ልጥፎች

የፍቅር ተፈጥሮ ሙያ ሊሆን ይገባል። Die Natur der Liebe sollte ein Beruf sein. Aber wie?

ምስል

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ።

ምስል
  ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የህወሃት ህገ - መንግሥት ተጥሶ ከምል #ተጠቅጥቆ ፦ የፓርላማው ጉባኤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት #ጭብጥብጥ ተደርጎ በራሳቸው ፈቃድ በአናርኪዝም መርኽ ሚኒስተሮቹን ሿሿሙ ---:ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ።    ለሚያረገርገው ካቤኒያቸው በዬጊዜው ሲያነሱ፤ ሚኒስተሮቻቸውን ሲያሽቀነጥሩ፤ በዲሞሽን ሲያንበሸብሹ ባሊህ ባይ የላትም ኢትዮጵያ። #ሃግ የሚልም የለም። በስንት ሽልንግ #ጦቢያን ዶር አብይ አህመድ አሊ እንደ ሸመቷት አይታወቅም። እንዲያ ወፍ የቀናው ዕለት በሥርዓተ አልበኝነት ህግ ጥሰው የሹመት ዓዋጁን ያስነኩታል። በሳቸው #የተጨባበጠው ፓርላማም ባሰኛቸው ቀን #ይሁንታ ይሰጥላቸዋል። መታደል ይባል መገደል አላውቅም።    ኢንጂነር አንሻን የመከላከያ ሚር አደረጓቸው። ወዲያው በዲሞሽን ከሆነ ቦታ ወስደው ሸጎጧቸው። በዛ ሰሞን ደግሞ ቀኑ ላልታወቀ ጊዜ ተልዕኮው ለምን እንደሆን ባናውቅም ዶር አብርኃም በላይ ተነስተው ኢንጂነር አንሻ የመከላከያ ሚር ሆነው ተሹመው አይተናል። የሚባንን ጉድ።   ወደ ቀደመው ጉዳዬ ስመለስ በዚህኛው የሹመት ሂደት እንዲያው በመፈንቅል ይሁን፦ በተፈጥሮ ሁኔታ አንድ ነገር ቢፈጠር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ማን በብልጽግና ሠፈር ይተካል ለሚለው የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ስጋት፦ እራሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መልስ ሰጥተዋል። ቀዳማዊ እመቤትነቱም በፍትህ ሚኒስተርነት ቀድመው ቁብ አድርገዋል። የህግ ባለሙያው ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ ከዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ጋር ይተዋወቁ ዘንድ ሁለተኛ ዕድል ...

የጃርት ጉባኤ ርደት። Poesie By Sergute Selassie Der Mensch wurde zum Guten gesc...

ምስል
የጃርት ጉባኤ ርደት         *** ባድም በጃርት ተሰቅዛ ... በአረማሞ አራሙቻ ናውዛ።   እህህን ሰንቃ ደንዝዛ ... ሰቀቀን ታጥቃ አርግዛ።   በ’ሬት ጨጎጎት ተደልዛ ... መቀነት በእሾህ ተገንዛ ... ቁም ስቅሏን አዬች - ይህው በልዛ።   ጃርተ - ምርት፣ እሾህ ... ፍጥረተ - ነገሯ፣ ውጋት። ... በበቀል ተዋቅራ በደም ተቋድሳ በደጋን ታምሳ ተደቁሳ። እሾህ አዘራች መልሳ   .. የጃርት ገላ መላልሳ።   ህልም ራዕዩ ምልግልግ የላንቁሶ ውሃ ዝልግልግ። ጃርተ- ልብ፣ የእሾህ ልግ የአሜኬላ የቋሳ ድግዳግ።   ጃርትስ አሰኛት የበቀል ብቅል የአብሾ ጠላ ዝልል። ቋቱ የማያውቅ ግልግል የጃርት ህሊና የውጋት ግልገል ... ... ሰባራ ገል።   እሾህስ አልቦ የለም ጃርት ከዘረ እሾህ የለም ምርት። የጠቀራ ናስ ሃሞት ዙሪያ - ገባው፣ ማት ... ... ህልፈት የሐገር ቅብረት።   አንተ አለህ እና በቤትህ ትሰማለህም ታያለህም የጃርተን-ትእቢት፤... የቀን ጥሰትን የበቀል አምላክ አትለፋት የሕዝብን ዕንባ ህማማት ... እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ-! እም-እ-እ-እእ    ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም አንደልፊንገን-ሲዊዘርላንድ    

"በሰሜን ጎጃም ዞን ድሮንን ጨምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ" bbc

  https://www.bbc.com/amharic/articles/c8elz7gzg8jo በሰሜን ጎጃም ዞን ድሮንን ጨምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ   18 ጥቅምት 2024 በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ “ የመንግሥት ኃይሎች ” ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ ፈጸሟቸው በተባሉ ጥቃቶች ከ 100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። በወረዳው ዋና ከተማ ገርጨጭ ከጥቅምት 01 እስከ ጥቅምት 04/2017 ዓ . ም . በድሮን ጥቃት እና በዘፈቀደ በተፈጸሙ ጥቃቶች ህጻናትን ጨምሮ ሽማግሌዎች እንዲሁም ወጣቶች መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ ) ስለተፈጸሙት ግድያዎች ሪፖርቶች እንደደረሱት እና መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የፋኖ ኃይሎች አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጾ፤ “53 የጽንፈኛው አባላትን ” መግደሉን አስታውቋል። አርብ ጥቅምት 01/2017 ዓ . ም . እኩለ ቀን 7 ፡ 00 አካባቢ በከተማው የሚገኘው መሀል ገነት ጤና ጣቢያ ላይ በተፈጸመ “ ተደጋጋሚ ” የድሮን ጥቃት የዘጠኝ ዓመት ህጻንን ጨምሮ ስምንት ሠዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተፈጸመው ተደጋጋሚ ጥቃት ከጤና ጣቢያው ባሻገር በአቅራቢያ የነበሩ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ገልጸዋል። “ ጢዝ የምትል ድምጽ ዓይነት አላት። አ...