃይሉን መወንጀል። ይህ ማለት ትግራይ ውስጥ ለተፈጸመው የሰባዕዊ መብት ረገጣ እና ግፍ ሁሉ ተጠያቂው የአማራ ልዩ ኃይል ነው። ሁልጊዜ ወንጀለኛው አማራ። ተግድሎም፤ ተጨፍጭፎም፤ ተሳዶም፤ ታርዶም። ተዘልዝሎ ቋንጣ ሆኖም ይህም አይበቃም። መድቀቅ አመድ ትቢያ መሆን አለበት። ግፍ በዛ። ከረፋም።

አቤቱ ወሌለው እኔ እንደ ማስበው አይደለም ከዛ ኦሮምያ ላይ እያወከ ያለው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ነው ብለው ለልዑኩ ይገለጣሉ። አፋርም ሰሞኑን ይጠበቅ። ሊከስ ይችላል። ጋንቤላስ? ሰሜን እና ደቡብ ሱዳንንም የ አማራ ልዩ ኃይል ነው የቀጠናውን ሰላም የነሳውም ይኖርበታል። ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢነሳ አማራ አስነሳው አይቀሬ ነው።

ኦሮምያ ላይ ለተፈጠረው ችግር ሰላም የነሳው ይኸው ሃይል ነው በማለት በቀጥታ የአሜሪካን ፍላጎት ለማስፈጸም የአማራን ልዩ ኃይል ከወልቃይት ከጠገዴ፤ ከራያ ማስወጣት ይቻላል ማለት ነው። መቅጣትም። ማሰርም። አብይ መሪ እያለ ደግሞ አማራ ማፈሪያ ሰልፍ አድርጎ ነበር አሉ አሜሪካ። የሎቢ ሥራም ተጠናክሮ ሲሰራ ነው የነበረው። አጀንዳን ትቶ የባይረስን ኦፕሬሽን ማስፈጸም የት ያስመድብ ይሆን?!

 እኔ ታውቃላችሁ በሚሆነው፤ በተደረገው ነገር ሁሉ ይህ እንደሚሆን አውቅ ስለነበር እስኪ ደስታችሁ ሲዘልቅ አያለሁ ስል ነበር። እንዲያውም ደስታችሁን ሁለት ነገር እሰቡለት፤ አንደኛው ተጨማሪ ደስታ ብታገኙ ያን የሚስተናግድ መደርደሪያው እንዳይሞላ ቦታ አስቀሩ፤ ሁለተኛው ደስታችሁን ከተቀማችሁ ተስፋ ቆራጭ እንዳትሆኑ ደስታችሁን በልክ አድርጉት ሁሉ እያልኩኝ በተደጋጋሚ ጽፌያለሁኝ።

እንዲያውም „ህወሃት ይወገድ እንጂ ሌላው ገብስ ነው“ አገር ምድሩን ያጥለቀለቀ ሞቶ ነበር። አማራ ትግሉንም አማራነቱንም አላወቀበትም። ከፌድራሉ በላይ እኮ እኔ ነኝ  ባይም ነበር አይደል። አሁን ሁሉንም አጥቶ ቁጭ ሆነ። የህልውና ትግል ቀርቶ አኮ አሁን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ላይ ነው የነበረው አይደለም ሙቀቱ? አማራነት ተረስቶ ሌላ የደላው አጀንዳ ላይ ነው ሠርግ እና መልሱ። አልመተዋወቅ የህልውና ተጋድሎ እና ዲስፕሊንን።

·       ላው ግን ህዝቡ የአማራ መልሱ ምን ይሆናል ነው?

አልፎ አልፎ ስጠያይቅ ቋያ የሆነ መልስ ነው የሚሰጡኝ። ይለይልናል ነው የሚሉት። ይህን ነበር ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የሚሹት። የስሜን ፖለቲካን ድቅቅ አድርጎ፤ የተዋህዶን መሠረት ውድም አድርጎ ኦሮሙማን ማንገሥ መንገዱ ይህ ነበር። የተጋሩም የአማራም ሊሂቃን ከዕውነተኛው ሚስጥራቸው ከጫፉ ሳይደርሱ የአቶ ሽሜ ጭፈራ አሰመጣቸው። ከሳቸው አንሰው። በዚህኛው ዘመን ሁለቱ ህዝቦችም ሆነ ባዕቶችም ከእንግዲህ ሰላም ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም። ፈጠሪ ረድቶን ጭምት መሪ ከሰማዬ ሰማዬት ምርቃት ካልተሰጠን በስተቀር። የተሰበረ ብርጭቆ መልሶ ውሃ አይይዝም። የሆነው በሁለቱ ህዝቦች ይኸው ነው።

