"ሮበርት ፕሪቮስት አዲሱ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ማን ናቸው? BBC
የሰላም ያድርገው። አሜን። BBC ምን አለ። የጀርመኑ ቀደምት ሚዲያ ZDFስ? https://www.youtube.com/watch?v=W0thXkiF6rM https://www.bbc.com/amharic/articles/cgj8vwjpn24o • "ሮበርት ፕሪቮስት አዲሱ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ማን ናቸው? ትናንት ከሰዓት በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰባሰበው ሕዝብ የተመረጡት አዲስ ሊቀ ጳጳስ ማን መሆናቸው በይፋ ከመነገሩ በፊት 'ረዥም ሕይወት ለጳጳሳችን' እያለ ድምጹን ጮክ አድርጎ ደስታውን ሲገልጽ ነበር። የ69 ዓመቱ ሮበርት ፕሪቮስት 267ኛ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ሲሾሙ መጠሪያቸውም ሊዮ 14ኛ እንደሚሆን ተነግሯል። ምንም እንኳ አብዛኛውን የአገልግሎት ዘመናቸውን ያሳለፉት በላቲን አሜሪካ ቢሆንም፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ለመጀመርያ ጊዜ አሜሪካዊ ሊቀ ጳጳስ መሾሟ ነው። ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ጵጵስናቸውን ከመቀበላቸው በፊት በፔሩ በሚሽነርነት ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል። በ1955 በስፔናዊ እናታቸው እና የፈረንሳይ እና ጣልያን ደም ካላቸው አባታቸው በቺካጎ የተወለዱት ፕሪቮስት፣ በ1982 ቅስናቸውን ተቀብለዋል። ከሦስት ዓመት በኋላ ወደ ፔሩ ቢያመሩም ወደ አሜሪካ ለተለያዩ አገልግሎቶች ይመላለሱ ነበር። የፔሩ ዜግነት ያላቸው ፕሪቮስት ከተገለሉ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በመስራት እንዲሁም ልዩነቶችን ለማጥበብ በመጣር ይታወቃሉ። በሰሜናዊ ምዕራብ ፔሩ የአንድ ቤተክርስትያን መጋቢ በመሆን ለ10 ዓመት ያህል ያገለገሉት ፕሪቮስት፣ በካቶሊክ ሴሚናሪ ውስጥ በመምህርነትም ሰርተዋል። ሊዮ 14ኛ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኋላ በተናገሩት የመጀመርያ ንግግር በሞት ለተለዩት ሊቀ ጳ...