"ምርጫ ጠብቁ፤ በቀጣዩ ምርጫ ተወዳደሩ።"

 

"ምርጫ ጠብቁ፤ በቀጣዩ ምርጫ ተወዳደሩ።"
"ወዮ ወዮልሽ ይላል ጌታ እግዚአብሄር ከክፋትሽ ሁሉ
በሗላ የምንዝርናን ሥፍራ በዬአደባባዩ ከፍ ያለን ቦታ ሠራሽ።"

(ትንቢተ ህዝቃዬል ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲፪)


 
ይህ ልግጫ ይመስለኛ። እርግጫም። ምርጫ አልተካሄደም እያልኩ አይደለም። ምርጫው እንደምን ተፈፀመ ነው ጉዳዬ። አስር ዙር ምርጫ ቢካሄድ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ዘመን ምርጫን ተወዳድሮ ማሸነፍ ይቻላል ብሎ ማሰብ ፀሐይ ጨረቃን ትተካለች እንደማለት ነው።
 
ይህን ጉዳይ በወቅቱ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያ በአውንታዊነት ሲገልፁት፤ ዬኛም ሰወች በሰላም ተጠናቀቀ ሲሉ ጽፌበት ነበር። አሁን በአማርኛ ቋንቋ አብራርቼ ልፃፈው። በተለይ አቶ ወንድም አቤ ቱኩቻው አዘውትሮ ስለሚገልፀው።
 
ከምርጫ በፊት ምን ተከናወነ?
 