የወለሌ ገባታው ጠቅላይ ሚስኒሰተር ሌት እና ቀን እሚማስኑት ያን እጅግ ዘግናኝ ጥፋት፤ ያን የታሪክ፤ የትውፊት፤ የቅርስ፤ የሰባዕዊ መብት ጥሰት፤ የሃይማኖታት ጥፋትና ውድመት፤ ያን መጠን የለሽ የኢኮኖሚ ድቀት ያመጣውን እርባና ቢስ ጦርነት ተረስቶላቸው እንደገና አዎን እንደገና ከህወሃት ጋር እርቀ ሰላም አውርደው የእማጅኔሽን ትርትር ትልትላቸውን ተግባራዊ ስለማድረግ ነው የሚያልሙት።

·       ሌሉት።

ዬትናንት የፓርላማ ውሎ ውይይቱን ስታዳምጡት እሳቸው ከህሊናቸው ጋር ስለመሆናቸው እራሱ ያጠራጥራል። በቅርቡ ለሥነ - ልቦና ህመም ይዳረጋሉ ሳይሆን ታመዋልም ብዬ አስባለሁኝ። መርከቡ እዬሰመጠ እሳቸው በህልም ዓለም ባቡር ቩቩቩ እያሉ በልጅነቴ አደረግኩት እንዳሉት አሁንም ከዛ የልጅነታቸው ፈንጠዝያ ላይ ነበሩ። የሚገርመኝ መካሪ የሌላቸው መሆኑን። አንድ የትዳር አካል በዚህ ሁሉ ቀውስ ሲወድቅ ቀዳማዊነት እምኑ ላይ ስለመሆናቸው እራሱ ግርም ይለኛል።

በአማራ በኩል እኮ ትግሉ ለድል የበቃ ይመስል እንደ ዘማናዮች የሚደርገው ቅብጥ ያለ ዘመናይነትን ነበር እኔ እማስተውለው። የህልውና ተጋድሎ በዚህ መልክ ለድል መብቃት ቀርቶ እራሱን ችሎ ለመቆምም ጋዳ ነው። ለዚህ ነው ጥምረቱ ሆነ መሰል ሴሪሞኒው አጀንዳዬ ሊሆን ያልቻለው። ዴሞግራፊው ለማን ነው? ለማን ታስቦ ተፈጸመ? ይህ አንድም ቀን ቀርቶ አንድም ደቂቃ አጀንዳ አልነበረም። ለኦነግ ያለው ስስ ልብ ለህወሃት የለም። አልነበረም።

አሁን ይጸጽታቸው ይሆናል አቶ ቴወድሮስ ትርፌ ያን ያህል የደከሙበትን ተግባር ሳይቋጩት ሌላ እጅግ ከባድ ንብርብር መከራ ላይ እንዲህ ሲወደቅ የአማራ ህዝብ። ለእኔ የአማራ ቀን ገና አልተጸነሰም ብዬ ነው እማስበው። የውሸት ወዳጅ እንኳን የለውም አማራ እንኳንስ የልብ ዕውነተኛ ወዳጅ።

አሁን ጠቅላዩ የሚፈልጉት የአማራንን ልዩ ኃይል በፍጥነት ከጥቅም ውጭ አድረገው ልብ የገጠሙላቸውን ዶር ሙሉ ነጋን አብረው ለዋንጫችን ማለት ነው። በጥቂቱንም አሜሪካን ታዛዥሽ ነኝ ማለት። ነገረ ኤኢርትራ ብዙ በጣም ብዙ ውስብስብ መከራ ያለበት ነው። አልነካካውም።

