ልጥፎች

ልጆቼ መፅሀፉን ቀደው ወረቀቱን በሉት. . .ሁለቱም ድል ባለ ሰርግ ተዳሩ! ማንም ካላየ አይገምትም #ethiopia...

ምስል
ይህችን የዘመን ቅኔ እባካችሁ አዳምጧት። ከአውስትራልያ ሄዳ እናትነትን በተግባር እንደምን እንዳስጌጠችው፤ ጋዜጠኝነትን እንደምን ምስባክ እንዳደረገችው፤ ሴትነትን እንደምን እንዳነፀችው በአስተውሎት መርምሩት። ኢትዮጵያ እናታችን ጎደሎዋ ብዙ ነው። ቀዳዳዋ ወዘተረፈ ነው። እንደ ድንግል ዳሳሽ ያገኙት ወንድሞቻችን ፈዋሽ እናት ሰጣቸው ፈጣሪ አላህ። ተመስገን። የእኔ ክብሮች ሰንበትን ለተፈጥሯዊነት አውለን ያለችነን እንለግስ ዘንድ ዝቅ ብዬ እለምናችኋለሁኝ። ዬባንክ ቁጥሩ 1000453519094 ነው። ለበረከት እሽቅድድም፤ ለመልካምነት ትጋት ይኑር። ፈጣሪ ይርዳን። ብሩካን ያወጋሉ። ይህ የመልካምነት ሊቀ ትጉኃን ወንድማችንም የሰጠው ነው። ሽልማታችንም ነው። እሷም ቅድስታችን። ይባረኩ። አሜን። • https://www.youtube.com/watch?v=Wl3XM6lkoDc ልጆቼ መፅሀፉን ቀደው ወረቀቱን በሉት. . .ሁለቱም ድል ባለ ሰርግ ተዳሩ! ማንም ካላየ አይገምትም #ethiopia #new #adiction #wedding • 1000453519094 ግን እንዴት ነን? አይዞን። ያልፋል። ኑሩልኝ። ደህና ዋሉ። ደህና እደሩልኝ። ሼር በማድረግ አነሰ አደገ ሳትሉ የምትችሉትን አድርጉላት። አይዞሽም ስጦታ ነው። ተባዕቶች ውጪ የምትኖሩ ልብሶችን፤ የህክምና ባለሙያወች መዳህኒቶችን፤ ስትችሉ በኦን ላይንም በነፃ የትምህርት የቴራፒ አገልግሎት ብትሰጡቸው ትባረካላችሁ። በፋይናንስ የምትችሉም እንዲሁ፤ በሚዲያም በማስተዋወቅ መርዳት ኢትዮጵያን የሚገልጽ ገፀ በረከት ይሆናል። መልካም ማሰብ በራሱ መልካምነት ነው። መታደል በጉነት ነው። ድንቂት ድንቅነቷ ምንጯ ከአበው እና እመው መንጭቶ ይህን አሳካች። ለማግሥት ባለ አሻራ ሆነች። አሻራችን እናሳድገው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ...

የሰማይ እና የምድር ንጉሥ እዬሱስ ክርስቶስ "#ክንፍ" አለውን? የወሮ ዝናሽ ታያቸው ውኃ ያልነካው ፈጣጣ ፈንጣጣም አስተምህሮ ሃግ ሊባል ይገባል።

ምስል
  የሰማይ እና የምድር ንጉሥ እዬሱስ ክርስቶስ " #ክንፍ " አለውን? የወሮ ዝናሽ ታያቸው ውኃ ያልነካው ፈጣጣ ፈንጣጣም አስተምህሮ ሃግ ሊባል ይገባል። ስለ ቃሉ ንሰኃ እገባበታለሁ አይደለም ብራና ዘርግቶ ሥንኝ ጽፎ በአደባባይ ለመዘመር ቀርቶ? #ለሚመለከተው ሁሉ። "አቤቱ ከድፍረት ኃጢያት ባርያህን ጠብቀኝ።   ወደ እግዚአብሄር አምላክ ለሚቀርብ ምስጋና እንዲህ በድፍረት እና በማናአለብኝነት ተንጠራርቶ ጥሰት ውስጥ መዘፈቅ የጤና አይመስለኝም። ለነገሩ የ፬ኪሎው ቤተ መንግሥት ሽብር፤ ጭንቅ ውስጥ እንደባጀ ያመሳጥራል። ሌላላው የሰማይ እና የምድርን ፈጣሪ አማኑኤል ለእነሱ ዬግፍ ሥልጣን ብቻ ምርቃት እንዳደረገም ያሳጣል። ሥንኞቹ የባለቤታቸው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አይደሉም። ዘዬው፤ ዘኃ ግራው የሳቸው የቀዳማዊዋ እመቤት ወሮ ዝናሽ ታያቸው ይመስላል። ምቱም በዚህው ዙሪያ ነው። ጭንቀት፤ መራድ፤ ሽብር እና ራድ ቤተመንግሥቱን መናጡን ያመሳጥራል። ለምን ፈታ ደይሊ እንደዘለለው ሥንኙን አላውቅም። የአነበበውም አሟልቶ አይደለም። አንዷ ፊደል ስትጠብቅ፤ ስትላላ ብዙ እጅግ ብዙ ጉዳዮችን ታመሳጥራለች። አማርኛ ቋንቋ ቅኔም ነው የምለውም ለዚህ ነው። ዘማሪ ዝናሽ ታያቸው አዲስ የዶግማ ፍልሰት መጥረቢያ ይዘው ከች ብለዋል። ጭብጡ እግዚአብሄር ክንፍ አለው ከሚለው አፈንጋጭ ዕምነት እና ዕሳቤ ይመነጫል። እዬገረመኝ ያለው ጉድ የኢትዮጵያ አንስት አማንያን በሃይማኖት ዙሪያ ያላቸው አሁናዊ ድፍረት ነው። ሎቱ ስብኃት። አበስኩ ገበርኩኝ። አሁን በዘመናችን ወደ አራት ተጠግተዋል። በአዲስ ፍልስፍና ፍልሰት ላይ ያሉት ማለቴ ነው። አባቶቻችንም ሃግ አይሉም። እሱ ብቻ ሳይሆን አንጡራ ጥሪታቸው ለሌላ ሃይማኖት ተቋም መጠሪያ ሲሆንም አንተ ታውቃለህ ብለው ዝም ሆኋ...

