«አማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የመብት ጥሰት እንዲመረመር የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ»
«አማራ ክልል እየተፈጸመ ያለው የመብት ጥሰት እንዲመረመር የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ» ሲሳይ ሳህሉ ቀን: October 20, 2024 https://www.ethiopianreporter.com/134542/ «ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ ባስቆጠረውና በአማራ ክልል በሁለት ተፋላሚ ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት እየደረሰ ያለውን የከፋ የመብት ጥሰት፣ አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምርመራ እንዲያደርጉበት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ጠየቀ፡፡ ፎረሙ በጦርነት እየታመሰ ባለው የአማራ ክልል የጤና ተቋማትና አገልግሎት ላይ እየደረሰ ነው ላለው ቀውስ ምላሽ መስጫ ስትራቴጂ ይፋ አድርጓል፡፡ ይፋ በተደረገው ባለ 45 ገጽ ስትራቴጂ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ዩኒሴፍ፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የተመድ የሥነ ሕዝብ ድርጅት፣ የአማራ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተሳትፈውበታል፡፡ በስትራቴጂክ ሰነዱ እንደተብራራው፣ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ አደጋ እንደተደቀነበትና በጦርነት ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት ሥራ ማቆማቸውን፣ ከ1,100 በላይ ሠራተኞች መፈናቀላቸውን እና መገደላቸው ተመላክቷል፡፡ በሰነዱ ከ5,000 በላይ ሰዎች ለፆታዊ ጥቃት መጋለጣቸው የተጠቀሰ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ ወደ ጤና ተቋም የመጡትና የተመዘገቡትን ብቻ የሚይዝ ስለመሆኑ የፎረሙ ዋና ጸሀፊ ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በቀጠለው የደኅንነትና የፀጥታ ሥጋት የተነሳ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና የልማት አጋሮች በክልሉ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴና ድጋፍ በጊዜያነት ለማቆም እየተገደዱ ስለመሆኑም አመላክቷል፡፡ በበረታ...