ልጥፎች

"የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ" BBC.

  ኦኦ።   " የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ" BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/cq8qzgn19ylo ከ 3 ሰአት በፊት "የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢቲሀድ ኤርዌይስ ሕግ በመጣሳቸው በገንዘብ እንዲቀጡ ወስኗል። ሚኒስቴሩ ባለፈው ሐሙስ ባወጣው መግለጫ መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሜሪካው ዩናይትድ ኤርላይንስ መለያ (ኮድ) በመብረሩ 425 ሺህ ዶላር እንዲቀጣ ተወስኗል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ኤቲሀድ አየር መንገድ ደግሞ ጄትብሉ በተባለው የአሜሪካ አየር መንገድ መለያ ቁጥር በመብረሩ 400 ሺህ ዶላር ተቀጥቷል። ሚኒስቴሩ በድረ-ገፁ ባወጣው መረጃ እንዳለው ሁለቱ አየር መንገዶች፤ በፌዴራል አቪዬሽን ባለሥልጣን (ኤፍኤኤ) የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩ በተከለከሉባቸው የአየር ክልሎች በመብረራቸው ነው ሕግ የጣሱት። ሁለቱ አየር መንገዶች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ተዘግቧል። አቪዬሽን ኮንሲዩመር ፕሮቴክሽን የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ቢሮ ባደረገው ምርመራ ከአውሮፓውያኑ የካቲት 2020 እስካ ታኅሣሥ 2022 ባለው ጊዜ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥፋቱን ፈፅሟል የተባለው። በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዩናይትድ ኤርላይንስን ኮድ ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ጂቡቲ በርካታ በረራዎችን አድርጓል፤ ይህ የአየር ክልል ደግሞ የአሜሪካ አየር መንገዶች እንዳይበሩበት በፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ክልከላ የተደረገበት ነው ይላል። የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ይህንን ድርጊት የፈፀመው ከዩናይትድ ስቴትስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ፈቃድ ውጭ መሆኑን መግለጫው ያ...

«የበሻር አል አሳድ እና ቤተሰባቸው ቀጣይ ሕይወት ምን ሊሆን ይችላል?» BBC.

  https://www.bbc.com/amharic/articles/cjr2nl2p18go «የበሻር አል አሳድ እና ቤተሰባቸው ቀጣይ ሕይወት ምን ሊሆን ይችላል ?»   15 ታህሳስ 2024, 07:27 EAT «ባለፈው ሳምንት እሁድ በሻር አል አሳድ ለ 24 ዓመት የሙጢኝ ብለው ከያዙት ሥልጣን ሲወገዱ፣ የእርሳቸው የፕሬዝዳንትነት ዘመን ዶሴ ብቻ ሳይሆን፣ ቤተሰባቸው ከ 50 ዓመታት በላይ ሶሪያን ሲገዛ የነበረው መዝገብ አቧራው ተራግፎ መነበብ ጀምሯል። አሳድ በአውሮፓውያኑ 2000 መንበረ ሥልጣኑን ከመረከባቸው በፊት አባታቸው ሐፊዝ አል አሳድ አገሪቷን ለሦስት አስርታት መርተዋታል። አሁን፣ በእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሃያት ታህሪር - አል ሻም ( ኤችቲኤስ ) የሚመሩት አማፂያን የሽግግር መንግሥት የመሠረቱ ሲሆን፤ ከሥልጣን የተነሱት ፕሬዝዳንት፣ ባለቤታቸው እና የሦስት ልጆቻቸው የወደፊት መጻዒ ዕጣ ፈንታ አይታወቅም። አሁን ከነቤተሰቦቻቸው በሩሲያ ጥገኝነት ጠይቀው የሚገኙት የቀድሞው የሶሪያ ፕሬዝዳንት ምን ይጠብቃቸዋል ? አሳድ ለምን ወደ ሩሲያ ሸሹ ? ሩሲያ በሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ለአሳድ ጠንካራ አጋር የነበረች ሲሆን፣ በመካከለኛዋ ምሥራቅ አገር ሶሪያ ሁለት ቁልፍ የጦር ሰፈሮች አሏት። በአውሮፓውያኑ 2015 ሩሲያ አሳድን በመደገፍ የአየር ጥቃት ዘመቻ የጀመረች ሲሆን፣ ይህም በጦር ሜዳ ያለው ድል ወደ መንግሥት እንዲያዘነብል አድርጎ ነበር። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኝ ሶሪያን በቅርበት የሚከታተል አንድ ...