ልጥፎች
ባለ ተስፋዋ ኢትዮጵያ #እንኳን #ደስ #አለሽ። እማማ አፍሪካም። ዘለግ ሲል ግሎባሉም።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ባለ ተስፋዋ ኢትዮጵያ #እንኳን #ደስ #አለሽ ። እማማ አፍሪካም። ዘለግ ሲል ግሎባሉም። "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱) ዛሬ ልጅ መሳይ በምስራች ነበር ዝግጅቱን አህዱ ያለው። ኢኮኖሚ ሳይንስነቱን ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊነቱን የሚያስተምሩት #ርጉ የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንት ፕሮፌሰር ተሾመ አበበ ዛሬ ከልጅ መሳይ ጋር ቃለ ምልልሳቸውን አህዱ ያሉት በብሥራት ዜና ነበር። ተመስገንም ብያለሁ። ሰበር ዜና ናላችን እረፍት ስላሳጣው። የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያችን የደስታ ብቻ ሳይሆን #የሐሴትም ቀን ነው። ሐሴት ከደስታ የላቀ ነው። መንፈሳዊውን ዓለም እና ገህዱን አለም በተስፋ ያዋህዳልና። መንፈሱም ዘላቂ ነው። በውነቱ ብዙ ረኃብ አለብን። ጥማትም። #ሩቅ ነው ህልማችን፦ #ረቂቅ ነው ምኞታችንም። ተስፋችን አምላካችን አላኃችንም ነው። ሲጎድልብን እንዲህ ተስፋችን ቲፍ ያደርገዋል። በገኃድ አምላካችን አላሃችን መጽናኛ እንደላከልን አስብማለሁ። በብዙ ተጎድተናል። ለጋህዱ ዓለም ብቻችን ነን። መሪነት ቅንነት - ትጋት - #ሰወ #ወዳድነት - ማህበራዊነት - ቀለማዊነት - ህግ አክባሪነት- አድማጭነት ሁሉም ድል አድርገው ጥረቱም ስኬቱም የምሥራቹ ተጋሪ እንሆ አደረገን። የሊቀ ሊቃውንታት ጉባኤ #ብጡለ #ሊቅነት ። ተመስገን። እኔ ከዚህ በላይም እመኛለሁ። ከዚህ በላይም ተስፋ እጠብቃለሁ። ለኢትዮጵያ #አይዞሽም ነው። ውስጣችን ማስኖ እረፍት ላጣም ልዩ በረከት። ክብሮቼ እንዴት አደራችሁ። ዛሬ ሌሊት ምን እንደታዬኝ ባላውቅም ስለመሪነት ትንሽ ብዬ ነበር። ሲነጋም ይህን ዜና አገኜሁ። ይህ የኢትዮጵያ ሐሴት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም፤ የግሎባሉ አለምም ነው። #ሰው ...