የbbc የአማርኛው ዘገባ። «ከ30 ዓመታት በላይ ሕይወቱን ለኪነጥበብ የሰጠው ኩራባቸው ደነቀ በወዳጆቹ እንዴት ይታወሳል?»

 

 

 

የbbc የአማርኛው ዘገባ።

«ከ30 ዓመታት በላይ ሕይወቱን ለኪነጥበብ የሰጠው ኩራባቸው ደነቀ በወዳጆቹ እንዴት ይታወሳል

https://www.bbc.com/amharic/articles/c62830d5kymo

«ከ1980ዎቹ መጀመርያ ጀምሮ በተለያዩ ቴአትር ቤቶች በትወና እና በአዘጋጅነት ሰርቷል።

በአዲስ አበባ በሚገኙት አራቱ ቴአትር ቤቶች በትወና፣ በዝግጅት፣ አንዲሁም በአመራርነት እውቀቱን አካፍሏል።

የሙያ ባልደረቦቹ ኩራባቸው ከማለት ይልቅኩራእያሉ መጥራትን ይመርጣሉ።

ሁሉም በአንድ ቃል ለሙያው ካለው ፍቅር ባሻገርጨዋታ ወዳድ፣ ወግ አዋቂመሆኑንም ይመሰክራሉ።

መካሪ፣ መንገድ መሪሲሉ የሚገልጹትም አሉ።

ለሦስት አስርታት በላይ በኢትዮጵያ የኪነጥበብ አድማስ ደምቆ የኖረው ኩራባቸው ደነቀ የተወለደው 1957 .. በሐረር ነበር።

ኩራባቸው የመጀመርያ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጭሮ ከተማ ነው የተከታተለው።

1979 .. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቴአትር ጥበባት የትምህርት ክፍል የተመረቀው ኩራባቸው፤ 1980 .. ጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር አርባ ምንጭ በጀማሪ የቴአትር ኤክስፐርትነት ተመድቦ ሥራ ጀመረ።

በአርባ ምንጭ ቆይታው ለኪነጥበብ ዝንባሌ ያላቸውን ወጣቶች በተለያየ መልኩ ይደግፍ እና ያበረታታ እንደነበር የሚነገርለት ኩራባቸውን በተመለከተ ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የራሱን ገጠመኝ በማንሳት ". . . እንደ መኪና ሮዴታ ከነበርኩበት ግራ መጋባት መንጭቆ አወጣኝ. . . " ሲል መስክሮለታል።

ኩራባቸው 1982 .. ጀምሮ በሕጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ቤት መስራት የጀመረ ሲሆን በዚያም ከተሳተፈባቸው ተውኔቶች መካከል 'የዝናቧ እመቤት ' እና 'የገንፎ ተራራ' ቴአትሮች ይጠቀሳሉ።

ኩራባቸው ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በጋራ በመሆን ባቋቋመው ንጋት የቴአትር ኢንተርፕራይዘም 'ቅርጫው' የተሰኘ ቴአትር ባህል ማዕከል ሰርቶ በራስ ቴአትር አቅርቧል።

ለሁለት ዓመታት ያህል በሕጻናት እና ወጣቶች ቴአትር የሰራው ኩራባቸው ቀጣይ መዳረሻው ሀገር ፍቅር ቴአትር ነበር።

ለሀገር ፍቅር ቴአትር ለየት ያለ ፍቅር አለው የሚባለው ኩራ 'የጨረቃ ቤት' 'ዓይነ ሞራ' 'ንጉሥ ሊር' 'ፍሬህይወት' 'ጥሎሽ' 'አሉ' 'ጣውንቶቹ' 'ከራስ በላይ ራስ' እና 'የሸክላ ጌጥ' ቴአትሮች በመድረኩ ላይ ተጫውቷል።

በሀገር ፍቅር ቴአትር 1994 . . ፅፎ ያዘጋጀው 'መዳኛ' የተሰኘው የአዘቦት ቀን የቴአትር ድርሰቱ አዳዲስ ቴክኒኮችን የተጠቀመበት እና ከፍተኛ ተወዳጅነት ያተረፈለት መሆኑ በባለሙያዎች ይገለጻል።

በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ደግሞ 'የጫጉላ ሽርሽር' ቴአትርን በራስ ቴአትር እንዲሁ 'ቅርጫው' የተሰኘው ቴአትር ኩራባቸው ከተወናቸው መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

ለኩራባቸው በትወናው እና በዝግጅቱ ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸው የሚገልፁት አርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) “የማዘጋጃ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ነው የማውቀውይላሉ።

ተሰጥኦውን ጠቅሰው ካደነቁ በኋላ ስለ አመራር ብቃቱጥሩ አመራር የሚሰጥ፣ ከዚያም ባሻገር በርካታ ቴአትሮችን ያዘጋጀም ነው። . . . አመራር በመስጠት ግሩም ነው። . . .በሥነ ምግባሩም ከማንኛውም በላይ የማከብረው እና የማደንቀው ነው። ትሁት ነው። . . . ለቴአትር ቤቱ ባለሙያዎች የተለየ አክብሮት አለው። ይህንን በርቀትም ቢሆን ማየት ችያለሁብለዋል።

እረኛዬ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ በደራሲነት እና በትወና አብራው የተሳተፈችው ደራሲ፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ አዜብ ወርቁ፣ ኩራባቸውን ከትወናው ባሻገር የምታውቀው የአዲስ አበባ ቴአተር እና ባህል አዳራሽ ሥራ አስኪያጅ እያለ ነው።

በወቅቱ አዜብ እና ጓደኞቿ ወደ ቴአትር ቤቱ በሚሄዱበት ወቅትእኛ ቴአትር ይዘን በምንሄድበት ሰዓት ጥሩ አቀባበል ነበረው። ደጋፊያችንም ነበርትላለች።

የሙዚቃ ባለሙያው ሠርፀ ፍሬስብሀት በፌስቡክ ገፁ ላይ ስለ ኩራባቸውኩራባቸው ደነቀ፥ ከምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ምሩቃን አንዱ ነበር። የቴአትር መድረክን ፈተና በብቃት የተወጣ ጥንቅቅ ያለ ባለሙያም ነበር። ከክዋኔ ባለሙያነቱ ትይዩ፥ የቴአትር ንድፈ ሐሳባዊ (Theoretical) ዕውቀቱም ከፍ ያለ ነበርብሏል።

ከአርቲስት ተስፋዬ አበበ እና አዜብ ጋርም የሚስማማ ሀሳቡን ሲያክልከትወና እና ከዝግጅት ችሎታው የማይተናነስ፥ የጽሑፍ ችሎታው፣ የንባብ ትጋቱ እና አስተዳደራዊ ብቃቱም ግሩም ነበርበማለት ነው።

 አቶ ተስፋዬ አበበ እንዳሉት ኩራባቸው ከትወና ባሻገር በአዘጋጅነትም በርካታ ተውኔቶችን አዘጋጅቶ ለመድረክ አብቅቷል።

ከእነዚህም መካከል 'ስጦታ' 'ጥሎሽ' እና 'መዳኛ' ቴአትሮች በቴአትርና ባህል አዳራሽ 'ሶስና' 'አንድ ክረምት' ጥቁሩ መናኝ' እና የጫጉላ ሽርሽር' (በአዘጋጅነት እና በተዋንያንነት ) ቴአትሮች በራስ ቴአትር 'ትንታግ' ይጠቀሱለታል።

ኩራባቸው ሙዚቃዊ ድራማዎች በማዘጋጀትም ስሙን በደማቁ ጽፏል። በአንጋፋዋ አርቲስት አስናቀች ወርቁ ህይወት ላይ ተመስርቶ የተፃፈውና ያዘጋጀው 'አስናቀች ኢትዮጵያ' እንዲሁም 'እስከመቼ' በሚል ርዕስ በቴአትርና ባህል አዳራሽ የቀረበው ከሸገር ሰርከስ ቡድን አባላት ከቴአትር ቤቱ ባለሙያዎች ጋር በጋራ የተሳተፉበት ተጠቃሽ ስራዎቹ ናቸው።

ደራሲ እና አዘጋጅ አዜብ፣ የእረኛዬ ድራማ ቀረጻ ላይ ኩራባቸውን ዳግም በቅርበት የማወቅ እድል ማግኘቷን ገልጻ፣ በቡድኑ ውስጥ በልምድ ከእርሱ የሚያንሱ ሰዎች ጋር እየሰራ እንኳታዛዥ፣ ጨዋታ ወዳድ፣ ወግ አዋቂ፣ ተግባቢ፣ ባለሙያዎችን አክባሪሆኖ ማየቷን ታስረዳለች።

ድራማው በቴሌቪዥን ተላልፎ ካበቃ በኋላም በነበራቸው የአሜሪካ ጉዞ ወቅት የበለጠ መቀራረባቸውን የምታስረዳው አዜብ፣ደስታን በጣም የሚወድ፣ ለራሱ በጣም ጥንቃቄ የሚያደርግ፣ የእግር ጉዞ ወዳድ ሆኖ ነው ያገኘሁትብላለች።

ኩራባቸው ከፃፋቸው የሬዲዮ ድራማዎች 'እናትና ልጆቹ' የተሰኘው ተከታታይ ድራማ 1990 .. 47 ሳምንታት በኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ ጣቢያ የተላለፈው እና 'የመጨረሻዋ ሌሊት' የተሰኘው ደግሞ በብሔራዊ ሬዲዮ ጣቢያ ለሁለት ሳምንታት የተላለፈ መሆኑን ይጠቅሳል።

ኩራባቸው ከተሳተፈባቸው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች 'ገመና 1' እና 'ገመና 2' እንዲሁም በአርትስ ቴሌቪዥን 48 ክፍሎች የቀረበው 'እረኛዬ' ይጠቀሳሉ።

ኩራባቸው ደነቀ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበር።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።