«በጠለምት በናዳ የተቀበሩ የሁለት ሰዎችን አስክሬን ለማውጣት ሲሞክሩ ከነበሩት የ7ቱ ሕይወት አለፈ" bbc
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0mnprenz00o «በጠለምት በናዳ የተቀበሩ የሁለት ሰዎችን አስክሬን ለማውጣት ሲሞክሩ ከነበሩት የ 7 ቱ ሕይወት አለፈ" 26 ነሐሴ 2024 "በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ በናዳ የተቀበሩ የሁለት ሰዎችን አስክሬን በመፈለግ ላይ ከነበሩት የ 7 ቱ ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። የወረዳው አስተዳዳሪ ጋሻው እንግዳው ለቢቢሲ እንደገለጹት የሰባቱ ግለሰቦች ሕይወት ያለፈው ባለፈው ዐርብ ነሐሴ 17/2016 ዓ . ም . አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በናዳ የተቀበሩ ሰዎችን በመፈለግ ላይ ሳሉ በድጋሚ በተከሰተ አደጋ ነው። በአደጋው እናትና ልጅን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጠቀሱት አቶ ጋሻው፣ ክስተቱ ባጋጠመበት ወቅት የልጁ አስክሬን ወዲያው ሲገኝ የሁለቱ የቤተሰብ አባላት አስክሬን ግን ሳይገኝ እንዳደረ ተናግረዋል። በማግስቱ ቅዳሜ ነሐሴ 18/2016 ዓ . ም ጠዋትም የሁለቱን ሰዎች አስክሬን ለማውጣት የተሰባሰቡ ከ 18 በላይ የሚሆኑ ዘመድ አዝማድና የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍለጋ በተሰማሩበት ወቅት ድጋሜ በተከሰተ ናዳ የሰባቱ ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል አስተዳዳሪው። በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪም በስምንት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል። በሁለቱም አደጋዎች ከሞቱት መካከል የአራት ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን የቀሪዎቹ አለመገኘቱንና ፍለጋውም መቋረጡን ...