ላምን #ስላልፈቀድኩ ብቻ ዘገዬሁ። ኢትዮጵያ ያጣችው #ዓውራ ጥበበኛ።

 

ላምን #ስላልፈቀድኩ ብቻ ዘገዬሁ። ኢትዮጵያ ያጣችው #ዓውራ ጥበበኛ።
 
 
 
በፍፁም ማመን አቃተኝ። አልፎ አልፎ እንደሚወጡ አሳሳች መረጃወች ነበር የቆጠርኩት። የዛሬ ሁለት ዓመት በእሱ ዙሪያ አንድ መጣጥፍ ጽፌ ነበር። ተውኔትም፤ ቲያትርም፤ ጥበብም ይባል ውስጡ #የውስጥ ነበር። #ዋርካ #የጥበብ #ሰው። 
 
አወን ዋርካ የጥበብ ሰው። ተውኔት መሆኑን እስክትረሱት ድረስ ገፀ ባህሪያትን ተላብሶ ሲጫወት #ያስደምማል#ይመስጣል#የተሰጠው #የጥበብ #ባለፀጋ። ለዘርፋ ሽልማትም ነበር። እንዲህ እንደ ዋዛ መራራ ስንብት። 
 
የሚናፈቅ፤ የሚወደድ፤ የማይጠገብ ብዙ የሚዲያ ሰው ያልነበረ፦ መታዬትን ብዙ የማይቫ ቁጥብ። ግን በጥሪው ልክ ሆኖ በሥጋ የተለዬን። #የማይደገም#የማይሰለስ #ልዩ ፍፁም ልዩ ተዋናይ።
 
 እኔን ጨምሮ ለሚያከብሩት፤ ለሚሳሱለት ቤተሰቦቹ ሁሉ መጽናናትን ልመኝ። አርቲስት ኩራ ቸኮለ። በጣም ቸኮለ። ኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ሁለት ጥበበኞችን አጣች። ወጣት እና ጎልማሳ የጥበብ ልጆቿን። ያሳዝናል። 
 https://www.youtube.com/watch?v=FymiluMUvdQ
የአርቲስቱ ሞት እና አሳዛኙ የምርመራ ውጤት | ሀገሬ ቴቪ
 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉትሻ 27/08/2024
 
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።