"ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ፡ በእስራኤል የአየር ጥቃት ስር በምትገኘው ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ" ፈጣሪ ይጠብቃቸው። አሜን።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx257vzkxxyo ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ፡ በእስራኤል የአየር ጥቃት ስር በምትገኘው ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ 25 መስከረም 2024, 07:15 EAT "እስራኤል ተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀመችባት ባለችው ሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ መሆናቸውን ለቢቢሲ ገለፁ። ቢቢሲ ካነጋገራቸው በቤይሩት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆነችው ትዝታ ነዋሪነቷ በደቡባዊ ሊባኖስ ቢሆንም የእስራኤል ጥቃት ግን እርሷ ከምትኖርበት ራቅ ያሉ አካባቢዎች ላይ እየደረሰ መሆኑን ተናግራለች። የአየር ድብደባ ሲደርስ እርሷ በምትኖርበት አካባቢ እንደሚሰማ፣ ከአየር ድብደባው የተነሳ ቤቶች እንደሚነቃነቁም ትናገራለች። “በባሕር ዳርቻው አካባቢ የሚኖሩ፣ ለምሳሌ ሱራ አካባቢ፣ መውጫ አጥተው ልጆቻቸውን ይዘው ባሕር ዳርቻው አካባቢ ያደሩ ሰዎች [ኢትዮጵያውያን] አሉ” ስትል ከጥቃቱ ለመሸሽ በወጡ ሰዎች መንገዶች መዘጋጋታቸውን ተናግራለች። የእስራኤል አየር ኃይል ከፍተኛ ጥቃት እየፈጸመባቸው ካሉ የሊባኖስ ግዛቶች ለመውጣት መኪኖቻቸውን እና ያገኙትን መጓጓዣ እየተጠቀሙ በመጣደፍ ላይ ሲሆኑ፣ ዋና ዋና ጎዳናዎች በተሽከርካሪዎች ተጨናንቀዋል። ከዚህ ቀደም 20 ደቂቃ ይፈጅ የነበረው መንገድ አሁን ከስምንት እስከ 16 ሰዓት ይወስዳል ስትልም መንገዶች ከጥቃቱ በሚሸሹ ሰዎች መጨናነቁን ትናገራለች። በሊባኖስ የኢትዮጵያውያን በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው ‘እኛ ለእኛ በስደት’ ምክትል ዳይሬክተር እና በቤሩይት ነዋሪ የሆነችው እኑ በበኩሏ በእስራኤል የሚፈጸመው “ጥቃት እየከፋ” መምጣቱን ትናገራለች። ወትሮም በአስቸጋሪ ሁኔታ በሊባኖስ ውስጥ በቤት ውስጥ ሥራ ላይ ተሳማርተው ለሚገኙት ኢትዮጵ...