ለዋንጫችን ከአቶ ደመቀ መኮንን ጋርም ይሆናል። ለዋንጫችን ከሳጅን ተመስገን ጥሩነህ ጋርም ይሆናል። ቅደመ መሰናዶው እንደ ድምዳሜው በውስጥ ለውስጥ ተመክሮበት የተከወነ ነው። እነሱ ጫናን በማቻቻል እንደምን ወንበራችን ይቀጥል ነው። ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ከልኩ ሲያልፍ ሊፈነዳ እንደሚችል አላሰቡትም። ፈጽሞ።  ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል። የሚሹት የ አማራ ህዝብ በዘር ማጽዳት ወንጀል እንደ ኦህዴድ ኦነግ፤ እንደ ህወሃት ተጠያቂ እንዲሆን ነው። ይህ ሁሉ ትርምስ።

ችግሩ አናባቢውም ተነባቢውም የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ ሙት መሬት ላይ መሆነኑን ተረድቶ በልኩ የህሊና ትጥቅ አለመሟላቱ ነው። ሙት መሬት ላይ ያለ ነገር ሽንፈት ግድ ይለዋል። ሙት መሬት ትጠጣ የሚባልበት አመክንዮ ትልቁ ጉዳይ ደግሞ ዴሞግራፊ ላይ ተቀምጠህ „ተረኝነት“ እያልክ እራስህን ስታታልል ነው። ሌላው ቀርቶ የአቶ ሽመልስ ንግግር እንኳን እንደ ቼኮሌት ነበር የታዬው። ከዛ በኋላ ነው አይደል ሌላ „ኮንቢንስ እና ኮንፌውዝድ ዓመት ድገም ተብሎ የካባ፤ የጃኖ ሽልማት ድራማ ተጠናቆ፤ የጋሻ ሽልማት የቀለጠው።

ሰሞኑም የጦር መኮንነኖች ሽልማት እና „እንኳን ደስ አላችሁም“ ተከናውኗል። አንድ ጠቢብ በአንድ ውይይት ወቅት „እኔ እምናደደው“ አሉ „አስተካክለው መሳሳት እንኳን አለመቻላቸው ነው“ አሉ። እውነት ነው። ወሮ አዳነች አበቤን ከአቃቢ ህግ ለማንሳት እስረኛ ጥዬቃ ዋዜማ ነበር፤ አቶ በላይን ይቅርታ ጥዬቃ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊነትም በማግስቱ ነበር እንዲሁ የተከወነው፤ ዛሬ ደግሞ የጦር መኮንነኖች ሽልማት፤ እንደገናም ደግሞ ውንጀላ፤ ነገ ደግሞ ህልፈት ወይ እርሻና …

አለመግባት፤ አለመረዳት ያመጣው ጣጣ ገናንም ገናም ነው ውልቅልቅ አውጥቶ ዘነዘና እሚያስቀረው። ለዚህ ነው እኔ በማናቸውም ሁኔታ አማራ አቅሙን መጥኖ፤ ቆጥቦ ማስተዳደር አለበት እምለው። ለዚህም ነው በዕለታዊ ጉዳዮች ተውጬ አቅምን በገፍ እማላፈሰው። ከፌስታውም ውስጥ አልነበርኩም። ዕንባ ነው የሚቀርበኝ። ድምጽ አልባ ለሆነው አመክንዮ፤ ወይንም ሰብ ላይ አትኩሮቴም የሆነው። ዛሬ እኛ እያለን እንዲህ የተሆነው የዛሬ 20/30/ ዓመት ሲታሰብ ከጨለማም ያለፈ ድቅድቅ ነው።

በቃ! ተምጦ ቢወለድ እንኳን በእጃችን ያለው ተቋም ቀርቶ የተደራጀ ሃሳብ እንኳን የለንም። የኃይል አሰላለፉ እራሱ ስርንቅ ነው። ማን የማን ስለመሆኑ የሚታወቅ ነገር የለም። ጥሞና አብዝቶ ያስፈልገዋል ትግሉ። ዜሮ ላይ ነን። ቢመርም ቢጎመዝዝም። ተስፋ ቆርጬ አለመተዌ ግን ይገርመኛል። አሁንም ተስፋ አደርጋለሁኝ። በፈጣሪዬ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

 

ከሥርጉተ©ሥላሴ  (Sergute©Sselassie)
24.03.2021 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

በቃን አምጦ መውለድ ግድ ይላል።

ጎዳናዬ ሥርነቀል ለውጥ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።