ይህ አስደንጋጭ ዜና እና የአማራ ትውልድ እጣ ፈንታ #ግራጫማ ተስፋ።
ይህ አስደንጋጭ ዜና እና የአማራ ትውልድ እጣ ፈንታ #ግራጫማ ተስፋ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ይህ ቤተሰብ፤ እነኝህ የነገ #አበባወች እንደምን ይሆኑ ይሆን? በምን ቀመር #ህፃናቱ ተረጋግተው ትምህርታቸውን ይከታተሉ ይሆን? ህፃናቱ በምን ሁኔታ ካለ አባት #በአንድ ክንድ መኖራቸው ይቀጥል ይሆን? ለዚህ ቤተሰብ ቀጣይ የመኖር ዕጣ ፈንታ #ዋስትና ሰጩ ማን ይሆን? የአማራ ትውልድ እና ትምህርት በምን ሁኔታ በተስፋ #ይቀጥሉ ይሆን? ይህቺ ሸበላ ወጣት፤ ትዳሯን በአፍላ ዕድሜዋ የተዘረፈችስ ቀጣዩን ውስብስብ ፈተና በምን አግባብ #ትወጣው ይሆን? መርዶውን ከሰማሁበት ቅጽበት ጀምሮ ውስጤ ሙግት ላይ ነው። ሌላ ሥራ መስራት አልቻልኩም። ተስፋ እንዲህ በግፍ እዬተቀበረ ተስፋን ማሰብ ሆነ ማስቀጠል እንደምን ይቻል ይሆን? ከባድ ነው። እጅግ ከባድ። ይህን ያህል ዘመን የደከመ፤ የለፋ ሊቀ - ሊቃውንት አስፓልት ላይ በባሩድ #ተደብድቦ ነፍሱ ሲነጠቅ የአማራ ክልል መንግሥት አለሁ ሊል ይችል ይሆን? ማነውስ ኃላፊነቱን የሚወስደው? በቀጣይ በዚህ ደረጃ የሚገኙ በዬትም ቦታ የሚኖሩ የአገር ኮከብ የሆኑ የአማራ ልዩ ጸጋ እና ችሎታ ያላቸው ሊቀ -:ሊቃውንት ቀጣይ የሆነውን የመኖራቸውን ሃዲድ እንደምን ያስቀጥሉ ይሆን??? ሆዴ - አብዝቶ ይረበሻል። በጣም ባርባር ይለኛል። ነገ በእጅጉ ያስፈራኛል። ከውስጤ የምጥ ያህል ይጨንቀኛል። አጀንዳዬ #ትውልዱ ነው። ትውልድ ከሌለ አገርም፦ አደራም የለም። የሰለጠነ፤ በዕውቀት የዳበረ፤ ተምሳሌት የሚሆን አባ ቅንዬን ሩህሩህን ዶር አንዱአለም ዳኜን ያጣ ህዝብ #ነገው ምን ይመስል ይሆን? ያስፈራል። ይጨንቃል። ወላጅ እናቱ ይኖ...