"ምርጫ ጠብቁ፤ በቀጣዩ ምርጫ ተወዳደሩ።"
"ምርጫ ጠብቁ፤ በቀጣዩ ምርጫ ተወዳደሩ።" "ወዮ ወዮልሽ ይላል ጌታ እግዚአብሄር ከክፋትሽ ሁሉ በሗላ የምንዝርናን ሥፍራ በዬአደባባዩ ከፍ ያለን ቦታ ሠራሽ።" (ትንቢተ ህዝቃዬል ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲፪) ይህ ልግጫ ይመስለኛ። እርግጫም። ምርጫ አልተካሄደም እያልኩ አይደለም። ምርጫው እንደምን ተፈፀመ ነው ጉዳዬ። አስር ዙር ምርጫ ቢካሄድ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዘመን ምርጫን ተወዳድሮ ማሸነፍ ይቻላል ብሎ ማሰብ ፀሐይ ጨረቃን ትተካለች እንደማለት ነው። ይህን ጉዳይ በወቅቱ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያ በአውንታዊነት ሲገልፁት፤ ዬኛም ሰወች በሰላም ተጠናቀቀ ሲሉ ጽፌበት ነበር። አሁን በአማርኛ ቋንቋ አብራርቼ ልፃፈው። በተለይ አቶ ወንድም አቤ ቱኩቻው አዘውትሮ ስለሚገልፀው። ከምርጫ በፊት ምን ተከናወነ? 1) የተፎካካሪ ኃይሎችን ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ ጫጉላ ቤት አስገቧቸው። እስከ እንግዶቻቸውድረስ ሆቴል ተከራይተው ቅብጥ እና ቅልጥ አደረጓቸው። ቀልባቸው የወደደውን አጠጋጉት። ጠንካሮችም ዛሉ። መስተንግዶው በዛ። የእኛአገር ሰው ደግሞ ይሉኝተኛ ነው። አልፎ አልፎም አምስትም አስርም አባል የያዙትን በሥም እዬጠሩ ማቆለማመጥ ተያያዙት። እና የሰባዕዊ መብት ተሟጋች የነበረው፦ አራት ዓይናማው ጋዜጠኛ፦ ሞጋች ፀሐፍት፤ የጥበብ ሰው ከውጭ ወደ አገር የገባ ሁሉ በዓይኔ ሂድ ተባሉ። ያ ትልቁ መደላድል ነበር። 2) በሰላም ሚኒስተር መቋቋም እና ሂደቱ በራሱ ለኖቤል እጮኝነት ዓውድ ነበር። ለምርጫም ጥርጊያ መንገድ። 3) ለአንድ ቀን ብቻ ሥራ ላይ የዋለ የተፎካካሪ ፓርቲ ሊቀመናብርትን፤ በህዝብ ተወዳጅ እና ተጽዕኖ ፈጣሪያትን በተለያዬ ኮሚሽን በማደራጀት ሹመት ተሰጠ። ማዘያ። 4) ተስፋ የተጣለባቸው የአማራ ክልል መሪወች ...