1) የተፎካካሪ ኃይሎችን ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ ጫጉላ ቤት አስገቧቸው። እስከ እንግዶቻቸውድረስ ሆቴል ተከራይተው ቅብጥ እና ቅልጥ አደረጓቸው። ቀልባቸው የወደደውን አጠጋጉት። ጠንካሮችም ዛሉ። መስተንግዶው በዛ። የእኛአገር ሰው ደግሞ ይሉኝተኛ ነው። አልፎ አልፎም አምስትም አስርም አባል የያዙትን በሥም እዬጠሩ ማቆለማመጥ ተያያዙት። እና የሰባዕዊ መብት ተሟጋች የነበረው፦ አራት ዓይናማው ጋዜጠኛ፦ ሞጋች ፀሐፍት፤ የጥበብ ሰው ከውጭ ወደ አገር የገባ ሁሉ በዓይኔ ሂድ ተባሉ። ያ ትልቁ መደላድል ነበር።
2) በሰላም ሚኒስተር መቋቋም እና ሂደቱ በራሱ ለኖቤል እጮኝነት ዓውድ ነበር። ለምርጫም ጥርጊያ መንገድ።
3) ለአንድ ቀን ብቻ ሥራ ላይ የዋለ የተፎካካሪ ፓርቲ ሊቀመናብርትን፤ በህዝብ ተወዳጅ እና ተጽዕኖ ፈጣሪያትን በተለያዬ ኮሚሽን በማደራጀት ሹመት ተሰጠ። ማዘያ።
4) ተስፋ የተጣለባቸው የአማራ ክልል መሪወች ተፈጁ።
5) ከተሞች ነደዱ። የአዲስ አበባ ዙሪያከተሞችም እልቂት ተፈፀመባቸው።ይህ የአዲስ አበባ ህዝብን ለማስጨነቅ የተከወነ ነው።
6) ኢኃን፤ ኢዲፓ በይፋ ተሰረዙ።
7) የኦነጉ አቶ ዳውድ የቁም እስረኛ፤ ዶር ለማ ስደት ተከወነ።
 ያላቋረጠ የአማራ ህዝብ እልቂት፤ መፈናቀል፤ እገታ ተፈፀመ።
9) ያሰጋሉ ለምርጫው የተባሉ በሁለት ዙር ታሰሩ። መጀመሪያ አብን እና ባልደራስን፤ በኋላ አብን፤ ባልደራስ፤ ኦፌኮ እና የኦነግ አመራሮች ታሰሩ።
10) ጉዳዩን በትጋት የሚያስከውን ካድሬ በገፍ ተስማራ።
11)የህወሃት እና የፌድራሉ ጦርነትም አጋዢ ክስተት ነበር። ህዝቡ አማራጭ እንዲያጣ እንዲጨነቅ፤ እንዲጠበብ ተደረገ።
12) አዲስ አበባ ላይ ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ታገደ። ሰልፎቹ አማራ ክልል ብቻ እንዲወሰኑ ተገደዱ።
13) በኢትዮጵያ ባጀትየተለያዩ ማህበረሰቦችን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እያሰባሰቡስብከታቸውን ከታቀደው ቀን ቀድመውከወኑ።
13) አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ተገደለ።
14) ባለቤታቸው ቀዳማዊ እመቤት ወሮ ዝናሽ ታያቸው በአዳዲስ ዝማሬ አማንያን ቀልብ ጨበጡ።
15) የገፍ እስር፤ መሰወር። አፍኖ መልቀቅ ወዘተ ታቅዶ ተከወነ።
አቤዋ በዚህ ሁሉ የጭንቀት፤ የቀውስ ማዕበል ጫና ምርጫ ተካሄደ። የጠቅላዩ የዞግ ፓርቲ ጉባኤ ሳያካሂድ ከመርህ ውጪ አሸነፈ ተባለ። ይህ ለእኔ ምርጫ አልለውም። ማምታታ፤ ማላገጥ፤ እና ርግጫም ነው።
አስቀድሞ በገፍ እስር ይኖራል።
ከጎረቤት አገሮችጋር ግጭት ሊከሰት ይችላል። በፌክ ኢትዮጵያዊነት ህዝብን ማሰለፍ የሱሴ ውርስ ነውና።
የሚሰውም ይኖራሉ።
በጭካኔ ያልተለመዱ ድርጊት የሚፈፅመው መንግስት አዳዲስ ትራጀዲውንም ይሄኔ አደራጅቶ ይጠብቅ ይሆናል።
የሰበር ዜና ሱናሜም ተጠባቂ ነው
ጭንቀትን የሚያፋፍሙ ኩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ። በስልክ እዬደወሉም እስከ ማስፈራራትም።
ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሙያቸው ሰላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚር በሙያቸው ሰላይ ናቸው።
እንደ አንድ የመንግሥት ጉልላት የሚታዩት ኢትዮጵያዊ ሚዲያወች በሙሉ መሪወቻቸው ሰላዮች ናቸው።
የመከላከያ ሚሩ ካልተነሱ እሳቸውም ሰላይ የነበሩ ናቸው።
በሰላይ የምትመራ አገር የተሻለ ነገ ይኖራታል ብዬ አላምንም። ለዛውም ጠሚር አብይ አህመድ አሳቻ መሪ ናቸው። ምናቸውንም መገመት የማይቻል። አሁን የሚሠሩትን ትዕይንት ሁሉ ስክርቢቱንጽፈው የጨረሱት ከ6 ዓመት በፊት ነው። የሹመት ንግግራቸውን እስኪ እሰቡት እንደምን አስተኛኝ እንደነበረ።
ታስታውሳላችሁን? ሁለተኛው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ታውጆ እንዲፀድቅ ሲበሰቡ ጠሚር አብይ አህመድ አልተገኙም ነበር። ቤርሙዳ ትርያንግልን ሚስጢር ዓለማችን አልተካነችበትም። ኢትዮጵያም የመሪዋን ቤርሙዳነት እምትደርስበት አይመስለኝም። ነገረ ፒኮክም እንዳይረሳ የራሱ ጉዳይ አለበት እና።
እና ነገም በምርጫ እኔ ተስፋ አላደርግም። ስምንት ነጥብ በቃለ አጋኖ። ።።! ቀልደኞች ቀልዳችሁን አቁሙ። በውድድር ዶር አብይን ማሸነፍ አይቻልም። ፈጽሞ።
 የአቶ በቴ ኡርጌሳ የግፍ አገዳደልም የቀጣዩ ምርጫ መሰናዶ ማስጀመሪያ ደወል ነው። ቀጣይም ይኖራል። የምርጫ ቀኑ ሲደርስ ፀጥ ይላል። ቀድሞ የሚወገደው ተወግዶ፤ የጭንቀት ድባብ ተጫጭኖ፤ ለካቴና የተላከውም በግፍ ወደ ወህኒ ተወርውሮ። ሌላም አዳዲስ ማስወገጃ ይኖራል። ክብካቤ ላይ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የነገ ገጠመኞቻቸው አይታወቅም። በአጃቢነት ለመቀጠል ላይፈቀድ ይችላል። መሰረዝም አለና። በጥሞና ይታይ።

ይህ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የምርጫ አርት ቀለቡ ነው። ለዚህ ነው የሥርዓት ለውጥ የሚስፈልገው።
 
#ምን መደረግ አለበት???
እኔ ጠቅላይ ሚር አብይ ፈቅደው ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ቲም ኢትዮጵያን ቢመራት እመኛለሁ።
#ድርብ ስጋቴ።
1) መፈንቅለ መንግሥት ከሆነ አደጋው ሰፊ ነው።
2) እሳቸውን በኃይል ለማስወገድ ቢታሰብ ጥፋቱ ልክ የማይወጣለት ይሆናል።
#እና ምን ይደረግ???
ተግቶ መፀለይ ነው። ፈጣሪ መከራውን አይቶ ጥበብ ይኖረዋል ባይ ነኝ። ተመልሶ ለቀጣይ አምስት ዓመት ይግዙ ግን ሰባዕዊነት ይንደድ፤ ይጭስ ትቢያ ይልበስ ዓይነት ይሆናል።
ሌላው ተጽዕኖ ሊመጡ የሚችሉ የጥበብ ቅምረት ቢታሰብ።
ውዶቼ እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ደህናም እደሩ። ቸር ሁኑልኝ። አሜን። ኑሩልኝም። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/05/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።