ግን ዶር ዳንኤል በቀለ በህይወት አሉን? እስከመቼ ድረስ ይህን ኢ- ሰባዕዊ፦ ኢ- ተፈጥሯዊ ዬአረመኔ ሥርዓት አገልጋይ ሆነው ይቀጥላሉ? መቼ ነው የኃላፊነት መለቀቂያ የሚያስገቡት???? በጉጉት እጠብቃለሁ። ንስኃም፤ ፀፀትም።

ምስል
ግን ዶር ዳንኤል በቀለ በህይወት አሉን? እስከመቼ ድረስ ይህን ኢ- ሰባዕዊ፦ ኢ- ተፈጥሯዊ ዬአረመኔ ሥርዓት አገልጋይ ሆነው ይቀጥላሉ? መቼ ነው የኃላፊነት መለቀቂያ የሚያስገቡት???? በጉጉት እጠብቃለሁ። ንስኃም፤ ፀፀትም። ስክነት ስንቃችሁ የሆነው የቤታችን ቤተኞችእባካችሁ ሼር አድርጉልኝ። አመሰግናለሁ። "አቤቱ የመዳህኒቴ አምላክ በቀን እና በሌሊትበፊትህ ጮኽሁ፤ ፀሎቴ ወደ ቤትህ ትግባ፥ ጆሮህን ወደ ጩኽቴ አዘንብል፤ ነፍሴ መከራን ጠግባለች እና፥ ህይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለች እና፥ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቆጠርሁ፤ ረዳት እንደ ሌለው ሰው ሆንሁ።" (መዝሙረ ዳዊት ፹፯ ከቁ ፩- ፬)     ለማከብረወት ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር። አዲስ አበባ።   እኔ በምን ሁኔታ ላይ እንደምገኝ ድንግል ብቻ ታውቃለች። መከራን ገድሞ ማስተናገድ የፈተናወች ሁሉ ቁንጮ ነውና። የሆነ ሆኖ ዶር ዳንኤል በቀለ የዘመን መለወጫን በምን ሁኔት አከበሩ? ቀለል ያለች ጓዘ ቀላል ጥያቄ ናት። በዘመኔ ትዝ ሳይሉኝ ሁሉም አውደዓመቶች አልፈዋል። የዘንድሮው መርግ ነበር። ዕንባማ ተራራ። እኔ አገሬን ከለቀቅኩ በቤተ - እግዚአብሄር ዓውደ ምህረት ላይ ከሚከበሩት በስተቀር አክብሬው እማውቀው ዓውደ ዓመት የለም። ያም ሆኖ ግን ቀኑም፤ ሌቱም፤ ሰከንዱም፤ ደቂቃትም መርግ ሆኖ ያለፈው የዘንድሮው ነው። መሸከም - አልቻልኩም። ማስታገስ - አልቻልኩም። ማስተባበልም አልቻልኩም። ማሰብም - ማስታወስም አልፈለግሁም ነበር ግን እንዴት ይቻል???? የአብይዝም የመቃብር ስፍራው፤ የአሳቻው የአብይዝም ሙሉ ካቢኔያችሁ ደግሞ ድልቂያ ላይ ነበር። ማህበረዕብን። ማህከነ። ተሳህለነ። እግዚኦ!! #የሆነ ሆኖ! ዶር ዳንኤል በቀለ ሆይ! ነፍሰወት - አለችን...

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ የኋንስ በሰላም ደረሳችሁ።

ምስል
    የ እኔ ክብሮች እንዴት ናችሁ፧ እንኳን ከዘመነ ማ ርቆስ ወደ ዘመነ የ ኋ ንስ በሰላም ደረሳችሁ። እንቁጣጣሽ። ኑሩልኝ። አሜን። መጪው ዘመን የቅንነት፤የሐሤት ይሁንልን። አሜን።