ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል። 25/03/2024
ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል። • ጨካኞች በሽተኛ ናቸው። እንደ ሙሉ ሰው ሊታዩ አይገባም። • ጨካኞች ያልሰለጠኑ ናቸው። ሥልጣኔ ኢንተግሪቲ ነውና። • ጭካኔ ዬአስተሳሰብ ድህነት ነው ወደ ኋላ አብራራዋለሁኝ። • ጭካኔ ዬድንጋይ ዘመን ህዳሴ ነው። ጭካኔ ሰብዕናን ገድሎ ጫካዊነትን ማነፅ ነው። • ጨካኝ ሱፍ እና ገበርዲን ከረባት እና ቀሚስ አደለም ሰብእናዊ ቀለም ነው። • ጨካኞች አመክንዮ ስለመፈጠሩ አያውቁም፣ እርካታቸው አመክንዮን መስቀል ነውና። • ጨካኝነትን ለፋክክር ዬሚያቀርቡ ልሙጥ ሰብዕና ያላቸው ናቸው እና። እንሰሳነት ስለማያስቀና። #ኋላቀርነት ። በኢኮኖሚ ሳይንቲስቶች ኋላቀርነት በኢኮኖሚ ዕድገት አለመመጣጠን ይሉታል። እኔ ደግሞ በአስተሳሰብ ዘሃ ዬህሊና ድህነት እለዋለሁኝ። ልቆ አይፈጠርም የሰው ልጅ። ቅዱሳን አሉ በቅብዓ ዬሚሰጡ። ነገር ግን ዬሰው ልጅ ዲግሪውን ቁብ አድርጎ አይፈጠረም። ሂደት ትምህርት ቤት ነው። መኖር ትምህርት ቤት ነው። ቤተሰብ ትምህርት ቤት ነው። የአኗኗር ዘይቤ ትምህርት ቤት ነው። ተፈጥሮ ትምህርት ቤት ነው። ቀደመው ዬታነፁ፤ ዬተገነቡ ቅርስ እና ውርሶች ትምህርት ቤት ነው። ታሪክ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤት ዬግድ ዩንቨርስቲ መግባት ብቻ አይሆንም። ዕድሉን ያገኙ ሁለገቡን ተምረውበት ክህሎቱን በሥልጠና ያዘምኑታል። ይህ ለታደሉት ነው። ላልታደሉት ደግሞ ትውስቱም፤ ውራጁም ብርቃቸው ነው። አሁን ለፋንታዚው ልዑል ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የውሃ ዳንስ፤ የፓርክ ግንባታ፤ የኩሬ ውሃ ዋና ብርቅ እና ድንቃቸው ነው። ይህ ግን አንዱን ቤተ ጊዮርጊስ የሚሰጠውን ሚስጢር አቻ ሊሆነው አይችልም። ግብግቡ ዬጭካኔው ውርስ የሥልጣኔውን...