ልጥፎች

365 x 3 = 1095 x 24= 26,280

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ    በሰላም መጡልኝ። ዕለተ ሰኞ ዕለተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።“ (ትንቢተ ዕንባቁም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ዕለተ ሰኞ ማዕዶት ጠባቂ ሁሉም አጀንዳ የሚሰናገድበት ዕለት ነው። መንፈሴ በይ ያለኝን ሁሉ ያለገደብ የሚኮለምበት። ዛሬ የቀናው አጀንዳ እንዴት ሰነበታችሁ? ሰንበት እንዴት አለፈ? ኢትዮጵያስ እንደምን እያሆነች ነው ይላል። ·          365 x 3 = 1095 x 24= 26,280   የቁጥር ተማሪ አይደለሁኝም። በቁጥር ትምህርት እጅግ ደካማ ነበርኩኝ። ስለዚህ ስህትት ሊኖርበት ቢችልም እርዕሴ አይፈረድበትም። እኔ የባይወሎጂ እና የኬሚስትሪ ጎበዝ ተማሪ ነበር የነበርኩት፤ እንዲያውም 11/12ኛ በደረጃ ነበር ተሸልሜ ያለፈኩት። የሆነ ሆኖ ወደ ዕርዕሰ ጉዳዬ ምልሰት ሳደርግ ሰውኛ ኢትዮጵያ ውስጥ በዬደቂቃው አደጋ ውስጥ ነው። ህዝብ እያለቀ ነው። ሞቱ ብቻ አይደለም በስጋት እና በሽብር ኢትዮጵያዊው ሰው ከጽንሰት ጀምሮ እዬተረሸነ ነው። ሰው አለን ለማለት አንችልም። እንዲያውም እኔ ቤት ሆኜ ሳስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል የሥነ - ልቦና ባለሙያ ይኖር ይሆን እላለሁኝ። መጪው ጊዜ መርግ ነው። ችግሩ አልተጀመረም ብዬ ነው እማስበው። ·        ም ክንያቱም … ከአጤ ዝናቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጀምሮ የሥነ - ልቦና ህመም የለብኝም የሚል ሊኖር ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደለሁም። እያንዳንዱ ደቂቃ በደም ውስጥ ያለፈ ...

የአመቱ ምርጥ አፍቃሪ! ከኢትዮጵያኑ ሮሚዮ እና ጁሊየት ጋር የተደረገ ቆይታ! Ethiopia | Eyoha Media ...

ምስል

የፊልም ታሪክ የሚመስለው የቅጣው እና የሳራ የፍቅር ህይወት!

ምስል

የኢትዮጵያ ዕለቶች ዕንባ እዬለቀሙ። 09 04 2021

ምስል

ኢትዮጵያዊነት ምንጩና አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነው።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   ኢትዮጵያዊነት ምንጩና አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነው። ጥፈተኛው ማን ነው?   „ከቀና ህግ ወጥተን ሳትን“ (መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮) ·        እፍታ። ·          ማዕዶተ ኢትዮጵያዊ። ኢትዮጵያዊነት ዘለግ ያለ ፍልስፍና ነውና አንዲት ነቁጥ አንስቼ ሃሳቤ ረዘሟል። እምጽፈው ለቅኖች፤ ለገራገሮች ስለሆነ ብዙም ጭንቅ የለብኝም ዘለግ ያለ ስለመሆኑ። እኔን ሽተው ለሚመጡ ደጎቼ ውስጤን ገልጬ ስጽፍም ሰቀቀን የለብኝም እንደ ማለት። ግልጽ እና ቀጥተኛ ሴትም ነኝ። ሰው ጫካ አይደለም እና። ·        መንፈስ!   እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ ?  ኢትዮጵያ ሻሸመኔ፤ ኢትዮጵያ ቡራዩ፤ ኢትዮጵያ ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ኢትዮጵያ ወለጋ፤ ኢትዮጵያ ሙሉ ኦሮምያ፤ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ፤ ኢትዮጵያ ደቡብ፤ ኢትዮጵያ ከሚሴ - አጣዬ - ማጀቴ - ደራ፤ ኢትዮጵያ ማህል ጎንደር፤ ኢትዮጵያ ትግራይም፤ ኢትዮጵያ አፋር እና ሱማሌም ፍጥጫ ላይ ነው የባጁት፤ ያሉት፤ የሰው እልቂት ምድሪቱን ከቧታል። ደሙም አጉርፏል።    ገና ውጥን ላይ እያለ ጭካኔው ቁጣ አልነበረም ቀጠለ። የቆዬ ስለመሆኑ አይደለም ጉዳዩ ዛሬም   የኦሮሙማ ባጀቱ ሰው መግደል ነው፤ ሬሳ መቁጠር፤ ሰኔል እና ቹቻ በቦንዳ ማከ...