ልጥፎች

#የኮበሌ መንፈስ ያዘነበላቸው ሚዲያወች ቅኝት። ለእኔ - የአንካራው ሥምምነት።

  #የኮበሌ መንፈስ ያዘነበላቸው ሚዲያወች ቅኝት። ለእኔ - የአንካራው ሥምምነት። "የቤትህ ቅናት በላኝ።   • https://www.bbc.com/amharic/articles/cly25z39pdpo "ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት የደረሱበት ሰነድ ምን ይዟል?"   ሙሉ 11ወር ያልነካካሁት አጀንዳ ነበር። የኢትዮጵያ እና የሱማሌ ላንድ የመግባቢያ ሰነድ #ግጥግጦሽ ። እርግጥ ነው በዚህ ምክንያት የሱማሌ ላንድን ምርጫ ሂደት ከውስጤ ተከታትዬዋለሁኝ። በአንድም በሌላም የእምዬ ጉዳይ ስላለበት። ነባሩ መሪ በተፎካካሪያቸው ተሸንፈዋል። ስለዚህም አዲስ ሁኔታ ይኖራል እራሱ በሱማሌ ላንድ ፖለቲካ። ሱማሌ ላንዶች ጠቅላይ ሚር አብይ በጠረጉላቸው ጎዳና የዓለም ዓቀፍ ሚዲያ ሽፋን በስፋት አግኝተዋል። ስለዚህ + አትርፈዋል። ሰነዱ ሲቀደድ ደግሞ ከስረዋል - ይሆናል። ምን አልባት ዕውቅናውን #ሌላ #አገር ሊደፍረው ይችል ይሆናል። አሁን የሱማሌ ላንድ ህዝብ ግብረ መልሱ ምን ይሆናል ደስታቸውን ስለተነጠቁ??? የሱማሌ ህዝብስ ሲግረጨረጩ ስለባጁ?   የኢትዮጵያ ሚዲያወች አብይዝምን የሚደግፋ #ኮበሌ ኮበሌ የሚል ጠረን ያለው ዕርዕስ ሰጥተው እዬዘገቡት ነው። ግርም ብሎኛል። ዕውን ለኢትዮጵያ "ደህንነቱ አስተማማኝ የባህር በር" የአንካራው ስምምነት ያስገኝ ይሆን? ለመሆኑ ሱማሌ የረጋ መንግስታዊ ስርዓት አላትን? አስተማማኝነት ከአንድ አገር የደህንነት አቅም ጋር ስለሚለካካ። አስተማማኝ የመንግሥት ሥርዓት የካርቢያን አገሮች ሲዊዲን፤ ዴንማርክ ኖርወይ፤ ሲዊዘርላንድ ወዘተ ናቸው፤ አውሮፓ እንኳን አሁን በጭንቅም በጦርነትም ላይ ናቸው ነገረ ዩክሬንን ተከትሎ። ፖላንድ፤ ኢስቶንያ፤ ጀርመን ፈረንሳ ይ ……    #ግነቱ የሚተናነቅው ሃቅ ም...

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት የደረሱበት ሰነድ ምን ይዟል? የአንካራ ስምምነት ዋነኛ ነጥቦች...የእኔም ዕይታ።

    ዶር አብይን ያመነ ጉም የዘገነ ነው። የፈረንጆች 2025 አዲስ ዓመት ሲመጣ አንድ አመት የሚሞላው ስምምነት ጨነገፈ። እኔ በዚህ ዙሪያ ምንም አላልኩም ነበር። ዝም ብዬ ነበር የባጀሁት። ምክንያቴ አስተማማኝ የፖለቲካ አቅም፤ አቋምም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መሪ ስለለ። የሆነ ሆኖ በዚህ የአንካራ ስምምነት ሰላም በኢትዮጵያ እና በሱማሌ ሉዓላዊ አገራት #መታጨቱ ግን ያስደስተኛል። ይህ እርምጃ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅም፤ ለቱርኪ ለአንከራ፤ ለሱማሌ መንግሥት ምን አትርፎ ምን ሊያከስር እንደሚችል የዘርፋ ባለሙያወች ይተንትኑት። ለእኔ የሰላም #ቃጭሏ ናት ወሳኝ ጉዳይ። ዓለምዓቀፍ ማህበረሰቡም የስምምነቱን ይዘት እንደምን እንደሚመለከተው እንጠብቃለን። ባለ ተስፋ ጠባቂው የሱማሌ ላንድ መንግሥት እና ህዝብስ ከአዲሱ መሪው ጋር ይህን መርዶ እንደምን ያስተናግዱት ይሆን? አማፂው የሱማሌው አልሸባብስ???? በቅድሚያ ከBBC አማርኛ ዜና ያገኘሁትን የስምምነቱን ነጥብ አንስቼ የራሴን ዕይታ አቀርባለሁ። የአብይዝም ሚዲያወች ደግሞ አሁን ምን ለማለት ይጣደፋ ይሆን??? ወዘተረፈ ጋራጅ ስላላቸው። ጥገናክፍላችው በርካታ ነውና።   "ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት የደረሱበት ሰነድ ምን ይዟል ?"  https://www.bbc.com/amharic/articles/cly25z39pdpo ከ 4 ሰአት በፊት "ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንድ ዓመት ሊሞላው የተቃረበውን አለመግባባት በቱርኩ ፕሬዝዳንት አቀራራቢነት አንካራ ላይ በተደረገ ውይይት ለመፍታት የሚያስችል ስምምነት ላይ ደረሱ። ከሁለቱ አገራት አልፎ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ ውጥረትን አንግሶ የቆየው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውዝ...