ልጥፎች
«በአማራ ክልል አራት ካምፖች “ለጅምላ ማሰሪያነት” መዋላቸውን አምነስቲ አስታወቀ
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9gxlvyyzro «በአማራ ክልል አራት ካምፖች “ ለጅምላ ማሰሪያነት ” መዋላቸውን አምነስቲ አስታወቀ በአማራ ክልል ለአንድ ወር በዘለቀው “ የዘፈቀደ እስር ” የተያዙ “ በሺዎች የሚቆጠሩ ” ነዋሪዎች በዳንግላ፣ ኮምቦልቻ እና ሸዋ ሮቢት ከተሞች እንዲሁም በጭልጋ ወረዳ በሚገኙ ጊዜያዊ የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። አምነስቲ፤ “ ኢትዮጵያ ለአገራዊ፣ ለአህጉራዊና ለዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ግዴታዎች ግድ የለሽ ወደመሆን አዲስ ምዕራፍ ገብታለች ” ሲል ወቅሷል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ይህንን ያለው ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለውን “ የዘፈቀደ እስር ” በተመለከተ ትናንት ረቡዕ ጥቅምት 27 ፤ 2017 ዓ . ም . ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው መግለጫው ነው። ተቋሙ፤ በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን እስር እና የእስረኞች አያያዝ በተመለከተ ከእስር ካምፖች የወጡ ሰዎችን ጨምሮ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት እንዳነጋገረ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። አምነስቲ፤ እስሩን አስመልክቶ ባደረገው ጥናት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ አራት የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ እንደደረሰበት አስታውቋል። “ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት፤ ግብረ ኃይሉ በመላው አማራ ክልል የሚገኙ አራት ጊዜያዊ የእስር ካምፖችን በሺዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መሙላቱን አረጋግጧል ” ሲል በጥ
የአለምን አትኩሮት ስቦ የቆዬው የአሜሪካ የ2024 ፕሬዚዳንታዊ እና በዬደረጃው ያሉ ምርጫ አካቶ #በሰላም ተጠናቋል። ተመስገን። አሜን።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የአለምን አትኩሮት ስቦ የቆዬው የአሜሪካ የ2024 ፕሬዚዳንታዊ እና በዬደረጃው ያሉ ምርጫ አካቶ #በሰላም ተጠናቋል። ተመስገን። አሜን። አሜሪካ ለዴሞክራሲ የምርጫ ሥርዓት መንፈስም ነው። የሚስብ ነገር አለው። "አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሄር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።" (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር፯) የእኔ ጭንቀት ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ነበር። እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን በሰላም ተጠናቋል። እርግጥ ነው ዴሞክራቶች በሰፋ ልዩነት ተሸንፈዋል። ውድድር ለመሸነፍም // ለማሸነፍም ነውና ዴሞክራቶች መሸነፋቸውን በፀጋ ስለሚቀበሉ የምርጫው ውጤት #በሰላማዊ ሽግግር ይፈጸማል። ሪፕብሊኮች ተሸንፈው ቢሆን ግን ከባድ ችግር ይከሰት ይሆን በሚል ስጋት አድሮብኝ ነበር። እግዚአብሄር የወደደው ተፈጽሟል። የእግዚአብሄር ፈቃድ ከእኛ በላይ ለአለሙ ሰላም ይጠናቀቃል - እና። በተረፈ ይህን መሰል ዕድል ለአገሬ ለኢትዮጵያም ይገጥማት ዘንድ እመኛለሁ። ህዝብ ካለምንም ጠበንጃ የፈለገውን፤ ያሻውን ደስ ብሎት መምረጥ የሚችልበት የዴሞክራሲ ጥበብ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ #ህልም ነው። የአሜሪካ አገር የየዘመኑ የምርጫወች ሂደት እጅግ አጓጊ እና ቀልብን የሚይዝ ነው። የዘንድሮ ምርጫ ፋክክሩ በጠሩ ፋክቶች ላይ ስለነበር መሳጭ ነበር። ስለሆነም ከውስጤ ነበር የተከታተልኩት። የሴት እጩ ፕሬዚዳንትም መኖር የበለጠ አትኩሮቴን ስቦት ነበር። ዴሞክራቶች በእጩ ፕሬዚዳንታቸው ጎን በምክትል ፕሬዚዳንትበክብርት ወ/ ሮ ካሜላ ሃሪስ (ኮሚላ ሃሪስ) ዙሪያ ተግተዋል። ተጽዕኖ ፈጣሪወች አብዛኞቹ ከጎናቸው አሰልፈውም ነበሩ። በተደጋጋሚ ሴት የዴሞክራሲ እጩወች ለፕሬዚዳንትነት ተወዳድረው አልተሳካላቸውም። ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህ