ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ አቤቱታ። አብይ ሆይ!

                            አብይ ሆይ! 
                        ኢትዮጵያዊ ዜጋ 
                           ከሆንኩኝማ
                     እኔም ዘለግ ያለ ህላዊ 
                          አቤቱታ አለኝ።
                                                                     ከሥርጉተ - ሥላሴ 
                                                           (ከገዳማዊቷ አገር ከልባሟ ሲዊዘርላንድ።)

                
                   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፣ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱“)

ለክቡር ዶር. አብይ አህመድ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር
አዲስ አበባ፤
ግልባጭ
ለጠ/ሚር ቢሮ
አዲስ አበባ፤
ግልባጭ ለክቡር የኦሮምያ ክልላዊ ፕሬዚዳንት ለአቶ ለማ መግርሳ።
አዳማ።
ቀን እ.አ.አ. 01.06.2018           
  • ·         ልአዛሯ ኢትዮጵያ።

በቅድምያ በትሁት ኢትዮጵያዊ ባህል እና ወግ መነሻነት ከውስጤ በፈለቀ ቅንነት የከበረ ሰላምታዬ ይድረስልኝ።

ክብሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

ዛሬ በነጮች የቀን አቆጣጠር መባቻ ነው። „መቋሚያ“ መነሻዬ ነበር። አዲሶቹ የኦህዴድ ወጣት ሊሂቃንም ኢትዮጵያዊ ናቸው፤ ስለ አካዳሚ ነጻነት የሚታገሉ ሊቃውንተ ሙሁራን የእነዚህን ቀንበጥ ፖለቲካኞችንም መንፈሳቸውን ማቀፍ አለበት የሚል ዕድምታ ነበረው። መሠረቱ VOA ከሁለት ሊሂቃን ጋር ያደረገው ውይይት ነበር። የአብቹ አንበሶች በሚል ስለ „ጣና ኬኛ“ ከዛም ሌላው ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ጋር አያይዤ የለማን መንፈስ የጻፍኩበት ነበር ስለ „ምህላም“። በመቀጠል „መባቻ“ የሚልም ጽፌ ነበር። የዛሬው የመባቻ ለመሰንበቻ በታሰብ ተስፋ ላይ ሰሳ ያሉትን ጉዳዮች በአቤቱታ መልክ አቅርባለሁኝ፤ የ60 ቀን የጠ/ ሚር ተግባራትን በሚመለከት ድርጊቱ ራሱን ስለሚገልጽ ተከራካሪ አያስፈልገውም።

ክቡር የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

እንደ ማንኛውም ቅን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እኔም ክቡርነተዎት በዚህ አጅግም ፈተኛ በሆነ የተስፋ የጣረሞት ወቅት በነፍስ አባትነት ለዚህ ግማድ በመቀባተዎት ደስታ ሳይሆን ከደስታም ከፍ ባለ ሁኔታ ሐሤት ተስምቶኛል። የተስፋዬ መሰንበቻ ጥግ ስላገኜ። እኔም ብቻ ሳልሆን የፖለቲካ ተሳትፎዬ ብዙም የማይመቻቸው ውጪ አገር የሚኖሩ መላ ቤተሰቦቼ መሰል ስሜት እንደ ተሰማቸው የገለጡልኝ በቅርቡ ነው። ሰላማቸውን ላለማወክ ለዓመታት በተዕቅቦ ነበር እኔ ኑሮዬን የወሰንኩበት። አስታራቂው፤ አነጋጋሪው፤ አግባቢው መንፈስ አብያዊ ነበር። ለዚህም ብሩክ ማዕልት እግዚአብሄርንም አመስግነዋለሁ። ስለሆነም አልአዛሯ ኢትዮጵያ የሸለመችን ልዩ ክስተታዊ ወቅት ነው። መባቻው አምሮበታል መሰንበቻውም ያምርበታል። የእኔ ተመስጦ በብዙ መልኩ ይለይ ይሆናል። እንደ ተፈጥሮዬ። መሪነት ለእኔ የውስጥ ውበት ነው። ይህን ፈጣሪ አልነሳነም ባይ ነኝ። ውስጠዎት ውሃማ ነው። የክብሩነተዎት የተለዬ ጸጋ በእኔ ዕይታ የወስጥዎት ስፋት በመቻል መሆን የተቃኜ ስለሆነ ነው። ከሰሞናቱ የክቡርነተዎትን ውሎ በወለጋ ደንቢደሎ ሳዳምጥ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሆኑ በግል የሚታገሉት ታታሪዎች እከሌ ተከሌ ሳይባል የራዕያቸው አስፈጻሚ መሳሪያ አልባ እንደሆነ ነው። ዶር መራራ ጉዲና ጠ/ ሚር ሆነው ቢመረጡም ለደንቢ ደሎ የተስፋ መንፈስ እርካታ አይሰጠውም። በዚህ መንፈስ ውስጥ ደንቢ ደሎ የለም። የኦሮሞነት አክቲቢስቱም፤ ፈርስታውያን ነን የሚሉትም፤ ኦንግውያንም፤ የተፎከካሪ የፖለቲካ ድርጅት አብሶ ኦፌኮን መሪዎች መሬት ላይ ያሉት እሰከ ማንፌስቷቸው መንፈሳቸውን የሚቀርብ ሁኔታ የለም። ሌላ መንገድን የተከተለ ነው፤ ጥልቀት ጥናት የሚያስፈልገው የተቋጠረ ጠጠርማ አምክንዮ አለበት። በሌላ በኩል የ27 ዓመቱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የብሄር እና ብሄራሰቦች እኩልነት ልግጫም ወና መሆኑን ተመልክቻለሁኝ።

የኢህአዴግ የለወጥ ዘመን በግንባሬ፤ በድርጅቴ ጥንካሬ አምጥቸዋለሁኝም የሚለውም መንፈሱ በእውቀት ደረጃ እንኳን ምንም ነው። የ4 ጥምር ፓርቲ ስብስብ ስለመሆኑ በድምጽ እንደሚወስን ሊያገናዝቡት አልቻሉም። የፖለቲካ ድርጅት ጽንሰ ሃሳቡ ደክሞታል። ስለሆነም ለክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጥናቱን አብዝቶ እንዲሰጥልኝ ልዑል እግዚአብሄርን እለምነዋለሁኝ። አዬር ላይ የተንጠለጠለው የቪሊዮን ፍላጎት ናፍቆተኛም መሬት የረገጠ ግንዛቤውን ለማዳበር መጣር ያለበት ይመስለኛል። ራያችን እና እኛ በውል አንተዋወቅም። ለምንቃወም የመልካም ነገር አምክንዮ ሊመጥን የሚችል መካች የመንፈስ ሃይሉ ራሱን ችሎ የሚቆም አይደለም። እስከ ዛሬ የባከነው የሰው ልጅ መንፈስ፤ ህይወት እና መዋዕለ ንዋይ የተቀራረበ ዕድሉን መተርጎም አልቻለም። የህሊና ድርቀት አብዝቶ ጨምድዶ ይዞናል። በመፈለግ ብቻ ወደ ግብ ስለመድረሳችን እንኳን ፈታኙን አመክንዮ እራሱ የሚያቀርብልን ሞጋች ሃሳብ መመለስ አልቻልነም። የሃይል አሰላለፍ ሚዛናዊ ትኩረት ለራዕያችን ቅርበቱን መዝኖ ሊጠቅም በሚችል መልኩ የመምራት ክህሎቱም የዛኑ ያህል ክፍተት አለበት። ይህ እውነትም ረቂቅም ነው። 

ክቡሩ ዶር አብይ አህመድ ሆይ!

የወጡበት ድርጅት ኦህዴድም ለዚህ ብሄራዊ የነፍስ አድን፤ አገር አድን፤ ብሄራዊነትን አድን፤ ሰው አድን፤ ተፈጥሮን አድን፤ የዘመቻ ወቅት ሃላፊነቱን መረከቡ ለእኔ ከገሃዱ ዓለም ትርጉም ይልቅ መንፈሳዊ ሚስጢሩ ይልቅብኛል። ስለዚህም ኦህዴድ በፈጣሪ አምላኬ በቅዱስ እግዚአብሄር ታምራዊ የቁርጥ ቀን እንደ አሮን በትር አዬዋለሁኝ፤ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጽኑ መንፈስም መኖሩ የፈጣሪ ምርቃት ነው። በተሟላ ብቃት ውስጥነት ጥምረቱ ሆኖ በታማኝነት ዘልቆ በመገኘቱ ምስጋና ላቀርበለት እፈቅዳለሁኝ። ለጤናማው ወጥ የግራ ቀኙ ቅዱስ መንፈስ መኖርን እመኝለታለሁኝ። አደራ መቀበል ቀላል አይደለም ለዛውም የ100 ሚሊዮን ነፍስ። ከሶስት ሺህ ከዛም የሚዘል የታሪክ አደራን ማስቀጠል? አላዛሯን ኢትዮጵያንም ከነ ሙሉ ክብር እና ሞገሷ ለማስቀጠልም እንደ ፖለቲካ ድርጅት በኦህዴድ ተስፋዬ ጽኑ ነው። እኔ ልዑል እግዚአብሄርን ስለማምንበት መታመኔን እምግልጽበት የአምላኬ ተስፋኛ መሆኔን በማጽናት ነው። ሰለሆነም ለሆነው መልካም ነገር ሁሉ ልዑል እግዚአብሄርን አመሰግነዋለሁኝ። ፈጣሪ አምላካችን ንጉሥ እዬሱስ ክርስቶስ እኛን የፈጠረበት ረቂቅ ሚስጢር ሳይገባን እና ለክብሩም ሳንመጥን እንድናመሰግነው ብቻ ነው እኛን የሰጠን። „ምስጋና“ ትልቁ የፍቅር ተፈጥሯዊ መርኽዊ አዋታር እጬጌም ነው። „ምስጋናን“ የማያወቅ ሰው የተፈጠረበትን ዋና ማዕከላዊ ዶግማ ያላስተዋለ ብቻ ነው። እኛን የፈጠረን የፈጣሪ የፍቅር የቀራንዮ ውል ነው። ስለሆነም እኛን የሰጠን ፈጣሪም ሆነ ስለ እኛ የሚያድርግልን መልካም ነገር ሁሉ ለፈጣሪው ለራሱ ፈቅዶ እና ወዶ በንጽህና አስጊጦ መመለስ ይገባል። ያም „ምስጋናን“ ነው። ፈጣሪ „ምስጋናንም“ ባይፈጥርልን ምድር የጥቁር ኩርንችት ዓውድ ትሆን ነበር። ዓይን እያለን የማናስተውል፤ ህሊና እያለን የማናስብ፤ ጆሮ እያለን የማናዳምጥ በሆንም ነበር። ፈጣሪ አማላካችን ልዑል እግዚአብሄርም፤ ከቦታም፣ ከተራራም፤ ከምድርም፤ ከወንዝም፤ ከኮረብታም፤ ከእንሰሳም ከሰው ልጅም ይመርጣል።

እርሰዎን ዘመን ባላሰበበት ወቅት እና ሰዓት ከሁሉም ለዬት አድርጎ ሙሴ ሲሰጠን፤ እረኛ ሲሰጠን ስላደረገልን ቸርነት ሁሉ ልናመሰግነው ይገባል - ቅኖች። እኔ እምጽፈው ለቅኖች እና ወደ ቅን መንፈስ ለመምጣት ለፈቀዱት ብቻ ነው። ቅኖች አጀንዳቸው በጎ ማስብ ስለሆነ። ለፈጣሪ ቅን መንፈስ፤ መልካምነት፤ ጥሩነት፤ ርህርህና፤ ደግነት፤ ምህረት፤ ፍቅር፤ መታመን፤ አድናቆት አክብሮት፤ ይቅር ባይነት፤ ሌሎች ደስ እንዲላቸው መትጋት ንብረቶቹ ናቸው እና። ሰውም የተፈጠረው ለዚህ የመልካምነት መኖር እና ማስኖር ነበር። ለእነዚህ የሰውነት መንፈሳዊ ሃብቶች ቅድመ ሁኔታ ማዘጋጀት ራስን ከሰዋዊ ሰብዕና የማገለል ያህል ነው - ለእኔ ለእህተዎት ለአቤቱታ አቅራቢዋ ለሥርጉተ ሥላሴ። ስለሆነም በሙሉ መንፈስ አምነወታለሁ። እምነቴ የዛሬ አይደለም። በሚሉት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ገልጠው ባልነገሩን ጥልቅ የመልካምነት ተፈጥሮውት ውስጥ ሁነውበት መኖረዎትን አሳምሬ አውቃለሁኝ።

„አንቺም ኢትዮጵያዊ ነሽን፤ አንተም፤ እኛም ሁላችንም ኢትዮጵያ ታስፈልጋታለች“ በጽሞና ነበር የተከታተልኩት። ይህ የዛሬ አይደለም „ኢትዮጵያ ያላት ሃብትም የህዝቧ ህሊና“ ስለመሆኑ አበክረው ገልጠዋል። ይህም የዛሬ አገለላጽ አይደለም ሳጠናችሁ ቆይቻለሁኝ ክቡርነተዎትን እና ዶር ምህረት ደበበን ስለራሴ የፍቅራዊነት ፕሮጀክት ስል። ከዛ ብሄራዊ የብሩክ ዕለት ደቂቃ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ንዑድ የህሊና መሬት እንዲኖር በሰፋ በሆደ ሰፊነት መባተለዎት፤ ለውጤታማ ትውልድ መትጋተዎትን፤ መንፈስን ለማረጋጋት ቅንነትን በመመገብ መድከመዎትን፤ ለተግባራዊ ጭብጥ መጣደፈዎትን፤ ይህም ጠ/ ሚር ስለሆኑ የተለጠፈበወት አለመሆኑን መረጃዎች አሉኝ። ስለሆነም በውስጤ የደሜ ድምፄ ሆኖ የቆዬ ነው። ለዚህም ከፍ ያለ ተወዳጅ ምስጋና አቀርባለሁኝ - በትሁት መንፈስ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ ድንግልዬም ትጠብቅልኝ። እንኳንም የእኛ ሆኑልንን በድጋሚ አትሜበታለሁኝ። ድጋሚ የተባለበት የቀደመ ነገር መታመን ስለነበረበት ነው። አንድ ጹሑፍ „ይህን ቀን ማን ጠብቆት ነበር“ የሚል ጹሑፍ ከሰሞኑ አነበብኩኝ። እኔ እና ሳተናውማ ጠብቀነው ነበር። 

„መቋሚያ“ ጀምሮ የነበረው ከ40 ባላይ የወግ ገበታ እና ሥነ - ግጥም ተሰርቶበታል። ቀንበጥ ብሎግም የጀምርኩት ለዚህ መንፈስ ነው። የኔት ጉግስ እኮ ይሄው ነው የነበረው የተባጀውም። ታዲያ ለማውያን ነን ብለን የወጣነው የማንን ጎፈሬ ልናበጥር ነበር። የዛሬ ደጋፊው ሁሉ ቀደም ባለው ጊዜ ሲጽፍ፤ በፕሮግራም ሲያብጠጥል የነበረውን አርኬቡን ያነጋግር። በዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ውስጥ ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁም ነገር አለ፤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ተስፋ ነው፤ ኢትዮጵያዊ ኪንግ ማርቲን ሉተር ነው ተብሎ ተጥፏል። ከዚህም ገፋ ተደርጎ ልባቸውን ክፍት አድርገው መከራን አድምጡ ሲባሉ ለባጁት እሩህሩሃንም ለዕጩ ጠ/ ሚር ሲወዳደሩ እባካችሁ እንደ ቀደመው ውስጣችሁን ለግሱን ተብሎም ለነጮቹ አቤቱታ ተጥፏል። ኦህዴድን፤ የለማ እና የገዱ መንፈስን እመኑልንም ተብሏል። ቃሉ ሳይለወጥ፤ ሳይከለስ። ለኦህዴድም መልካም ዕድልን ራሱን በቻለ ጡሁፍ ተልኮለታል፤ ዕዮባዊነት በእጅጉ ያነሰናልም ተብሏል። ምን ያልተባለ አለ። እንኳን ማህተሙ የሁለት የሦስት ሰዎች ብቻ ሆኖ አለቀረ። „ሰውን ትክክለኛ ወደ አልሆነ አቅጣጫ እዬመራሽው ነው አቁሚ የሚያነብልሽ የለም ተብዬም ነበር፤“ ዘለፋም ነበረበት። አሁን ያ መንፈስ ጉልበታም ደጋፊ ሆኖ ቀን ከሌት ይተጋል። ይህም ትልቅ ጥንካሬ ነው። ተነግሮት የሚዳምጥ ህሊና ጠፍቶ ነው ይህን ያህል ህዝብ ሲያልቅ የኖረው። ይህ ዕድል ለስኬት እንዳይበቃ ፍርሻ እንዲኖርም ስንት ሞጋች ጉዳዮች ነበሩበት ኦህዴድ በራሳችን በነፃነት ፈላጊው። ተቋርጦ እንዲቀር ተፈልጎ ነበር። ብቻ „እውነት እና ንጋት እያደር“ ይላሉ ጎንደሬዎቹ። እንዲህ ዕውነትን እያመኑ መምጣት በራሱ የሥልጣኔ ምልክት ነው። አሁን ወደ ቀደመው።

ክቡር ዶር አብይ አህመድ ሆይ! በዘመነ አብይ …

ውጪ በርቀት በሰው አገር የምኖር በቅርብም ያሉ ሚሊዮኖች ድህነታቸውን ታቅፈው እንኳን ሰላማቸው ተጠብቆላቸው የመንፈስ፤ የህሊና፤ የአካል፤ የሥነ - ልቦና መፈናቀል እንዳይኖርባቸው በአጽህኖት ላሳስብ እሻለሁኝ። ይህም በ60 ቀናት ከተጠበቀው በላይ ተከውኗል። ያልታወቀው የ27 ዓመቱ የወል ህመም በሥነ - ልቦና ላይ የደረሰው ጥቃት ነበር። ረቅቅም ነው። በሥነ - ልቦና ላይ የተፈጸመው በደል። ክብሩነተዎት አንደሚረዱት በሥነ - ልቦና ህክምና ያሉን ሙያተኞች ከአፍሪካ ብንሻልም ደግሞ አጅግ ቁጥራቸው አናሳ ነው። 100 ሚሊዮን ህዝብ የውስጥ መንፈስ መስከን ከሌለው ይህ አይቀሬ ነው ህመሙ መከሰቱ የግድ ነው። ስጋት እና ፍርሃት የበሽታው አምራቾች ናቸው። ችግራችን ስፋቱ ጥልቅ ነው። በዚህ የመንፈስ መፈናቀል ውስጥ ማግስት አለ፤ ለማግስት ልዩ አትኩሮት አለወት እና በዚህ ዙሪያ ያልታከተ ተግባር እና ሃላፊነት ለመወጣት ወጥ የሆነ የክልሎች የማድረግ አቅም የለም። ሁሉም ክልል የኦህዴድን ያህል አቅም አምጥተው የተመጣጠነ ተግባራዊ አግልግሎት ይሰጡ ዘንድ ዝቅ ባለ መንፈስ ላሳስብ እወዳለሁኝ። እጅግ ተዛነፍ ጭራሽም ያልተነካ ሁኔታ አያለሁኝ፤ በተለይም በአማራ ክልላዊ አስተዳደር። ይህን ለማስተካከል ታንቀው የታያዙ አምክንዮች አሉ። አማራ መሬት ላይ የሳጅን በረከት ስምዖን ቡድን ከበጎ እሳቤ ጋር የተጣላው መንፈስ ተወግዶ የአማራ የፖለቲካ ሊሂቃን ከታች ጀምሮ የተሟላ የአቅም ሽግሽግ እና ጥራት ያለው ተግባር ሲከውኑ ብቻ ነው ተስፋው መሬት የሚይዘው። በዚህ ዘርፍ ክፍት በሆነ ቁጥር አሁንም የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ድንኳን ውስጥ መሆናቸው አይቀሬ ነው። ድሉም የተዘነጠለ ግንጥል ጌጥ ይሆናል።

የቀደመውን ለመተው አሁንም በቀል እና በደል መቆም ካልቻለ፤ ቁስሉ እያገረሽ የሰበሰቡት እዬተበተነ እዬተናደ ይሄዳል። እግረዎትን እዬተከተሉ የሚከወኑ የክፉዎች እኩይም ይሄው ነው ዓላማው። ፍቅር፤ ምህረት፤ ይቅርታ ሊኖር የሚችለው በደሉ መቆም ሲችል ብቻ ነው። የበደለው ደግሞ በደሉን ሲያቆም እና ይቅርታ ሲጠይቅ ብቻ ነው። አቮው „ፆም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት“ የሚሉትም ለዚህ ነው። በዳዮች አሁንም ከመበደላቸው አልታቀቡም። እንዲያውም ልዩ መሰናዶ እያደረጉም ነው። በዚህች ቅጽበት አሁንም በዓይነት በሰው እጅ የተሠራ መከራ ምድሪቱን እያስጨነቃት ነው። ምድሪቱም አሁን ሃላፊነት የሚሰማው ልጅ ስላላት አቤት እያለች ነው። እኔም አንዷ ነኝ። አቤቱታዬን ከዚህ በሚከተለው መልክ አቅርባለሁኝ። ከዚህ አቤቱታዬ በኋዋላም አንዲህ በቅርብ ጊዜ የማመለክተው አይኖረኝም። እስከ መጪው የምርጫ ዘመን ድረስ በአቤቱታ አልመለሰም በህይወት ከኖርኩኝ።

ክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

በተጨማሪም በግልጽነት የሆዴን አውጥቼ፤ እራሴን በቅድመ ምርመራ ሳላስቸግር በግልጥን በቀጥተኝነት ስለማቀርበለዎት እንደ አገር መሪነተዎት፤ አንደ ኖሩበት ጸጋዎት በሆደ ሰፊነት ያሰተናግዱታል ብዬ አስባለሁኝ። ለስሜቴ፣ ለቁስለቴ መጋረጃ አይስፈልገውም። ይህ የኖርኩበት ዕምነቴ ነው። ሳልፍም በእቅፌ እንዳለ ዓለምን በወልዮሽ እንሰናበታታለን። 

በዚህ ብርሃናማ ዘመን አላዛሯ ኢትዮጵያ መንግሥት አላት ብዬ በጽናት አምናለሁኝ። ቀደም ባለው ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት የቀደሙት ጸሐፊ እስኪ ለአገርሽ መንግሥት አማክሪ ሲሉኝ ኢትዮጵያ ሃላፊነት የሚሰማው እና ሚዛኑን የጠበቀ መሪ አላት ብዬ አምን ስላልነበረ፤ አንድ ቅን ሰው እንኳን ማግኘት የጾም ውሃ ስለነበረ፤ መልሱን መንግሥት የለኝም ብዬ በዝምታ አልፈው ነበር። ከእንግዲህ ነጮችን ማስቸገርን አልፈቅደውም። ደግሞም ቃል ገብቻለሁኝ እሳቸው ከተመረጡ አላስቸግርም ብዬ። ይህን ብተላለፍ ፈጣሪዬም ይቀጣኛል። የጠበቅኩትን ሰጥቶኛል እና። አብዛኛው ጉዳይ እዮባዊነትን የሚጠይቅ ስለሆነ ቱማታ፤ ሱሪ ባንገት መልስ ይሰጠው ብዬ አላስቸግረዎትም። ጊዜውም ገና ልጅ ነው። በ60 ቀን አንድ አዲስ የተወለደ ልጅ አራስ እርጥብ ነው የሚባለው። በዛ ላይ እሳት ላይ በግራ በቀኝ ተጥደው እንዳሉ በሚገባ አውቃለሁኝ። ነገር ግን ግንባር ለግንባር ተገናኝተን በህዝባዊ ስብሰባ ስለማልገልጽለዎት የሚሰሙኝን አቀርባለሁኝ - በትህትና። ነጥቦቹን ይዘው የሚሆኑትን እንሚሆን እንዲያደርጓቸው፤ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸውንም አሻሽለው፤ አሳድገው አንዲያበልጽጓቸው፤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የማይበጁ ከሆነም እኔም አልከፋበዎትም ከተገባው ቦታ ቢያስቀምጡቱ ሁሉም መንገድ ለእኔ ይመቸኛል። እኔ ለይሁናልም // ለአይሆንም፤ ለእሺም // ለአይም እኩል ቦታ እና ክብር ነው የምሰጣቸው። ሁለቱንም ውሳኔዎትን በተመጣጠነ ሙቀት እና ደረጃ ተስፋን ሰንቄ የምጠብቃቸው ይሆናል። እርግጥ ነው አስከ ሞጋች ማብራሪያዎች ስለሰራሁት ረጅም ትዕግስት፤ ደልደል ያለ የመድመጥ አቅምን ይጠይቃል። ለዚህ ደግሞ ብቁ ነዎት ከምል ጸጋዎት ነው ማለት ይሻለኛል። የብዙ ተናፋቂ መክሊት ባለቤት ነዎት። አንድ ልናገር፣ --- ችሎታን ለሌላው የማውረስ፤ የማስተላለፍ ፈቃድዎት ማብቃትን የማብቀል፤ የማድረግም ጥበበዎት የተመሰጥኩበት ነው። ህሊናዎት አምጦ የሚወልደውን አዲስ ራዕይ ለሌላው ለማጋራት አይቆጥቡም። በፍጹም ሁኔታ የሃሳብ አፍላቂነት ለጋስም ነዎት። ይህ እንግዲህ ለእኔ እንደ ታምር የማዬው ነው። ተመክሮዬ ብዙ ስላስተማረኝ። 

ክቡር ዶር አብይ አህመድ ሆይ! ይሄውና አቤቱታዬ በርከት ይላል … ትዕግስተዎትን እባክዎን ይሸልሙልኝ? 
  • ·         ቤቱታ አንድ።

በ2009/ 2010 የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግስት እንደ ዜጋ በማይቆጠረን፤ „አሸባሪ“ ብሎ በፈረጀን ውጭ በምንኖር ኢትዮጵያውያን ላይ „ብርቱ ሚስጢር“ በሚል ያስተላለፈው ሰነድ ነበር። በእጄም ይገኛል። ያ ሰነድ በታቀደ ዘመቻ በህሊና ሽብር የሚፈጥር ስርኩላር ነበር። መጀመሪያ ነገር ዜጋ ካልሆን የመንፈስ እስር ቤት ስለምን ማደራጀት እንደ አቀደ አመክንዮው ፍቀት ያደራበት መሆኑን ያሳያል። እኛ እንደ ዜጋ ካልተቆጠርን ስለምን ይፈራናል? ውጪ እንደሚኖሩት እንደ ኬንያውያን፤ እንደ ኡጋንዳውያን፤ እንደ ናይጀሪያውያን ማዬት ነበረበት። እንደ ሌለን የተቆጠርን ዜጎች ነን እኮ።

የሆነ ሆኖ ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ከዛ ሰርኩላር በኋዋላ በይፋ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል የምንል ለሁለገብ ፍትሃዊ አዲስ የእኩልነት ሥርዓት ተጋድሏችን ቀጠለን። በግልም በጋራም። ኢትዮጵውያን የቻሉት ፓርቲ አደራጅተው፤ ወይንም ከፖለቲካ ምልከታ የተለዬ ሰዋዊነትን ማዕከሉ ያደረገ ማህበረሰባዊ ማህበር በመፍጠር፤ ፓርቲ አያስፈልገንም በግል እንታገላለን ያልን በግል፤ በሚዲያም በህዝባዊ ስብሰባም፤ በተቃውሞ ሰልፎችም በራሳችን ወጪ ስንተጋ ኖርን። ይህ ሰብዕዊነት፤ ሀገር ወዳድነት እንጂ የሚያስኮንንም የሚያስወቅስም፤ የሚስከስስም አልነበረም። እንዲያውም ኢትዮጵያውያን ከሌሎች አፍሪካዊ አገሮች ህዝቦች በተለዬ ሁኔታ በአገር ፍቅር መንገብገባችን የሚያስከብር እንጂ ዜግነታችን ሆነ መኖራችን የሚያስቀማ አልነበረም። ይህን ለመግታት በህጋዊ ቪዛ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በገፍ ካድሬዎችን በተለይ አውሮፓ ላይ አስገባ። አገር ቤት ባለመኖራችን ተጋድሏችን በካቴና በማሰር እና በቶርች በቀሉን ማወራረድ ያልቻለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ እኛን በመንፈስ ለማስር፤ በሥነ - ልቦና ለማሸበር እና ለመቅጣት ሰፊ ዘመቻ ከፈተብን። 

ካድሬዎቹ በህጋዊ ቪዛ ከእነ ሙሉ ቤተሰባቸው ጋር ይመጣሉ፤ በሌላ መልክ የሚመጡትም ቢሆኑ ውጭ የሚገኘው ህዋሱ ወዲያው ሃዲድ ፈጥሮ ድርጅታዊ የማሳደድ ዘማቻቸውን በነፍስ ወከፍ ኑሮ ላይ ይጀምራሉ። አንዴት እንደሚገናኙ ሁሉ ግራ እስኪገባ ድረስ። ሳውዲ የሀገሪቱ መንግሥት ወገኖቻችን ያሳድዳል፤ እዚህ የሲዊዝ መንግሥት ደግሞ አገራችንም ወላጅ እናታችንም የማታደርገውን ያደርግልናል፤ ነገር ግን የወያኔ ሃርነት ትግራይ በአምሳሉ ማንፌስቶው የቀረፃቸው ክፉዎች እነሱም በሰው አገር ተቀምጠው ልክ እንደ እኛ የሲዊዝ መንግሥት የሚያደርገውን ማናቸውም ነገር ሳይጓደልባቸው ግን መንፈሳችን ለማፈናቅል ሰፊ ዘመቻ እና ጥቃት ይፈጽማሉ፤ ኢንባሲዎቹ ዋና ተግባራቸው የዜጋቸውን ነፍስ መጠበቅ እና ማስጠበቅ ሳይሆን እኛን እያደኑ የሚያሳድዱ ቡድኖችን በስውር ማደራጀት፤ መሰለል እና መምራት ነው። … ስለሆነም … ውጪ አገር በምንኖረው ዜጎቸዎት ላይ …
1.1  አገር ቤት ላይ እስራት እና የሞት ፍርድ በፍርድ ቤት በማስወሰን በቤተሰብ ላይ ሽብር በመንዛት፤ ይህ አሁን ተመልሷል።
1.2 በምንኖርበት አካባቢ ከኮንፒተር ጋር የተያያዙ ተግባራትን ሃክ በማድርግ፤ የግል ኑሯችን በማወክ እና በስደት ውስጥ የምንሰራባቸውን ቦታዎች በማጥናት ከሥራ እንድንፈናቀል በማድረግ እና በማስደረግ፤
1.3 የቤት ሰልክ በተለያዩ ቁጥሮች በተከታታይ በመደወል እና ሁከት በመፍጠር። የእጅ ከሆነ አሰፈሪ መልዕክቶችን በመላክ፤
1.4 በመኖሪያ ቤታችን ባለው የፖስታ ሳጥናችን፤ ያለቁ የሲጋራ ቀርጥራጮችን ስብስብ በፖስታ በማሸግ፤ ያለቀ ካልሲ በስጦታ ዕቃ በመጠቅለል፤ የጠርሙስ ስብርባሪ በባኮ አሽጎ አድራሻ አልባ በማስቀመጠ ወዘተ …
1.5 በሰፈር በአካበቢ ያሉ የሌሎች አፓርትመንት ሰዎችን በመቅረብ ባልተለመዱ ሰዓት ማዕከላዊ ሌሊት ላይ ሊሆን ይችላል የቤታችን ደወል በማስደወል።
1.6 የህዝብ አገልግሎት የምንሥራ ከሆነ ከቦታው በግልና በጋራ በመሆን በማወክ፤ የሥራ ሰዓትን በማጥናት ከሥራ በፊት እና በኋዋላ ውጪ በመጠበቅ እና ስጋት እንዲያድርብን በተደራጀ ቡድን መግቢያ መውጫ በማሳጣት፤ ከሥራ እንድንፈናቀል በማስደረግም።
1.7 ሚዲያ ራዲዮ ከሆነም የቴክኒክ ክፍሉ ጋር በመወዳጀት በሚገርም ሁኔታ ከተልዕኮ ውጪ ፕሮግራሙን በማድረግ።
ከቁጥር 1.2 እስከ 1.7 ድርስ በእኔ በራሴ ከደረሰው በጥቂቱ ነው። ዋናው ተልዕኮው ሰው ፈርተን ተገለን እንድኖር ማድረግ ሲሆን፤ የህሊና ሽብር ፈጥሮ ጥንካሬያችን በመፈታተን የተለያዩ የመንፈስ ዝቅጠቶች እንዲደርሱብን የታሰበ ነበር። በተጨማሪም አገር ሰላም ነው ብለን የምናገኛቸውን የምንተዋወቃቸውን የሀገር ልጆችንም በማጥመድ እና ተደራቢ ዳረንጎታዊ ግዳጅ በመስጠት በውስጥ አዋቂ መስመር ጉዳት በማስደረስ። በዚህም በሰው ላይ ዕምነት እንዲጠፋ በማድረግ እና ያቅርብነው ወገን በቆይታው ስውር ጥቃትን በመፈጸም እና በማስፈጸም ሰፊ የሆነ ረቂቅ በደል ይፈጸማል።

እኔ በሰላም ሰርቼ የማወቀው የምሥራበት ቦታ እስኪታወቅ ድረስ ብቻ ነው። ወደ ሥራ እዬሄድኩኝ የማውቀው ሰው አግኝቼ „የት እዬሄድሽ ነው?“ ብሎ ቢጠይቀኝ እንኳን አልናገረም። ት/ቤትም፤ ማሰልጠኛም በር ላይ ከሆነ ተመሳሳዩ አጣብቂኝ አይቀሬ ነው። አንድ ቀን አድራሻው ከታወቀ መቀጠል አልችልም። ይህን ደግሞ ቀንም፣ ሰዓትም ስቀይር ትክክለኛ መግቢያና መውጫ ሰዓቴን እስኪውቁ ድረስ በጣት ለሚቆጠሩ ሳምንታት ሰላም ይኖረኛል። ጫናው መተንፈሻ ሲያሳጣኝ ሲበዛ በተለይ የሥራ ከሆነ የዓመት እረፍት በመውሰድ እረፍት ሳገኝ፤ ተመልሼ ስራ ስጀምር የተወሰነ ጊዜ የለችም ብለው ሲያስቡ አይመጡም፤ በዚህን ጊዜ ሰላም ይኖረኛል። ከዛ በኋዋላ ግን መግባቴን ካረጋገጡ በሌላ አዲስ ሰው ክፉ ተግባራቸው ይቀጥላል። ቀደም ባለው እስከ ሦስት የሚደርሱ ነበሩ እዬተለዋወጡ በግልጽ። በኔትም ቁጥራቸውን መገምት የማልችለው። አሁን ግን በግልጹ የጥቃት ዘመቻ ብዙ ናቸው። የሰላዮች ማህበር እንዲህ በተደራጀ ሁኔታ በግፍ ሲንቀሳቀስ ሳዬ በህይወቴ የመጀመሪያ ነው። እንዲህ ዓይነት ተልዕኮ አዩኝ // አላዩኝ ተብሎ እንጂ እንዲህ በአደባባይ የሚገርም ነው። ሥልጠናቸው በደመነፍስ በጦፈ ዘረኝነት ስሜት ብቻ የሚከወን በመሆኑ ደማቸው ሲንተከተክ ማዬት የተለመደ ነው። 

እንዴት እንደሚከታተሉኝ አንዲት ምሳሌ ላንሳ … እኔ ወደ ሥራዬ ስገባ ሲያይ ውጪ የሚጠበቅኝ ሰው ስልክ ይደውላል። ወደ ውስጥ ስገባ አብረውኝ ለሚሰሩት እናገራለሁ፤ አሁን በርከት ብለው ይመጣሉ በማለት። እኔ ስገባ ግን አንድ ሰው ብቻ ነው የነበረው ብዬ ሪፖርት አደርጋለሁኝ። ወጥተው አብረው የሚሰሩት ያያሉ፤ ያረጋግጣሉ። ወዲያውኑ ተደራጅተው ይመጣሉ። ምንም ማድረግ አይችሉም ግን ተጽዕኖ ፈጥሮ ሰላምን ማወክ ብቻ ነው። 6 ከሆኑ ሌላ ነገር አያዩም የስድስቱ ዓይን ከእኔ ላይ አይነቀለም። አፍጦ ማዬት። በዓይን ጦር መዋጋት። የሄው ነው አንዱ የተጽዕኖው ዓይነት ዘመቻው። ጸረ ሰው፤ ጸረ ተፈጥሮ፤ ጸረ ሴትም።

እያንዳንዱ እኔ ካለሁበት ከተማ የሚኖር የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰላይ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ትውውቅ የሚያደርገው ከእኔ ገፅ ጋር ነው። ጥያቄው ተስርቶ በፎርም ስለሚሰጣቸው አንድ ዓይነት ነው። አዲስ ገቡ ሙሉውን ሰዓት የሚፈጀው እኔን ኢንተርቪው በማድረግ ነው። በቡድን ነው የሚሠሩት። ድርጅቱ ለእኔ ጥበቃ ማድረጉን ከደረሱበት ወሳኙን ሰው በለመዱት መንገድ ይይዙታል። ከዛ ያለው አማራጭ መልቀቅ ብቻ ይሆናል። ያ በጥንቃቄ፤ ጥበቃ በማድረግ በአክብሮት ሲመራኝ የነበረው አለቃ ለውጡ የቅጽበት ነው የሚሆነው። ያ ቅጽበታዊ ለውጥ እኔ አደጋ ላይ እንዳለሁ አመልካች ነው። ስለሆነም አገር መግባቱ ቀርቶብን እዚህ ያለው የስለላ መረብ ሙሉ ለሙሉ ይቋረጥ ዘንድ መመሪያ እንዲሰጠልን ስል በታላቅ ትህትና፤ ሃዘን ባበለዘው ታምቆ በኖረ የውስጥ ስቃይ ዘመን ሥም እጠይቀወታለሁኝ። ይህ የፖሊሲ ውሳኔ የሚጠይቅም ነው። ሰው ተሰዶም እንዴት ሰላሙ ይታወካል? የተሰደድንበት አገር ያላደረገውን?  የሌሎች አገር ስደተኞች በሰላም እና በፍስሃ ተቀምጠው ስለምን ለእኛ ድርብርብ ስደት ይታወጅብናል? እንዴት ያለ ጉድ ነው? የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት መፍረስ አይደለም ከመፈርስም በላይ ሌላ ነገር ቢኖር ያሰኛል። የት እንድረስላቸው? ሜሪኩሪ ላይ እንመንጠቅን? ለሰሚውም ለፍርድም ግራ ነው።

ክቡር ሆይ!

ሰው ግን ከደም እና ከሥጋ ወይንስ በተጨማሪነት ከትንሽ የብረት ቁርጥራጭ ነውን የተሰራው? ዕውነት ለመናገር „ኢትዮጵያዊ“ የሚለው ሥም ለመተርጎም አቅም እስከ አጣ ድረስ በግራ በቀኙ ተሰቃይቻለሁኝ። ክቡርነተዎት ማድመጥን ስለሚፈቅዱት የሚያዳምጥ ህሊና እና የሚያስተውል አዕምሮም ስላለዎት ይህን ወደ ተጨባጭ መፍትሄ ይለውጡታል ብዬ በጽኑ አስባለሁኝ፤ አምናለሁኝም። አገር ለቅቄ፤ ሥራ በዬጊዜው እዬለቀቅኩኝ እስከ መቼ? ማታ ትምህርት መማር አቋርጬያለሁኝ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰላዮቻቸው እያንዳዷን ቅንጣት እንቅስቃሴን ማወክ ነው ተግባራቸው። ከቶ እነኝህን ያ ቅዱስ የኢትዮጵያ መሬት ነውን ያበቀላቸው? ወይንስ የእሬት እሾህ? ይቻላል እነሱኑ መክስስ መረጃው ስላለ፤ ምስክርም ስላለ። ፎቶም በተወሰነ ደረጃ በስተመጨረሻ ስላለ። ግን ኢትዮጵውያዊ አንድ ሰው ብቻ አይደለም የሚታሰረው። ወገኑንም ይዞ ነው የሚታሰረው። አንዲት እናት ስደት ላይ ያለ ልጅሽ ታሰረ ስትባል ምን ይሰማታል? በድንጋጤ አንድ ነገር ብትሆንስ? የእኔ እናት ብትሆን ምን ይሰማታል? እንዲሁም ኢትዮጵዊው ሰው ከተሰደደ ወገኖቹን ይረዳል። ስለዚህ እኔን በሚሰልሉኝ፤ በሚያሳድዱኝ ግለሰቦች ሥር የሚተዳደሩ ነፍሰጡር እህት፤ እናት፤ ህፃናት፤ አዛውንታት፤ ህመምተኞች፤ አካላቸው የጎደሉ ከፍ ሲል በተለይ ለአሁኑ የለውጥ መንፈስ የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ የእነሱን እጅ የሚጠብቁ ናቸው። ስለሆነም ጉሮሮ መዝጋት ይሆንብኛል።

ሁለተኛው ከዚህ ሲመጡ ትግረኛ ስለሚናገሩ ኤርትራዊ ነን ብለው ዜግነታቸውን ቀይረው ነው። ይህ ከታወቀ መላው አውሮፓ የስደተኝነት ጥያቄውን እንደ ገና ሊመረምረው ይገደዳል። የእኔ አቤቱታ ደግሞ ጉልበታም ነው። ይህን ባደረገው ለእኔ ስብዕና ምቹ አይደለም ህሊናዬን ስለምፈራ። እነሱ ወገኖቻችን ባይሉንም፤ እነሱ የሚሰሩትን ጥፋት እኔ እንዴት ልድገመው? ያው ወገን ነው የሚጎዳው። በዚህ ምክንያት ሙሉ 5 ዓመት ችግሩን እኔው ችዬው ኖሪያለሁኝ። ስለሆነም በዘመነ አብይ የማያወላዳ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል። ከዚህ ላይ የሚከብድ ሁኔታም አለ። ኤርትራዊ ዜጋ ነን ብለው እጅ  ስለሚሰጡም የኢትዮጵያ ኢንባሲ ለመካድ ይመቸዋል። እነሱም እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለነም ሊሉ ይችላሉ። ግን ተገፍቶ ከተሄደ ዛሬ ግሎባል ዓለም ብዙ ነገሮችን በመረጃነት ማቅረብ ይቻላል። ከዚህ ሁሉ መከራ ለመውጣት የውጭ ጉዳይ የአንባሳደር ምደባ ላይ፤ የደህንነት ቢሮው ላይ የተጋ የጠራ ተግባር ያስፈልገዋል። ኢንባሲ ላይ የማንፌስቶ ማህበርተኛ ባይሆን እንዴት ማርከሻ ውሳኔ በሆነ ነበር። የበጠበጠው የማህበርተኛ የማልያ አፍቅሮት ነው። በሽታው ይሄው ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚታመሰውም ለዚህ ነው። ሰውር ስቃዩ ይህ ነው ተብሎ ሊገለጽ አይችልም።

ብሄራዊነት የሚሰማው ሰው መሆን አለበት ለአንባሳደርነት ሆነ ለቢሮው መታጨት ያለበት አንድ ሰው። አሁን አውስትራልያ በብዛት ጎንደሬዎች ያሉበት ነው። አቶ አባይ ወልዱ በምን ህሊና እርሰዎ ከሚያስቡት ቅን መንፈስ ጋር ታርቀው ጎንደሬዎች አገር አለኝ፤ የአገሬ ወኪል እዚህ አለ ማለት እንዴት ይቻላቸዋል? አሜሪካም አቶ ካሳ ተክለማርያም አሉ በምን ስሌት በሚያገናኝ ሁኔት ከአማራ ማህበረሰብ ጋር ግጥም ይኖራቸዋል? አንድም ቅንጣት ነፍስ አማራ አገር ቤት ድርጅት አለው ብሎ አያምንም። ብአዴን የማነው? የትግራኝ ትግርኝ ድርጅት ነው። ጠረኑ እራሱ የእኛ አይደለም። የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጤነኛ መንፈስ እዛ መኖሩን ግን አንዘልም። ግን ተጠርቅቆ የተያዘ ነው። ውጪ ነፍስ ግቢ ነፍስ ላይ ነው ያለው አሁን የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቅን መንፈስ። ስለምን? ለኦህዲድ ልቡን ስለ ሸለመ። ወደ አገር ተመለሱ የሚለው ቅን እሳቤ ዙሪያ ገባውን ያለውን መከራ መዳሰስ የሚያስፈልገው ይመስለኛል። ለናሙና ያን የጥንግ ድርብ የምናብ ጸሐፊ የ31 ዓመቱን ወጣት ምስባእከ ወርቁን ማዬቱ፤ የፕ/ ዶር. እምሩ ስዩም ደመ ከልብ ታሪክ አቅርቦ ማጥናት ይጠይቃል። ይህ የነጠረ ጥያቄ ነው። አቶ በረከት ስምዖን ማለት ሰው ስለመሆናቸው ወይንም 666 ስለመሆናቸው ዘመን ይፈታዋል። ስንቶቹን የመከራ ሌሊቶች ስትገላገል አላዛሯ ኢትዮጵያ ሰላሟ እንደሚመለስ አማኑኤል ይወቀው? ይፍረደውም። ቅኝ ግዛትም ነው አማራ በአቶ በረከት ስምዖን ሥር መውደቁ። ነፍስ ያለው አማራ በተለይም ጎንደሬ አገር አለኝ ብሎ ሊገባ አቶ በረከት ስምዖን በህይወት እያሉ? ዕብን መሆን ይኖርበታል። በጣም ከባድ ነው። 
 
  • ·         አቤቱታ ሁለት።

ክቡር ጠ/ ሚር ሞት እና እስራት የተፈረደባቸው ውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ የነፃነት አርበኞች ባለፈው ጊዜ በማከብረው ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ስለ ክቡርነተዎት ያለውን ግልጽ አቋም ስጽፍ አስታውሼዎት ነበር። አሁን ትናንት ጥሩ የምስራች ሰምቻለሁኝ። በሌሉበት የተፈረደባቸው ሁሉ ነፃ እንደሚወጡ። ይህ ግን በጊዜያዊ መንገድ ሳይሆን ለዘለቄታ ቋሚ የህግ መሠረት እና ዕውቅና ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ሰው እና እንጨት ተሰባሪ ስለሆነ። ግፍ እኮ ነው ስደተኛን የራሱ መንግሥት በስደትም ዜጋውን ሲያሳድደው። ሰላሙን ሲያውከው።
 
እኔ እኮ በጀግናው ረ/ አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ምክንያት በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አምላኪዎች በስውር „አሸባሪ“ ተብዬ  በሲዊዝ መንግሥት ወደ አገሬም እንደምመለስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኝ ነበር። ዛቻም ደርሶብኝ ነበር። ግን አልተቻለም። በእኔ ላይም ጫናው ፊት ለፊት እቤቴ ድረስ መጥቶ ሞግቶኛል። እኔ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መንግሥት የሞትም፤ የእስራትም ውሳኔ የለብኝም። በእኔ ላይ የተወሰነብኝ ዕለታዊ እንቅስቃሴዬን ማሸበር ነው። ቤቴን በተለያዬ ቁጥር በስልክ ጩኽት ማወክ ነው። ዕለታዊ ኑሮዬን መበጥበጥ ነው፤ መቅኖ ማሳጣት ነው። ለዛውም እኮ ሰው ከሚገምተው በላይ እጅግ ጥንቁቅ እና ራሴን ጠብቄ ገዳሚዊ ህይወት ነው የምኖረው። በምንም አይነት አንዳች የሰብዕና ጉድለት፤ በብካይ ነገር ከልጅነት እስከ እውቀት ልዕልት ኢትዮጵያን አስጠርቼ አላውቅም፤ በባዛ ቁጥብነት ራሴን ቀጥቼ የምኖር፤ ምንም ነገር የማያጓጓኝ „ይበቃኛልን“ የታጠቅኩ ሴት ነኝ። የትም ስዝረከረከክ አልገኝም። ግን አላስቀምጠኝ አሉ። የት ልድረስላቸው?

ብዙ ወገኖቻችን ስደት ላይ እያሉ ይህን አዲስ ቀን እንደ ናፈቁ ገዳያቸው ሳይታወቅ ሁሉ አጥተናል። የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት ማህጸን ይመስክረው። በስውር ክትትል በስውር መከራ ማሳዬት ይህ እኮ መታሰር ነው። ነፃ ነህ መባል እና ታስረሃል፤ ወይንም ሞት ተፈርዶብሃል ተብሎ መኖር፤ መኖር የተሰረዘበት የመኖር ሳንጃ ነው። ዜጋው እራሱን እዬተጠራጠረ፤ ሌላውንም እዬጠረጠረ፤ ቀኑንም ወሩንም እዬጠረጠረ፤ ወገኑንም እዬተጠራጠረ መኖር? መኖርን ማኖር ያልቻለ የወረዛበት መኖር ለዛውም በስደት፤ ስደት እኮ ያለልክ የተሰፋ ሽብሽቦ ነው። ስደት ሽርሽር አይደለም። ስደት የመኖር እርግማን ነው። ይህም ተቀንቶበት ያሳድዱናል። 

  • ·         አቤቱታ ሦስት።

ክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

አማራ አገሩ የት ነው? ለመሆኑ አማራ አገር አለውን? ለመሆኑ አማራ በኢትጵያ መሬት ባላርስት ነው ወይንስ ከኡጋንዳ የፈለሰ ህዝብ ነው? ግን አማራ ኢትጵያዊ ዜጋ ነውን? ስለምን ይሆን ቄሮ ስለፈጸመው ገድል በአደባባይ ብሄራዊ ግርማ እና ሞገስ ተስጥቶት አማራ ላይ ሲደርስ ውሹ ሳይነሳ የቀረው? ከዚህም በተጨማሪ ግን አማራ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው ክቡር ጠ/ ሚር? እርግጥ ነው እግረዎት ተጠበቆ ነው ቤንሻንጉል ላይ ጥቃቱ ታቅዶ የተከወነ ነው። ንጹህ መንፈስም የለም ከቦታው፤ የአሶሳውን ህዝባዊ ጉባኤ አስተያዬት ሳዳምጥ በቀጥታ አማራ ክልል ላይ የተነጣጠረ ፉክክርም የያዘ ነበር። ነገር ግን ኦቦ ለማ መግርሳ በህይወት እያሉልን ኦሮምያ ውስጥ እንዴት አማራ ሊፈናቀል ይቻላል? እንዴት? ከበደኝ። በተወሰነ ደረጃ ሴራ አለበት ብዬ ባምንም፤ ግን ከኦቦ ለማ መግርሳ፤ ከወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ ከአቶ አዲሱ ረጋሳ እንደ ድርጅት ከኦህዴድ ክልላዊ ምክር ቤት አቅም በላይ ነው ብዬ አላምንም። ምክንያቱም ኦህዴድን እስከ አባ ገዳ +  ፎሌ በሚገባ አጥንቸዋለሁኝ። አቦ ለማ መግርሳ ዘመን ከሚሰጠው በላይ የሰማይ ሽልማት ስለሆኑ። ኦህዴድ እኮ ያለው የብቃት ቁልፍ ማንም የለውም። ለዚህ ነው እኔ ኦህዴድ ብሄራዊ አደራ ለመወጣት ብሄራዊ አቅም አለው ብዬ ስሞግትም የባጀሁት። የጋንቤላው ስብሰባ ላይ ክቡርነታቸው ታች ከህዝብ ጋር ቁጭ ብለው፤ ግን ዕውቅና የሰጡት የሀገር መሪ መድረክ ላይ ሆኖ ማደመጥን በፍቅር ለመመራት የፈቀደ በ100/200/ 300 ዓመትም የማይገኝ የሊሂቃን ሊሂቅ ሙሴ ናቸው አቦ ለማ መግርሳ። እኔ እንደ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ነው የማያቸው ኦቦ ለማ መግርሳን። ሚስጢር አለበት ይህን የምልበት።

ክቡር ጠ/ ሚር ሆይ!

በፖሊሲ ደረጃ አማራ ኢትዮጵያ አገሩ ስለመሆኑ በይፋ ሊወሰንለት ይገባል። ምክንያቱም በፖሊሲ ደረጃ በጠላትን የተፈረደበት ስለሆነ። የአማራ ህፃናት 27 ዓመት ሙሉ ይሄን እዬሰሙ ነው ያደጉት ውጪ አገር ተወልደው ያደጉትም። ጎብጠው። አሁን ነፃነታቸው ሊታወጅላቸው ይገባል። ይህ ለውጥ ይሄ ቀን እንዲመጣ ጥያቄውን አጎልተው በማውጣት ወገኖቻቸው ደም እና ኑሯቸውን የገበረቡት ለውጥ ነውና። ከሌሎቹ ጋር ተዛንቆ አይደለም የነገረ አማራ አምክንዮ ራሱን ችሎ የፖሊሲ ውሳኔ ይጠይቃል። ተነጥሎ ነው በተደራጀ ዓላማ 43 ዓመት ሙሉ የተጠቃው / እዬተጠቃም ነው ያለው። አሁን ያለው ጥቃት እኮ ኦህዴድን ደገፍክ፤ ኢትዮጵያ ሱማሌ ላይ ቁርሾ ሰንቀህ ኦሮሞን አላጠቃህም፤ ያልነህን አልፈጸምክም እኮ ነው። አሁን ያለው የጥቃት ሰለባነት እኮ በወልድያ፤ በትግራይ በተለያዩ የትግራይ ዩንቨርስቲዎች የደረሰው የሞት አዋጅ ምንጩ እኮ አማራ ኦሮሞን ደገፈ በፍቅር ተቀበለ ነው። አማራ መንፈሱን ለኦህዴድ ሸለመ ነው። 

ስለሆነም ለዚህ መንፈስ ጋሻ፤ ጥግ፤ ጠበቃ አሁን መሆን ካልተቻለው ኦህዴድ ለመቼ ሊሆነው ነው? አማራ በዘመነ አብይ መንፈስም መፈናቅል፤ መንገድ አዳሪ መሆን፤ የብትን አፈር ተጠዋሪ መሆን አለበትን? አልገባኝም እንዲገባኝም አልፈቅድለትም። ይህን ምን ልበለው? ማንስ ብዬ ሥም አውጥቼ ልሰይመው? በአብይ ለማ ዘመን የአማራ መፈናቀል? ለሰሚው ግራ ነው። የአማራ ጥቃት አውጪ እኮ ማን ይሁንለት? የሴራው አቦይ አቶ በረከት ስምዖን? እኮ ማን? ይህ ሂደት „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ አቅሙን የሚፈትን አይደለምን? ታሪኩንስ ጥላሽት አይቀባውንም „የኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን? ለመሆኑ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የት ሄደ?  ለእኔ እኮ ታቦቴ ነው እንደ ሎሬቱ መንፈስ። ግልጽ መልስ እፈልጋለሁኝ ከጠ/ ሚር ቢሮም፤ ከኦህዴድ ጽ/ ቤትም። ከኦህዴድ ማዕከላዊ ምክር ቤትም። እኔ ብቻም አይደለሁም እዮርም ይጠይቃል? መዳህኒተ ዓለም ፍጡሩን እይረሳም እና። የአማራ ዕንባ የአቤል ነው። አማራ ፍቅር ብቻ ነው ከዬትኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚጠይቀው።
  • ·         አቤቱታ አራት።

 ክቡር ሆይ!

እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ የትኛውንም ጠንከር ያለውን ብሄርተኝነት አልወደውም። አንዲያውም ከአማራ ተጋድሎ መገለል በኋዋላ ነው ትውልዴ ከወደ አማራ መሆኔን እራሱ ያወቅኩት። ሌላው ቀርቶ ብሄራዊነትን ያህል ሃላፊነት ተሸክመው የኦሮሞ ፕሮቴስ ሲሉ DW and VOA የአማራን ተጋድሎ ግን ክፉኛ አገለሉት እስከ አሁን ድረስ። እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ የአማራ ተጋድሎ ብሎ መጥራቱን አይደፍሩትም። ለምን? ለሚለው ዕውቀቱን እራሳቸው ያውቁታል። የዛን ጊዜ የት ነው ያለሁት እኔ ብዬ እራሴን ሞገትኩት። በቤተሰብ ደረጃ አማራ ነሽ‘“ ተብዬ አላድኩኝም። ተወልጄ ባደኩበት በጎንደር ከተማ ሆነ ከገጠር እስከ ከተማ የገበሬ እና የሠራተኛ አደራጅም፤ የህዝባዊ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበረት የክ/ ሀገር የፓርቲ አደራጅ ሆኜ ህዝቤን አውቀዋለሁኝ። እንኳንስ እኔን ዘርሽ ይሄ ነው ተብዬ ልነገር እዛው የተወለድኩትን ቀርቶ ማንኛውም የሰው ልጅ ከዬት መጣህ፤ ዘርህ ምንድነው? ሃይማኖትህስ? የኑሮ ደረጃህስ? ተብሎ ተጠይቆ አያውቅም። እራሱ ይህ ጥያቄ እዛ ቅዱስ አንባ አልተፈጠረም። 

እኔ ሳድግ የፈጣሪ ፍጡር መሆኔ እዬተነገረኝ፤ መሬትን ስረግጣት እንዳልደበድባት ቀስ ብዬ መራመድ እንዳለብኝ ሰብከተ ወንጌል በቤተሰብ ቤት ውስጥ እዬተሰጠኝ፤ በር ስከፍት እና ስዘጋ ጎረቤት ሰላሙ እዳይታወክ መጠንቀቅ እንዳለብኝ እዬተማርኩ ነው ያደግኩት። ለጎረቤት እንድታዛዝ፤ ሰው ሲያልፍ ቆሜ በአክብሮት እንዳሳልፍ፤ ድምፄ ራሱ ጮኽ እንዳይል ሁሉ ገሪ ነበረው። ስልክ ላይ አኮ ድምፄ አይሰማም። ስብሳባ ላይ ቀስ እያለ ይደምቃል ነው እምለው። ራዲዮ ሞደሬተር ኮርስ ነበረኝ እና ትልቁ ችግር የድምጼ አለመሰማት ነበር። በሂደት ነው እያሻሻልኩት የመጣሁት። ድምፄ ከመጮኽ ጋር የተፋታ ነበር። እንዲህ ነው የጎንደር ማህበረሰብ ልጁን የሚያሳድገው። „አማራ“ የሚለውን ቃል ተወልጄ እስከ አድግ ቃሉን ራሱ ሰምቼው አላውቅም። በፍጹም። ሰው ነህ ነው ጎንደር የሚለው፤ እንደ ሰው ሁን ነው ጎንደር ላይ ብሂሉ። ወላጆቼ አማራ ተብለው ቢያድጉበት ያስተምሩኝ ነበር። የእኛ ዘመንም ሶሻሊዝም ደግሞ „ዓለም የወዛደሮች ትሆናለች“ ነው የነበረው። አሁን ይሄ የትግራይ ሰው ተፈናቀል ጦር አውርድ መሬት ድብደባ ወያኔ ሰራሽ ድራማ ነው። ማን ማንን ያፈናቅላል? ስለምንስ? እህት እና ወንድሞች እኮ አሉን። የሠርጉ ቪዲዮ ቢታይ እኮ ይመልሰዋል። እነሱ ነው የሚያሳድዱን ተሰደን እንኳን።
  
እኔ የቀደሙት ጹሑፎቼ ሁሉ ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል የሚል መርህ ነው ሳራምድ የቆዬሁት። በፍቅራዊነት አንስተኛ ፕሮጀክቴም ዓለምን ስሞግት የኖርኩት የዓለም የአስፈሪነት ምንጩ ፍቅርን በሙያ ደረጃ መማር ስላልችልን ነው፤ ሰውና ተፈጥሮ እዬተሳደዱ ያሉት በማለት ነው የምተጋው። ፍቅር ስል በዓለማዊ ትርጓሜው የሰው ልጆችን ብቻ የተመለከተ አይደለም። ተፈጥሮን በሙሉ ያካትታል። ደን ጭፍጨፋን ይቃዋማል፤ የእንሰሳት መሳደድን ይቃወማል ፕሮጀክቴ። ሁሉም ለተፈጥሮ ፈገግታ ያስፈልጉታል ተፈጥሯዊነትም፤ ሰዋዊነትም።  7ቱም መጸሐፍቶቼ ውስጥ አንዲት ቃል አማራ የምትል የለባትም። ለሰብዕዊ መብት ተማጋቹ ትውልድ ከቶውንም ሊተካቸው ለማይችለው ክቡር / አስራት ወልደዬስ መታሰቢያበኵራት“ በሚል ከሰራሁት የሥነ - ግጥም ውስጠት በስተቀር። መጸሐፍቶቼ እራሳቸው ምስክር ናቸው።

እኔ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ሆነ ሻብያን ዛሬ አይደለም የማውቃቸው። ወያኔ ሃርነት ትግራይን እስከ ገመናው ጫካ እያለ በለጋ ዕድሜ አሳምሬ አውቀዋለሁኝ። የራዲዮ ጣቢያው መደበኛ ተከተታይ ነበርኩኝ። በልጅነት ማንፌሰቶውን አንቀጽ በአንቀጽ ነበር የማውቀው እስከ ማብራሪያው። ስለሆነም የነበረው አቋሜ አማራን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖሊሲውን  አጀንዳ አድርጎ ቢጠቀምበትም ኢትዮጵያ ከእስር ስትለቀቅ ሁሉም የችግር ዓይነት ይፈታል የሚል ሙሉ እምነት ነበረኝ። ይህን ሃላፊነት የሚወስድ ለነፃነት የሚታገል የፖለቲካ ድርጅት አለ ብዬም በጽኑ አምን ነበር። የተጋሁትም በዚህ መንፈስ ነበር። ለዛውም ተገልዬ፤ ተረግጬ፤ አፈር ትቢያ እንደሆን ተወስኖብኝ። አማራ ግፍ በዛብኝ ብሎ ጩኽት ሲያሰማም ጫታ ውስጥ ነበርኩኝ። ነገር ግን እዛ አልበቃ ብሎ ውጪ አገር የወሉ የደም ግብር ተጋድሎው ያን ያክል ሲገለል፤ ባሊህ ባይ ሲያጣ፤ ሚዲያ ሲያጣ፤ ዘጋርድያን ሳይቀር ጎንደር ሚዲያ አልባ መሆኗን ሲዘግብ፤ አጀንዳው ተውጦ እንዲቀር ሲሰላ ዛሬ ስልጣን ሳይያዝ ይህ ከሆነ ነገማ ሌላ ነው በማለት መንፈሴን አሸንፌ ፈተናውን ጥሼ ወጣሁኝ። ከባድ ፈተና ነበር ለእኔ አማራ ነኝ ብዬ ለመውጣት።

ግን የወጣት አደራጅም ስለነበርኩኝ በወጣቶች የሥነ -  ልቦና ጥቃት ድርድር የለም በእኔ ቤት። በሌላ በኩልም ማዕበሉ እራሴንም ሳያሰምጠኝ ለማዳንእኔ አማራ ነኝ ብዬ ወጣሁኝ። በዚህም እጅግ ደስተኛ ነኝ። አማራ መሆኔን እወደዋለሁኝ። አማራ መሆኔን አከብረዋለሁኝ።የአማራ ራዲዮን፤ የአማራ ቴሌቪዥን፤“ የሚለው ራሱ ውስጤ ነው። ለዚህም 20 ሺህ ወገኖቼ ራሳቸውን፤ ኑሯቸውን ገብረው የሰጡኝ ልዩ ሽልማት ስለሆነ እንደ አንድ የመኖሬ ጌጥ ሽልማትም አድርጌ አዬዋለሁኝ። ግን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊነትም፤ ግሎባል የሰውነት ተፈጥሯዊ ዕሳቤዬም በጣም በበዛ ሁኔታ ይጫኑኛል። ይህንም የውስጥ ብርሃኔ ስለሆነም እፈቅደዋለሁኝ። ይህም ቅዱስ ሥጦታዬ ነው። ሙሉ ስብዕና ከሰው ከተፈጥሮ ተነስቶ አምጣ የወለደችኝን የእናቴን ማህጸን፤ የአባቴም አብራክ በጣምራዊ አህታዊ ህብርነት ጣዕሙ መቀበል ነውና። ሰዋዊነትም ነው። አማራነትን መቀበል የሰባዕዊነት መለኪያም ነው። ለእሱም መሟገት የሰብዕዊ መብት ተፋላሚነት ነው።

ክቡር ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ፤

የሆነ ሆኖ ጎንደርም ጎጃም የነበረው ግፍ የወለደው ቁርጠኝነት ሳይ የእርሰዎን ያህል ደንግጫለሁኝ። ያን ያህል የአማራነት ህሊናዊ አቅም መጎልበቱ እና ማደጉን አላውቅም ነበር። አሁን የደንቢ ደሎውን ሦስተኛ መንገድ ሳዳማጥ ደግሞ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁኝ። አሁን እኮ የኦሮሞ ብሄርተኛ መሥራቾቹ ነው አገር የገቡት። የኦፌኮን መሪዎችም የኦሮሞ ብሄርተኛ ነን ነው የሚሉት። እነ ኦቦ ሌንጮ ለታ ስለበደሉት ማህበርሰብ እንኳን እራፊ ዓይን እርግብ አልሰሩለትም። ይቅርታ መጠዬቅን በፍጹም አይደፍሩትም። አብዝቶ ማዳመጥ ስለምወድ ውይይታቸውን፤ ንግግራቸውን አዘውትሬ አዳምጣለሁኝ። በፍጹም ሁኔታ ከአማራ መንፈስ ጋር ሊቀራረብ የሚችል ቅናዊ ሰዋዊ መንፈስ አይቼ አላውቅም። ሰሞኑን ትንሽ የምትሻል ሽራፊ ነገር ሰምቻለሁኝ። ያም የፖለቲካ ስልት እና ስተራቴጂ አድርጌ ነው የምቀበለው እንጂ እንደ ኦህዴድ ዕምነት እምጥልበት አንድም የተፎካካሪ ድርጅት የለም።
ቀድሞ ነገር የአማራ እና የኦሮሞ በባህርዳር መገናኘትን አልወደዱትም የኦሮሞ ሊሂቃን። ያልበሰለ ጥሬ ነው፤ የታሪኩን ፈተና ማለፍ አያስችለውም ኦህዴድ የያዘው አቋም የሚል ነው። 

የደንቢ ደሎውን ስመለከት ደግሞ እነሱ ራሳቸው በግንባር ዲል ያለ ፈተና ይጠብቃቸዋል። ስለዚህ አማራ ከእንግዲህ ተኝተህ በለኝ የሚልበት ዘመን ማክተም አለበት ባይ ነኝ። ኦ ሌንጮ ለታ ሰሞኑን በሰጡት ቃለ ምልልስ  „ እኔ የኦሮሞ ብሄርተኛ ነኝብለው  በግልጽ ተናግረዋል። እግዚአብሄር ይስጣቸው። የኦሮሞ ብሄርተኞችን አንጥፋ፤ ጎዝጉዛ፤ ንጉሥ አድርጋ ሚዲያ አስልፋ ዘንከት ባለው እልፍኟ የተቀበለች አላአዛሯ ኢትዮጵያ ለዛውም አልተፈጠርሽም ያላትን፤ አብዝቶ የተጠዬፋትን፤ ማንነት አልነበረሽም ያላትን፤ ልጆቿ አረብ አገር እና ሊቢያ ሲጨፈጨፉ ጉዳዩ ያልነበረን ድርጅት በእቅፏ የተቀበለች አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለምን የአማራን ተጋድሎ ለዛውም ለብሄርተኝነት ደረጃ ገና ያልደረሰውን ለጋውን አግባቢ መንፈስ በሚዲያዋም፤ በአንደበቷም ትፈራዋለች?
ሁሉም ጫፍ ላይ እያለ አሁንም ጮርቃው አማራዊ ሥነ - ልቦና ጎብጠህ አስተናግድ ከሆነ እውነቱን መናገር ጥሩ ነው አይደል ያሉት አዋሳ ላይ፤ የተገባ አይደለም። 

እያንዳንዱ የአማራ ልጅ መንፈሱን ሰብስቦ የቆመበትን መሬት መመርመር፤ የወደፊቱን አቅጣጫ በጥንቃቄ መራመድ አለበት - በጥሞና። 43 ዓመት ሙሉ የተዶለተበትን ስውር ነቀዛዊ የስታሊናዊ ቀመር ጽዋ አስኪበቃው በኑሮ አሳንጋላ ብቻውን ተጎንጭቷል። ከእንግዲህ ግን ራሱን በቻለ ፖለቲካዊ ዕውቅና ጸንቶ መቆም አለበት - አማራ። የክብሩ የአገር ባለቤትነቱ ተጠማኝ መሆን የለበትም። የቁርሾ መወጣጫ መሆን የለበትም። መሸጋገሪያ ድልዳልም መሆን የለበትም። በብልህነት እና በጥበብ መራመድ አለበት - አማራ። ደም ገብሮ በአገኘው አዲስ የለውጥ መንፈስ በልኩ፤ በአቋሙ፤ በመጠኑ የተገባው የፖለቲካ ዕውቅና ጥርት ባለ መንገድ እና ሁኔታ መዳፉ ላይ ስለመኖሩ ማረጋገጥ አለበት - አማራ። በህዝብ ቁጥር፤ በመልክዕምድራዊ አቀማመጡ ታች እንዲወርድ ነው ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ራያ፤ መተከል የተወሰደው። አባይን ያህል መለያውን የተቀማው። ኢትዮጵያ እኔ ነኝ፤ አንተ ነህ፤ አንቺ ነሽከሆነ ንጥር ያለ ፍትህ ይጠይቃል ያ ግፍ የጠናበት ወገን።

·         ማመጣጠን ለትውልድ ሥነ - ልቦና ሲባል።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ የእነ ኦ ሊንጮን ለታን ትጥቅ ትግል ከሚያራምድ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በጥምረት እሰራለሁኝ ብሎ አቋሙን ወዶ እና ተስማማቶ እስከ የሽግግር ሰነድ (የተሜንት መንግሥት ዓይነት) የመሰረተን መንፈስ በዐጼነት ደረጃ የተቀበለች አላዛሯ ኢትዮጵያ፤ በጎበዝ አለቃነት በቀዬው በዱር በገደሉ ኑሮውን ትቶ ወደ ሰላማዊ ተጋድሎ፤ በእርቅና በሽምግልና ሰሞኑን መግባቱን አርበኛ ደጀኔ ማሩ ከወደ ሳተናው ብራና አንብቤያለሁ። እስኪ የሰው ትልቅ እና ትንሽ የማታበጀውን አልአዛሯ ኢትዮጵያና የቤተ መንግስቷ መንፈስ ለዚህ ቆራጥ ጀግና ወጣት የሚያደረግለትን አቀባበል እናያለን። የአማራ ጀግና በከረባት እና በገበርዲን ሳይሆን በደነቀዝ ጫማ እና በቁምጣ በሁለት ዙር ትጥቅ ነው የሚገባው። ይህ ባህሉ ወጉ እና ልማዱ ትውፊቱ ነው። በዛ ላይ ዝንፍ የማይል፤ ካኖሩት የሚገኝ ተከታይ ሳይሆን ሙሉ ትጥቅ ያለው ቋሚ የመንፈስ ሰራዊት አለው በስተጀርባው። የገቡበትም ቀን ተመሳሳይ ነው። ዕለቱ ታሪካዊ ነው። ባለ ከረባቶች በቦሌ እና ባለ ዝናሩ በወለቃ በር፤

የነፃነት አረበኛም በሲሶ፤ በደረበብ፤ በእርቦ ወይንስ በሙላት ክብር ዜጋዋን አላዛሯ ኢትዮጵያ ትቀበለው ይሆን ብያለሁኝ? ሁለቱም በአንድ ቀን ነው። አንደኛው ባህር ማዶ የኖረ ሌላው በአርማጭሆ በራሃ። የደረጃው መመጣጠን እስቲ ይታያል። እስከ አሁን ብኤዴን ሆነ ማዕከላዊ መንግሥት ለደህሚቱ አቶ ሞላ አስገዶም የሰጠውን የሚዲያ ዕውቅና ያህል አልሰጠውም። ስለምን? ለዛውም በራሱ ዱር እና ጫካ የነበረ ጀግና ነው። አቶ ሞላ አስገዶም ኤርትራ ውስጥ ነው የነበሩት። እንዴት ነው የዜግነት ሲሶ እና እርቦ አለውን? ይህ ሳተና አርበኛ ስለ ህይወቱም አርግጠኝነት ሊኖር የሚችለው ዕውቅናው ጎልቶ ሲወጣ ነው። በስተቀር አርበኛ አበጀ በለውን የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበርን የመንፈስ ጽንስ መስራቹ ዕጣ ፈንታ ቢገጥመው ጉዳዩ የውሻ ሞት ሆኖ ነው የሚቀረው። አርበኛ አበጀ በለው አሟሟቱ በምህረት ከገባ በኋዋላ ነበር የተሰወረው። 

ነፍሳቸውን ይማረው እና በጓድ ገዛህኝ ወርቄ ዘመን፤ ለዛውም እሳቸው ቀና የነበሩ ፍጹም ደግ ሰው ነበሩ፤ እንዴት ይህን ግድፈት እንደ ፈጸሙት አላውቅም። ስለሆነም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጎንደርን እንደ ያዘ ጎንደር ከተማን የጦርነት አውድማ አላደርጋትም ብለው ኮማንድ ፖስቱን /ማዕክላዊ ማዘዣ ጣቢያውን/ ወደ ላይ አርምጭሆ አዛወሩት። ከዛም በዱር በገደሉ ሆኜ ትግሉን እቀጥላለሁ ሲሉ የአርበኛ አበጀ በለው የቁርጥ ቀን ውሳኔ ሰጪ ህዝብ አመጸ እና እስከ ልጃቸው እዛው አለፉ። ያ ቅን ህዝብ እንደ ለመደበት እና እንደ ኖረበት ትውፊቱ የኢትዮጵያን  ሃብት አደራ ለማወጣት አልተቻለውም፤ አንበሳውን ስለተቀማ። ጎንደር ሲወድም ሲጠላም ሥነ - ልቦናው ከባድ ነው። አርማጭሆ እንደ አንድ ቀዬ ብቻ መታዬት የለበትም አገር ነው። ቁጣውም ፍቅሩም የተለዬ ነው። ቁጣው ከገነፈለ የሚተርፍ የለም። አራማጭሆ እጅግ በጥበብና በአክብሮት ሊያዝ የሚገባው አካባቢ ነው። በውስጡ የንግሥና ዘውድ የደፋ ማህበረሰብ ነው። መደፈርን „አሜን!“ ብሎ የማይቀበል። ሥርዓቱም ተፈጥሯዊ ነው

·         ፈሪነት። 

በጣም አስፈሪው ነገር የፈሪነት ሰብዕና ነው። ስለ አማራ ታገድሎ አማራን ወከልኩ የሚሉት አቶ ደመቀ መኮነን አንቦ ተገኝተውቄሮን በይፋ ጀግናዬ ብለው በአደባባይ በአመሰገኑበትአንደበት ጎንደርም፤ ባህርዳርም ምድር ተገኝተው አንዲት ቃል መተንፈስ ስለምን አልቻሉም? ስለምን? ድፍረቱ ስለምን አይመጣም? ስለምንስ ከልዑኩ ተንጥለው ቀሩ? አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እኮ አዋሳ ላይ ተገኝተዋል። ኦቦ ለማ መግርሳ አንቦ፤ ባሌ፤ ደንቢ ደሎ ላይ ተገኝተው ለሚነሱ ጥያቄዎች የተገባውን መልስ ሲሰጡ አዳምጫለሁኝ። አንቦ ላይ የተገኘው ልዑክ ሙሉዑ ነበር። ይገባልም። አንቦን የሚተረጉመው እንደ ጎንደር ዘመን ብቻ ነው።  ልዑኩ በሙሉ ልብ ምስጋናለቄሮበኢትዮጵያ ሥም አቅርቧል። ቄሮ ድርጁ ሆኖ አማራ ግን ባለቤት የሌለው ነገረ ስስ? እኔ ለአማራ ወጣቶች፤ ታዳጊ ወጣቶች ሥነ- ልቦና ጥንቃቄ አጀንዳ ልኩ በምን ይመተር ባይ ነኝ ክቡር ጠ/ ሚር? 27 ዓመት የኖረበት ድቅድቅ የጨለማ ዘመን አልበቃ ብሎ፤  በግራ በቀኝ ተሰቅዞ ለዚህ ላበቃ ተጋድሎ ክብሩ በውነቱ ተደፍሯል። ተረስቷልም

ምስጋና ሲሰጥ በሙሉ መንግሥታዊ አቅም ነበር ለቄሮ አንቦ ላይ፤ እንደ በግ ለተሸለት፤ ሴት ልጅ መርዝ ተውግታ 760 /ሜትር በላይ ተጉዛ አድራ ውላ ጥፍሯ እስኪወልቅ ድረስ ለሳምንታት አትሰማም// አትለማም፤ ቆይቶም መርዙ ምን እንደሚያመጣ አይታወቅም ጠንቁ የዕድሜ ልክ ነው፤ ለዚህ መሰል ከሰው ውጭ ግፍ ለተቀበለ ማህበረሰብ ተጋድሎ ክብር መቼ ትጠብቅ ሥርጉተ ሥላሴ ዶር አብይ ሆይ!? የአማራ 20 ሺህ ወጣትስ በርሃ ላይ እንደ እንሰሳ የተጎተተው፤ ሌሊት በዱላ ብዛት ቀብር የዋለው? 50 የባህርዳር ኖሪዎች በአንድ ልቡን በነፋ አጋዚ በባሩድ የተጨፈጨፉት ሰማዕታትስ? የጎንደር የቅዳሜ ገብያ የዘመናት ምስክር ቃጠሎስ? 26  የአንባ ጊዮርጊስ ህፃናት ጭፍጨፋስ? አሁን እንኳን እስሩ አልቆመም። የፋሲልን ማልያ ለበሳችሁ ተብለው እዬተደበደቡ፤ እዬታሰሩ ነው፤ እኩል መታዬትን መቼ እንጠብቅ? ቢያንስ ተጋድሎውን ይፋዊ እናመሰግናለን ስለምን ይሰሰትበታል? ታሪካችን እኮ ነው። አሞኛል። የኦሮሞ ብሄርተኛ መሪዎችን በክብር አቀባበል እኮ የአማራ ደም ዋጋ ነው። የአረና ፓርቲ እኩል በስብሰባ ታዳሚነትም የአማራ የደም ዋጋ ነው። ለሁሉም የአማራ የዕንባ ዕሴት ነው። ድምጽ እኮ ነው የዚህ ተስፋ ትንሳዔን በሙሉ ድምጽ ፈቃድ የአሸናፊነት አዋጅን ነጋሪቱን የጎሰመው።  
   
የኦሮሞን ብሄርተኝነት አብቅሎ፤ ኮትኩቶ አሳድጎ በጠፋች ኢትዮጵያ ላይ የነበረው ህልም ዛሬ ኢትዮጵያ አገሬ ብሎ ማተቡን ጠብቆ ፍዳን በከፈለ ህዝብ ሰቆቃ በቆዬች አገር፤ ይህም ማለት ኢትዮጵያዊ መንፈስ ከነክብሩ፣ ከነግርማ ሞገሱ መከራ ጠጥቶ ያቆዬው እኮ አማራ ነው። ይህ መቼም አሊ አይባልም። የዚህ ተጠቂ የሆኑ የጥበብ ሰዎች፤ ሙሁራን ሁሉ አሉ። አማራ ሁን ተብሎ አልሆንም ብሎ፤ አማራ አይደለህም ተብሎ ደግሞ ቀዩ ድረስ በረት ገልባጭ ሲመጣ ግን አንበሳው አገሳ ጥቃቱትን በአቅሙ ልክ አሳዬ። ይህ ነጎድጓዳማ የአትንኩኝ የወል ድምጽ እኩል ክብር መሰጠት ካልተቻለ መጪው ጊዜ እጅግ አስፈሪ ነው። እንኳንስ ብሄርተኝነት ሌላም ሊያመጣ ይችላል። የተገለበጠ ዕጣ ዕዳም ይፈትነዋል አዲሱ ተስፋችን። ዝም ጥሩ አይደለም። በዝምታ ውስጥ ያንዣበበ ደመና የተደረመሰ ቀን ይጫናል።

ኦቦ ሌንጮ ለታን እስከ ሙሉ ቡድናቸው በክብር የተቀበለ መንፈስ ሌላውም በአቅሙ ልክ መንፈሱን ኮትኩቶ ቢያሳድግ አስፈሪ ሊሆን ከቶውንመ አይገባም። ስጋቱ ሊሆን የሚገባው ኦህዴድም ይሁን የጠቅላይ / ቢሮ አሁን ከሚደራደራቸው ወገኖቹ ጋር ሊሆን ይገባል እንጂ ከዛ እሸት አማራነት ጋር ሊሆን አይገባም።  ኦህዲድም ሊዋጥ የሚችልበት አጋጣሚ ሁሉ ሊኖርበት ይችላል። ይልቅ አሁን ሌላ ቀይ መስመር አለ።

አማራ እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በፖሊሲ ደረጃ የጥቃት ሰለባ ሆነው 27 ዓመት ሙሉ በመኖራቸው ያለውን ሚዛናዊ የፖለቲካ አቅም ስብጥር ሌላ ቦታ ሳይኬድ የጠ/ ሚሩን ቢሮ፤ የተወካዮች ምክር ቤት እና የፌድሬሽን ምክር ቤቶችን ቁልፍ ቦታዎች በሥነ - አዕምሮ መዳሰሱ በቂ ነው። አማራ እና ኦርቶዶክስ ሲኮረኮሙ በመኖራቸው ምክንያት ቡቃያቸው ጫጭቶ እንዲከስም ወይንም መሬት ሆኖ ስለቀረ ዕንቡጣቸውን ማዬት አልተቻለም። ልክ እኔን ከዚህ በግራ በቀኝ ጫና ከስሜ እንድቀር እንደ ተዶለተው። ቡቃያዎቻችን በዘመቻ ፈልሰዋል። ወጣት ትንታግ ብቁ ብልህ አማራ ሴትን ህሊናዬ ይናፍቃታል። አንዲትስም እንኳን ፌድራል ላይ አትታይም። በጣምራ የማዬው ነገር ለእኔ መልዕክት አለው። ልብ አለኝ። 

ስለሆነም የዚህ ጠባሳ 27 ዓመት የግዞት ዘመን ግብረ ምላሹ መመርመር አለበት - በጥሞና - በተደሞ - በአጽህኖት። ከባድ የሚባለው መናገር አይደለም ዝም ማለት ነው። ዶፉም የዛኑ ያህል ግዙፍ ነው የአባ ዝምታ። በሁሉም ዘርፍ ምን ያህል በዬለም ደረጃ ስለመሆኑ ማዬት ይቻላል። ወጣት ሴት አማራ የፖለቲካ ሊሂቅ አማራ መሬት ላይ በቅላ፣ ጸድቃ መዬት አልተቻለም። በ27 ዓመት ውስጥ አንዲት እንደ ወልዴ ወጣት ንግሥት ይርጋ ደፍራ ወጣች እሷም የመረዝ መመኮሪያ ሆነች… ጥፍሯ ወለቀ። አሁንም የትሜና ወድቃለች። እነ አቶ አብርሃም ደስታ ለተገኙበት የሊሂቃኑ ስብሰባ የአማራ ሳታና የታጋድሎው አውራ ወጣቶች ባይታዋር ናቸው ዛሬም እንደ ትናንቱ። ሰው መሆንን የሚፈትኑ ግፎች በቀላሉ ከሰውነት ተፈጥሮ ጋር ማለመድ ከባድ ነው። ለዛውም እናመሰግናለን፤ ይቅርታ ሳይባል። ለመሆኑ የነገረ አማራ ብቃት፤ ልቅና እሰከ መቼ ነው ተሸፍኖ ተጠቅልሎ፤ ታሽጎ ጓዳ አድማቂ ሆኖ እንዲቀመጥ የሚፈለገው? እስከ መቼ? እስከመቼ  የአማራ መስዋዕትነት ተመስጥሮ የውሽማ ሞት ሆኖ እዬታሸ ይዝለቅ?!!
·         እኔስ እላለሁ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ጥሩ ቀን ስለማልም ተስፈኛም ስለሆንኩኝ።
ነገም በዚህ እንዳይቀጥል በዚህ ዙሪያ ተመጣጣኝ ተከተታይ ተግባር መከወን አለበት። ለዚህም የፖሊሲ ለውጥ ያስፈልጋል። አማራ መሬት ላይ የአማራ የፖለቲካ ድርጅት እንዲቋቋም መፈቀድ ብቻ ሳይሆን አቅም እንዲያበቅል ሙሉ ዕገዛ ሊደረግለት ይገባል፤ በተለዬ ሁኔታ። ቡቃያው ሲነቀል ነው የተኖረው። ከሳጅን በረከት ሴራ እና ከክንፈ የደህንነት እስር ቤት የተረፉት የፕ/ ዶር እምሩ ስዩም ህልፈት እና የሩቅ ጊዜ ትልመኛው ፈላስፋ የምስባከ ወርቁ በዬለም ያለው ነፍስ ዕጣ ያልደረሳቸው የአማራ ሊሂቃን የማንፌስቶ ማህበርተኝነቱን የሚጠዬፉት እስኪ ወደ ተወካዮች ምክር ቤትም፤ ወደ ፌድሬሽን ምክር ቤት በሙያቸው፤ በአማካሪነት ይለፍ ይሰጣቸው።

አማራ ወሳኝ ቦታ ታምኖ ይሰጠው እስኪ። አቅም በሙሉነት ያላቸው አሉ፤ እንደ ረ/ ፕ/ አበባው አያሌው ያሉ ሲደመጡ ውለው ቢያድሩ ከሙሉ ሞራላዊ ብቃት፤ ክህሎት ጋር በፍጽምና መረጋጋት የተሰጣቸው፤ ከሞት የተረፉ ግን የማንፌስቶ ማህበርተኛ ያልሆኑ።  አሁን የአቶ አስመላሽ ወ/ሥላሴ ሥልጣን 12 ቦታ የቀደመው ሲጨመርበት አራት አንድ ሰው 16 ቦታ? ይሄን ለዓለም ሚዲያ እንዲመዝነው፤ የዓለም መንግሥታትም እንዲያውቁት ቢደረግ ምን ሊባል ነው? የአማራ ቴሌቪዥን በ27 ዓመት ባገለለው ማህበረሰብ ላይ የአዲግራቱ፤ የአክሱሙ የመቀሌው የታዳጊ ወጣቶች ለትግራይ ህዝብ የሰጠውን ታማኝነት በልቶ በታዬው ጭፍጫፋ በተመለከተ ለ49ደቂቃ ከ44 ሰከንድ አንድ ቃለ ምልልስ የአማራ ቴሌቪዥን ከሊሂቃኑ ጋር አደረገ ተብሎ ለዛውም ዘር እንኳን አልጠቀሱም ውይይት ላይ እጅግ በጥንቃቄ ነበር ስለ ወደፊቷ ኢትዮጵያ የተጨነቁት፤ ያን የብሮድካስት ስብሰባው በይፋ ነበር ያወገዘው። በውስጥ መስመርም ወቀሳ እንደ ተላከ ያ ጉደኛ ስብሰባ ኩም አድርጎ የትግራዊነትን የበላይነት አፈር በማልበስ አትንኩኝ ባይነትን በተደላደለ የመንፈስ አቅሙን አሳይቶታል። ግፉ በዛ። 

አንድ ሰው 16 የሃላፊነት ቦታ ይህን ያህል አልአዛሯ ኢትዮጵያ የሰው የሊሂቅ፣ የሙሁር፣ የብቁ ሰው ድርቀት አለባትን? ካልሲያቸው ሳይቀር እኮ ነው ሹመት ጀባ የተባለለት። ወይንም ለእያንዳንዱ የሰራ አካላታቸው ክፍለ ተፈጥሮ ሽልማት ታደሎታል፤ ለአንጀታቸው ለታላቁ እና ለታናሹ፤ ለኩላሊታቸው ለግራና ቀኙ፤ ለጉሮሯቸው አስከ ትናጋቸው፤ ለጣፊያቸው እስከ ሃሞት ከረጢቱ፤ ለሳንባቸው ለግራ ቀኙ፤ ለወገብ በላይ እና ለበታቹ ምን ለፊጢጣቸው ሳይቀር። ህም! ዜጋው በባይታዋርነት መኖር እንኳን አልተፈቀደለትም በአላዛሯ ኢትዮጵያ። አማራማ የማይታሰብ ነው። በዬተገኘበት መኮርኮሙ፣ በስውር መገደሉ ከእርሰተ ጉልቱ መነቀሉ ቢቀርለት ምንኛ መኖር አለ በተባለ በዚያች በአላዛሯ ኢትዮጵያ የፍልስጤምን ሃሞት ይጎንጭ አማራው ያልታደለ። 

·         የተከበሩ የአልዛሯ ኢትዮጵያ የተስፋዋ በር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

በአማራ መሬት እሸት ቅመሱን በምን ስሌት ይተርጎም? ብአዴን እንዳለ የሚቆጠር አይደለም። ከአቶ ገዱ መንፈስ ውጪ አሁንም የአማራ ሊሂቅ መንፈሱ እስር ቤት ነው። ብአዴን አማራንም አይወክልም። አማራ መሬት ያለው ድርጅት አማራን በጠላትነት የያዘ የትግራይ ትግርኝ ባለሟሎች የኢህአፓ ዝንጣፊ ማህበር ነው። አሁን ሥራ እዬተሠራ ያለው ኦሮምያ ላይ ሲሆን የለም መሬቱን ዕድል በአግባቡ በስልት እና በዘዴ በዝምታው ውስጥ እዬተጠቀመበት ነው ልባሙ የለማ መንፈስ። አማራ ደግሞ የእንቅልፍ መዳህኒቱን ሸምቶ ለሽ ብሎ ተኝቷል። ሰፊው የአማራ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ህዝብ በደሙ ለነፍሱ ሳይሰሰት አብሶ ጎጃም እና ጎንደር ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ነባቢት መድረሱን ሁሉ የዕውቅናውን ደረጃ የመረመረው አይመስልም ዘመኑ። ለኢትዮጵያ ህዝብ የአማራ ተጋድሎ እንዲህ የውሽም ሞት ሆኖ ሳይሆን በግልጽ ሊነገረው፤ በአደባባይ እንዲያውቀው ሊደረግ ይገባል። ቄሮ እና ሌላውም የሚለው ስንኝ ለአቤል የመከራ ጩኽት አይመጥነውም። ሁለቱ ተጋድሎች ጥርት ባለ ቋንቋ እና አገላለጽ ለህዝብ በህጋዊነት ይፋ መሆን አለባቸው። የተጋድሎውን አዳምጮችም የለማ የአብይ እና የገዱ የአንቤ መንፈስ ስለመሆናቸው በውል ሊዋዋል ይገባዋል። ታሪክ ነው ይሄ። ከአድዋ ጦርነት ያለነሰ ውጊያ እኮ ነው የነበረው። 
 
ስለዚህ ለአማራ ተጋድሎ ለቄሮ ንቅናቄ እንደሚደረግለት ልዩ እንክባበካቤ ሁሉ ሚዛኑን የጠበቀ ጥበቃ፤ ተመጣጥኝ ክትትል፤ ርትሃዊ ፍትህ፤ የእኔ ባይነት ከሙሉ ክብር እና ሞገስ ጋር ሊኖር ግድ ይላል። በስተቀር መጪው ያስፈራል፤ ሞቱን የፈቀደ ህዝብ ነው። 43 ዓመት ሙሉ ሙቷል ለሌሎች ሥም እና ዝና። አሁን እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ህይወቴ ስለመቀጠሉ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም። በማንኛውም ቀን እዚህ እያሳደዱኝ ያሉት ክፉዎች ሊገድሉኝ ይቻላሉ። እኔ አንድ ነኝ። ይበቃኛል ብዬ የወሰንኩኝ ነኝ። ግን መላ የአማራ ህዝብ ነፃነቱ ሊታወጅለት ይገባል። ኢትዮጵያን በሙሉ ልቡ አገሬ ሊላት የሚችለው እሱን የሚመጥን ዕውቅና ሲሰጠው ብቻ ነው። ተጋድሎውና ትርፉ ያመጣው ለውጥ በይፋ የብሄራዊነት የታሪክ ባለድርሻ መሆኑ በስማ በለው ሳይሆን በህግ አግባብ ዝክረ ህላዊነቱ ሲረጋግጥለት ብቻ ነው። አሁን እንደ ዝንጣፊ ወይንም እንደ ቅርንጫፍ እዬታዬ ነው ያለው የአማራ ተጋድሎ ዬህልውና አብዮት፤ መስዋዕትነቱም የተቀበለው መከራ እንዲሁም፤ ከኢጎ ጋር የማይቀራረበው ቅኑ የገዱ ቅዱስ መንፈስ ተጋድሎም በቂ ዕወቅና አልተሰጠውም። ህብረ ብሄር የሚባሉት አገር ቤት ያሉት የአማራ ተጋድሎን አይወክሉትም። አማራ ተጋድሎ መሪ አለው። አማራ ተጋድሎ መከራ የተቀበሉ ሰማዕታት አሉት። ድርድሩ ከእነሱ ጋር ነው መሆን ያለበት።

·         ባሊህ አልቦሽነት …
መሞቱ አማራ፤ መስዋዕትነቱ አማራ እንደ ሌሎቹ ኢትዮጵውያን ሁሉ በቀደመው ጊዜም ደሙን በከፈለላት ቀደምት አገሩ በዬኣካባቢው እዬተፈናቀለ ስላለ ባሊህ ባይ አልባ እዬተንከራተተ ነው - ዛሬም። አማራ ሞሞቱ ካልቀረ ክብሩን ሰላማዊ በሆነ ትግል በሞቱ ማስመለስ ግድ ይለዋል። ተገርፎም ተደብድቦም ቢሆን። አንድ አባት እኮጎጃም ከአባይ እስከ አባነው ያሉት ያለ ምክንያት አይደለም። መተከልን ተቀምቶ፤ አባይን ተቀምቶ፤ ወገራና ስሜን አውራጃን ተቀምቶ፤ አሁንማ አርማጭሆም በግጨው በኩል ደርሷል፤ ራያን ተቀምቶ የት ይሂድ አማራ? ሌላ ቦታም ሂዱልን አሁን እዬተባለ፤  ሊሂቃኑ በግልጽም በስውርም እዬተገደሉ ነው፤ ቡቃያው በጫት፤ ጠላ ቤት፤ ሺሻ ቤት በመክፈት መንፈሱ እንዲላሽቅ በስልት ተደርጓል። ምን ይሁን አማራ? መሬቱን ነፍሱን ተቀምቶ፤ በአጭሩ ተጎርዶ፤ ለዛም ሰላሙ ተቀምቶ የሚሆን አይሆንም። ዝምታው እዮርን ያንካኳል - ቢያንስ። 
 
ኢትዮጵያ ሱማሌ ላይ ያን ያህል ወገን ቢፈናቀልም ኦህዴድን ያህል ጠንካራ በኦሮሞነቱ ውስጥ ዘልቆ የሰከነ ብልህ ድርጅት አለው አማራ ግን ሁሉንም ያጣ መከረኛ ነው። ቢያንስ ጌጣችን ያልነዎት ክቡር /ሚር አብይ አህመድ አለሁልህ ሊሉት ይገባል - ትእዛዝ ግን አይደለም ልክ ለፈጣሪዬ እንደምነግረው አቤቱታ ነው - ትሁት። ታሪከዎትም ነው። ድምጹን ከቦታው ተገኝተው ማድመጠውት፤ አትሂድ እዬተባሉ ከሥፍራው መገኘተዎት ልዩ ስጦታ መሆኑ፤ የለህም ለተባለ ማህብረሰብ የምድር ሳይሆን የእዮር ምርቃት ነው። እዛ አትሂድ ያለው ክፉ መንፈስ ዝለለው ለተባለ ማህበረሰብ የግፉ ቁና ምድር ከቻለችው እዮርም ፍርዱን መስጠት ከተሳነው የሚታይ ይሆናል። ዕንባ በፈጣሪዋ ዘንድ ዋጋ አላት ጠብታዋ። ሌላ ምን አለን አዘውትረን እናለቅሳለን፤ ፈጣሪን አቤት እንላለን፤ በዚህ ሁሉ መከራ ውስጥ ያለ ማህብረሰብ ስለሆነ አማራ፤ በአማራነት ዙሪያ ያለውን የሥነ - ልቦና መነቃቃትም የተስፋ መሪ በር ስለሆነም ክቡር ጠ/ ሚር መንፈሱን ሊደግፉት ይገባል፤ በቅርብም ሊከታተሉት ይገባል - አሁንም በአክብሮት። ዕንቡጥ ነው ቅኔ ገና አማራነት። የተደራጀ ሥራ አልሰራንበትም። በቀጣይ እንሠራበታለን።

ታሪኩ የእሱ ደሙን በገበረበት ውስጥ ቢያንስ የእኩል ተጠቃሚነት ድርሻው ከተሟላ እናመሰግንሃለን ጋር ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል። የአማራ ተጋድሎን በአጀንዳ ደረጃ የጠ/ ሚር ቢሮ ሊወያይበት ይገባልውሳኔም ሊሰጥበት ይገባል። የነበረ እኮ ነው አገሬው ሳይመቸው ሲቀር ጫካውን ጥራኝ ማለቱ። ለዛውም በግል ነፃነቱ ቤቱ ድረስ ጥጋብ፤ ትዕቢት መጥቶ እኮ ነው በባሩድ የተቀቀለው እስከ ህጣናቱ። የቀደሙት አባቶቻችን የአገር መሪዎች „ማረኛ በድዬሃለሁ ብለው ድንጋይ ተሸክመው፤ ከእግሩ ሥር ወድቀው አቨውን ልከው፤ ታቦት አስይዘው ነው ጀግናን አክብረው ሹመው ሸልመው“ ነው የአገርን ሰላምን የሚያስጠብቁት። ጎንደር ይቅርታ አድርግልን ሊባል ይገባል። ማናቸውም የጎንደሬዎች ማሳደድ መቆም አለበት። ሜድሮክስን ማስቆም ተችሎ የለምን?
ተገፍተህም ተጎንብሰህ ሂድ አያስኬድም። ገዳዮችህ በሠረገላ አንተ ትቢያ ላይ፤ አይሆንም። አቶ አባይ ወልዱ አንባሳደር ለዛውም አህጉር እና አገር ለሆነችው አውስትራልያ፤ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ የቁም እስር፤ አያስኬድም። አንዱ ልጅ ሌላው እንጀራ ልጅ፤ አያስኬድም። የዜግነት እርቦ ሲሶ የለውም። ውሳኔው ገርጭራጫ ነው። 

የአመላካከት ለውጥ ያስፈልጋል። አማራ ማለትን ክብሩነተዎትም እንደ ቀደመው ተጋድሎወት ሊሆኑለት ይገባል ‚አሁን እምናገረው በአዲሱ ማንነቴ ነው፤ ነገርዬው ተለውጧል አይደል ያሉት“ የእኔም ጥያቄዬ በአዲሱ ማንነተዎት ውስጥ ስለ አማራ የነበረዎት ተቆርቋሪነት ዕድሉን እንዲጠቀም ይፍቀዱለት ነው። ይህን ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን ቀድመውም ልጄ ብለው በተከፋው ታዳጊ ወጣት መንፈስ ልክ ራስዎትን፤ ጊዜዎትን፤ ከሚማርበት ት/ቤት ድረስ ሄደው ቀልበዎትን ውስጠወትን የሰጡበት መሰረታዊ አምክንዮ ስላለ ብዙም የሚከብድ አይሆንም። በሃላፊነት በነበሩበት ቦታ ሁሉ ለሁሉም እኩል የሚያኮራ ተግባር መፈጸመዎት የታወቀ የተመሰከረ ነው። ስለሆነም የኖሩበት ህይወት ሰለሆነ አይከብደወትም። አማራ መደራጀት አለበት። በመደራጀት የተጎዳውን ሥነ - ልቦና የሚከስ የሥነ - ልቦና ክትትል እና ጥበቃ በመንግሥት ሊያደረግለት ይገባል። አማራ በተሰረዘበት መሬት እና መንፈስ ውስጥ ነው እዬኖረ ያለው። ወደፊትም እንዲኖር የሚፈለገው በዚህ ጠጣር አምክንዮ ውስጥ ነው። ግን ይህ የተከደነ ጠጣር አመክንዮ ሊደፈር ተፈታቶ ሊመረመር በሥነ - ሰው ፍልስፍና ሊፈተሽ ይገባዋል። አማራም ሰው ነው። አማራም የፈጣሪ ፍጡር ነው። አማራም የአላዛሯ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው። አማራም የዓለም ዜጋ ነው - ኢትዮጵያ እኔ ነኝ፤ አንተ ነህ፤ አንቺ ነሽ ይዳኘው!
  • ·         አቤቱታ አምስት።

ክቡር ሆይ! በኢትዮጵያዊነት ላይም ጫና አማራነት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት አለዎት። ሊሂቃኑ መከራቸውን ቻል አድርገው የቤት ሥራቸውን እንዲሰሩ ትህትና ተለግሷቸዋል። 27 ዓመት እኮ እንደ እዳሪ የተጣለውን ኢትዮጵያዊነት መኖሩን ዘሩን በማስነቀል ለግሶ ያቆዬው የአማራ መንፈስ ብቻና ብቻ ነው። የተገደለውም እኮ በዚኸው ነው። ዘሩ የፈለሰው እኮ በዚህ ነው። በውነቱ ይሄ ክቡር ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ስጋተዎት አይሁን። አማራ ልጁን ሲያሳድግ ኢትዮጵያዊ አድርጎ ነው። ይሄን በውስጠዎት ያለውን መንፈስ በትዝታ የቅኔ ማህጥንተ ጽንስ ዘጉባኤ ተወልደ ትንሳኤውን የሚያውቁት ትውፊተዎት ነው። ኢትዮጵያዊነት ለክቡርነተዎት እንደ መጤ ክስተት እንደሆነ የሚጥፉ ሰዎች አንብቤያለሁኝ። መልሱ ተጥፏል ተሰናድቷል። ነጥቡን ያነሱቱን እሞግታቸዋለሁኝ። 

ስለ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን ስለሰው ልጅነት ነው የተፈጠሩት። ጥቁርነት እራሱ ለክብርነተዎት ጌጠዎት ነው። የዓለም ጥቁር ጉልበት አቅም ዓለምን እንደሠራት እምነተዎት መሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ። ስለሆነም በማነሳው ሃሳብ ውስጥ በአጠቃላይ ያለውን ብሄራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ሊሂቃን ዕይታን ያከተተ ነው። አማራ ባልሆንም እምለውን ነው። ኦሮሞ ስለሆንኩ አልነበረም የቀድሞ የተባባሩት ምንግሥታት ጸሐፊን ያን ያህል መንፈስን የሚፈተን መልዕክት በእሬቻ የ600 ወገኖቼ አቧራ የለበሰ እልቂት በኧርጀንት የላኩት። ሊያልፉትም ሊተውቱም የማይችሉት ሞጋች አቤቱታ ነበር። ክቡሩነታቸውም በአደባባይ ወጥተው ሶልዳሪቲውን ተቀላቅለዋል የተከበሩት አቶ Ban Ki-moon። ፍጹም ደግ ሰው ነበሩ።

ስለፍቅራዊነት LoVeIsme ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘትም ለጻፍኩላቸው አቤቱታ መልሱን አድራሻዬን ፖስታው ላይ በእጅ ጹሑፋቸው ነበር በ2015 የላኩልኝ። እሳቸው መላዕክ ናቸው ለእኔ። እኛ ግን የራሳችን ሊሂቃንን እንደዛ በፈለገነው ጊዜ አናገኛቸውም። የምንጽፈውንም አያነቡትም። አያዳምጡነም - ለዛውም ሴት፤ ለዛውም ጎንደሬ ሴት። ለዚህም ነው የታመቀው ትእግስት ሲፈነዳ ገዳቢ የሚያጣው። ለኢትዮጵያ ሊሂቃን አቤቱታ ስጽፍ የመጀመሪያዬ ዶር አብይ አህመድ ነዎት። ስለምን? ውስጥወት ጠረኑ ማዳን ስለሆነ። አንድ የፖለቲካ ሊሂቅ እረኛ ምን አለ ብሎ ማድመጥ ዋና መደበኛ ተግባሩ ሊሆን ይገባል። የኞቹ ግን አልነበሩበትም። ምክንያቱም አስቀድሜ እምናገረው እምጽፈው ነገር ሥራዬ ብለው ስለማያዳምጡት። እንዲያውም ደጋፊዎቻቸው ያሳድዱኛል። እኔ ግን ታሪካቸው ሾልኮ እንዳይቀር ነበር የደከምኩት። እነሱ አቅጣጫው ተሰባሪ የሆነውን የማንፌስቶ ማህርበተኛኝ የራሳቸውን ጣዕም ብቻ ነው ማድመጥም፤ ዕውቅና መስጠትም፤ መንከባከብም የሚሹት። ያ ታሪካቸውን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ የሚመራው ሰው ጄኒራላቸው ነው። አብሮ መውደቅ። ማጣፊያ ሲያጥር ደግሞ ሳቢያ ፈልጎ መቀላቀል። በቃ። 

ልባም መሪ ግን ትቢያ ላይ ያለው ጨርቅ ለባሹ ምን እያለ ነው ብሎ ያዳምጣል፤ ያን ሥራዬ ብሎ መርሁ ያደርገዋል። ተጨማሪ ልብ፤ ተጨማሪ ህሊና በዬቀኑ ስለሚያመርትለት ለመልካም ነገር ያውለዋል። ሁሉ ሰው እኮ መክሊት አለው። ሌላው ባለው መክሊት ፈቅዶ የባለቤት መብትነቱን ሳይጫኑ መጠቀም ብልህነት ነበር።

ከረባት ገበርዲን አይደለም የብልህነት መለኪያው። የቀደመ፤ የበሰለ፤ በተመክሮ የበቀለ፤ በመከራ የጸደቀ ህሊና ነው የፖለቲካ ብስለት መለኪያ። ሊመጣ የሚችለውን አጥንቶ አቅምን ሳያባክኑ በዛ ላይ ብቻ ማዋል ያ ነው ፖለቲካዊ ብልህነት። ከውድቅት መልስ ከሆነ ብዙ መንፈሶች ያመልጣሉ። ፖለቲካ ሊመራው የሚገባ ብልህነት እንጂ ብልጥነት ሊሆን አይገባም። ብልህነት የታሪኩ መሰረት ነው። ብልጠት ደግሞ የገብያ ግርግር ነው። ገብያ ሰዉ ሲበትን ግርማ የለሽ ነው የሚሆነው፤ ይፈታል። ከሁሉ በላይ ታሪክ ያመልጣል። ታሪክ ዕወቅናውን ይነፍጋል። ህዝብም ፊቱን ያዞራል። ህዝብ ያላቀፈው ማንኛውም አንቱ የተባለ ድርጅት ከባህር የወጣ አሳ ነው። ቢያንስ መንፈስ እዬሳሳ ይሄዳል እዬተባለ እዬተነገረ፤ በዛው መቀጠል ብልህነት አይደለም። „ቁሞ የሚጠብቅ stagnate የሆነ አምክንዮ ዓለም አስተናግዳ አታውቅም“ ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ። ማን ያድምጠው። አንድ ሊሂቅ ምን ነበር ጥፋቴ ብሎ ወደ ራስ መመለስ የፖለቲካ ብልሆች ፍልስፍና ነው። ኦቦ ለማ መግርሳ፤ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለዚህ ክብር ያበቃቸው ይሄው ነው። እራስን ለማድመጥ፤ ለማረም መፍጠን፤ በአዲስ እሳቤ ለመገስገስ መቆረጥ። መሆንም። ማድመጥ ወቅትን ከምንም በላይ አትራፊ ነው። የቀድሞው የተባባሩት መንግሥታት ጸሐፊም ከሁሉም ሊሂቃን የሚለያቸውም ይሄው ነው። ዛሬም እኔ እንደ ታቦቴ ነው የማያቸው። የወጣላቸው አድማጭ ናቸው።
 
·         ትዮጵያዊነት እና ኦህዴድ። 
 
አሁን የብሄርተኝነት አባ ወራዎችን እጁን ዘርግቶ የተቀበለው ኦህዴድ እንደ ድርጅት ሊሰራበት የሚገባ መስኩ ሊሆን ይገባል ኢትዮጵያዊነትን። እጁን መሰስ አድርጎ የወጣው ያ ታምራዊ አውራ ማንነት ነው። አንዲትም ቦታ እኮ የጥንት የጥዋቱ ብሄራዊ ልሙጡን ሰንደቅ ዓላማ በኦሮምያ ክልል ከቲ - ሸርት ላይ እንኳን በስህተት ከአንድም ወገን ላይ ፈጽሞ አይታይም። በተፎካካሪዎችም ዘንድም በፍጹም ሁኔታ የተፈራ ነው። አማራ መሬት ላይ ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከገባ ከ10 ዓመት በኋላ የተወለዱ የአማራ ልጆች ያላቸውን ኢትጵያዊነት አቋም የቅኔው ዕንቡጥ የጠቢቡን ቴውድሮስ ካሳሁን የባህርዳር ኮንሰርት ማዬት ብቻውን በቂ ነው። አማራ ቴሌቬዥን አርኬቡ ላይ አለ። አቶ ንጉሡ ጥላሁንም ተከሰሰውት በልኩ እና በአቅሙ „በልክ ሁኑ!“ ብለው ፊት ለፊት መልስ ሰጥተውበታል። እስኪ ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን አዲስ አበባ ላይ እንደ ቅኔው አጫሉ ዕድሉ ይሰጠው። ስለ ኢትዮጵያዊነት ይዘመር በድፍረት። የባይታወርነቱን ዲካ እኮ ከዚህ በላይ የታሪክ ዝክረ ነገር የለም። ይህም እንዲመጣጠን ከተፈለገ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማችን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ነፃነቱ ይታወጅ።

የዴያስፖራውም ፍቅራዊ ብሄራዊ ጥሪ ከዚህ የነጠረ የኢትዮጵያዊነት ጣዝማ ነፃነት መነሳት አለበት። በዚህ የታሰሩ ጎንደር ውስጥ እሰረኞች አሁንም አሉን። በ2010 በዕለ አስተሮዬ በጥምቀት የተቋጠረ ቂም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተወራርዷል። በወልድያ ኳስ ጨዋታ የተቋጠረው ቂም አስተርዮ ላይ፤ መቀሌ ዩንቨርስቲ፤ አዲግራት ዩንቨርስቲ፤ አክሱም ዩንቨርስቲ እንደ ተዋራረደው። ቀን ሳይሰጥ አርበኛችን ሸማችን ሊፈታ ይገባዋል። አማራ መሬት ላይ ኢትዮጵያዊነትን ለማመጣጠን የጠ/ ሚር ቢሮ ከናፈቀው ብሄራዊ ሰንደቁን ከእስር መልቀቅ ወሳኙ ጉዳይ ሲሆን፤ ጥያቄዎቹንም፤ ተጋድሎዎቹንም አክብሮ መነሳት ይገባዋል። እወቅና መስጠት ለተጋድሎው ሚዲያው መድፈር አለበት። የአማራ ቴሌቪዥን ተብዬውም እንዲሁ። እስከ አሁን ዝም ብሎ ሻታ ነው የሚዞረው። ጀግናውን ኮ/ ደመቀ መኮነን እንኳን ሰፊ በሆነ ዝግጅት ሊያስተናግደው አልቻለም። ቴወድሮስን ማከብር ማለት ይሄው ነው። ጀግናው በላይ ዘለቅን፤ ጀግናው ገብርዬን፤ ጀግናው ገልሞን ማክበር ማለት ይሄው ነው። አማራ ቴሌቪዥን ተብሎ አንድም ቀን እንደ OBN የሰራው የለም በጀግኖቻችን በሰማዕቶቻችን ላይ። ስለምን ተንበርካኪ ስለሆነ ለትግራይ ትግርኝ መንፈስ።

ይህንን አቤቱታ ለማጠቃለል አንድ መሰረታዊ አመክንዮ ደግሜ ማስገንዘብ እምሻው ለመሆኑ አቶ ደመቀ መኮነን በማን ሥም ነው ም/ ጠሚር የሆኑት? ምስል ናቸውን? ስለምን ይሆን አንቦ ላይ ተገኝተው „ቄሮ ጀግናዬ“ ያሉትን አማራ መሬት ላይ የአማራ ተጋድሎ አርበኞች ጀግና ለማለትም ሆነ ፍቅር ለመለገስም ከቦታውም ለመገኘት ያልቻሉበት ምክንያት ምንድን ነው? ራሳቸውን ራሳቸው ሰርዘውታል። ዘመን ይፈትሸው።
  • ·         አቤቱታ ስድስት።

አማራ በግንቦት 7 ሥም የሚከሰስብት ሁኔታ የኢህዴግ የፖለቲካ የአስተሳሰብ ድህነት፤ የፖለቲካ አቅም ማነስ ይመስለኛል። ባለፉት ቀናት ኦቦ ሌንጮ ለታ ቃለ ምልልስ ነበራቸው „ማን አላችሁ? ምንስ አላችሁ ሲባሉ?“ „ማን አለን? ምንስ አለን? ያው ህዝባችን ነው ያለን“ ነው ያሉት ዕውነቱ ይሄው ነው። አሁንም ኢትዮጵያ ሲገቡ „ተከታዮቻችን ውጪ አገር ነው የሚኖሩት“ ብለዋል። „ተከታይ“ አባል አይደለም። ለዛውም ምን ያህል? የት ቦታ? አራት ሰው ሺህ ጥያቄ ያነገበ፤ በቃ። ቢሮው ስልክ ነው። የፍላጎት ምክር ቤቱ ደግሞ ኔት ነው።  „በህጋዊ ተመዝገብን ወይንም ካሉት ጋር ተዋህደን ወይንም ተጣምረን የሚሆነው ይሆናል“ ነው የሚሉት። በዚህ የከሰረ ፖለቲካዊ አደረጃጀት ሚሊዮን ልጅ የኢትዮጵያ እናት ትገበር ዛሬም ይሄው ነው ጩኽቱ። ሁለቱም ቁልጭ ያለ ዕውነት ነው የተናገሩት። ምንም እንደሌላቸው። የማያስፈራውን ነበር የምትፈሩት። ኔት ላይ ካለውስ መሬት ላይ ያሉት ሁለት ተጋድሎዎች ነው መፈራት ያለባቸው።

ወያኔ ሃርነት ትግራይ እነዛን ንጹሃን በገፍ እስር ቤት ያሰቃያቸው ምክንያቱ በምንም ነው። በሌለ ነገር ላይ። ሁለቱም ተጋድሎዎች በራሳቸው ባህሪና አመክንዮ የተነሱ አብዮቶች ናቸው። ዬትኛውም ማንፌስቶ ጥገኞች አይደሉም። ስለሆነም ለተጎዳው የኦሮሞ ህዝብ እና ለአማራ ህዝብ ይቅርታ ሊጠዬቅ ይገባል መንግሥት ሆነ የፖለቲካ ድርጀቱ ግንባር ኢህአዴግ። የፖለቲካ ሥም መኖር እና አባል መኖር የተለዬ ነው። ውጪ አለን ያሉት „ተከታይ ነው“  „ተከታይ“ ማለት አባል ማለት አይደለም። ደጋፊም ማለት „አባል“ ማለት አይደለም። ይህ በፖለቲካ ትርጉሙ የገብያ ውሎ ወይንም የመንገድ ላይ ትርኢት ታዳሚ ማለት ነው። በቃ በዚህ ነው የኦሮሞ ልጅ እና  የአማራ ልጅ ሲታረድ የኖረው። አብሶ ስሜን ጎንደር የቀራንዮን ጽዋ በግንቦት 7 ሥም የተቀበለው። ሌላው ቦታ በሰላም እዬኖረ ቡቃያውን አብቅሏ ለክብር ሲያበቃ ጎንደር ግን ከዘር ተነቀለ፤ በሌለበት ለእሱ ባልተፈጠረ አመክንዮ ምክንያት። ዛሬም አላባራም። በዘመነ ኢህአፓ ይሄው ነው የነበረው፤ ያን ጊዜስ ይሁን። በዘመነ ግንቦት 7 ግን ሰማይ እና መሬት ገጥሞ የመስፋት ያህል ነው የክሱ ጭብጥ እና የወረደበት የመከራ በረዶ።  የመላ ጎንደር የክሱ ጭብጥ መሰረታዊ አናት የቂም ማወራረጃ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ ያን የመሰለ ዓለም ዓቀፍ ሥልጡን ሁለ ገብ፤ ሁል አቅፍ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ አስተናግዳ አታውቅም። ይህን መሰል ሰላማዊ ስልፍ የማደራጀትም የመምራትም አቅም ከዬት ይመጣል? እንተዋወቃለን።
 
ጎንደር ላይ በተንጠለጠለ በዛ መከረኛ ህዝብ ደም ሥምን ማንገሥ። እውነት ለመናገር ግንቦት 7 የተፈጠረው የጎንደርን ህዝብ በጠላትነት በጥርሱ ለያዘው ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥጋ ለማቀበል ነው። ለመላው የኢትዮጳያ መሬት ነፃነት ስለምን ጎንደር የበቀል ማወራረጃነት ተመረጠ? ይህን ጎንደሬዎች ሁሉ ወደ ልባቸው ተመልስው ከራሳቸው ጋር ሊመክሩበት ይገባል። ጎጃም ባይኖር እኮ ያን የመከራ ዓመታት አያልፈውም ነበር ጎንደር። መስዋዕትነቱን እኔም እጋራለሁ ብሎ ለጎንደር ሲል ጎጃም ፊት ለፊት ወጥቶ ግንባሩን ሰጥቶ ደሙን ባይገብር ጎንደር አንድም ሰው አይተርፍም ነበር። የጎንደር ሰው እረፍት ጊዜውን ማሳለፍ ያለበት የጎጃምን እያንዳንዱን ቀዬ እዬሄደ በማዬት መሆን አለበት። ውጪ አገር የሚኖረውም ወደ ባዕቱ ሲሄድ ጎጃምን ማቀድ አለበት። ጎጃም ነፍሱን ነው የሰጠን። ጎንደር በተለዬ ሁኔታ ለጎጃም የእናመሰግናለን ዝግጅትም፤ የጸሎት ሥርዓት ሊያደረግለት ይገባል። ጎጃም ጎንደርን ነው መልሶ የሰጠው፤ ጎጃም ጎንደርን ዳግም ወለደው። ጎጃም ቴወድሮስን ነው ከሞት ያስናሳው፤ ፋሲልን፤ በካፋን፤ ሱስንዮስን፤ አድም ሰገድን እያሱን፤ ተዋቡን፤ ጣይቱን፤ ምንተዋብን፤ ግብርዬን፤ ጻድቁ ዮሖንስን፤ ገልሞን፤ አለማዬሁን፤ አባ ፊታውራሪን መለሰ ሃይሉን፤ ውቤን፤ አዳነን ወዘተ ነው ከሞት ያስነሳው። ማተቤ ክርስትና ነው የሚል ጎጃም ማተቤ ነው ማለት አለበት ጎንደሬው። እምነቴ እስልምና ነው የሚልም እምነቴ ጎጃም ነው ማለት አለበት ጎንደሬው። ጎጃም አዲስ ዘመኑ ነው ለጎንደር። ጎጃም የአባይ ግንድ ጥልቅ የምዕት የተግባር ማሳ ነው። ጎጃም ኪዳን ነው የቀራንዮ። ጎጃም ድርሳን ነው ቀን ከሌት በህሊና ሊጸለይለት የሚገባ ቅን ህዝብ። ውስጡ ንጹህ የጠራ። አማራነት ነው ለዚህ ድል ያበቃው። ስለዚህም የጎንደሬ አማራ አማራነቱን የሰጠውን ክብር እና ልዕልና የሰጠውን ያህል በዬትኛውም ዘመን ስሌለ ለአማራነቱ እስከ መጨረሻው መትጋት አለበት ጎንደር። መሞትም ካለ ይሙትለት።

·         ባልነት በፈቃደኝነት።  

የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ፈቃደኝነት ነው። ይህ ዶግማው ነው። ይህን ለማሳከት መልማዩ ከተመልማዩ የተሻለ ሰብዕና የብቃት አቅም ሊኖረው ይገባል። ይህ የለም። አንድ የፖለቲካ ድርጅት መሰረታዊ ሰንዶቹ ምን እና ምን እንደሚባሉ እንኳን ውጪ አገር የሚያውቀው የለም። „ሰንድ“ የሚባል አያውቁትም። አባልነት የተወሰኑት ብቻ እንጂ የገብያው ሰው ሁሉ እንዲሆን ነው የሚፈለገው በዘመን አመጣሹ ፍልስፍና። አባልነት ፈቃደኝነት ነው። ፈቃደኝነት ደግሞ ፊት ለፊት ምልምሉን ተገኝቶ ህሊናውን በተከታታይ ተሰናድቶ፤ ደንቡን አጥንቶ፤ ፕሮግራሙን ፈትሾ መሬት ላይ ተፈትኖ መጀመሪያ እጩ አባል ሆኖ በክትትል ይታያል፤ ብቃቱ ሲረጋገጥ አባል ይሆናል። ያ የራዕይ ጽኑ መሰረት ይሆናል። ደንብ ፕሮግራም በእጁ የሌላ ስለዛ ምንም የማያውቅ አባል ኑሮ አያውቅም። በዚህ ነው የጎንደር ሰው ሲታጨድ መሞከሪያ ሲሆን የባጀው።

በአዋጅ የፓርቲ አባልነት፤ በሞገድ የፖለቲካ ድርጅት ጽ/ ቤት የለም። ወይንም ብዙ ገንዘብ በማዋጣት የፖለቲካ ድርጅት አይፈጠረም። በተለይ ገንዘብን መሰረት ያደረገ ከሆነ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ከፖለቲካ ድርጅትነት ይልቅ የአክስዮን ማህበር ቢባል ይቀላል። ፖለቲካ እኮ ሳይንስ ነው። መሬት የረገጠ በድካም ውስጥ፤ በልፋት ውስጥ፤ በማብቃት ውስጥ የተበ የተግባር ውጤት ነው የፖለቲካ ድርጅት ማለት። የፖለቲካ ድርጅት ሥራ ሌሊት እና ቀን ተስርቶበትም እንኳን ቋት አይገፋም። ቢሮ እዬታደረ እንኳን ከባድ ነው። ውሽልሽል አይደለም ፍልስፍናው። 

ስለሆነም አዲሱ የጠ/ ሚር ቢሮ ይህን ግልጽ የፖለቲካ አቅምን የማገናዘብ የቀደመ ስስነት አስወግዶ „አማራ“ ነኝ አትበል ከሆነ አማራ በዛ ይታሰር / ትታሰር። ይገረፍ / ትገረፍ። ጥፍሩ ይውለቅ / ጥፍሯ ይውለቅ፤ መርዝ ተወግቶ ህሊናውን ይሳት / ትሳት። የዘር መፍጠሪያው ይፍለስ። አፋሩ አፍር ነኝ፤ ኦሮሞው ኦሮሞ ለዛውም ብሄርተኛ ኦሮሞ ነኝ፤ ትግሬው ትግሬ ነኝ ለዛውም ብሄርተኛ ነኝ፤ ከንባታው ከንባታ ነኝ፤ ቤንሻንጉሉ ቤንሻጉል ነኝ ለዛውም ብሄርተኛ ነኝ ሲል አይታሰርም፤ አይነገላታም። አሁን ሊታገሉ የገቡት ኦነግውያን እኮ „የኦሮሞ ብሄርተኛ ነኝ“ እያሉ ነው አገር የገቡት፤ ይሁን ይፈቀድ ምህረት የክትና የዘወትር ስለሌለው። አማራስ? ከቶ ስለአማራ ሌላ ኢትዮጵያ መቼ ትሰራ፤ መቼስ ትፈጠር ስንት ዘመንስ ይጠበቅ? ስለመሆኑ ኢትዮጵያ አማራ ያልተፈጠረባት አገር ናትን? ይህም ይሁን በአማራነቱ በሥሙ፤ ሥሙ ሙሉ ዕውቅና አግኝቶ ታሪኩ ነውና ይታሰርይንገላታ ለዛውም በዘመነ አብይ። በጸጋ ይስተናገዳል። ስለምን እዮር ስላለ። የእስራኤልን ህዝብ ነፃ ያወጣ አምላክ አማራንም በቃህ ይለዋል አንድ ቀን። አማራ በኢትጵያ ምድር ብቻ ሳይሆን ውጪ አገርም ልክ እንደ ፍልስጤም ህዝብ ነው የሚሳደደው። ዛሬ ባህርዳር ላይ ጎዳና ላይ የአማራ እናት ልጆቿን በትና ትገኛለች። የወላጅ ፍቅር ያጡ ልጆቼ ትላለች። ታነባለች፣ ትቆጫለች በመፈጠሯ በመፍጠሯም። ክረምቱ እዬገባ ነው ጎርፉንስ እንዴት ይቻሉት? በወለጋስ በባህርዳርስ ያሉ አማራዎች? አባ ገዳዎች እራሳቸው ለቃችሁ ውጡ እያሉ እዬመከሩ ነው።
  
እኔ ክቡር ጠ/ ሚሩን በንጹህ ህሊና የምጠይቀው አሁንም አማራን ማሰር ከተፈለገ፤ የቀረ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ቂም በቀል አለና ይመቸው እና የቂም ቁርሾውን ያወራርድ በተለመደው መንገድ፤ በአማራነቱ ይተሠረ ይሰቃይ? መታሰሩ ይቅር ብዬ አይደለም ይህን አቤቱታ እማቀርበው ክቡርነተዎት ስንቱን ይቆጣጠሩታል፤ ለዛውም አንድ አይዞህ ባይ በሌለበት ሁኔታ። በዛ ላይ አድባሩ እራሱ የአማራ ዕንባ ካላዬ፤ አዬሩ እራሱ የአማራን እንግልት የስቃይ ተውኔት ካላዬ አይሆንለትም እና …. ግን በሥሙ „አማራ ነህ/ አማራ ነሽ“ ተብሎ ይሁን ነው ሙግቱ። የክስ መዝገቡ በራሱ በአማራነቱ ይሁን። ለታሪክም ይመቻል። ለፈጣሪ ውሳኔም ይደላል። ለጸሎትም ያተጋል። ለስግደትም ያበረታል። ለሱባዔም ስንቅ ይሆናል። አላዛሯም ኢትዮጵያ እዮርን ቁጣ ከቻለችው ትቀጥል። 
·         አቤቱታ ሰባት።
እኔ ከ5 ዓመት ያለነሰ እናቴን ማግኘት አልቻልኩኝም በስልክ፣ በኢሚል፣ በስካይፒ፣ በሜሴንጀር፤ ቤተሰቦቼ በተለያዬ ምክንያት በእኔው የፖለቲካ አቋም አባታቸውን ቀደም ባለው በሰውር ሴራ አጥተዋል የአባቴ ልጆች፤ የእናቴ ልጆች ያላሳለፉት መከራ የለም። ስለሆነም ሰላማቸውን ላለማወክ፤ እዚህም መውጫ መግቢያ ስለነሱኝ ስልክ አልደውልም። ጎድቻቸዋለሁኝ። እኔም ተጎድቻለሁኝ። ስለዚህ በቤተሰቤ ተጽዕኖ፤ ጫና ይደርሰበታል የሚል ማንኛውም ስደት ላይ ያለ ስጋት ከሥሩ መነቀል አለበት። አዲስ ትውልድ እንዲህ ተሳቆ ማደግ የለበትም። እኔን መሰል ኢትዮጵያዊ መከረኞችም እንዳሉ አምናለሁኝ። የታናሽ እህቶቼ ወንድሞቼ ልጆች ስሜን ቢያውቁ እንጂ ድምጼን አያውቁትም። ወላጅ እናቴም ብትሆን ከመንኮሰች መቆዬቷን አሁን ሰምቻለሁኝ ክቡርነተዎ ጎንደር አደባባይ ንግግር እያደረጉ ሳለ ነበር ውጪ የሚኖሩት ቤተሰቦቼ የነገሩኝ። በጣም ነበር የደነግጥኩት። አልቅሻለሁም። ከአማራ የህልውና ተጋድሎው በኋዋላ ጎንደር ከተማ አክስቴን ጨምሮ በርካታ እናቶች እንደ መነኮሱ ነው የሰማሁትም። ይህም ሌላ የዘመን መቀነት ነው። 

እናቴ የመነኮሰችበት አብይ ጉዳይም በውስጥ ሃዘን መበራከት እንደሚሆን አስባለሁኝ። ምክንያቷ እኔው ነኝ። ስለዚህ ቢያንስ ድምጽዋን ብሰማ ደስ ይለኛል። እንደ እኔ ያሉ ምንዱባን ስደተኞችም እንዲሁ ህሊናቸው ነፃ ሊወጣ ይገባዋል። ለዚህም በፖለሲ ደረጃ አንድ ሁነኛ ሥርዓት ቢቀያዬርም ዘላቂ ለሁልጊዜ የሚያገለግል ህጋዊ መሰረት ያለው ውሳኔ ሲወሰን ብቻ ነው። ከቶ ምናችን ነው የሚሰለለው? አሁን ከእኔ ቤት ስፍር ቁጥር የሌለው ማስታወሻ ደብተር እና ስክርቢቶ ብቻ ነው ያለው። የትግራይ ሰዎች ከራሳችን ሊወርዱ ይገባል። እኔ የምጠይቀው በቱማታ እንዲመለሰልኝ አይደለም። ክቡርነተዎት ኢትዮጵያዊ ወገኔን ህዝብ ሰብስበው እንደሚያወያዩት እኔ ዕድሉን ማግኘት ባልችልም በዚህ መልክ ሃሳቤን መግለጥ ግድ ስለሆነ ነው። እኔ ከሥጋዊ ነፃነት ይልቅ የእኔ ተጋድሎ መንፈስ ነፃ መውጣት አለበት የሚል ነው። የተቀሙ የሥነ - ልቦና ማንነቶች ወደ ቀያቸው፤ ወደ ተፈጠሩበት የመንፈስ ነፃነት ወደ ባዕታቸው ይመለሱ ነው ጥያቄዬ። በመንፈስ እኮ ለሰከንድ ከሀገራችን ውጪ አይደለንም። ግን ህሊናችን ታስሮ ነው አምንመላለሰው። እዚህ ያሉ ነጮች ጓደኞቼ ከእኔ በላይ ቁስል ነው የሚሉት። ገመናችን ያውቁታል።
ጠ/ሚር አብይ ሆይ! መንፈሳችን በዬአለንበት እባክዎትን ያስፈቱልን ስል ከአደራም ጭምር ነው። የጸሎት ፊርማም ይታከልበት። ቋሚ ህግ ይኑረው። ሥልጣን በተቀዬረ ቁጥር ስደተኛ የማይተመስበት፤ የማይሰለልበት። ከቤተሶቦቹ የማይነጠልበት። የማይሰጋበት የሆነ መድህን የሆነ መላ ይፈለግለት።
  • ·         አቤቱታ ስምንት።

ኢትዮጵያ ያሉ ጸሐፍት ሥም እዬጠቀሱ እክሌ ይፈታ እያሉ ያሳስባሉ። እኔ የምለው ግን አላዛሯ ኢትዮጵያ በመንፈስ ከነክብራዊ ጃኗዋ ታስራለች እና ትፈታ ነው። የሰው ህሊናው ከታሰር ተስፋን „ተስፋ“ ማድረግ አይቻለውም። በታሰረ ህሊና እንዴት ተስፋን መቀበል ይቻላል፤ አንዴትስ ማቆዬት ይቻላል። ስለሆነም „ባዶ ስድስት“ ትግራይ ላይ፤ አዲስ አባባ ኮቴቤ ክንፈ የደህንነት ማስልጠኛ፤ በዬቤቱ ባሉ እስር ቤቶች፤ በዬትናንሽ ከተሞች የካድሬዎች የቁንጫን መውጫ የሆኑ ዜጎቻችን በሚመለከት የፖሊሲ ውሳኔ የሚያስፈልገው ይሆናል። ለመሆኑ በጠቅላላ በአላዛሯ ኢትዮጵያ ምን ያህል ፖለቲካዊ እሰረኞች አሉን? ቁጥራቸው ይታወቃልን? ህግም መንግሥትም የማያውቃቸው ኢትዮጵያ የባዕድ አገር የሆነችባቸው ዜጎችም አሉን በባዶ ስድስት፤ በክንፈ የደህንነት ማሰልጠኛ፤ በማናውቃቸው ማነቂያዎች ሁሉ። እትዮጵያ እኮ የፈርዖኖች፤ የናዚዎች ዕጣ ፈንታ ነው የገጠማት። ይህን የ27 ዓመት ኦሾቲዝ የምንጠራ ሥራ መልክ የሚይዝበት እርምጃ ጥረቱ ከጠብቅኩት በላይ ቢሆንም የባዶ ስድስት፤ የክንፈ ማስልጠኛ ስውር የመግደያ ቦታ ሁኔታ ህሊናን እረፍት አይሰጥም።

የበዳይ እና የተበዳይ ጉዳይ አይደለም፤ በዳይም ተበዳይም እናት አላቸው። ጥላቻን ጥላቻ አያክመውም። እናትን ነፃ የማድረግ ጉዳይ ነው። እናቶች፤ ሚስቶች ተነገላተዋል። አሁን በሰሞናቱ የኮ/ መንግስቱ ሃይለማርያም እና የኮ / አጥናፉ አባተ ሁለቱ ባለቤቶች የገዳይ የትዳር ደርባባ እመቤት እና የሟች ደርባባ እመቤት አንገት ለአንገት ተያይዘው „ባሌን ባልሽ ገደለብኝ“ ጥቁር ታሪክ የሰሞኑ ቢቢሲ ልዩ ዘጋባ አቀርቧል። እኔ ቀደም ብዬ ሞቶዬ አድርጌ „ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ ሴቶች / እናቶች ዕንባ ድምጽ“ በሚል ስተጋበት የነበረው ጉዳይም ለዚህ ነው። ተጎጂው ማህጸን ነው። ተጎጂዎች የነገ የትውልድ ሃብቶች ናቸው። እርግጥ ይህ መረጃ እስከ አሁን ስለምን ታፈነ? የአሁኑ ወቅትስ ስለምን ተፈቀደ? ሌላ ፖለቲካዊ ትንተና ያስፈልገዋል።
የሆነ ሆኖ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ የነገ እናት/ የነገ ሚስት / የነገ ህፃናት በዚህ ዕንባ ውስጥ ማደግ የለባቸውም። 

43 ዓመት የኢትዮጵያ ሴቶች የጥቃቱ፤ የመከራው፤ የፍዳው ማህጸን ናቸው። በቃችሁ መካራችሁ ሊባሉ ይገባል። እሰረኛ የትዳር አጋሯ፤ እስረኛ ወንድሟ፤ እስረኛ እህቷ፤ እስረኛ እናቷ፤ እስረኛ ፍቅረኛዋ፤ እስረኛ ስደተኛ ልጇ፤ ተፈናቃይ ቤተሰቧ፤ እስረኛዋ እህቷ ራሷ እስረኛዋ እናት ተፈናቃያዋ እናት መንፈሳቸው መፈታት አለበት። ሁላችንም እስረኞች ነን። ነፃነትን በጉልበተኞች የተቀማን። „ማሰር ቀላል የመሆኑን ያህል ማስፈታት ከባድ ነው“ ብለዋል ክቡር ጠ/ ሚር። እግዚአብሄር ስለሚረዳዎት ደፍረውታል መጨረሻውንም ያሳምረው። ሁላችንም በቃችሁ ብለው ከእስር ያስለቅቁን። ብሄራዊ ሰንደቃችንም እስኪ ንጹህ አዬር ይምርበት እና ያግኝ። ኢትየጵያ እኮ የኢህአዴግ ብቻ አገር አይደለችም። አላዛሯን ኢትዮጵያን ሸማዋ ቢያንስ ከእናንተው ዓርማ ጋር እኩል ደረጃ ይሰጠው። ፍቅር የማይቻለው የለም። እስር ቤቶች ስውሮቹን የበቀል አምራቾችን ጨምሮ ከደረቅ ወንጀለኞች በስተቀር ነጻ ቢሆኑ የነፍስ መዳህኒት ነው። ጽድቅም ነው። ለዚህም የማያወላዳ የእርግጥ እርሾ አለው የተስፋዬ ናፍቆት።

  • ·         ቤቱታ ዘጠኝ። ሙግት ግን በአክብሮት።

ክቡር ሆይ!
በዚህ በነገረ ሌብነት በኤርትራው መሪ በፕ/ በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ንጽህና ዕውነቱን ብናገር የመንፈስ ቅናት ነበረብኝ። እንደ ተርታ ዜጋ እራሳቸውን ለማኖር፤ ልጆቻቸውንም በዚህ ሞራላዊ ሥነ - ምግባር ለማሳደግ የሄዱበት መንገድ ለአፍሪካ ናሙና ነው። እጅግ የማከብረው ሰብዕናቸውም ነው። ክቡርነተዎትም ዛሬ ሳይሆን በቀደሙት ንግግረዎት፤ ገለጻዎት ሁሉ ሌብነትን የተጠዬፉ ብቻ ሳይሆን ሌብነትን በጥልቀት የተረጐሙ ነወት። አዎን ሌብነት ህገ መንግሥቱ ላይ የለም። ሌብነት በእርስዎ ትርጓሜ የማህብረሰብ ትውፊት ወደ መሆን ማደጉን ነበር ቀደም ብለው ያመሳጠሩልን። የትራፊክ መብራት ጥሰት በናሙናነት በማቅረብ። የመሬት ዘረፋም፤ የወሰን ጥሰትም፤ የደንበር ግፊያም፤ ከዛ የሚገኘው አንጡራ ሃብት ስርቆትም፤ የማንነትም ዘረፋም፤ የሥነ - ልቦናም ወረራም ያው ሌብነት ነው። 

የባለቅኔው ጠ/ ሚር የሌብነት የእድምታ ሚስጢር ይሄው ነው። በዚህ ከክቡርነተዎት ጋር እንስማማለን። የእኔ ጥያቄ ህገ መንግሥቱ ላይ „ሥረቁ፤ ዝረፉ፤ ውረሩ“ የሚል አንቀጽ ድንጋጌ ብፈልግ አላገኘሁም። ስለዚህም ስለምን የወልቃይት - የጠገዴ - የራያ መሬት፤ አንጡራ ሃብት፤ የሥነ - ልቦና፤ የባህል፤ የወግ፤ የልማድ የማንነት ዘረፋ እና ሌብነት ህገ መንግሥታዊ ውሳኔ እንደሚጠብቅ ግን በእውነት አላመንኩበትም። በፍጹም አላሳመነኝም። ሌብነትን ለማስቆም ምንም የህግ ድንጋጌያዊ እግዳ የለበትም። በትክክል „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ኢትዮጵያውያን እኩል እንደሚይ ስለማምን በህግ አግባብ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከወሰነ ድንጋጌ የሌላቸውን የሃብት፤ የመሬት፤ የሥነ - ልቦና ወረራ ሁሉ ወደ ባላቤቱ ወደ ህዝብ የህሊና ቅርስ መመለስ አለበት። ቅድመ ሁኔታ አያስፈልገውም እንደ እኔ። የሃሳብ መታረቅ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። የመልክዕምድራዊ ታሪክ እርቅ ብቻ ነው የሚጠይቀው። ሌብነት እኮ ያሳፍራል እንደ ማህበረሰብም ውርዴትም ውርዴም ነው። አዲሱን የትግራይ ትውልድ እኮ ሌብነተን በትምርት ደረጃ እያስተማሩት ነው።

ማህበረሰባችን በታሪክ ፊት አዋርደናል ማለት ማግስትን ከቂም ማጽዳት ነው። ለዛውም ለወግ አጣባቂው ለትግራይ ህዝብ። ማግስትን ከሚያሳፍር የትውልድ ግንባታ ማውጣት ማለት ደግሞ ሰው ለመሆን መቻል ነው። ህሊናዊነት። ሌብነት ሽንጥን ገትሮ የሚከራከሩለት ሳይሆን ደብቁኝ የሚሰኝ እጅግ አሳፋሪ የዘገጠ ማንነት ላንቁሷዊ መገለጫ ነው። ከሁሉ የሚከፋው ሌብነትን ለትውልድ ለማውረስ ከራስ ጋር መታረቅ ዳገት ሲሆን ነው። ሌብነትን ለልጅ ልጅ፤ ለማህበረስብ እንዴት ውረሰው ይባላል¡ የነቀዘ ታሪክ ነው። እንደ ቅርስህ ጠበቀው እንዴት ይባላል¡? አሳፋሪ ነው። ጸያፍም። እንዲያውም አንድ ጊዜ ስለምን አዲስ አበባ ላይ የህግ ፋክሊቲ ኖረ ሁሉ ብዬ ጽፌያለሁ። ህግ ህልውና ከሌለው ለእሱ የሚወጣው መዋለ ንዋይ መጠለያ አጥተው መንገድ ላይ ለሚወለዱ፤ አራሽ ለሌላቸው አራሶች ፕሮጀክትንት ቢውል ይሻላል ባይም ነኝ። ግን ህግ ኢትዮጵያ ላይ ሚና አለውን? እስተ ዛሬ አልነበረውም። መስረቅ እኮ ጀግንነት፤ አዋቂነት ነው ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት የመሳፍንቶች ዘመን። 

ከዚህ አቤቱታ ጋር የራያ፤ የወልቃይት የጠገዴ እና የመተከል አማራዎች እጥፍ መከራ ውስጥ ናቸው። ቻይና፤ እስራኤል የጀርመን እግር ኳስ የባዬር ሙንሽን ቡድን ደጋፊዎች ናቸው። እኔም እዚህ ሲዊዝ እዬኖርኩኝ ደጋፊያቸው ነኝ። አሁን እኮ በጉልበት በታያዙ ቦታዎች „የፋሲል ከነማን“ ማልያ መልበስ ከሰሞኑ እስር ተፈርዶበታል አዲረመጽ/ ማይጸምሪ። ይህ ገመና ለፊፋ ቢጻፍ ምን ሊኮን ነው? ፊፋ እኮ ዙሪክ ነው ያለው። እርግጥ ነው በሁሉም አካባቢ ሁለገብ ችግር እንዳለ አዳምጫለሁ አፋር ብቻ ነው ገና  እድሉ ያልደረሰው ስሜቱን ያላዳምጥኩት፤ የሆነ ሆኖ በግፍ በተወሰዱ አካባቢዎች እነኝህ ባለቤት የሌላቸው ዜጎቸዎት ወደ እናት ቤተሰባቸው እሲኪቀላቀሉ ድረስ በደሉ በሦስት እጥፍ የተገመደ ስለሆነ በወፍ በረር የጠ/ ሚር ቢሮ ልዩ ጥበቃ ክትትል ሊያደርግበት ይገባል። አሁን እነዛ ምንዱባን አባት አላቸው እና።

እነዚህ ቦታዎች ልክ እንደ ሳውዲ፤ እንደ ኬንያ፤ እንደ ሱዳን ስደተኛ ለኢትዮጵውያን ዕንባ ቅርብ የሆኑት ኢትዮጵያዊ ሙሴም አትኩሮት ይሻል ይህ መሰረታዊ ጉዳይ። አገላለጼ ለክቡርነተዎት ሊከብድ ይችላል፤ ግን ራሴን ቅድመ ምርመራ ሳላደርግበት ቁልጭ ባለ አገላለጽ ራያ፤ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ መተከል ያሉ አማራዎች ጠላት እጅ ውስጥ ነው ያሉት። ኑሯቸው በውጪ ወራሪ ሃይል እንኳን አላዛሯ ኢትዮጵያ ብትያዝ የማይደርስ መከራ ነው ያለባቸው። ልጆች እኮ በአባት መጠራት ቀርቶባቸው የሚጠሩት በእናታቸው ሥም ነው ወልቃይት ጠገዴ ውስጥ። ይሄ ቅኔ ቤት ትርጉም ተዘርግቶ የሊቀ - ሊቃውነቱ ዕድምታዊ የጉባኤ ውሳኔ የሚሰጡበት ነው። „በእናት ሥም መጠራት“ እም! ወያኔ አውሬ ነው።

ወያኔ ጨካኝ ነው። የመጨረሻው ቀን ሲደርስ እንኳንስ በወረራ በያዛቸው ቦታዎች ያሉ ለዛውም አማራዎች ቀርቶ ለትግራይ ህዝብም ይሉኝታ ይኖረዋል ብዬ እኔ በግሌ አላስብም። ስለምን? ጭካኔን የሥነ - ልቦና ችግር ያለበት ሰው ስለሚከውነው። ታማሚ ሰው ነው ጨካኝ የሚሆነው። የአዕምሮ ጉድለት ያለበት ሰው ነው ኢ- ሰብዕዊ የሚሆነው። ጨካኞች፤ አረመኔዎች ከሰው ሰብዕና ይልቅ የጫካዊ አውሬነትን ሰብዕና የተላበሱ ናቸው። ሰው ወደ አውሬነት ባህሪ ሲቀዬር ነው ጨካኝ የሚሆነው ብስጩም የሚሆነው። መንፈሱም የጨለማው ነው። ይህን መሰል የጨካኝ የገነገነ መንፈስ ለማዳን እንኳንስ ኢትዮጵያ ዓለምም የሰብዕና ቀረፃ ሁለንትናዊ ት/ ቤት የላትም። ሁሉም አይችልም። የፍቅር ተፈጥሮ እና ዶግማ ግን ይችላል። ይህን ለማድረግም ሂደት ብቻ ሳይሆን ተቋም ያስፈልገዋል። ቢያንስ በሚዲያም መትጋት ይገባዋል። ይህ ለነገ ይቀጠር የማይባል ትውልዳዊ ድርሻችን ነው፤ ከእያንዳንዳችን በግል ከሁላችንም በጋራ የሚጠዬቅ የህሊና በትረ ጉዳይ ነው። ግንዶቹ ግን ይለወጣሉ ብዬ አላስብም፤ አንዲት እራፊ የመንፈስ መጠለያ በሌላው ህብረተሰብ ተቀባይነት ያላገኝ ድርጅት ልቡን ነፍቶ እንደ ተንጠለጠለ ነው አሁንም ያለው። ስለሆነም ብንችል ቅርንጫፌዎችን ለማዳን መመኮር አይከፋም። ገና ለመፀነስ ስላልታሰቡት የትግራይ ህፃናት ሲባል።     
  • ·         አቤቱታ አስር።

እኔ በግሌ ማድመጥ የምሻው ንግግረዎትን ሆኖ ሳለ ንግግረዎት ግን ብዙ እዬተቆራረጠ፤ ጥራት እዬጎደለው በ50ዎቹ መጀመሪያ አውሮፓውያኑ ከነበረቡት እንኳ ደረጃ ሊደርስ አላስቻለውም። የሴራ ቤተኛ የሆነው አገር ቤት ያለው የወያኔ ሃርነት መንፈስ ያደራበት የኢትዮጵያ ሚዲያ የመንግሥትም ይሁን የግሉ ለአንድ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ የሰጠውን ትኩረት ያህል ክብር ለጠ/ሚሩ ቃለ ምህዳን የለውም። እኔ እንደ ማስበው የጠ/ ሚር ቢሮ የሚመራው ራሱን የቻለ ሚዲያ ቢኖር በጣም መልካም ነው። ጥራቱን የጠበቀ ፎቶ አንሺም፤ ደረጃውን የጠበቀ ዩቱብ ቻናልም። ሚዲያው የጥቃት ሰላባ ያደረገው የክብሩነተዎትን ጉዞ በስልት በማጨለም መሆኑን በጥልቀት ተገንዝቤያለሁኝ። የአቀራረብ ይዘቱም ልናዬውም፤ ልናዳምጠውም ወደ ማንፈልገው፤ በዝምታ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደመበት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ሆድ ዕቃ ውስጥ ነው ያለው። እያንዳንዱ ነጥባዊ ቦታ ክፍተት አለበት። ኢትዮጵያዊ ሰው መኖሩ ብቻ ሳይሆን ልክ እንደ እኛ ስደት ላይ እንዳለነው አገር ቤት ያለውም የመቀበሪያ አፈሩ ጉዳይ ህሊናውን ሰላም ነስቶታል። „መሬት ደም ጠጥታ ኖረች“ ይህ ማለት አዝዕርት ስታበቀል ኢትዮጵያዊቷ መሬት በግፍ በፈሰሰ የደም ዝናባማነት ነው። 

ስለዚህም በግፍ በፈሰሰ ደም የበቀለ ምርት እዬበላ ቋሚው አለሁ ይላል ሲሉ አንድ ቅኔኛ ጋንቤላ ላይ ተናግረዋል። መራራ ነገር እኮ ነው። እንዴት ወደ እዛ ምልሰት ሚዲያው ራሱ መንፈሱን ያደርጋል። በሰው ላይ የወረደው ስቃይ እኮ ቀንን ጨለማ ሳያደርገው መቆዬቱ የሚገርመኝ ነገር ነው። ህሊና ከሚሸከመው በላይ ነው ግፉ። መንግሥት እና ህዝብ የተለያዩበት አብዩ ጉዳይ ይሄው ነው። 27 ዓመት ከበቂ በላይ ነው። ይህን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሆድ ዕቃ መንፈስ ትግራይ ላይ ባለው ሚዲያ መከወን ይቻላል። የጀግኖቹ ትሩፋት „ግንቦት 20 ድላችን“ ነው ስለሚሉ። የሚገርመው አማራ ለዘሩ ጥፋት የባህርዳሩን አውሮፕላን ማረፊያ „ግንቦት 20¡“ ብሎታል። ግንቦት ወር ለአማራ መጥፊያ መመንጠሪያ የተፈጠረ ነው። የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ በተገለበጠ ብልጠት እንዲጫንበት አለመፈቅዱ ብቻ ሳይሆን በተስፋው ላይ መርዝ በስልት እዬተነሰነሰበት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። የሚሰጡ መግለጫዎችም በዛው ልክ ከዛ መንፈስ ጋር እንዲነካኩ ማድረግ ወደ ባዕቱ በመመለስ ላይ ያለውን ቅናዊ የምልዕት መንፈስ፤ በጨካኙ አገዛዝ ሥር የወደቀው ምክንያታዊ የሸፈተው ልቦና ሁሉ የሰጠውን ሙሉ የፍቅር እና የአክብሮት ሰብል እንዳይሰበሰብ የማስጠንቀቂያ ደወል በመሆኑ የጠ/ ሚር ቢሮ በአጀንዳ ይዞ መልክ ቢያስዘው ጥሩ ነው።

የጠ/ ሚሩ ቢሮ የእኔ የሚለው፤ ራሱ በቀጥታ የሚመራው፤ የሚያሰተዳድረው ሮቦታዊ ሳይሆን ሰዋዊ የሚዲያ መንፈስ ቢኖረውም የተሻለ ነው። ተፎካክሮ በጥራቱ ልቅና አሸናፊ ሆኖ መውጣት የሚችል። ሪፖርተሮችም እንደዚሁ። አሁን ዘመቻ ላይ ናችሁ። እኔ እምመኘው ሚዲያ የፖለቲካ ድርጅት ማንፌሰቶ መጠቅለያ ጋዜጣ ያልሆነ መሆን አለበት። እንደዛ ከሆነ ጊዜ ማባከን አይገባም። የትኛውም ሚዲያ ከወረቀት ጋር ነፍሱን ክርስትና ካናሳ መንፈስን ማባከን ነው የሚሆነው እሱን ማድመጥ። እርግጥ ነው በዚህ ኢትዮጵያ ዕድለኛ ሆና አታውቅም። ጋዜጠኛ ካድሬ ከሆነ ሰዋዊነት ከዛው ላይ ቀራንዮ ተፈርዶበት፤ አምልኮታዊ ወረቀት ትንሳኤው ታወጀለት ማለት ነው። እራሱ ሙያው ክርችም ብሎ ጉድጓድ ውስጥ ይቀበራል። ጋዜጠኛ ሌብነት እና የፓርቲ አባልነትን በጽኑ ሊጸዬፈው ይገባል። ለወረቀት ስላልተፈጠረ።  

ዜጋ“ ‚ሰው“ „ተፈጥሮ‘ „ትውፊት“ የሚል መርህን መከተል አለበት አንድ ጋዜጠኛ። ሰውኛ ያልሆነ ጥቁር ልብም አይመጥነውም። ክቡርነተዎት ለተነሱበት ዓላማ የሶሻሊዝም የዝገት ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገንም። ለክቡርነተዎት ንግግር ቀስቃሽ አያስፈለገውም ህዝቡ። ስለ ክብሩነተዎት መንፈስም የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ካድሬ ተንታኝ አንፈልግም። እንደ ቅኔው ማህሌት ቅኝት ቀጥ ብሎ ህሊናን የሚገዛ እና የሚገራ ስለሆነ - ለቅኖች። ማብራሪያም፤ ገላጨም አንሻም። አብራሪ ሪፖርተርም አንሻም። ቅኖች ህሊናችን ማባከን አንፈልግም። ሌላው በውይይቶች ሁሉ ገላጮቹም፤ ሰብሳቢዎችም ካድሬዎች ናቸው። ይሄ የመገለውን የውስጥ ቁስልን እንዲሽር አያደርገውም፤ እንዲያውም እያገረሸ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ላልተመቻቸው የአሉታዊ ዘማች ነጋድራሶች ስንቅ ማዳበሪያ ቃል አቃባይ ነው የሚሆነው። አቅም የለንም ያን በደም የተነከረ ዘመን ደግመን ለማዬትም፤ ለማዳመጥ፤ ለማስታወስም።

ሚዲያውም ሆነ ይህ የሙሁራን ስብሰባ የአወያዮች መንፈስ ከክቡርነተዎት የመልካም ጅማሮ ጋር የደፈጣ ውጊያ ላይ ነው ያለው። የተነሱበትን ፍቅራዊነት ምህንድስናዊ ጉዞ በታቀደ ስልት አረም እያበቀሉበት፤ እዬበረዙት ነው። ይህ የለውጥ መንፈስ ለድል ካልበቃ እስከቤተሰባቸው ሰማጭ ስለመሆናቸው በፍጹም አልተረዱትም። ኢሠፓ ሲፈርስ ቋሚ አካሉ ብቻውን እስከ ቤተሰቡ መከራውን ይጋፈጠዋል ሲባል ሁሉም አብሮ ፈለሰ። የሚድን የለም።

ቢያንስ መልክ እስኪይዝ ድረስ እንደ አማራጭ OBN ሃላፊነቱን ቢወሰድ መንፈሱም ጤነኛ ስለሆነ መልካም ነው። በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥር ለ27 ዓመት ወድቀው የኖሩት ሚዲያዎች ሁሉ ከአዲሱ መንፈስ ጋር ጦርነት መግጠማቸውን በስፋት እያስተዋልኩት ስለሆነ። ፈተናቸው ይረዳኛል የካድሬነት ችግር ነው፤ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌስቶ ነፍስ የማስቀጠል መሟሟት ነው። ለዚህም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም ሳጅን በረከት ስምዖንም አያርፉለትም። የፖሊሲ ሶፍት ዌር ኣዘጋጅነት ነዳፊነትም እንጦርጦስ ስለተላከ። ልሳናቸው በመከርቸሙ፤ ብዕራቸውም እስር ቤት ስለገባች ይተኙለታል ብዬ አላስብም። ለዚህም ተግተው እሾኽን የሚያማርቱ እሾኾች መሆናቸው ይታወቃል።

ክቡሩነተዎት እንዲሚያውቁትም ከዚህ በተጨማሪ መልካምነት እንደ ተቃራኒው መንገዱ ሰፊ አይደለም፤ የመደመጥ ዕድሉም ጠባብ ነው። ፈተናውም ውሃ ያዘለ ተራራ ነው። አጣይ መንፈሶች እና አፍራሽ ዝግኖች ሺዎችን ሲያሰልፍ አስታራቂ መንፈሶች እና አዎንታዊ መንፈሶች ግን አስሮችን እንኳን ማሰለፍ አይቻላቸውም። አጣይ መንፈሶች ፈጣኖች ሲሆኑ ሁሉንም ቦታ ለመበከል ሲችሉ፤ አዋዳጅ መንፈሶች ደግሞ እንቅፋት ያዬለባቸው ጠባብ መንገድ በመሆናቸው አዝጋሚ ናቸው። እንዲያውም ክቡሩነተዎት ዕድለኛ ነዎት እጅግ ሰፊ የሆነ የመንፈስ አቅም ነው በአጭር ጊዜ ያለዎት። በሥመዎት የእዬለቱን የጉግልን ታዳሚ ስለምቆጣጠር ወደ ሁለት ሚሊዮን እዬገባ አገኘዋለሁኝ። ይህ ቀጣይ ይሆን ዘንድ የጠ/ ሚር ቢሮ እና እኛ የመንፈስ ሃዲድ የሚዲያው ነገር በቂ ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው ባይ ነኝ። ንብርብር ሴራ ነው ያለበት። ይህ አዲስ የለውጥ መንፈስ የወያኔ ሃርነት ፈቃድም ችሮታም አይደለም። ፈቀደ እግዚአበሄር ነው። በሰውኛ ትርጉሙ የአማራ የህልውና ተጋድሎ እና የቄሮ ንቅናቄ ደም ገብረው ያስገኙት ሲሆን፤ በሁለቱም ወገን ያለውን መከፋት ያደመጠ አዲስ ብቻ ሳይሆን በውስጥ የበቀለ መንፈስ በመፈጠሩ ነው። ስለዚህ ለማስቀጠል መካች ሚደያ ወሳኝ ድርሻ አለው። ይህን ድርሻ ለመወጣት በለውጡ አንቀሳቃሽ አሰኳል ላይ መመስረት አለበት። የዓለም ማህበረሰብ በጥንቃቄ እና በአትኩሮት እየተከታተሉት ነው።
 
ወደ ቀደመው እንደ አቮው ስመለስ አንድ ንግግር ሊደመጥ የሚችለው የንግግሩ ፍሬ ነገር ብቻ ሳይሆን የቴክኒክ ጥራቱም ወሳኝ ነው። ሚደያ አዬር ላይ ጥራት ከሌለው ለዛውም በ21ኛው ምዕት በዘመነ ዲጅታል ድካሙ ሁሉ ከንቱ ነው። አሁን ክቡርነተዎት በዬቦታ እዬሄዱ ያደረጓቸው ውይይቶች „የማለዳ ኮከቦች“ ዝግጅትን ያህል  1/10 ጥራት የለውም። ጥራቱ ከሌላ የማደመጥን ትዕግስትን ሃብት አደርጎ ማቆዬት አይቻልም። አቅል፤ መንፈስ ወደ ተሻለው ይሄዳል። ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል። ወቅቱ ካመለጠ ደግሞ ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል። በይ ያጣ እንጀራም ይሻግታል። አባይ አወራራጅ የሌለው እንጀራም ያንቃል። ስለሆነም መደከም ካለበት የተደማጭነቱን የጥራት ደረጃም ታቅዱ እንጂ በትውስት ባለቤት መሆን አይገባውም። 

አሁን እኮ ተልዕኮ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ጥገኛ ነው በሚዲያው ዘርፍ። ይህ የተልዕኮው ጉዞ የአዲሱ ራዕይ ጭንቅላት ጉዳይ ነው። ስለሆነም የጠ/ ሚሩ ቢሮ በቅርብ በሚከታተለው፤ በሚያሰተዳድረው፤ በሚመራው፤ በሚቆጣጠረው ሁኔታ መደራጀት አለበት። እጅግ ዝግተኛ ነው ጥራቱ። ከዬለም የማይሻል። ተቆራርጦ ተበጣጥሶ ጎሽቶ ተስረክርኮ ነው የሚደርሰው።
ዛሬ የተለቀቀ አንድ „ጠ/ሚ አብይ አህመድ የመጀመሪያዎቹ 60 ቀናት ብሄራዊ መግባባትን“ የሚል ፎቶውን እስኪ ልብ ብለው ይመልከቱት። ሆን ተብሎ ቀዶ ጥገናው ያልጨረሰ ገጸ ባህሪ አላብሰው ገመምተኛ እና ስንጥቅጥቅ ያለ፤ በለቅ የበላው አድረገው ነበር ያቀረቡት። ገጽ በስፋቱ ከሁለት ተጎርድ  አፍንጫ የላይ እና የታች ሰርተውለታል። ግራ እና ቀኙም ሌላ ባዕድ አካል መጥቶ ተለጥፎበታል። ሰብዕናን በገዘፈ መልኩ የተፈታተነ ሴራ ነው ይሄ። ግማሽ ፊት፤ ጉድን ፊት የተለበጠበት ፎቶ። ይህ ሌላ የወንጀል ሥራ ነው። 100 ሚሊዮን ህዝብ ደስታንም ጥቁር ማልበስ፤ ማቅ ውስጥ መክተት እና ሳቅን መቀማት ነው። ተስፋን እንዲህ ነው ዴያቢሎሳዊ መንፈስ የሚፈታተነው። እሚጠገንም አይደለም። 

የጠ/ ሚር ቢሮ ጋር የሚሰራ ሌላ ሚዲያ ያስፍልጋል። „መሪነት ለላቀ ህይወት“ ዶር ገመቺስ ደስታ LTV Ethiopia ዝግጅታቸውን እከታተላለሁኝ፤ ፍቅሬም አክብሮቴም የተለዬ ነው። እንደ እሳቸው ያለውን ብቁ ሰው በአቅም አሟልቶ ማምጣት ለዕውነተኛ ሚዲያ መንፈሱ ቅርብ ነው። የሚገርሙ ጋዜጠኛች አሉት የአማራ ብዙሃን ሚዲያ። የጋዜጠኝነት የሥነ - ምግባሩን ፍልስፍናዊ ጥልቀት በውል ያጤኑ። አንበሳ አንስትም አለችው። ተንታኝ ሞጋች እንደ እሷ ዓይነት ወጣት ለዛውም ርህርሂት እና የሰከነች አንስት ገጥሞኝ አያውቅም። ሁለገብ አቅሟ ይደንቃል። ጋዜጠኛ ማህደር ብርሌው ሊቅ ናት። አማራ ሚዲያን አቶ በረከት ስምዖንን ቢገላገል ቃናዊ አቅሙ፤ ጣዕሙ ልክ የለውም። ግን ታንቆ ተይዟል። ፍትኃትን ይማጸናል።

·         ቤቱታ አስራአንድ ከ200 ዓመት በኋዋላ ስለሚመጣው አደጋ ዕይታ፤

በተገኘ ዕድል ጥያቄን ሁለገብ ፍንጭ ሰጪ አድርጎ በማቅረብ እረገድ የጋንቤላ ስብሰባ በሳል ነበር፤ ዓለምአቀፋዊ ይዘትም ነበረው። አንድ ምሳሌ ብቻ ላንሳ። ፍቅርን የሰው ልጅ የሚዬው ከሰው ጋር በተገናኘ እጅግ አጣብቆ ነው። ፍቅር የደስታ ምንጭ ነው። ፍቅርም የሀዘን ምንጭ ነው። እንደ ሥርጉተ ፍልስፍና ነው ሃሳቤን እማቀርበው። ፍቅር የደስታ ምንጭ ነው ስል „እሳተ ጎመራ“ አይቶ ደስ የሚለው ሰው አለ። ደስታውን ፈጥሮለታል ማለት ነው። እሱን ብቻ ለማዬት ከአገር አገር የሚንከራተቱም የእሳተ ጎመራ ፍቅረኞች አሉ። የፎቶ የሥነ - ጥበብ አካልም ነው አንድ የሥራ የሙያ ዘርፍ ነው እንደ ማለት። ሙያም ነው። ለአንዱ ደስታ ፈጣሪ የሆነው የእሳተ ጎመራ የቀለጦ ፍስት የሚያስከትለው ጦስ እና የመሬት መናጥ ደግሞ የሚያሰጋው ሰው አለ። ስጋት የሀዘን መቀስቀሻ ነው። ቀለም የለሾቹ ሰብዕውያን ውስጣቸው ሲያዝን አፍጋን ድረስ ሄደው አካላቸውን ያጣሉ። ጋዜጠኞችም በጦርነት መሃል ተገኝተው መከራውን ይዘግባሉ። ያ የውስጣቸው ሃዘን እራሳቸውን እንዲሰጡ አሰውስኗቸዋል። ሊጎዱ ይችላሉ፤ መወሰናቸውን አካላቸውን አጥተው እንኳን ይደሰቱበታል። ለቤተሰብ ደግሞ የምር ሃዘን ይሆናል። በሌላ በኩል ተጎጂዎች ስለሰው ልጅ ፍቅር ፈቅደው ስላደረጉት ሰናይን ያገኙበታል። ስለሆነም ተፈጥሮን በሰውኛ የተረጎመ ጥልቅ ስብሰባ ነበር የጋንቤላው አሉታዊውም // አዎንታዊ አገላለጽ አቅጣጫ አመላካች ፍንጪ ሰጪ ነበር። ለሰው ልጅ የደስታ ምንጭ ለተፈጥሮ የተጨነቀ የተጠበበ። እንዲያውም እንደ እኔ በማከብረውም እጅግም በምሳሳለትም በዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ መንፈስ ውስጥ ያዬኋዋች ወገኖቼ ሁሉ አሉ እዛው ጋንቤላው ጉባኤ ላይ።

ወደ ተነሳሁበት ስመለስ „ከጋንቤላ ኗሪ ይልቅ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ቁጥር ይበልጣል“ ነው ያሉት ተሰብሳቢዎች። ይህ በማህበራዊ ኑሮ፤ በኢኮኖሚ የሚያስከትለው ቀውስ ባለቤት ላልነበራት አገር፤ ስንዱ የሆነ የመቆጣጣሪያ ስልት ልቅ በነበረበት አገር ጉዳቱ ከባድ ነው። ጀርመኖች ብዙ ስደተኞችን ከሶርያ ሲረከቡ የህዝቡ ስጋትም ይሄው ነበር። አዲስ ፓርቲ እንዲፈጥሩ ያደረጋቸው ይሄው ነበር። ያ አዲስ ፓርቲ ከቀደሙት አንጋፋዎች ጋር ተወዳድሮ የሦስተኛውን ደረጃ ያገኘውም ባለፈው ዓመት ምርጫም ከህዝቡ ከስጋቱ የተነሳ ነው። ከሚችለው በላይ ሙገት ሲበዛበትም የጀርመን መንግሥት የዓለም ስጋት ተጨምሮ ማህበራዊ ሚደያን የሚቆጣጠር ህግ እስከ ማውጣት የተደረሰበትም በዚኽው ነው። በቀጥታ ህዝቡ ምልሰት ያደረገው ወደ ናዚያዊ አመለካከት ነው። እንግዲህ ጀርመኖች በሁሉም መስክ የማይደፈር አቅም እንዳላቸው ይታወቃል። ይህም ሆኖ ማለት ነው ስደት እና ቀውሱ የሚያስከትለው የህሊና አብዬት በአሉታም/ በአዎንታም ከባድ ነው።

እንደ እኛ ባለች አገር የጎረቤት አገር ስደተኞችን ስትቀበል ለጊዚያዊ ጉዳይ ሳይሆን ረጅሙን የትውልዱን ዕጣ ማዬት የተገባ ይመስለኛል። እርግጥ ነው ስደተኛ መቀበል እንደ ዓለም ማህበረሰብ አባልነቷ ለህግጋቱ መገዛት አለባት። ግን ራሱን የቻለም ቋሚ ህግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። የህግ ባለሙያ አይደለሁኝም። ዘመንም፤ ሥርዓትም፤ መሪም በተለዋወጠ ቁጥር ማዕከላዊ የሆነ አቅም ያለው ሁነኛ ነገር ያስፈልጋል። ስደተኛ የጎረቤት አገር ከሆነ ባዶ እጁን አይመጣም። ጣምራ ተልዕኮ ነው ይዞ ነው የሚመጣው። ዛሬ ጋንቤላ ላይ ከኗሪው በላይ ያለው የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ነገ የዛሬ 200 ዓመት አዲስ አበባ የማይደርስበት ምን ምክንያት አለው? ምን አስተማማኝ ጋራንቲ አለ? ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ደንቢ ደሎ ይደርሳል። ደግሞ ነገ አዲስ አባባ መባል ቀርቶ ሌላ ሥም፤ የሥራ ቋንቋ አረብኛ ይሁንልን ይመጣል። በቀደመ ትውፊታዊ ሥያሜ ያሉት ተቋማት ውርስነታቸው ቀርቶ በአረብኛ ሥማቸው ይሁን ይባላል። 

ኗሬው ዜጋው ተሳዳጅ መጤው ደግሞ አሳዳጅ ይሆናል። ይህ እከሌ ተከሌ ሳይባል ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለው የስደተኛ ጉዳይ ዛሬ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ከምታገኘው የሰብዕዊነት አስጠባቂነት ክብር በላይ ራሷን ነገ ሊያሳጣት ወይንም ወጥ ትውፊታዊ ዕሴቷን ሊቀይጠው፤ ሊነጥቀውም ይችላል፤ በጥንቃቄ በተመጣጠነ ጥበብ ካልተያዘ። የደህንነት ተግባራትን የሚከውኑም ሊኖሩ ይቻላሉ። በሌላ በኩልም የሃይማኖት ጉዳይም አለ። በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ጠንካር በህብረ ቀለማት የዕምነት ተቋማት መቻቻላዊ ናሙናነት ኢትዮጵያ ባለ አሻራ ናት። ነገ ይህን ለማስቀጠል አደጋው ሰፊ ነው። አሁን እንደ ቀደመው በሃይል አይደለም። በስልት እና በጥበብ ነው። ይህን ጠረፍ ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የሚያሰጋቸው ጉዳይ ነው። ነገ ሲታሰብ በመኖር ውስጥ የሚገጥም ፈተናዎች ብቻ ሳይሆን ማንነት፤ ከማንነት ጋር በውል የተደራጁ ዕሴቶችን ትውፊታዊ ጉዞ ሁሉ መታሰብ አለበት። በአግባቡም መሰናዶ ማድረግ ይገባል። ይህ ካልሆን በልቅነት በርን ፏ ማድረግ በጣም አስፈሪ አደገኛም ነው። ጋብቻው፤ መዋለዱ ሲጨመር የባለርስትነት ጥያቄው ብንፈራውም ነገ አይቀሬ ነው። ያን የመሰለ ንጹህ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ማጣት ደግሞ ሃዘን ነው። „ዳሩ ሲደፈር ማህሉ ዳር“ ይሆናል።
  • ·         አቤቱታ አስራሁለት።

የአማራ ገበሬ የትጥቅ የመፍታት ጉዳይ ትውፊትን መቀማት፤ ሱሪህ አውልቀህ እርቃንህን ዘነዘናህን ሂድ የማለት ነው። መሳቂያ መሳለቂያ ሁን ማለትም ነው። ራስህን አዋርደህ ኑር ማለትም ነው። መሳሪያውን የተቀማ ወንድ „ተብዕት“ ሆነህ አልተፈጠርክም ነው። አይበዛም ወይ ግፉ?!! ልክ አላለፈም ወይ በደሉ?!! እማዳምጠው እኮ የሰውነቱን መሰረዝ ነው። በታሪኩ የጎንደር ገበሬ ትጥቅ ፈቶ አያውቅም። ታሪኩ - ትውፊቱ - ወርሱ - ቅርሱ - ትሩፋቱ ሊከበርለት ይገባል ጎንደርም የአላዛሯ ኢትዮጵያ ዜጋ ከሆነ። ሰው መሆኑን እንደ ዜጋ መታዬቱ ምስክሩ ሰው ነህ ተብሎ ዕውቅና ሲሰጠው ብቻ ነው። ሰው ከሆነ ደግሞ ባህል አለው፤ ወግ አለው፤ ልማዳዊ እሴት አለው፤ ማንነት አለው፤ ቤተሰባዊ እሴት አለው፤ ሃይማኖታዊ ዕሴት አለው፤ ማህበራዊ ዕሴት አለው። ይህ ጉዳይ ከመኖርም በላይ ነው እዛ ለተፈጠረ ሰው። ኦሮምያ ላይ ብትር ጥልቅ ዕሴት ነው። አማራ መሬት ላይም ከብትር በተጨማሪ ሙሉ ትጥቅ ራሱን ተወልጄውን የደሙ ጠብታ ማለት ነው። ማንነቱ መለያው ነው። ሰው ሲሞት፤ ሲዳር፤ ሲሾም፤ ልጅ ሲወለድ፤ ዓመታቱ ሲታወስ በተለይ ጀግና ከሆነ ሩምታ ይተኮሳል። ልክ ለክቡርነተዎት ኬኒያ ሲገቡ እንደተደረገለዎት ታላቅ ክብር ሁሉ።

መስቀል ዋዜማ መላ የጎንደር ገበሬ ሙሉ ሌሊት ጅራፍ ሲያጨኽ ነው የሚያደረው። „ዕብድ ሃሙስ“ የሚባል ሪቷልም ደግሞ አለ። አብይ ፆም ከመግባቱ በፊት ያለው ሃሙስ ማለት ነው። ይህም የጾም ጊዜው ረጅም ስለሆነ ሠርግ በብዛት የሚከወንበት የወል የፍሰሃ ዕለት ነው። በዚህ ዕለት የህብረት ሠርግ ትውፊት ነው ጎንደር ያለው። በአንድ የቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ቢያንስ አስር ሠርግ ሊኖር ይችላል። እንግዲህ አንድ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በ20 ጋሻ ክልል ነው የሚደራጀው በዬካቲት 67ቱ በመሬት ላራሹ አዋጅ። የአስር ሰው ሙሽራ ጀንበር ስታዘቀዝቅ በዛ ገበሬ መንደር ሲደርስ ሙሽራው ሙሽሪትን ይዞ ወደ ዳሱ ሲገባ በቀዬው አባባ ነው የሚሆነው በአብሪ ጥይት፤ ርችት ይተኮሳል። ደስታ ነው፤ ሰማይ ፍንድቅድቅ ብሎ ይስቃል። ፍሰሃ ነው፤ በሌላ በኩልም የአዲስ ህይወት መጀመሪያ የመባቻ የምሥራችም ነው። እንኳን ለዚህ አበቃህም ነው። የባሩድ እልልታ እንደ ማለት ነው።

አሁን አባ ገዳዎች ከግንባራቸው ላይ የሚያደርጉት የክብር ትውፊት አለ። በጥበብ የተሰራ ብትርም አለ። መቼም ኦሮምያ ላይ ይህን አውልቁ አይባልም። ለነገሩ እነሱን ማን ደፍሮ? ልክ እንደዛም ለአማራ የነፍሱ ተክሊል ነው መሳሪያው። ቀድሞ ነገር የወንድነቱ ማንነት መለኪያው፤ መለያው፤ መስፈርያው መሳሪያው ሙሉ ዝናሩ፤ ጋሻ እና ጡሩራው ነው። መሳሪያውን ያስረከበ ተብዕት ሚስትም አያገኝም፤ ቢያገባም አብራው አትቆይም - በጥዋቱ ነው ትታው የምትሄደው። „አልጫ“ ነው የምትለው። እንደ ማጫ ነው ትጥቅ የሚታዬው። እንደ ከብት እንደ መሬት። ስለዚህ „ጎንደር ምን በደለ?“ ያሉ አንድ ወንድሜ በጎንደሩ ስብሰባ ላይ አድምጫለሁኝ። ስለምን ይሆን መከራችን እንዲህ የተበራከተው? ስለምንስ ጎንደር ሙሉ ህዝቡ እንዲታሰር ተፈለገ? የት ይድረስ ይህ ህዝብ? እንዲያው ሰማይ ቤተ ለጎንደሬው የቦታ ምሪት ካለ በሊዝ ቢሰጥ ምን አለበት። በቃ ጎንደር ላይ መከራ ብቻ ነው የሚደመጠው። ጎንደር መቼ ነው የሚስቀው? ሁሉ ቦታ ህዝባዊ ስብሰባ ተከታትያለሁኝ። አንቦ፤ ባሌ፤ አሶሳ፤ ጋንቤላ ህዝቡ በነፃነት ካለምንም ታጣቂ ነበር በአደባባይ ዬተሰበሰበው። 

ጎንደር ላይ በታጣቂ ሰልፍ ነበር የተከወነው? ህጻነቱ እኮ አብረው ነበሩ እዛ አደባባይ ላይ። ያማል? ታሪክን ያጠቁራል? መቼ ነው ለጎንደር የታወጀው ጨለማ ብርሃን የሚሰጠው ለዛውም በጌጡ በአብይ መንፈስ? ለጌጡ ለአብይ ነው ጎንደር የማይታመነው? አለሁ የሚል የ66ቱ የፖለቲካ አዛውነቱ ሊሂቅ እኮ እናቱ ጎንደር ናት። ክውን ሽክፍ አድርጋ ሁሉንም እንደ አመሉ ይዛ ለቀጣዩ አደራ ያሰረከበች። ጎንደር እኮ እናቱ ናት ለሁሉም። ክቡሩነተዎት አውሮፕላን ሲወርዱም መሳሪያ የታጠቀ ሰው አይቻለሁኝ። ያሳዘናል፤ ማህጸንን ደም ያስነባል። የአዋሳ እድገት ልማት እኮ የጎንደር እናት ተሸከማው በኖረችው የ43 ዓመት ተጋድሎ የተገኜ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቢሆን በማን ጉሮሮው ረጥቦ? ማንስ በከፈለው የደም ግብር? ሰው መሆንን ብቻ የሚጠይቅ አመክንዮ ነው። 
  • ·         አልሞ መተኮስ ባህላዊ እስፖርትም ነው።

ሌላው የዒላማ ልምምድ ነው። አገሬው ልጁን ተኩስ ያሰተምራል፤ መሳሪያ ቢያወርሰው ካላስተማረው ከተራ ብትር በታች ነው። መሬቱን እንደሚያስረክበው እርሻውን፤ ጉልጉሎውን፤ ማረም፤ ማጨድን በደቦ እንደሚያስተምረው ሁሉ መደበኛ ተኩስም ይማራል ተወልጄው። ሰለዚህ ትውፊቱ ት/ ቤትም ነው። ውጪ አገር እንደ ጎልፍ ትልቅ የስፖርት አይነት ነው አልሞ መተኮስ። እንዲያውም ኢትዮጵያ አልሞ በመተኮስ ስፖርት የቀረባት ትልቅ መስክ ነው። ሩጫ ኦሮምያ እንደ አለው ሁሉ ይህን ትውፊት ባሊህ ብትለው አላዛሯ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሩጫም በተሻለ የክብር ተክሊልን የበላይነት ያቀዳጃታል። ለዛውም ይህ ስፖርታዊ ትውፊት የሰው ዘር በአካባቢው ከሰፈረ ጀምሮ ስለሆነ ተመክሮው ዝቀሽ ነው፤ ምን ያህል ዘመን እንዳስቆጠረ ራሱ ማወቅ የሚቻል አይመስለኝም። አስልጣኙን ራሱ ተወዳዳሪው የመምህሩ አስተማሪ ነው የሚሆነው። የስፖርቱ ህግን መማር ካልሆነ አማራ አልሞ ለመተኮስ መምህር አያስፈልገውም። ይህ ባህላዊ የውስጥ ርግጠኝነትን፤ ይቻላልን በመገንባት እረገድም አንቱ ነው። የሥነ - ልቦናው ግንባታ እችላለሁ፤ አደርጋለሁን ማለትን ወጥ አድርጎ ያሳድገዋል። ብቃትን መሥራች ነው። የሚሰጠው ሐሴት ደግሞ ሌልኛ ነው። ይህን ሐሤት እቀወማለሁ ካለ የጠ/ ሚር ቢሮ ከራሱ ጋር ለመጣላት መንገድ ጀመሯል የሚያሰኝ ነው።

ሌላው ጎንደር ጠረፍ አካባቢ ነው። ለዳር ደንበር መከበር በሁሉም ቦታ ተከፋይ ወታደር አሰማርቶ የኢትጵያ መንግሥት አይችለውም። ህዝብን ማመን ያልቻለ መንግሥት በምርጫ ነገን አስተዳድራለሁ ለማለት ከባድ ነው። አሁን እኮ ጎንደር ሊታመን አለመቻሉ አንድ ሁለት ብዬ መዘርዘር እችላለሁ። ልንታመን አልቻልነም ለዛውም ዛሬ? ጎንደር ስንት ጊዜ ለመታመን ስንት ጊዜ ዳግሞ ያምጥ? ለለማ ለገዱ ለአብይ መንፈስ እኮ ሽንጡን ገትሮ ብራና ላይ የሞገተው ጎንደር ነው። ሥርጉተ ሥላሴ እኮ ጎንደሬ ናት። እኔ ለማዋያን ነኝ ብላ የቀራት ሊሂቅ፤ ድርጅት፤ ጋዜጠኛ፤ ሚዲያ፤ ተንታኝ የለም። ራሷን ማግዳ ፊት ለፊት ሞግታ የረታችው አንስት ብዕረኛ እኮ ጎንደሬ ናት። ትናንት ወቀሳ እዬለቀመ ፖስት ሲያደርገው የባጀው ሚዲያ ሁሉ ዛሬ እያዬንው ነው። መጠለያ ምንም የሌለው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ያለ ባተሌ ሴት አንድን አውራ ድርጅት፤ አንድን ገናና መንፈስ ትክክል አይደለህም ብሎ መሞገት በራስ ላይ ቤንዚን ማርከፍክፍ ነው። አንድን ቅን እሳቤ ውጪ አገር ደግፎ መውጣት በጠቅላላ ህይወትን መቃብር ቤት መላክ ማለት ነው። ጥቁር ከተባለ ጥቁር ማለት፤ መላዕክታኑ ሲቀበሉት መቀበል፤ ሲያወግዙት ማውገዝ፤ ያወገዙት መልሰው አከብሩ ሲባልም ማክበር። ህሊና አልጠፈተረልህም ነው ዘመቻው። ከሰውነት ውጪ። ከዚህ ማዕቀፍ ያፈነገጠች መንፈስ ድራሹን ነው የሚጠፋው። እስኪ የእኔን ጹሑፍ ከሳተናው ውጪ ማን ፖስት ያደርገዋል? ማንስ ሊንክ ያደርገዋል? አስተያዬት ሚዲያ ላይ ስተው እንኳን ድምጼን አይደፈሯትም። 

አንዲት ትንሽዬ ወቀሳ የዕድሜ ልክ ጦስ ነው፤ አይደለም ለወራት እንዲህ የዘለቀ ፍልሚያ ቀርቶ። ተደግፈውም፤ ተደክሟላቸውም አያቀርቡም፤ እንኳንስ ግድፈታቸው ተገልጦ። አንዲት የቃል ድፍረት ለዛውም የንጉሣውያኑን ቅዱሳኑን በመነካካት ከተደመጠ ማህበራዊ ኑሮን በዘመቻ ውልቅል አድርጎ አውጥቶ እራስ ለማጥፋት እስኪያስወስን ድርስ ሊዘልቅ ይችላል ዘመቻው። ስውሩ ተዋጊ ቡድን ልክ እንደ ሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከመሳሪያው ጦርነት በላይ የሆነ ፍልሚያ ነው የሚያካሂደው። እና ይሄን ፈተና ግማድ ይሁነኝ ብሎ ለተቀበለ የጎንደር የአማራ መንፈስ እንዴት ክቡር ሆይ ቀዩ እንዲህ በመከራ ሲታመስ የአይዟችሁ መንፈስ ይጣ? ፈጣሪ አምላክ እኮ ለአንድ ቅን ሲል ምህረቱ የሰፋ እና የተንሰራፋ ነው። ብቻ የህሊና ጉዳይ ነው።

አንድ ዕውነት ልናገር ከዚህ ላይ። ሰናድግ ከዚህ በቀደመው የነገሥታት ታሪክዊ ትውፊት ቃና ጋር ስለሆነ ደረጃውን የጠበቀ ክብርን አክብሮ፤ አስክብሮም መኖር ከደማችን ተዋህዶ ነው የሚያድገው። ደረጃውን ባልጠበቀ ጉዳይ የክብር መሸጫ፤ መሸቀጫ እና መመቀጫ መደብር ውስጥ ዘው የሚል አብዛኛው ጎንደሬ የለም። ለዚህም ነው በውሳኔያችን ሆነ በአኗኗር ዘይቤያችን ለዬት ያልነው፤ በፖለቲካ ተሳትፏችን በርከት ብለን እምንታዬው ከዚህ የመነጬ ነው። „እነዚህ ጎንደሬዎችን“ የሚለውን አባባል አሉታዊ ይሁን አዎንታዊ ወደነው የእኛ ብለን የተቀበልን ዜጎች ነን። በውስጣችን የእቴጌነት፤ የጌትነት መንፈስ አብሮ የበቀለ ነው። ፈልገነውም ወደነውም ሳይሆን የቀደመ የንጉሣዊ አስተዳደር መንፈስ አዬሩ ራሱ ያወርሳል። ልኩን ጠብቆ ሲመጣ ልብ ይሸለማል፤ ከዚያ በላይ የሆነ ሲገጥም ደግሞ በመጣበት መንገድ በዝምታ ውስጥ ይመለሳል። ሲወዱን በእጥፍ ፍቅርን አሳምረን በፈርጣማ ንጽህና፤ በፍጹም ታማኝነት፤ በግንባር ሥጋነት መሸለማችን ብቻ ሳይሆን ሲጠሉንም የዛያን ያህሉ መራሮች ነን። ሰው ስንጠራም አርቀን አይደለም። በውስጣችን አደላድለን አስቀምጠን ተባዕትም/ አንስትንም ይሁን እናትዬ፤ እናት ዓለምዬ / አባትዬ አባት ዓለምዬ/ ብለን ነው። እስር ቤት ካቴና ላይ ብንሆንም ቀለሃን ፈርተን አናጎበድድም። በፍጹም። ይህ የውስጡ ሸማችን መለዮችን ነው። ላከበረን ክብርን ለመስጠት ንፉጎች አይደለንም። መታመን ከእኛ በላይ በማተብ መጥናት ከጎንደሬዎች በላይ ይህን የእዮር አደባባይ ይፍረደው? ሌላማ ምን ይባላል። እውነት ነው አዝኛለሁኝ። መቼም የወያኔ ሃርነት ትግራይ በእኛ ላይ ያለውን የበቀል እርምጃ በሚመለከት ብቻ ፍርዱን ፈጣሪ ይሰጠዋል። በጣም ገለማን። ሌላው በሰላም ተቀምጦ እንዲህ ሌት ተቀን ለቀን ያደረሰን፤ የራህብ መዳህኒትን፤ ክፉ ቀን ያወጣን ህዝብ በበቀል ባለማባራት መጨቅጨቅ? ሌላው እንዳለፈው ሁሉ ይሄም ያልፋል። ጠብታ እዮር ታንኳኳለች፤ ሌላው ቢቀር። ሁሉንም አድርገው አሁን ደግሞ ትጥቅ ፍታ? ይገርማል።

·         አቤቱታ አስራሦስት። የሦስት አገር ደንበረኞች ደማማዊነት - ደማምነትም።

ይሄ ከባድ ሊሆን ይችል ይመስለኛል ክቡር ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ። አፋር እና ኢሳ ወገኖቻችን ሦስት ቦታ መንፈሳቸው ተከፍሏል። ኢትዮጵያ፤ ጅቡቲ እና ኤርትራ። መቼስ አንድ ሰው ፊቱ ሦስት አይደለም ገጹ አንድ ነው፤ ቢያንስ አንድ ገጸ - አዳራሽ በቀደምቲቱ የሰው ግብር በከፈሉባት አገራቸው በአላዛሯ ኢትዮጵያ ሊኗራቸው ይገባል የሚል እምነት አለኝ። አላዛሯ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ሙሴ ከገኘች ዘንዳ። አሻራቸውን የሚያማክል ተቋም ወይንም ሃውልት ወይንም ሙዚዬም ወይንም አዳራሽ ቤታችን የሚሉት በስማቸው የተሰራ ሊኖራቸው የሚገባ ይመስለኛል ለድንቅነሽ ፍልቆች። በፈለጉት ጊዜ የሚከፍቱት የዬኔነት የባለቤትነት እልፍኝ ቢኖራቸው መልካም ነው። የመንፈስ ቆንሲላዊ ነገር። ብቻ የሦስቱን አገሮች አፋሮች መገናኛ የሆነ ነገር ህሊናዬ ይሻል። በመንፈሴ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል። ዝንጥል ብለው የቀረቡኝ ያህል ይሰማኛል። የኤርትራው፤ የጁቡቲው የኢትዮጵያው አፋር እና ኢሳ የመንፈሱ ማዕከል ክብርት ኢትዮጵያ ልትሆን ይገባል ባይ ነኝ። የዓለም መነሻም ነው። አፋርና ኢሳ ልቡ ከተፈጠሮው ሚስጢር የተነሳ ነው። ደሙን በገበረላት መሬቱ ሁለንትናዊ የወልዮሽ የውሉ ባድማ፤ ባዕት ሊኖረው ይገባል። የእኔ ይህ አለኝ የሚለው ለልጅ ልጅ የሚያውርሰው የወልዮሽ የቅርስ፤ የትውፊት፤ የባህል ማዕከል። አፋር እና ኢሳ የዕንቁ ብራሃናት ናቸው። የመንፈሳቸውን ልቅና ልናጣው አይገባም። የውስጣቸውን ውርስ ልናጠው አይገባም። ጽናት እኮ ናቸው። ክብሮቻችን ናቸው። ክብርነታቸው ግን ተነጣጥለው በሦስት አገር ሆነው ሳይሆና አንድ የመንፈስ አዳራሽ ሲኖራቸው ብቻ ይሆናል። እንደ ምልክት የሆነ ነገር። በዚያውም እግዚአብሄር ይስጣችሁም ነው። ፍቅር ጥሩ ነው። ያስውባል። ያፋፋል። ያለመልማል።

·         ቤቱታ አስራአራት፤

ክቡር ሆይ! ህይወት ሽራፊ የላትም። ህይወት መፈጠሪያዋም ጽንሱ ልጅ ሆኖ መውጫዋም በእናት ማህጸን ነው። ዛሬ ስላለችው ኢትዮጵያ በመንፈስ ደረጃ ሚዛን እናስቀምጥ ቢባል ከእርሰዎ በላይ መሆን ያስገምተኛል። 27 ዓመት ሙሉ በዛ ክብር እና ልዕልና ውስጥ ኢትዮጵያ አልነበረችም። ይህን በማድረግ በማስደረግ ህጋዊ ዕውቅና በመሰጠት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ሥልጣኑን ይዞ ሲመራ የነበረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ነው። ይህን ማንፌስቶ ለሥልጣን ያበቁ ታጋዮች ሃውልት ተስርቶላቸው፤ ተቋማት ተፈጥሮላቸው፤ የቀደሙት ተቋማት እነ ሆለታ ገነት ትውፊት ተሰርዞ ሁሉ ክብር እና ልዕልና ተጎናጽፈው „ክንፈ ሃይሎም“ የሚል ሥም ተሰጥቷቸዋል። ኢትዮጵያ ያለ ወደብ መቅረቷ ብቻ ሳይሆን፤ በምንም ሁኔታ ልዩነት የሌለው ህዝብ ሲለያይ አግባብ ባለው መሆን ሲገባው ለጉርብት እና እንኳ በማያበቃ ቂም አብቅሎ ነበር የተከወነው።„ባርነት ወይም ነፃነት“ ማነው የኢትዮጵያ ጉዳይ ወሳኝ እና አራጊ ፈጣሪ የነበረው ኤርትራውያን አልነበሩንም? አይደለም ትናንት የዛሬው መታመስ እኮ ይሄው ነው። በዬጊዜው ነቀርሳ የሚያበቅሉት እነሱው ናቸው። አገርም ተብለን በተደራቢነት ቀጥቅጠን እንደ ለመደብን እንግዛ ነው አሁንም የእቴጌ ኤርትራ ጉዳይ። የሆነ ሆኖ በሁለቱ መካከል የነበረው የአብሮነት ፍቹ ሽማግሌም ግራጫማ ያልነበረበት ነበር። ይህ የመንፈስ ስብራት ጥገናው ሌላ አጀንዳ ስለሆነ ልተዎው። ይህ የሥነ - ልቦና አንድነት እንዳይኖር የታታሩት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ባለሟሎች አሁንም ጀግኖች ናቸው። አሁንም ካሳ ይጠይቃሉ። አይጠግቡም። የተረከቧት አገር፤ ምድር ሁሉም ደሙን ገብሮባት፤ ወጣትነታችን ገብርንባት ነው። ኤርትራን በጥላቻ እና በቂም በቀል መንፈስ ያስገነጠሉ፤ ኢትዮጵያዊነት እዬተዋጉ ጥገቷትን ሲያልቧት የኖሩ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ቤተኞች የአርበኝነት፤ የጀግንነት ክብር ሲሳጣቸው የትግራይ እናት ማህጸን ልዕልት ሆናለች።

ልዑላዊነታችን አናስደፍርም፤ ኢትዮጵያውነታችን አይነካም ያሉ የኢትዮጵያ እናቶች ማህጸን ፍሬዎች በትግራይ በኤርትራ በጎንደር እና በወሎ በርሃ ላይ ቀርተዋል። መሬታቸውም ደም ተጎንጭቷል። ሥልጣኔያዊ ዕድገታቸውም አፈር ግጧል። መንፈሳቸውም 43 ዓመት ሙሉ በጦርነት እሳት ተቀቅሏል። የግድ የቀለሃ ጩኽት ብቻ አይደለም 27 ዓመት ሙሉም የግለት መከራን ተሸከምው እዚህ አድርሰዋል። እነሱን የወለደች እናትም እናት ናት የጀግና እናት። ይሄው ከ28 ዓመት በኋዋላ ኢትዮጵያ ተፈላጊ ሆነች አይደለምን? ታዲያ ለዚህ ግብር የገበረች እናት በቀደመው በደርግ ጊዜ ልጅሽ ጀግና ነበር ተብላ የጡረታ አበል እንኳን ታገኝ ነበር። ለአካል ጉዳተኞች „የጀግኖች አንባ ነበር“ ወላጅ አልባ ለቀረቱ „ህፃናት እንባ“ ነበር። ለዛ ዘመን ቦታውን ሁለቱንም ዕድሉን አግኜቼ አይቸዋለሁኝ። 

ዛሬ አውሮፓ ላይ የማዬውን ያህል እንክብካቤ ይደረግበት ነበር። ሃሳቡም የተቀደስ ነበር። ተተኪ ጀግና ትውልድን የፈጠረ ታላቅ ትውፊት ነበር። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከያዘ በኋዋላ ደግሞ የመጀመሪያው የበቀል ማወራራጃ ሆኗል። የአሁኑን ለውጥ የማይሹት ወገኖች ያ እንዲደገም ስለሚፈልጉም ነው። ሁልጊዜ በጀምላ ማፍረስ ሱስ ስለያዛቸው። ያ አልጠቀመንም። አሉታዊውም // አዎንታዊውም በቅርስነት ማስቀመጥ ከ100 ዓመት በኋዋላ አንድ ትልቅ የገቢ ተቋም፤ የቱሪስት ማዕከል ይወጣዋል። ተተኪዎችም የዛሬ 50 ዓመት ወላጆቻችን በዚህ ይጠቀሙ ነበር ይላሉ። ይማሩበታል። ይምኩበታልም። ወቅትን ይሞግቱበታል። ማቆዬት ማስቀጠል ልባምነት ነው።

ወደ ቀደመው ምለስት ሲሆን እነዛ ጥንድ ብቁ የአንባሳ ግርማ የነበራቸው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅርስና ውርስ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ተቋማት አዬር ሃይል፤ ምድር ጦር፤ ባህር ሃይል ወደ ክብራቸው የመመለስ ተግባር ታላቁ የኢትዮጵያዊነት አምደብርሃን ነው። ለኢትዮጵያ እናቶች መንፈስ ጽድቁስ ቀርቶ በወጉ በኮነንኝ ሆኖ ያም ቀርቶ ልጅሽ ጀግና ነው ልትባል ግን ዛሬ ይገባታል። መንፈሷ ከእስር ሊለቀቅ ይገባል። ይሄው አሁን እኮ ምልሰቱ ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል፤ መዳኛችን እሱ ብቻ ነው አይደል? ስለዚህ ሻብያና የወያኔ ሃርነትን ሲታገሉ የነበሩት የንግድ ድርጅቴ ቀረ ብለው፤ የሸቀጥ ካንፓኒ ከፍተው ያን ለመቸብቸብ የገብያ ፍለጋ ለዝርፊያ አልነበረም። ያን ገናና የሰው ልጅ መገኛ የሆነው ቡኒ አፈር ከነ ሙሉ ክብሩ ለማስቀጠል ነበር። የአድዋን ድል ተልዕኮ፤ የባድመን ድል ተልዕኮ፤ የጅጅጋን ድል ተልዕኮ ይዘው ነው ከዚህ ውጭ ሌላ ዓላማ አልነበራቸውም ሰማዕት ጀግኖቻችን። ቁመታቸው ለግለግ ብለው የወጡ ከ14 ዓመት ጀምሮ ያሉ ወጣቶች ሁሉ ራሳቸውን የማገዱበት ለአገራቸው ሉዕላዊነት ሲሉ ብቻ እና ብቻ ነው። 

ስለ እነሱስ፤ ስለ አዛዦቻቸው፤ ስለቤተሰቦቻቸውስ፤ ስለ ትተዋቸው ስላለፉት ልጆቻቸው ጉዳይስ ከቶ አላዛር ኢትዮጵያ ምን ታስብ ይሆናል? ሁላችንም ወንድሞቻችን አጥተናል። ቤተሰቦቻችን ገብረናል። ወላጆቻችንም ማህጸናቸው ከስሎ ቀርቷል አፋ ቤት፤ በረንቱ ምጽዋ ወዘተ። ጀግና ወልደው ግን ደመ ከልብ ሆነው ቀርተዋል። ስለ ታላቋ ትግራይ እና ስለ ታናሿ ኢትዮጵያ የታገሉት ሰማዕታት፤ ስለታላቋ ኢትዮጵያ እና የዓለም ዘር መፈጠሪያ ስለሆነው ኢትዮጵያዊነት የታገሉት „ባንዳ?“ የተገለበጠ ነገር ነው። ይሄ ቀን ባይመጣ አቅጣጫችን የት እንደነበር ልብ ያለው፤ ህሊና የሰራለት ሰው ያውቀዋል። ቢታሰብበት አይከፋም። እውነት ለመናገር ሳይንስ ነው የተቀበረው። ሰራዊታችን ምጡቅ ጥበብ ነበረው የፍቅር ቤትም ነበር።

·         አቤቱታ አስራአምስት።

ኢትዮጳያ የገበሬ አገር ናት። ሥራ የጀመርኩት በጁኔዬር የገበሬ አደራጅነት ነው። ህሊናዬ ውስጥ ሙሉ የገበሬ ቅዱስ መንፈስ አለ። ከማንኛውም ማህበረሰብ ገበሬዎችን እወዳለሁኝ። መቼም ወጣት እያለሁኝ በሁለመናዬ ንቁ ነበርኩኝ፤ እናም የካቲት 66 ፖለቲካ ኢንስቲቱዩት ተስፋ ከተጣለባቸው ተማሪዎች አንዷ ነበርኩኝ፤ እና ተመርጬ አንድ ትልቅ ግዙፍ ከሆኑ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሊሂቅ ዘንድ ተላኩኝ።  ከውይይታችን በሆዋላ ምን እናድርግልሽ የሚል ጥያቄ ቀረበልኝ። መቼም ሥርጉተ ጉደኛ ናት። „የሰው ፍላጎት ማለቂያ የለውም። እኔ ግን አንድ ፍላጎት ብቻ ነው ነው ያለኝ። ወደ ገበሬ አደራጅነቴ እንድመለስ ብቻ ነው እምፈልገው“ አልኩኝ። መላ ተማሪው ደረጃው ላይ ቁጭ ብሎ ይጠብቀኝ ነበር። „እሙሃይ“ ነበር ሥሜ ገበሬዎቼም የሚጠሩኝ „አሙሃይ“ ነበር። እና እናማ „ወደ ገበሬ አደራጄ መልሱኝ አልኩኝ ስል“ ሁሉም ክው ነበር ያለው። ሰፊ ዕድል ነው የነበረኝ። ተደግሞ የማይገኝ ዕድል ነበር። ከዛው ላይ የፈለግኩትን የማግኘት ዕንቁ ዕድል ነበረኝ። ሌላው ቀርቶ በቀለም ትምህርት የመቀጠል ፍላጎቴን ማሳካት እችል ነበር። ግን የከተማ ልጅ ገበሬን ያፈቀረች ሆኜ ተገኘሁኝ።

ገበሬ ይናፍቀኛል። ጠረኑ የውስጡ ንጽህናው እዮራዊ ነው እንደ ተፈጠረ። የአነጋገር ዘይቤው ሁለመናው ሽው ይለኛል። የኢትዮጵያ ገበሬ ከፖለቲካ ውሳኔ በብሄራዊ ደረጃ ከተገለለ እንሆ 27 ዓመት ሆነው። በፌድራል ምክር ቤቱ ውስጥ ገበሬን ከእነ ሙሉዑ ውስጡ የሚወከል ዕውቅና የለም። ይህ የገበሬ አገር ለሆነችው ኢትዮጵያ የፖለቲካን የግንዛቤ ደረጃ የሚያስገምት አመክንዮዊ ጉዳይ ነው። የአላዛሯ ኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት ከፖለቲካዊ ውሳኔ የተገለለበት ዘመን፤ በዘመነ አብይ አብይዋ ርእሰ አጀንዳ ሊሆን ይገባል። ገበሬን ለብሄራዊ መሪነት የማብቃት ጉዳይ። በኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሜቴ ገበሬዎች ነበሩ። በአባልነትም // በተለዋጭ አባልነትም። ገበሬው ማህበረሰብ ከአንጋገሩ ዘይቤው ጀምሮ፤ ብልህነቱ ለዛ አለው፤ የኢትዮጵያዊነት መንፈሱ በሙሉ አቅሙ ነው ያለው። የትውስት ያልሆነ፤ ቅጂም ያልሆነ አዲስ እና ወጥ አቅም ያለው ኢትዮጵያዊ ውበት ከገበሬው ዘንድ አለ። 27 ዓመት ሙሉ ጥቅም ላይ ያልዋለው የብልህነት አግባብ ለወደፊቱ ቢታሰብበት መልካም ነው። ለድምጽ ኮረጆ መሙያ ብቻ ሳይሆን ገበሬው የሚፈለገው ለአገር ፖለቲካዊ ተሳትፎም መሆን አለበት። ገበሬው ከነሙሉ መንፈሱ የተወከለበት የፖለቲካ ሚዛን በእጅጉ ያስፈልገናል። መኖር ከገበሬ ውጪ ህልም ነው። አስተማሪው እንዲያስተምር፤ ሃኪሙ እንዲያክም፤ ወታደሩ እንዲጠበቅ እህል ውሃ ያስፈልገዋል። ሰውነቱ ምግብ ካለገኘ አይሰራም የሰው ልጅ። ስለዚህ ገበሬን አልባ ህይወትም ነፍስም፤ ሥልጣኔም እድገትም አይታሰበም። „የፌድራሊዝም“ ሥሙ አይደለም ህይወትን ያቆዬው። ሰውን ቁሞ እንዲሄድ የሚያደረገው በሬ ሆይ! ነው።

ገበሬ ንጽህናው ተመሳሳይ ነው የህሊናው ንጽህና ማለቴ ነው፤ በመንደር ምስረታ ተመክሮ ጎጃም እና ሽዋን አውቀቸዋለሁኝ። በሥራ አርሲ እና ጎንደርን አውቃቸዋለሁኝ። ለህክምና ሄጄ በቀዬሁባቸው ወቅትም ጋሞ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎችን አካሎቻችን አስጎብኝተውኛል፤ የትም ቦታ ይኑር ይህ ማህረሰብ ቅዱስ ነው። ለጋስ ነው ገበሬ። ተፈጥሮን ወዳጅ ነው ገበሬ። ለተፈጥሮ መብት ተሟጋች ነው ገበሬ። በዛሬው ቋንቋ ተፈጥሯዊ የተፈጥሮ አክቲቢስት ነው የኢትዮጵያ ገበሬ። ለነፍስ ገበሬው ከእነ ጣዕማዊ ለዛው ንጹህ አዬር ነው ኦክስጅን። እግዚአብሄርን እማመሰግነው ባለቅኔው ጠ/ ሚር የገበሬ ልጅ በመሆነዎትም ጭምር ነው። ጠረኑ በክቡርነተዎት ውስጥ አለ ተፈጥሯዊነት። አፈርን ዝቅ ብሎ ጠረኑን ማሽተት። የአፈርን ጠረን መማግ። ያ ነው የሰውነት ምህዋሩ።

ስለሆነም በመጪው የምርጫ ዘመን ማሻሻያ እርምጃዎች ሁሉ ገበሬው በፖለቲካ ውሳኔ ላይ እኩል የሚሳተፍበት መዋቅራዊ አቅም ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል። ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ከተማ ለከተማ ሳይሆን አቀበት ቁልቁለቷን፤ ዳጧን፤ ክምር ላይ - መደብ ላይ - መሬት ላይ - ጀንዴ ላይ - ጠፍር አልጋ ላይ - ቆጥ ላይ ማደሯን፤ ወንዝ ሲሞላ ሙላትን ተጋፍቶ ተሻግሮ፤ ውሃ ጥሙን ችሎ ሞጥሮ ታግሎ የገበሬ ውክል አካል የማውጣት ግዴታ አለባቸው። ለነገሩ ማብቃትን በ27 ዓመት ውስጥ እኔ ያዬሁኝ ከኦቦ ለማ መግርሳ እና ከዶር አብይ አህመድ ብቻ እና ብቻ ነው። አቅማቸውን ሲለግሱ በቅንነት ነው እማዬው። በሶሻሊዝም ብክል ዕሳቤ ደግሞ አቅምን መታገል፤ አቅም እንዳይበቅል ማጫጫት ነው። ተቀብረን የቀረነውም በዚኸው ዕሳቤ ነው። ስለዚህ መጪው የምርጫ ፉክክር የገበርዲን እና የከረባት ብቻ ሳይሆን የቁምጣም፤ የደንቀዝ ጫማም ተላባሽ ንጹህ ዜጋ እንደሚሆን ምኞቴ ነው።

·         አቤቱታ አስራስድስት።

ጣና ሆይ! ጣና ሆይ ይህ ጥቃት የደረሰበት የምናዕቡ ርቅቱ ዘመን ተርጎሞ የማይዘልቀው ዴርቶ ጋዳ የፈጠረው ስጋት ነው። ደራሲው ምስባከ ወርቁ በቁሙ እያለ ባዶውን እንዲሆን ያስደረገው ሚስጥርም ጣና ሆይ! ነው። ጣና በዝምታው ወስጥ መንፈስ ቅዱስ የሰፈነበት ስለሆነ የተበዬነበትን ፍርድ እዮር ይወስነዋል። ጣና እኮ የአፍሪካዊነትም መለያም ነው። ግን ጣና በመንግሥት ደረጃ ባለቤት አልባ መሆኑ እንደ አባይ ለቤንሻንጉል ተሸልሞ የአማራ ሥነ - ልቦና መቀጠቅጫ ሊሆን  ስላልተቻለ ስውር ጥቃት ተፈጽሞታል። በድንበርም ስለሌለ በወረራ እንደ ወልቃይት እና ጠገዴ፤ እንደ ራዕያ ሙሉ መዳፍ ውስጥ ጠቅልሎ ማስገባት አልተቻለም። መቼ ነው ስለ እንቦጭ አረም መንግሥት የእኔ ነው የሚል የተደራጀ የጥበቃ ተግባር ለመተርጎም ሥራ ጀመረን የሚለው ዜና የሚሰማው። በግለሰቦች ጥረት ይህን መከራ ጣና ሆይ! አይሸገረውም? አጀንዳው ዝርዝር ውስጥ ቢያዝ መልካም ነው። ከተፈጥሮ መከራዎች ሁሉ የከፋው የጣና ሆይ! መከራ ነው። „ጣና ኬኛም!“ መንፈሱ ለመላ ዓለም የጭንቀት መድህን ስለመሆኑም ሚስጢረ ሥላሴ ነው - ለእኔ።፡

·         አቤቱታ አስራሰባት።

ክቡር ሆይ ምህረት የአኩልነት መርህ ነው። በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ስለተሳተፉት ወገኖቼ ጉዳይ።

በ2008 እ.አ.አ የዓለምን የሴቶች እኩልነት ብሥራት የዓዋጅ መናህሪያ በሆነው በዴንማርኩ ኮፕን ሀገን ለተከታታይ ቀናት የኢትዮጵውያን ህዝባዊ የተቃውሞ ስልፍ እና ህዝባዊ ስብሰባ አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን ወደ እዛ በህብረት ተጉዘው ነበር። እኔም ከሲዊዝ ወደ ዴንማርክ ሄጄ ነበር። ሴታዊት ስለሆንኩኝ ዕድሉ የሰማይ ነበር። ዴንማርክን ማዬት መጋቢት 29 ቀንን ማዬት ስለሆነ። የዴን ልጆች አዘጋጆች ስምንት ብቻ ነበሩ። ስለሆነም ዴኖች በሁሉም መስክ ማገዝ ይገባ ነበር። ታሪክ ስለሆነ መነገር አለበት። ሲውዲኖች ጤፍ እንጀራ ተሸክመው ነበር የመጡት። እኔ ደግሞ ፆም ስለነበር ለሚጾሞት ተልባ እና ሰሊጥ እንደ አባት አደሩ አዘጋጅቼ፤ ለፆም መባያ የሚያዘጋጅ ቁልቲ እና ጤፍ እንጀራ እኛ ስሌለን እኛው የምናዘወትረውን አገርኛ እንጀራ ጋግሬ፤ የተለያዩ ፓስተሮች አዘጋጅቼ፤ በራሪ ጹሁፎችን አሰናድቼ ከበርን የአንድነት ፓርቲ የተላከልኝን የክብርት ብርቱካን ሜዴቅሳ በጨርቅ ላይ የተሰራ ስፊ ፖስተር ይዤ ነበር ወደ እዛ የተጓዝኩት። ለዛውም ያን ጊዜ ስደተኛ ካንፕ ውስጥ እኖር ስለነበር በረራዬ ከንጋቱ 6 ሰዓት ስለነበር ቀድሜ መገኘት፤ ስለነበረብኝ ቢያንስ ከንጋቱ 5.30 እዛ መድረስ ነበረብኝ፤ ስለዚህ እጅግ የማከብራቸው ቤተሰቦች ዘንድ ፈቃዳቸውን ጠይቄ እዛ ተሸኝቼ አደርኩኝ። ጥዋትም ዙሪክ እውሮፕላን ማረፊያ ወስደው አደረስኙ ከእነ ጓዜ። ታህሳስ መጨረሻ ስለነበር ክረምት ነበር። በረዶው ቁመት ይውጣል። ተራራ ነበር።  

ያን ጊዜ የሄሮድስ መለስ ዜናው G20 ላይ ለመገኘት እዛው ይገኙ ስለነበር ነው ከዛ አውሮፓ ውስጥ የምንኖር የነፃነት ራህብተኞች የተገናኘነው። ከካናዳ የመጣ ወንድም ሁሉ አግኝቼለሁኝ። ኦንግውያን እና ኡጋዲያዊያን ለብቻቸው ነበር ሰልፍ ያዘጋጁት። ዱላው ግን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕወ መንግሥት የጭካኔ እና የሰብዕዊ መብት ረገጣ ላይ ነበር። ቀን ሰላማዊ ሰልፍ ምሽት ስብሰባ ነበርን። ለዛ የአዳራሽ ዝግጅት ይዤ ከሄድኩት ፖስተር ውስጥ ከአዘጋጆች ጋር ስንመካከር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉ መኮንኖች የእነ ኮ/ አሳምነው ጽጌ ፓስተር ምስላቸው ያለበት አልተፈቀደልኝም ነበር። የተፈቀደልኝ የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እና ኢትዮጵያ ነክ ጉዳዮች ነበር። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ለውጪ ባለሃብቶች መሬቷ ልክ በዘጠኝ አስተዳደር እንደ ተቆራረጠችው ሁሉ ምን ያህል መሬት እና ፍሰት እንዳለው አመላካች የሆነ በትልቁ የተሰራ ፓስተር ነበረ። አሁን ሳስበው እነዚህ ወገኖች የከፈሉት መስዋዕትነት ቤተሰቦቻቸው ብቻ እንዲሸከሙት የተወሰነባቸው ዛሬ ሳይሆን ቀደም ብሎ ነው ማለት ነው። ሚዲያ ላይ ስለነሱ ማንም ማንም ብሎ አያውቅም። 

እኔም ያን ጊዜ ምን ያልገባኝ ነገር አለ ብዬ በዝምታ ነበር ያልፍኩት። የእኔ ጉዳዬ እስረኛ ከተባለ መከረኛ ነው። እስረኛ የሁላችን ጉዳይ ነው። በዬትኛውም ወገን ቢሆን እስረኛ በውስጡ የነፃነት አርበኛችን ነው የእከሌ ተከሌ ሳይባል። ስለዚህ ሁሉንም የሰው ልጅ መብት መከበር የሚታትር ሁሉ እኩል ሊያው ይገባል ነው የእኔ አምክንዮ። ስለዚህም ነበር እኔ ለአረናው አቶ አብርሃም ደስታ፤ ለድምጻችን ይሰማ ሰትጋ የቆዬሁት። አረና ያለውን አቋም አሳምሬ አውቃለሁኝ። እንዲታስር ግን አልሻም። ፖለቲካ ሃሳብ ነው። ሃሳቡን በገብያ አዳራሽ ማቅናት ነው። ስለዚህ ይህ የገብያ አዳራሽ እኩል ሜዳ ሊኖረው ይገባል። ገዢውም ሳይገደብ ደንበር ሳይሰራለት ህዝብ የፈለገውን መርጦ ይግዛ ነው የእኔ ተጋድሎ። ዛሬም ይሄው ነው። ስለዚህ ለእኔ እነዛ የኢህድግ መኮንነኖች ጀግናዬን ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙን አክሎ ሃሳብ አላቸው ይደመጡ ነው። ዘግይቶ አንድ ቃለ ምልልስ ሳዳምጥ እነሱ ታግለው ሥልጣኑን ግን ለግንቦት 7 ውሰድልን፤ ሃላፊነቱን ተሸከምልን በሚል ሙሉ ድርድር እንደ ነበር አዳምጫለሁኝ።

መቼም ይሄ ቅንነት ዛሬ ትንግርት የምንላቸውን የምዕት ቅኔውን ከአቶ ለማ መግርሳ ጋር የሚተካከል ፍጹም ጨዋነት ነበር። ደግነቱ የታገሉላቸው ሁለት ድርጅቶች ቀዳሚው ኢህአዴግም፤ ሁለተኛው ግንቦት 7 ለእነሱ የሰጠው ዕውቅና ኖረው በቁማቸው አይተውታል። ጥያቄዬ የአብይ መንፈስ እነዚህን መከረኞች እንዴት እያስተናጋዳቸው ነው? ከሁለቱም አልሆኑም እኮ። የእነሱ ያን ያህል መከራ መቀብል የውሽማ ሞት ሆን ነው የቀረው። እንግዲህ ከአማራ በመፈጠራቸው ምክንያት በመሆነ ነው። ሌላ የሂሳብ ስሌት ማቅረብ አይቻልም። ይህን የምለው የኢህአዴግ አካል የነበረው አሁንም በዛ መንፈስ ነኝ የሚሉት ኮ/ ደመቀ ዘውዴም አክብሮት እና ዕውቅናም የውሽማ ሞት ዓይነት ነው። ይህ ነገን ያበረከትልን? ይህ የወጣቱን ሥነ - ልቦናዊ ተስፋ እኩል ሚዛኑን ሊያስጠብቅ ይችላልን? አይመስለኝም። አብሶ  የአማራ ወጣት ዛሬ እንደ ተለመደው በተለመደው መንገድ ከሆነ ነገም ሌላ ድቀት ነው። በተሎ ይህ ነገር እልባት ካልተሰጠው መከራው ከባድ ነው።

እነሱ እኮ የመፈንቅለ መንግሥቱ መኮንኖችን ገፃቸውን እንኳን ማዬት አልተቻለም በሚዲያ? ድምጻቸውን መስማት አልቻልነም። ጀግኖቼ ስለሆኑ ላያቸውም፤ ላደምጣቸውም ይናፍቁኛል። ምነው እንደዚህ ተገለሉ? ስለምንስ? በህጋዊ በአደባባይ በቅርቡ እንኳን ጨለንቆ፤ ወልድያን፣ ሙያሌን የጨፈጨፉት የዓለም ሚዲያ የሚያወቀው እዬተሸለሙ፤ ተሰብሰብው ውይይት እዬተደረገላቸው፤ የሚፈልጉትን እያሰሩ፤ እዬደበደቡ፤ ለተሻለ አገራዊ መግባባት የታተሩ፤ ለዛውም ሥልጣን የሚረከብ አቅም ሲያፈላልጉ ለነበሩ ፍጹም ቅን፤ ፍጹም ንጹህ፤ ፍጹም ቅዱስ መኮነኖች ይሄ ይገባልን? ይህ ነገን አያበረክትም። በታሪክም ደረጃ ግማሽ ሹሩባ፤ ግንጥል ጌጥ ያደርገዋል ለታሰበው የፍቅር የአብሮነት ጉዞ። እነኝህ መከንኖች እኮ ከአማራ እናት እንወለድ ብለው ለፈጣሪ አላመለከቱም። ተነጥለው በተለዬ ሁኔታ የተገለሉበት ሚስጢር አማራነታቸው ብቻ እና ብቻ ነው። የአማራ እናት ሌላም መከራም አለባት። አማራ ሚስት ሌላም ፍዳ አለባት።

ወደ ቀደመው የኮፐን ሃገኑ የዴንማርክ ስብሰባ ስመለስ በአጋጣሚው እዛ የተገኙ ወገኖቼን ሁሉ ማመስገን እፈልገለሁኝ። ለዚህ ቀን ነበር የተጉት እና። ወቅቱ በረዶ ነበር በአውቶብስ በጋራ ሲጓጓዙ የሚደርሰው አይታውቅም ነበር። በአውሮፕላን የሄድነውም አንድ ወንድሜን ከጄኔባ እዛው ዴን አውሮፕላን ማረፊያ ቀድሞኝ እኔን አግኝቻለሁኝ፤ እዛው ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም ነበር፤ የአውሮፕላን አደጋ ቢገጥም ኖሮስ። ቅዝቃዜው እጅግ ከባድ ነበር። የዘላለም በሽታ ይዤ ነበር እኔ በግሌ የተመለስኩት። እግሬ አብጦ ነበር የተመልስኩት። አሁንም እንደ አበጠ አለ። ግን ያ ለዛ ያለው ፍቅር፤ አክብሮት በቀደመው ፓርቲዬ በኢሠፓ ከነበረው የሚተካከል ቤተሰባዊ ስለነበር ለተደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ እጅግ አድርጌ ሁሎችንም ተሳታፊዎች አመስግናለሁኝ - አዘጋጆቹን የዴን ኢትዮጵያዊ አንበሶችንም። 

ሴቶች ሌሊት ምግብ እንሰራለን ሲዊዲኖች መሪ ነበሩ፤ ወንዶች ሳንዱች ያዘጋጃሉ ቀን ቀን ሰላማዊ ሰልፍ እንደርጋለን። ልክ አድዋ ላይ እንደሆነው ተንቀሳቃሽ መሰናዶ ነው የነበረው። በጋራ ነው የሚታደረው። እዛው ተራራ ከሰራው በረዶ ስር ሆነን ስንቁም፤ ፍቅሩም፤ የወል ራዕዩም መከራውን መጋራትም ሁሉንም ተቀበለን። የሲዊዝ አንድነት ድጋፍ ሰጪ ድርጅቱ ጠንካራ ነበር። ለእኔ የነበራቸው ድጋፍ እና ፍቅርም በስደት ዘመኔ እማረሳው ነው። በአጋጣሚው የኢትዮጵያ የታሪክ አካል ናቸው እና ማውሳት ግድ ይለኛል። አግዘውኛል። እርድተውኛል። ሃሳቤን ምክሬን ጠይቀዋኛል። እንደ ሰውም ቆጥረውኛል። አሁንም ሙግት ላይ ያለችው ያችው ሥርጉት ለኢትዮጵያ ናት እና ዕውቅናቸውን መሬት ላይ አንጥፌ በተስፋ ቆራጭነት ካሊም ተከናንቤ፤ መገለሌን ስላለስቆዝምኩት ትክክለኛ ቦታ ላይ የቆመ አቅም የነበራቸው ስለመሆኑ ሊያገናዝቡት የሚችሉበት አጋጣሚ ነው። የሥርጉተ ለማውያን ውሳኔ የደረሰበትን የዕድገት ደረጃ በማዬት ሥርጉተ ማን ናት የሚለውን ቀድመው መልስ ስለሰጡበት የፋክት ሰው ስለመሆናቸው ሊያረጋግጡበት፤ ሊያመሳክሩበት ይችላሉ። ድውያኑ ስለምን እንደ ታገሉኝም ያረጋግጡበታል። ግን ዘመን መልካም ነው አሸንፌያቸዋለሁኝ - እኔን ሲቀናነቀን፤ አቅሜን ሲያስግደብ፤ ሲሳድደኝ የነበረውን መንፈስ ሁሉ ባዶውን ቀርቷል። ወና! ከዚህ በላይ የምሥራች ነባቢቴ አትሻም። ተጋድሎዬ በመልካም ዕንቁ ተቋጭቷልና።

ወደ ቀደመው ነገር ስመለስ በመፍንቅለ መንግሥቱ ስለተሳተፉት ጀግኖቼ ዕወቅና እና ውለታቸው ልክ እንደ ኢትዮጵያዊው ጎንደሬ ሜጄር ጄኖራል ፈንታ በላይ እና እንደ ሌሎቹም አስታዋሽ አልባነቱ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል። እነኝህ ወገኖችም እናት አላቸው። የኢትዮጵያ እናቶች አኩል መታዬት ማለት ልጆቻቸው ለከፈሉት መስዋዕትነት እኩል ዕወቅና እና ክብር መለገስ ማለት ነው። ይህ ተዛነፍ አካሄድ መስተካከል ካልቻለ ቂም እዬቋጠረ ሄዶ አንድ ቀን ደግሞ ይፈነዳል። እቴጌ ጣይቱ ብጡል ዘብርሃነ ኢትዮጵያ ሲገለሉ እና የቁም እስር ፍርድ ግዞት የተካሄደባቸው የራስ ተሰማ ናደው የአድማ ቅኝት ምልሰት እንዳደረገ እዬተሰማኝ ነው። አማካሪዎች እነማን ናቸው የሚል ዘለግ ያለ ቅኝት ላይ ነኝ? የአማራ ተጋድሎ መሪ ጀግና አንበሳ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ተገሎ፤ ኮ/ አሳምነው ጽጌ ተገለው? ምንድን ነው ነገሩ? ከቶ በቅኑ አብይ መንፈስ ወስጥ ማነው ይህን ስርክራኪ የቆዬ ቁርሾ ድርሻ እንዲያገግም ሚና እዬተጫወተ ያለው? ሁለት ሰዎችን እጠረጥራሁኝ። ለጊዜው ግን በዝምታዬ ውስጥ ይቀመጡ። ይህን ጉዳይ ኦቦ ለማ መግርሳ በተለይም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሥራዬ ብለው ሊከታተሉት ይገባል። በማን ደም ነው ይሄ ሽግግር ነፍስ የዘራው? ከደም ግብር በኋዋልስ ደም የገበረው የህዘብ ዕውቅና ደረጃው የት ላይ ነው ያለው? ወደፊትስ? „ልብ ያለው ሸብ“ ይላሉ ጎንደሬዎች። …   
   
·         አቤቱታ አስራስምንት። ከሆድ ውስጥ ስለታሰረው የግማድ ገመድ ።

ክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ! ይህ መንፈሴን እንደ ዱባ የቀረደደው ጉዳይ ነው።

ዴሚክራሲ ጥሩ ቃል ነው። ይጥማል። ይመስጣል። ያጓጓል። እርስዎ በአዋሳው ጉብኝተዎት ላይ ስለ አውሮፕላን ማረፊያ ተጨማሪነት ሲጠዬቁ „ በቅርብ ቀን አይመስለኝም፤ አያለሁ ብዬ ሄጄ ሳላዬው ከቀረሁስ?“ ብለው ነበር። እኔም እላለሁኝ በቀላል ቃል ልቤ የተቀረደደበትን የሹመት ሁኔታ መግለጽ አውዳለሁኝ። ያልታዬኝ ነው ብዬም ስለማስብ።  በወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚብሄር የመሪነት መንፈስ ዴሚክራሲን አይመስለኝም። አይታዬኝም። ተስፋን መሠረት ለማስያዝ ስላልመሰለኝ። ለአላዛሯ „ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ያስፈልገናል ይገባናልም“ ያሉትን በባዕለ ሹመተዎት ጊዜ አሁን በሹመት አሰጣጡ ላይ „አያስፈልግም በተለይ በዴሞክራሲ አግባብ አይገባንም፤ ከወያኔ ሃርነት እጅግ ከዛገ መንፈስ መውጣትም የለበትም፤ ለዛውም ሌብነት ደረቱን ገልብጦ ዴሞክራሲን ይምራ፤ ከማረተው የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ዝገት ጋር እንቀጥል“ የሚል ውሳኔ ቀጣይነት ታትሞበታል ባይ ነኝ። ስለዚህ ባለራዕዩ ዴሞክራሲ አልጋ ላይ ውሏል። ታሟል። 1% እንኳን ተስፋ የለውም። / ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ መሆን? የዚህ የመኖር ጉሮሮ ወሳኝ ሰው መሆን ነው? የሰውነት መሪ መሆን? የነፃነት አውራ ልሳነ ሙሴ መሆን? ለሞት ሁለተኛ መግደያ የተሰናዳለት ግዞት ነው። ግዞት እና ሞት። ሞት እና ግዞት በጣምራ።

ፈጣሪ ሰውን ፈጥሮ አፍ ባይሰራለት ኖሮ ምግብ የሰው መዳህኒት ይሆን ነበርን? ይሁን አፍም ይሥራለት እንበል፤ መውጫ ባያበጅለት ሰው አይፈነዳም ነበርን? አሁን ወይ አፍ ወይንም የመጻዳጃ አካል መፈጠር የለበትም ነው የዴሞክራሲ ህልም  በአልዛሯ ኢትዮጵያ። ዴሞክራሲ መጀመሪያ ሰው ሆኖ መገኘት እንጂ ጫካ ሆኖ መገኘት አይደለም። ለነገሩ ለእኔ ከዴሞክራሲ በላይ ነው ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት። ሴት መሆን ወለደችም አላወለደችም አንዲት ሴት // ሴት የሚለውን መስፈርት ለማሟላት „እናት“ የሚለውን እዮራዊ ጸጋዊ የፈጣሪ ቅብዕ አላት። ነገር ግን መፈጠሩ በራሱ በመፈጠሩ ውስጥ እንዲኖር ካልተፈቀደለት ጨለማ ነው። ጨለማ በህሊና ውስጥ ሲከትም እንደ ማለት። ህሊና በጨለማ ሲዋጥ በእዝነ ህሊና ሲታሰብ ሰው የሚለው ስብዕን ማሰብ አቁሟል ማለት ነው። ጨለማነት ሰውነት ሆኖ የዴሞክራሲ መሪ?!

ክቡር ሆይ!

ግን ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር እንደ ሰውም እንደ ሴትም ማዬት ይቻላልን? ትግሬ ስለሆኑ አይደለም። እኔ ምኞቴን ብነግረዎት አውስትራልያ ፐርዝ የሚኖሩት ቅዱስ የትግራይ ሰው በቀጠታ ሹመት አቶ ገ/ መድህን አርእያ ዶር ሙለቱ ተሾሞ ወርደው እሳቸው ፕሬዚዳንት ሆነው በቤተ መንግሥት ማዬት ይናፍቀኛል። ሰብዕናቸው የዕውነት ሥነ - መዘክር ስለሆነ። ሄሮድስ መለሰም ዜናዊም ቢሆኑ ትግሬ መሆናቸው እኔን ቅንጣት ታክል አይረብሽኝም። እኔን ፈጠረኝ የምለው ታቦቴ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ ጉራጌ ነው። ሰብዕናቸው ነው የእኔ መለኪዬ። ስለሆነም እሳቸው እራሳቸው ወ/ሮዋ ደም በተነከረ እጃቸው ዴሞክራሲን ያህል፤ ሰብዕዊነትን ያህል ግዙፍ የመንፈስ ሃላፊነትን፤ እናትነትን ያህል ቅዱስ ነገር እሸከማለሁ ብለው መረከባቸው ገርሞኛል። ሰብዕናቸው ይህን ታሪካዊ ድርሻ የመሸከም አቅም / አቅልም በህልሙም ሊያስበው አይገባም። እንደ አቶ ደመቀ መኮነን እራሳቸውን ከጠ/ ሚር በፈቃዳቸው እጩነት እንዳገለሉት ብልህነት፤ እንደ ቀድሞ ጠ/ ሚር ሃይለማርያም ደስአለኝ በፈቃዳቸው መልቀቅን እንደ ወደዱት ብሩኽነት አልመጥንም ብለው ሥልጣኑን መመለስ ይኖርባቸው ነበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር። ሰው ከሚለው ተፈጥሮ ጋር ለመተዋወቅ የማይፈቅዱ፤ በተዘጋ መንፈስ ውስጥ የሚኖሩ ዝምብሎ ሰው ናቸው። ፎቷቸው እኮ ይናገራል እንኳንስ ታሪካቸው። 
  
የተስፋዬ ክቡር ሆይ!

በዚህ ሹመት ተስፋችን መሞት ብቻ ሳይሆን የሥነ - ልቦና ጥቃትም ደርሷል። ከእስር የተፈታውን የአቶ አንዶአለም አራጌን ፎቶ እና ናዚዝም ሲያበቃ ከእስር የተፈቱትን አትሜ አስተያዬሁት አንድ ነው ተመሳሳይ። አሁን እኔ ብነግረዎት አርበኞቼን፤ ጀግኖቼን አቶ አንዱአለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እያዬዋቸው ማድመጥ አልችልም። መጻፍ አቅቶኝ አይደለም ከተፈቱ በኋዋላ እማልጽፈው ሳሰባቸው ዕንባዬን መቆጣጠር ስለማልችልም ነው። ኢሜል እንኳን በእነሱ ጉዳይ የማከብራቸው ወዳጆቼ ሲልኩልኝ ከአመሰግናለሁ ውጪ ቀጥዬ መጻፍ አልችልም። እነኝህ የነፃነት አርበኞች እኮ ልጅ አላቸው። አሁን በቅርቡም አርበኛ አንዳርጋቸውን ጽጌን ሳይ ከሙሉ ሰብዕናቸው ህሊናቸው በነበረበት ቦታ መሆኑን የሰማይ ታምር ነው። ቆራጣ ተስፋ ህሊናቸው እንደ ተፈጥሮው እናገኘዋለን ብዬ አስቤ አላውቅም። ከድንቅ በላይ ነው። ስንብት ነበር አማስበው። አካላቸው ግን እጅግ ተጎድተዋል። ሞልቼ ለማዬት አቅም አንሶኛል። ይህ በህፃናት አእምሮ ውስጥ በምን መልኩ ሊቀመጥ እንደሚችል ፍች የሌለው በትረ ጉዳይ ነው። እኔ እራሴ እንዴት አድርጌ ልያቸው? እኔ ፎቶ ውስጡን ነው የማዬው። ለእኔ ፎቶ ማለት ራዲዮሎጂ ሁለመና ማለት ነው። እራሳቸው የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ልጆች ምስላቸው በወያኔ ሃርነት ትግራይ በአልአዛሯ ኢትዮጵውያ ላይ የተፈጸመውን ጭካኔ በሥነ - ቅርስነት ደረጃ ምንም ነገር ሳያስፈልግ በሥነ- ዝክረነት ማስቀመጥ ይበቃል። የኢትዮጵያን የ27 ዓመት የመከራ ዘመን ዝም ብለው ወንበር ላይ እነኝህ አርበኞች ቢቀመጡ በዓለም አደባባይ፤ ቁጭ ቢሉ አንደ ቅርስ ሊታይ የሚገባው ጥቁሩ ታሪክ ነው። በዬዘመኑ ይሄው ነው የኢትዮጵያ እናቶች የመከራ ተራራ።

ሦስቱም የዕንባ ዘመን ቅርስ ናቸው። አሁን በቤንሻጉል ላይ የተፈጠረው ወገኔ ሲታይ ራሱ ቅርስ ነው ዓይን የሚወጣበት ዘመን። የሰው ልጅ በአላዛሯ ኢትዮጵያ መሞከሪያ ጣቢያ ነው የሆነው። በቃ ስለ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሌላ ማብራሪያ አያስፈለገውም። እና ከዛ መንፈስ ውስጥ ለዛውም ጫካ የነበሩ ሴት ከመጠን ባለፈ በትግራዊነት ያበዱ ሴት የአላዛሯ ኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ተስፋ ያሟላሉ ብሎ መታሰቡ ራሱ ለተስፋ የፈረደበት የሞት ፍርድ ነው። ቅጣት ነው። ለተበደለው ህዝብ ተጨማሪ መቅጣጫ ሳንጃ ነው። ያን በደል እስኪ እንርሳው ቢባል እንኳን እሳቸውን ከዚህ ቦታ አስቀምጦ በፍጹም አይሆንም። እንዴት ታሰበ እራሱ? 50 ሺህ ወጣት አንድ ወር ባልሞላው ጊዜ የታሰረው ለወ/ሮ ፈትለወርቅ የዴሞክራሲ ሚ/ርነት ማዕረግ ለመሪነት ነበርን? ይሰቀጥጣል። ይጎመዝዛል። ያንገሸግሻል።

ክቡር የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ የት ነው ያሉት? ቀደሞ ነገር ይህ መዋቅር የፖለቲካ ድርጅት ሰዎች የሌሉበት በነፃ የሚያስቡ ሰዎች ብቻ ሊሆኑ ይገባል። ከጽዳተኛ ሰራተኛ ጀምሮ አወቃቀሩ በዚህ መልክ መሆን አለበት። ጠረኑ የቢሮው የስታሊን መንፈስን የተጠዬፈ መሆን አለበት። ቢሮው የጫካዊነት አረመኒያዊ መንፈስ መሞከሪያ የምርምር ማዕከል መሆን አይገባውም። ዓውዱ ሰው የመሆንን ተፈጥሯዊነትን የሚገልጽ ሆኖ መደራጀት አለበት። ልክ ክብሩነተዎት ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ከቅጽር ግቢው ጀምሮ እንደ አደራጁት። ስለ ሰው አፈጣጠር ዕጹብ ድንቅነት የሚያዘክሩ የቅርስ ተቋም መሆን ይኖርበታል። በአዲሱ ቋንቋ ሰው ሰው የሚል ጠረን። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚልን ጠረን መሆን አለበት። ኢትዮጵያዊነት ለወ/ሮ ፈትለወርቅ ምናቸው ነው? ሰው ማለትስ? ተፈጥሮ ማለትስ? ሴት መሆን ማለትስ? ርህርናስ ምናቸው ነው? ደግነት ምናቸው ነው? ምንም ነው። ሴት የትግራይ መርማሪ እኮ የወንድ እሰረኞችን የዘር ማፍሪያ ደፍራ የምታንኮላሽበት ዘመን? ለዛውም ለወግ አጥባቂው ለትግራይ ማህበረሰብ። የወያኔ ማንፌስቶ ትርፉ፤ የግንቦት 20 ትሩፋቱ ይሄው ነው። ይህንን ነው ድላችን የሚሉት።

ለዚህ ሥፍራ ከፖለቲካ ውጪ የሆኑ ግን ሰለሰው ግድ የሚላቸው ሩሁሩሃን ብቻ ነው እዚህ መግባት ያለባቸው። ደግ ሰዎች በዬተቋሙ ተመርጠው። ባልደረቦቻቸው ራሳቸው ድምጽ የሰጧቸው መሆን አላባቸው። ግን ዕውቀቱ ያላቸው። እጅግ በበሰለ፣ በተጠና በጥንቃቄ መከወን አለበት። ሰው ስለመሆን ህጋዊ ዕወቅና የሚሰጥ ተቋም እኮ ነው ይህ ቢሮ። ከታች ጀምሮ በመልካም ሥነ - ምግባራቸው፤ በማህበረሰቡ ኑሮ ተቀባይነት፤ በኢትዮጵያዊነት ኩራታቸው፤ በተፈጥሯቸው ህግ አዋቂነታቸው፤ በዜግነት ተቆርቋሪነታቸው ርህህርህና ያላቸው መሆን አላባቸው። ኢትዮጵያዊነታቸውን የማያፍሩበት፤ የማይሸማቃቁበት፤ ኢትዮጵያዊነትን የክብሬ ተክሊል የሚሉ ዜጎች መሆን አለባቸው። ከዚህ ቅዱስ ስፍራ የሥራ ባልደረባ መሆን ያለባቸው ንጹሃን እንጂ የዘራፊዎች ማህበር መሪ፤ የጭካኔ መሪ፤ የሰው መንፈስ ሰራቂ መሪ መሆን አይኖርባቸውም። ለዚህ ቦታ ምቀኞች፤ ቂመኞች፤ ዘረኞች፤ ኢ - ሰባውያን፤ ኢጎ ውስጣቸው የሆነ ሳይሆኑ በፍጹም ሁኔታ የአውንታዊ አርበኛ የሆኑ ቅኖች መሆን አለባቸው ለዚህ ቦታ የሚታጩት። የተቀደሰ መንፈስ ነው ዴሞክራሲ። ዴሞክራሲ የሰባዕዊነት ቤተ እግዚአብሄርም ነው። ዴሞክራሲ እኮ የወንጌልም/ የቁራንም አካል ነው። መልካምነት። መደማመጥ። መምራት፤ ለመመራት መፍቀድ ቅድስና ነው። ራስን ለመምራት ለመግዛት መፍቀድ።

ለዚህ ቦታ ይመጥናሉ የሚባሉ ዜጎች በሰብዕናቸው ውስጥ ምንም እንጥፍጣፊ ምቀኝነት የሌላቸው፤ ህግ የማይተላለፉ፤ በዬትኛውም ሁኔታ በግድፈት እና በጉድፍ ሰብዕና የማይጠረጠሩ፤ ፈርሃ እግዚአብሄር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። ህግን ከተፈጥሮው የተረዱ። ሀገር በቀል ይሉኝታን ያከበሩ የወደዱም መሆን አለባቸው። በመንፈስም ሌቦች ያልሆኑ። ሌብነት ያልተጋባባቸው፤ ሌብነትንም የማይናፍቁ፤ የእነሱ ያልሆነውን ማናቸውንም የክብር ቁርጥራጭ የማያጩ መሆን አለባቸው። ለዚህ መዋቅር ካድሬነት፤ የማንፌስቶ ማህበርተኝነት፤ ጎሰኝነት መስፈርት ሊሆን አይገባም። የሚያስፈልገው ኢትዮጵያዊ ዜግነት ብቻ ነው። የሚያስፈልገው የመዳፍም የመንፈስም ንጽህና መኖር ብቻ መሆን ይገባዋል። የዴሞክራሲ ቁመና ለማኒፌስቶ ኢጓዊ መስመር አይገጥምም። መዋቅሩ ከላይ አስከታች በዚህ መንፈስ ነው መደራጀት የሚገባው።
 
ክቡር ሆይ!

አንድ ምሳሌ ልስጠወት እኔና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር በምን ቋንቋ እንግባባለን? ድልድዩ መገናኛው የተሰበረ ነው። እኔ እና ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ግን በመንፈስ ቤተኛ ነን በሚደንቅ ሁኔታ። ዛሬ አይደለም በቀደመ ሁኔታ። እኔ የዶር ምህረት ደበበ ቤተኛ ነን በመንፈስ ዕጹብ ድንቅ በሆነ ሁኔታ። እኔ የተዋህዶ አማኝ ነኝ። ጠንከር ያልኩ አማኝ። ዶር ምህረት ደበበ ደግሞ የፕሮቴስታን ዕምነት ሰባኪም ናቸው። ግን እኔ በስብከታቸው ውስጥ ያለው የህሊና ንጽህና እና እኔ ላለኝ የፍቅራዊነት አንስተኛ ፕሮጀክቴ ቅርብ ስለሆነ ተመችቶኝ ነው የማዳምጠው። ሰብዕናቸው በዛ ውስጥ ስላለ። ዶር ገመቺስ ደስታም በፍቅር ነው እመከታታላቸው። የማንተዋወቅ ሰዎች በአካል ግን የመንፈስ ንጽህና ራህብተኞች ስለሆነ ማህበርተኞች ነን - በቅንነት ጋላሪ። እነሱ አያውቁትም ከዚህ ሲዊዝ አንዲት ድሃ ማህበርተኛ እንዳለቻቸው። ሌላም ልጠቀስ የቡድሃ ሃይማኖት ተከታይ በስደት ህንድ የሚኖሩ የቲቤት ዜጋ የፍቅር አባት Dalai Lama (Tibetan spiritual leade) ጀርመን ካለው ንጹህ መንፈስን የመፍጠር ዩንቨርስቲ ጋር የሚሰሯቸው ድንቅ ተግባራት የልቤ ስለሆነ እከታተላቸዋለሁኝ። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ይህን ጉማም፤ ጎማማ ዓለም፤ ወደ እኛም ሲመጣ ኢትዮጵያንም ሊለውጡ ስለሚችሉ። ሰውን የሚመራው መንፈሱ እና ረቂቅ ስሜቱ ነው። ያን ቅጥ ማስያዝ ከተቻለ ማመጣጠን ይቻላል። መከራ እንኳን ቢሆን ይቻላል። 

ፍቅርን ተፈጥሮውን የማያውቁ ሰዎች ለማድመጥም ጊዜ የላቸውም። በፍቅር ውስጥ ለመኖር የፈቀዱ ሰዎች ለእኔ ሃይማኖታቸው፤ ዘራቸው፤ የቆዳ ቀለማቸው፤ የሚኖሩበት አህጉር ቦታ የለውም። ፍቅር ፍልስፍና ብቻ አይደለም ሰማይ እና መሬት ማለት ነው። እርእስ ጉዳዩ የዘመናት የመኖር የትምህርት ክ/ ጊዜ ነው። በስፋትም፣ በመጠንም፣ በቅርጽም፣ በይዘትም፣ በቀለም፣ በቁመናም ልንለካው አንችልም። ፍቅር ተፈጥሮው ክስተት ነው። አያልቅም፤ አይቆምም። ሰሞኑን የተካሄደውን  የታላቋ ብርታንያን የልዑል ሄሪ ቻርለስን ጋብቻ እንውሰደው። ጠይም ዕንቁ ተዋናዊት ሜገን ማርክል በህጋዊ ደረጃ አግብታ የፈታች፤ ወላጆቿ በጋብቻ ጸንተው ያልኖሩ፤ በቤተሰብ አመራር አደረጃጃት ወስጥ የጎደለ በብዙ ሁኔታ ያለበት፤ በዕድሜም ባለቤቷን የምትበልጥ፤ የታላቋ ብርቴን ሙሉ ደም የሌላት፤ የአፍሪካዊነት አማሪካዊነት ዝርያ ያላት፤ ከልጅነት እሰከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ በትጋት ውስጥ በሰዋዊነትን የኖረችበት፤ በወጣትነት ዕድሜዋ ባላት ዕወቅና ደረጃዋ ሰውነቷን አጋልጣ የካሜራ ራት ያላደረገች፤ ስለሴትነቷ ጠበቃ የሆነች፤ ስለድሃ የዓለም ዜጎች ዋቢ የሆነች፤ ያን ወግ አጥባቂውን የታላቋ ብርታንያ ቤተ መንግሥት ታሪክም ደግሞ የማያገኛቸውን የማጅስቲን ይሁንታ አግኝታ ጋብቻ ፈጸመች። በማን ሃይል? በማን አቅም? በማን ችሎት? በፍቅር ተፈጥሮ እና መርህ። ፍቅር የሌለው ሰብዕና በኢትዮጵያ የዴሚክራሲን ሥርዓቱን አይደለም ህልሙንም ማሰብ ይከብዳል። አቅሙ ደሃ ነው። ድህነት የፍቅር ያለበት ሰው የነቃው የህሊና ክፍሉም ደሃ ነው። ፍቅርን ተፈጥሮውን የማያውቅ ማንኛውም ሰው የህሊና ድርቀት ያለበት ነው። 

የፈለገ ይማር፤ የፈለገ ሥልጣን ይኖረው፤ የፈለገ ዴታ ይሁን፤ የፈለገ ተመክሮ ይኖረው፤ ፍቅራዊነት በመንፈሱ ውስጥ ባሉ ንጥረ ነገሮች ገላጭ ሁኔታዎች ከነጠፉበት ወና ነው። ኮትም፣ ሱሪም፣ ገበርዲንም፣ ከረባትም፣ እጀ ጠባብም፣ ግብግብም፣ ቁምጣም፤ ሽብሽቦ፤ ሙሉወርድ፤ ሱሪና ኮት የለበሰ ሰው እንዲሁ፤ ሰው ሁኖ በመፈጠር ውስጥ አለመፈጠርን የወሰነ ማለት ነው የፍቅርን ተፈጠሮ የከዳ። እኒህ ሴት እንዲህ ናቸው። ለራሳቸው ሳቅን የነፈጉ የዕድሜ ልክ የጸጸት ቤተኛ። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር የመኖርን ተፈጥሮው አልኖሩበትም። ኖርኩ ቢሉ በጥበት በጥብቆ በተቸነከረ መርዛም ዘረኝነት፤ ከቀለሃ ጋር እና ከዛ ድፍን ካለ የማረተ ርዕዮት ዓለም ጋር ነው። ልባቸው ጥቁር ነው። ለወደፊትም ከሰብዕናቸው ስነሳ ወደ ተሻለ ሰብዕና ለመምጣት ፈቃጅም አይደሉም። የሴት ጨካኝ ሴት መሆንን ይደምስሰዋል። ሴት ጨካኝ የሆነች እለት ጾታዊ ክብሯ ተገፏል።

·         የፈለገ ይሁን ቦታ ጊዜ፤ ሁኔታ የሚሰጠው ዕድል አሹላኪ ከሚያደርገው ዋነኛው አመክንዮ ታላቁ ይህ ወሳኝ ቦታ አለቦታው መቀርቀሩ ነው። የተገባ ውሳኔ አልነበረም። ሁሉም ቦታ ተግኝቶ ማስተካከል አይቻልም። ሃላፊነት ሲሰጥ የራስንም ሃላፊነት በተወሰነ ደረጃ የሚቀንስ፤ የሚረዳ መንፈስ መሆን ይገባል። መቼስ ጥሬ ተስጥቶ ሙሉ ቀን ዶሮ ሲጠብቁ ዓይነት ከሆነ የአቅም ብክነት ነው፤ ለሌላ ትኩረት ለሚሻማ አጣዳፊ ጊዜንም ይሻማል። ውጪ ጉዳይ ሚ/ር ላይ ስጋት የጠ/ ሚር ቢሮ ላይኖርበት ይቻላል። በአምሳሉ የፈጠረው መንፈስ እዛው በመልካም ሁኔታ ሰሞኑን ስላደላደለው። በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ ሚ/ርም ተከታዩ ዲኤታ ሹሙ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር ቢዛወሩ ችግር የለበትም አናቱ ተመሳሳዩ አቅም ስላለ ብዙ ሃላፊነቶችን ያቃልላል። ይህ እሸታዊ ዕድል ግን በዴሞክራሲ ግንባታ ላይ መታሰቡ፤ መወሰኑ ግን ፈጽሞ ሊታሰብም ሊገመትም ሊታለም አይችልም። ሌላ ቦታ ወስዶ እኮ ሚ/ር ማድረግ ይቻላል። መቼም ያ መከረኛ ህዝብ መመኮሪያ ነው እንደ ጥንቸል። ይህ ግን ፈጽሞ ሊሆን ያልተገባው ወሳኔ ነው። ራሱ ከኢህዴግ ግንባር አባልተኝነት ለዚህ ቢሮ መታሰብ አይኖርበትም። ጠቅላላ ቢሮው መጽዳት አለበት። ሽግሽጉ የሚ/ር መስሪያ ቤቶች ብቻ ሳይሆን ከላይ እስከ ታች ያለውም በጥራት እና ሰው በመሆን መንፈስ በአዲስ መልክ መገንባት ከሁሉ ቀዳሚው ተልዕኮ በሆነ ነበር። የኢትዮጵያ እንደ ገና መወለድ ማህተሙ ይህ ቢሮ ባለው አቅም እና ልክ ይወሰናል። ተስፋው ተስፋውን ከማያገኝበት ቦታ ነው የተቀረቀረው። ፍልስፍናው እኮ ነፍስን ማስቀጠል ነው። ለነፍስ ነፍስን አጥፊ መድቦ እና ሃላፊነት ሰጥቶ አይሆንም። ይሄ እርምጃ ኦህዴድንም ከነመርኩቡ የሚያሰምጥ ነው። እንደ ገና በእነ አቦይ ስብሃት ነጋ የፖለቲካ አማካሪነት። ታጥቦ ጭቃ ነው። ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። ተስፋውን ቀራንዮ ላይ ብቻ ሳይሆን ጎለጎታንም ያከለ ነው። ሞት እና መቃብር።
  • ·         ቢሆን? ከተቻለ?

ከት/ ተቋማት፤ ከጤና ተቋማት፤ ከመምህራን፤ ከኪነ ጥበብ ሰዎች፤ ከፈጠራ ሰዎች፤ ከህግ ባለሙያዎች፤ ከሽምግሌዎች፤ ካባህላዊ ዳኞች፤ ከህግ ባለሙያዎች የተውጣጣ ህብረ ቀለማት በእውቀት፤ በተምክሮ የተመሰረተ አካል ነው ለዚህ ቦታ ሊሆን የሚችል። እዚህ ቦታ ላይ ርፍራፊ፤ ቅንጥብጣቢ የኢህዴግ መንፈስ ወይንም የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት እንዲኖሩበት አልሻም እኔ በግሌ። ነፃ ሆኖ የሚያስብ፤ ነጻ ሆኖ የሚሠራ ንጹህ መንፈስ እንዲኖር ነው ምኞቴ። ስለሆነም ጥያቄው ጊዜ ተውስዶ፤ ተጥንቶ ጠቅላላ የመዋቅር ለውጥ ያስፈልጋዋል ባይ ነኝ። ጥገናዊ ለውጥ ለሌሎች ተቋማት ይሁን። እዚህ ግን እእ። እኛ እናንተን አብይ ለማ ገዱ አንባው መንፈሳችን የፈቀደነው እኮ ሰዋዊ መንፈሳችሁ እንጂ የግንባር ድርጅታችሁ ትዝ ብሎን አያውቅም። እሱን እማ ብናስብ አንቀራረብም ነበር። ብሄረሳባችሁ እና ሃይማኖታችሁ አስታውሰነው አናውቅም። የምናስበው መልካምነታችሁን፤ ምህረት መሆናችሁን ብቻ ነው። ለተስፋ የተላካችሁ ሐዋርያ መሆናችሁ ብቻ ነው የሚታሰብን - ለቅኖች። ይሄን መንፈስ ዕውን ለማድረግ አዲስ መዋቅር መሥራት ያስፈልገዋል ትላላች ትቢያ ላይ ያለችው ሥርጉተ ሥላሴ ዜጋ ከሆነች፤ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ሴት ልጅ ከሆነች፤ እኔም ከቤተሰቦቼ የወረስኩት ባድማ አገር አለኝ ብዬ ካመንኩኝ፤ መሪም አለኝ የምለው እኔንም ሩቅ ነው የምትኖር ደሃ ናት፤ ታዋቂ አይደለችም ሳይል ሊያደምጠኝ ሲፈቅድ ብቻ ነው። መዋለ ዕድሜያችን የባከነበት አመክንዮ እንደ ገና ከሳጥናኤል ሥር ወድቆ ፈቃድ ዴሞክራሲ አቧራ ለብሶ ተንበርክኮ ይለምን? ግፍ ነው። የእውነት ዱላ ነው። 

·         ለነፃ ሚዲያ፤ ለነፃ የሲቢል ድርጅት፤ ለነፃ የፍርድ ሥርዓት፤ ለነፃ አስተሳሰብ፤ ለነጻ የምርጫ ቦርድ፤ ለነጻ የመጻፍ፣ የመናገር፤ የመደራጀት፤ ለነፃ መኖር፤ ለነፃ መተንፈስ፤ ለነፃ በመኖር ውስጥ ለማይቀረው ለሞት ለራሱ ይህ መዋቅር ሰቁ ቅስቱም ነው። ስለዚህ በሹመቱ ተከፍቻለሁኝ። ልቤም እንደ ዱባ የተቀረደደበት ሹመት ነው። ተስፋዬን ባይረስ እንዲፈታተነው አድርጎታል። ሴት አቅም ከሌላት ሴት በመሆኗ የሚ/ር ደረጃ ቢሰጣት አያረካኝም። ስለዚህ ገዳይ፣ ጨካኝ፣ አረመኔ፣ ሌባ፣ ዘራፊ ስብዕና ሴት ስለሆነች ብቻ ትምራኝ አትልም ሥርጉተ ሥላሴ፤ ወ/ሮ ሄሮዳዳይ ዛረፊዋ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሴት ናቸው እኮ ላዛውም እሳቸው ቢክዱትም የቃብቲያ ሰው ናቸው ሌላው ቢቀር። ግን ስታገላቸው ነው የኖርኩት። እኔ መላ ይፈለግለት አይደለም የምጠይቀው የታቃዋሚ ድርጀቶች ተፎካካሪነት፤ የሲቢክስ ድርጀቶች ነፃነት፤ የሴቶች ተፈጥሯዊ የማድረግ አቅም እኩልነት ከተፈቀደ ይህ ድርጅት በጠቅላላ በአዲስ መንፈስ አዲስ መልክ ይዞ ይዋቀር ነው። ቢያንስ የዶልፊን ያህል አቅም ይኑረው።

·         የወንዶች የፖለቲካ ዓለም ሲያረጁም እስከ እነ እርጅናቸው ፖለቲካዊ ሥልጣን እንደ ጠማቸው አኖሯቸዋል። ስለዚህም ኢትዮጵያ ተስፋዋ ሁሉ በጎድን የተለካ ነው። ግን ሴቶች በፖለቲካው ዓለም እኩል ዕውቅና እንዲኖራቸው እምታገለው ለእኩልነታቸው እንጂ ሰውነታቸውን ለሰረዙ ለጥቁር ልቦች፤ ለጨካኞች አንስት አይደለም። ሰብዕናቸው የተሟላም ሆኖ ግን ለቦታው ካልመጠኑ ሴትነታቸው ይጋርድላቸው የሚል ልፍስፍስ ራሱን ያልቻለ ፍልስፍናም የለኝም። ሴት እኩል ለመሳተፍ አቅሟ ሴትነቷ የሰጣት ጸጋ ሳይሸራረፍ ተግባረዊ ለማድረግ የምትጥረዋን ነው እንዳትገለልብኝ የምፈልገው። ቁጥር - ኮታ - ተዋፆ - ይህን ያክል የሴት ሚ/ር ተሾመ በእኔ ቤት ቦታ የላቸውም። ራስን ማብቃት ያስፈልጋል። የጣረች፤ የተጋች፤ በተግባር የተፈተነች ምስጉን ሴት ማለትም በሶሻሊዝም አቅመ ቢስ ፍልስፍና የተደቆሰች ሁለገብ ሴት አቅሟ ዕውቅና አግኝቶ በልኳ፤ በመጠኗ፤ ፈጣሪ አምላክ ለይቶ በመረቃት እናታዊ ጸጋዋ፤ ስለእናቷ በእናትንት ትሁንላት ነው። 

       አቅም ላነሳትም ናሙና ሆነ ህይወቷ አንዲስተምር ሆና ትግኝ ነው። ሴትነት ሲባል ብቻ ያለ ቦታዋ፤ ያለ አቅሟ፤ ያለ ክህሎቷ ሹመት ይቆለልላት አይደለም ሙግቴ። አቅሙን እንድታመጣ ሁኔታ ይመቻችላት። ስትበቃ ደግሞ ከምትመጥነው ቦታ ፆታዋ ሳይገፋ አቅሟ የፈቀደው ደረጃ ይሰጣት ነው። በዚህ ኦሮምያ ላይ የተሻለ የአቅም እክብካቤ ነበርው። አሁን ቦታ ለመስጠት ችግር አልሆነበትም። ሌላ ቦታ ግን የከሳ ነው። አማራ ተቀብሮ የኖረ ነው። እንኳንስ አንስት ተብዕቱም ፍዳውን ሲከፈል ሲከረኮም ነው የኖረው። አቅም እና ችሎታ ሳይሆን መለኪያው ጎሳ ስለነበር፤ እድሉንም ያገኙት አቅምን በማጎልበት ሳይሆን ያው የጎሳውን ትክሻ ተጠልለው ስለሆነ ወደ ፊት የመራመድ አቅማቸው ሰላላ መላላ ነው።

·         እኔ የህልሜ ቀንበጥ እምላቸው አንስታዊት አንበሳ መሪ „ምን ይታዬናል? ድመት ሆነን አንበሳ? ወይንስ አንበሳ ሆነን ሰው? ወይንስ ሰው ሆነን ሰው? የሚሉትን ነው። እኒህ ብቁ ለግላጋ ወጣት ሙሁር፤ ትሁት፤ የሰውነት ታታሪ አንስት ይንፍቁኛል። ዴሞክራሲ ታጭቶ በወረቀት ኮታ አይሆንም። የመጀመሪያው የዴሞክራሲ ጥያቄ ሰው መሆን፤ ሴት ከሆነች ከጭካኔ ጋር ያልተነካካች፤ እጇ ደም ያልነካው፤ መንፈሷም ደምን የማያልም፤ ርሁሩህ እናታዊ ሰብዕና ያላት መሆን አለባት። ቢያንስ የኢትዮጵያ ህጻናት በሙሉ ልጆቼ ናቸው የምትል። ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ እኮ „ሳይንቲስት ለመሆን ሰው ብቻ መሆን ይበቃል፤ ከቶ ምን ይታዬናል? ድመት ሆነን አንበሳ ወይንስ አንበሳ ሆነን ድመት? ወይንስ ሰው ሆነን ሰው? መምህር ሆነን ተማሪዎቻችን፤ አለቃ ሆነን የበታቾቻን ለማብቃት ምን የጎደለን ነገር አለ? ሁላችንም አድገን አልጨረስንም።“ 

      ክቡሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ይህ እኮ ቃለ ህይወት ነው። ይህ እኮ ለእስልምና ዕምነት አማንያንም ቁራዕን ነው። በምድራዊ ሲተረጎም የተፈጥር የሰው ሥነ - አቅም፣ ሥነ - ሰብዕና፤ ሥነ - ሞራላዊ ፍልስፍና ነው። ይህችን የመሰለች የድንቆች እንቁ ያለቻት አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለምን የገዳይ መዳፍ ናፈቃት? ስለምንስ የጭካኔ ፍታውራሪት ሴት፤ የዘራፊ ሴት ተምሳሌን መሾም አሰኛት? ዴሞክራሲ እኮ ለነጻነት ጉሮሮው ማደሪያው፤ ማደራደሪያውም ነው። አላዛሯ ኢትዮጵያ ስለምን ወደኋላ ለመመለስ አለመች? ለመሆን የኢ - ሰብዕዊነትት መሪ ራህብተኛ ሆነችን? ጭካኔ እንደ ገና እንዴት ትናፈቅ ኢትዮጵያ? ደንብልብል ብሎብኛል። ጥገናዊ ለውጥ ሰጥቶ መቀበል ስለመሆኑ አውቀዋለሁኝ። ግን ጉሮሮ ተዘግቶ አይደለም። የወያኔ ማንፌስቶ ጽንፈኛ ሴት እንዴት ለሰብዕ ቀረፃ ይሾማሉ? እንዴት ለዚህ ቦታ ራሱ ይታጫሉ? መርግ ነው።

·         በፍጹም ሁኔታ የወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄርን የዕውነተኛ የዴሞክራሲ መሪነት ጉዳይ አንዲት ቅንጣት መንፈስ ይህን ውሳኔ አይደግፈውም። አንዲት ራፊ የህሊና ርስት አያገኝም ወሳኔው። ቅብዕ ሹመት ለመልካም ሆነ ለመልካም ላልሆነም ነው። የወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ደግሞ የ27 ዓመት መከራ እንዲያገረሽ፤ በቀል በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በስውር እንዲፈለፈል ለጥ ባለ ሜዳ እና ሰጋር ሰረገላ ተሸልሞ መጪ በል ተብሎለታል። ይህ ጥያቄ የሚሊዮኖች ድምጽ እንደሚሆን አስባለሁኝ። አንድ መልካም ነገር ብዙ ቁስሎችን እንደሚፈውስ ሁሉ አንድ ወደል የበደል መጨመሪያ ግድፍት ደግሞ የመቁስል አይደለም የመግደያ ባሩድ ነው። የተሰባሰብ ቅን መንፈስ መበተኛም መሳሪያ ነው። እንኳንስ ይህን መሰል የተጨማሪ ቁስል ማመርቀዣ ሹመት ቀርቶ በሰላሙ አገር የነበረውን መታመስ ያሉበት የነበሩበት ነው። ያን ሚዛኑን ለማስጠበቅ „ከጣና ኬኛ“ ጀምሮ የደከሙ ሰዎች ያውቁታል። አሁን በወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ሹመት ተጨማሪ ግዳጅ የማንችለው ግማድ ደረበብን የጠ/ ሚሩ ቢሮ።

·         ይገባኛል የክቡርነትወትን ንጽህና አስበው ነው ከመዳፍ አይወጣም ብለው ሊሆን ይችላል። ሰው ጥንቸል አይደለም። ሁልጊዜ ዜግነት መሞከሪያ ጣቢያ እንደ ጥንቸል ሊከፈትለት አይገባም። ወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌስቶ በቃኝ ማለት ይሔው ነው። ዴሞክራሲ ታንቆ ፍትሃዊ ምርጫ የለም። ይህ ሹመት ሌላ ቦታ ነው የሚሰራው 50 ሺህ የአማራ እና የኦሮሞ ወጣቶች፤ አዛውንታት፤ ጎልማሶች፤ ባህታውያን፤ ህጻናት ደም ገብረበውታል። አንብተውባታል። ዋጋው ተመጣጣኝ አይደለም። አንባ ጊዮርጊስ ጎንደር ወገራ አውራጃ ነው የሚገኘው። ይህ የድሆች ከተማ 26 ህጻናት ከሱዳን በታገዙ ወታደሮች ተጨፍጭፈዋል። እናቶች እናታችን ድንግል ማርያም ልጇን አዳኛችን ለማዳን ከእስራኤል ወደ ግብጽ የተሰደደችበት ዘመን በዛ ደሃ ከተማ ተፈጽሟል። የረባ በር ያለው ቤት እንኳን የለም። ህጻን ወንድ ልጅ ያላቸው እናቶች ሁሉ እስከ ቆላ ወገራ ድረስ በመዝለቅ ጫካ ገብተዋል። ወጀቡን ለማሳለፍ። ታዲያ እኒህ ሴት ለዚህ ለተጋፋ ማህበረሰብ ድምጹን የመስማት ቀጥተኛ አቅም አላቸውን? ግፍ ነው? እጅግ ግፍ ነው። ከበደልም የከረፋ ግፍ ነው። ይጎፈንናል።

ቢያንስ የእነኛ ምንም ሳያውቁ ሙሉ አካላቸውን መሸፈኛ የሌላቸው ህፃናት ደም እንደ አቤል ደም ይጮኸል! በእስር ቤትም የሚፈጸመውን ሰምተውት የማያውቁትን ክፉ ነገር፤ ዘር የሚነቅል ታሪክ በአካል ባገኘዎት እነግረውት ነበር። ቤተሰቦቼም አያውቁትም፤ እዚህ ያሉ ሁለት ነጭ ጓደኞቼ ብቻ ነው የሚያውቁት። ያ የራህብ የዴሞክራሲ የተስፋ ጊዜ እንደ ገና ለገዳይ ሲሸለም ያሳብዳል። ዕውነት ያሳብዳል። መጀመሪያ ሰው ይሆኑ ዘንድ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ሱባኤ ይግቡ ይጠመቁ፤ ለነገሩ ሃይማኖት የላቸውም። ይህም ቢቀር ሰው እንዲሆኑ ት/ ቤት ይከፈትላቸው። ሰው ያልሆነ ሰው ምስል ብቻውን ልብስ ስለለበሰ ሰብዕና አለው ማለት አይቻልም። ሰውን ለመምራት ሰው መሆን ይጠይቃል። 

ዴሞክራሲ በባህሪው ግሎባል ነው። ሰብዕን በሚቀርጽ ታላቅ ግሎባል ተልዕኮ ሰው የገደለ፤ አሁንም ለመግደል የሚናፍቅ፤ በደም የዘለበ ሰብዕና ይህን ታላቅ ዓለምዐቀፋዊ የሥልጣኔ መሰረት ግዳጅ ሊሰጠው ከቶውንም አይገባም። ሙሉ ለሙሉ ከወያኔ ሃርነትም አገር እና ትውፊት ገዳይ ማንፌስቶ ክፉ ጠረን፤ እንደ ግንባርም ከኢህአድግ መንፈስ ውጪ አዲስ ንደፍ እና ፕላን ያስፈልገዋል ቢሮው። ኢህአዴግም እኮ በመጪው ምርጫ እንደ ድርጅት ተወዳዳሪ ነው። በጓዳ ጅብ አስሮ አይሆን። ከዚህ በተረፈ አይደለም አንድ የሚ/ር ቦታ ጣምራም ሌላ ቦታ ቢሾሙ ክቡሩነታዎት ለሚሸከሙት ጥያቄ የለኝም። ይህ ቦታ ግን በቀጥታ የሞተ አስነስቶ ዲሞ የሚያስወጣ ነው። ስለ ዲሞክራሲ ፍልስፍና እና አፈጸፀም ከእንግዲህ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወ/ ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ከአቦይ ስብሃት የሴራ መረብ ተንበርክኮ፤ ተጎንብሶ የሚለምንበት ቅርጥምጣሚ ትዕግስት የለውም። አካሉን እዬፈቱ መንፈሱን ማሰር ለሞተለት ተጋድሎው ሌላ ሞት ሊታወጅለት አይገባም። መኖር ሙቷል፤ ለሞቱ ሌላ ሞት አያስፈልገውም። ሰው ስንት ጊዜ ይሞታል? ስንት ጊዜስ ይገደላል? መኖር ማለት ነፃነት ማለት ነው። ስንፈጠር የተሰጠን የነፃነት እዬር የሸለመን የተቀማን ምንዱባን ነን። ያልታደልን!

·         አውራ ጥያቄው ቢሮው ጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ሥር - ነቀል ለውጥ ይደረግለት ነው። ጠረኑ ሰውኛ ተፈጥሮኛ ይሁን። ጭቆና፤ ግድያ፤ እስራት፤ ዝርፊያ፤ ወራራ የሚያወግዙ ፓስተሮች፤ ትእግስትን፤ መቻቻልን፤ አክብሮትን፤ ትውፊትን፤ ቅርስን፤ መቻልን፤ ፍቅርን፤ ትህትናን፤ ምስጋናን፤ ህሊናን የሚከብሩ ፖስተሮች አውዱን ይቀኙት። አዳራሹ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት የሚያውጁ የጥበብ ሥራዎች ይንግሥባቸው። ከዛ ቢሮ ሲገባ ገነት የተገባ ያህል የሳቅ - የፍሰሃ ጭንቅና ችግር የሚረሳበት ሁኖ ይደራጅ። አዲስ ቀን፤ አዲስ ቀለም፤ አዲስ ተስፋ ፤ አዲስ ራዕይ፤ አዲስ ሰብዕና የሚናፍቅበት ዓወድ ምህረት ይሁን። ቤተ መጻህፍቱ ሲደራጅም በደጋግ ሰዎች መንፈስ፤ በተፈጥሮ ጸጋዎች ላይ ምርምር ያደረጉ ጸሐፍት ብቻ ማህበርተኛ የሚሆንበት ሆኖ ይደራጅ። ሁሉም ሰው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከአዕምሮዬ ጋር ነበርኩኝ ብሎ መቼም ራሱን መዋሸት አይችልም። ሁሉም ሥነ  - ልቦናው ተጎድቷል። ሁሉም ስጋት ላይ ነበር፤ አዋሳ ላይ አቶ አባተ ሲናገሩ „ቤቴ በሰላም እንደምገባ ተስፋ አለኝ“ ነበር ያሉት። የዜጋው መንፈሱ ተቀምቷል። ዜጋው ሥነ - ልቦናው ስጋት - ፍርሃት - እርግጠኛ አለመሆን ወሮታል።

የወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ ያለቀማው ነገር የለም። በቁመናው ሰዉ መሄድን፤ መልቀቅን እያሰበ ደመንፍሱን ነው የሚንቀሳቀሰውም ለዚህ ነው። መቀመጫ ስላጣ። መቆሚያ ብትን አፈር ስለተነፈገ። ስልጣን ላይ ያለውም የዘረፈውን፤ የገደለው፤ ያደማውም አራሱም ጭንቅ ላይ ነው እሱም ሽሽትን ያለመ ነው። ከመጋቢት 24 ቀን 2010 በፊት እኮ በመንፈስ 100 ሚሊዮኖች የሚኖሩበት ባዕት አልነበርም። ምድረ በዳ እኮ ነው የነበረው የአላዛሯ ኢትዮጵያ ልጅ የመንፈስ ቀዬ ሁሉ። ስለዚህ ኢትዮጵያዊው ዜጋ ወደዚህ ቢሮ ሲገባ፤ በደብዳቤ ግንኙነት ሲያደርግ፤ በስልክ ሲነጋገር፤ እንግዳ ሲቀበል፤ የመጣን እንግዳ ሲሸኝ ሁሉ ከመንፈስ የሚቀር መልካምነት መኖር ይገባል። ህሊናው በአግባቡ እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል። እዚህ ቢሮ ሰው ሲገባ አቀባበሉ ራሱ ፏ ያለ ቧ ያለ „ርግብ በር“ ያስፈልገዋል። በሩ እራሱ ጠረኑ ሰውኛ - ሳቅኛ - ፈገግተኛ መሆን አለበት። የመንፈስ እርጋታ የሰፈነበት አዬር ቅጽር ግቢውን በሙሉ መሙላት አለበት። 

የሎሬቱ ተስፋ እዚህ ቢሮ ውስጥ ዓርማ መሆን አለበት። የመጀመሪያው የአብይ የተሰባሰበ የአትኩሮት አቅማዊ መዋለ መንፈስ ማዕከል መሆን ያለበት ይህን ቢሮ በጥራቱ፤ በጠረኑ፤ በቋሚ ቅርጽነቱ መሰረት ማስያዝ ሊሆን ይገባል። የትውልድ ብቸኛ ቤት ነው ይህ ቢሮ። ይህ ቢሮ የአብይ መንፈስ የታሪክ ቀን ሃውልት መገንባት ያለበት እልፍኝ መሆን አለበት። ይህ ቢሮ የሰዋዊ ቀረጻ ቢሮ መሆን አለበት። የሚጎበኝ፤ ሊያዩት የሚናፍቁት ተቋማዊ ህይወቱ የሚያስተምር የሚናፈቅ መሆን አለበት። ለተከፉት ፈጣኖ የሚደርስ መሆን አለበት። ቢያንስ መከፋትን ሊያደምጥ የሚችል። የመንፈስ ሃብታት ሁሉ የነፃነት እናት ምድር ሊሆን የሚገባው ይህ ቢሮ ነው። ዲቢሎስን እዛ አስቀምጦ፤ ለሳጥናኤል ዙፋን ሰርቶ ግን አይሆንም፤ ሊታሰብብም አይገባም። ይህ ቢሮ የአማካሪዎች ሸንጎ ሁሉ ሲዳራጅ አንቱ የሞራል አባቶች/ እናቶች መነኮሳት ሳይቀሩ፤ ሸኾች ሳይቀሩ፤ ፓስተሮች ሳይቀሩ፤ ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ሙሉ መብታቸው ተከብሮ አቅማቸውን ወደ ተግባር ሊያሸጋግሩበት፤ ሊመክሩበት እና ሊዘክሩበት የሚችል የትውፊት ጉልላት መሆን አለበት። ለመልካምነት፤ ለቅንነት ሰፊ እልፍኝ መሆን አለበት። ዜግነት፤ ሰዋዊነት፤ ህላዊነት፤ ነባቢትነት፤ ልባዊነት፤ እርቃዊነት፤ እኛዊነት፤ ምህረታዊነት፤ መቻቻላዊነት፤ ፍቅራዊነት እስኪ በዘመነ አብይ ወደ ክብራቸው ይመለሱ። የአብይ ት/ ቤትም ይባል።

ይህ ቢሮ እንዲመጡልን ይናፈቃሉ፤ ሲመጡ ደግሞ ፍቅርን ከነሙሉ ክብሩ እና ተፈጥሮው ያገኙታል፤ በመስተንግዷችን የመልካምነት ስንቅን እናካፍለወታለን፤ ሰዋዊ መከበርን ሰነቀው ይመለሳሉ። የሚል መሆን አለበት።

ክቡር ሆይ! ይህ ለነገ የሚቀጠር አይደለም። በሃሳብ ደረጃ ተግባሩ መጀመር አለበት። ፍቅር በነጠፈበት ህሊና ውስጥ ዲሞክራሲን ማንጠፍ አይቻልም። በአንድ ወቅት የዓለም ትልቁ ሃብት የትነው ለሚለው የዓለም ተመራሪዎች ቡድን የደረሱበትን አምክንዮ መረጃ ገልጸው ነበር። ኑሮው መቃብር ውስጥ እንደሆነ። እኔ ደግሞ እንዲህም እላለሁ የዓለም ትልቁ የመኖር ንጥረ ነገር መቃብር ውስጥ ነው የምለው የፍቅር ተፈጥሯዊ መርሆዎችን እንደ አንድ የእውቀት ዘርፍ ልናመረው አለመቻላችን፤ ልንመረቅበት አለመቻላችን ነው። የፍቅር ተፈጥሮ ዕውቅና ማጣት የሰው ህሊና በክፉ ነገሮች የሚያጠፋው ጊዜ ራሱን በልቶታል፤ ወይንም መቃብር ልኮታል። በዓለም አንድም ቦታ የፍቅር ተፈጥሮ የምርምር ማዕከል የለም። አንድም ሳይንቲስት በፍቅር ተፈጥሮ የተጠበበ የለም። ፍቅርን ተፈጥሮውን መርምሮ ትውልድን የማዳን ተግባር ያልተሰራበት ፍጹም አዳኝ አምክንዮ ነው። አንድም ተቋም፤ ድርጅት የለም ስለፍቅር ተፈጥሮ ዓለምን የሚሞግት። 

አንድም ት/ ቤት፤ ኮሌጅ፤ ዩንቨርስቲ የለም። ፍቅር ትምህርትም፤ ሙያም አይደለም። የትምህርት መማሪያ መሳሪም ካሪኩለምም የለውም፤ መጸሐፍትም የለውም። የሰብዕና መለኪያም አይደለም። አቅሙ መለኪያ ያልተሰራለት፤ ፍልስፍናው ዳርቻ የሌለው ሳይንስ ነው የፍቅር ተፈጥሮ። አንድም ቀን ዓለም በፍቅር ተፈጥሮ ላይ ወርክሾፕ፤ ፓናል ዲስከሺን፤ ሰሚናር ህግ ራሱን አስችላ አዘጋጅታ አታውቅም። ዓለምአቀፍ የፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት ወላዊ ፌስቲባል፤ የመንገድ ላይ ትርኢት ዓለም አሰናድታ አታውቅም። „ማቻቻል፤ አክብሮት፤ ታጋሺነት፤ ፍቅራዊነት፤ ማድመጥ፤ ማዬት፤ ህላዊነት፤ እኛዊነት የሚል ሥያሜ ያለው ት/ ቤት እንኳን የላትም እመቤቲቱ ገሃዲቱ ዓለም። ዛሬ የሰው ልጅ ከሰው ይልቅ ማሽን አምላኪ እዬሆነ ነው። የቤተሰብ ዕሴት በድርቅ እዬተመታ ነው። ለዚህም ነው ዓለም አስፈሪ እዬሆነች የመጣችው። በ2015 አመልክቼ አድማጭ ሳጣ በ2017 የቃላት ፖስተራዊ ቻናል የጀመርኩትም ለዚህ ነው።

ወ/ሯ ከዚህ መንፈስ ጋር አስታርቆ ወደ ሰው የመሆን ፍልስፍና ለማምጣት የኢትዮጵያ ህዝብ መመኮሪያ ከሚሆን፤ ምጥ ላለው መከራ ገላጋይ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉን ሌሎችንም በዬቢሮው ያሉትን ደጎች ግን ማንፌስቶ አምላኪ ያለሁኑት ንጹህ ዜጎች ዕድሉ ተስጥቷቸው ቅንነታቸው፤ ቸርነታቸው፤ ፍቅራዊነታቸው መዋለ የመንፈስ ሃብታቸው ወደ ተግባር የሚያሸጋግሩበት ቢሮ ቢሆን የተሻለ ነው። ይህ ለወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር እና ለአቦይ ስብሃት ገጸ በረከት የተሰጠው ቦታ ሰብዕናው ሙሉ ለሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሰጠት አለበት እላለሁኝ፤ የተስፋ የፍቅር እልፍኝ ሰዋዊነት ነው። ለናሙና መውሰድ ይቻላል ገጣሚ ፍጹም አስፋው፤ አቶ ውብሽት ሞላ /የህግ ባለሙያ/  ዶር ደረጀ ገረፉ /የፖለቲካ ተንታኝ/  አቶ ታዬ ታዬ ደንዳዓ /የህግ ባለሙያ/ ወ/ሮ አለምጸሐይ መሰረት ታላቅ ሁለገብ ሙሁር፤ ኢንጂነር ሚኬኤል ሽፈራው የሎሬቱ ታቦት በልባቸው የታተመ ድንቅ ኢትዮጵያዊ አሉ። እነዚህ በተለያዬ አጋጣሚ ሚደያ ላይ የማዬቸውን ነው፤ ለዚህም ዕድሉን ያላገኙ ብዙ በርካታ ደግ ወገኖች አሉ። ለዚህ ቦታ እናታዊ አንጀት ነው የሚያስፈልገው። ተብዕት ከሆነ ሴት አንጀት የሚባል ዓይነት። ኢትዮጵያ አኮ በደም ዝናብ የበቀለ እህል እዬበላች „የእንባ ጠባቂ በሚ/ር“ ደረጃ ነበራት። ሴት ልጅ ጥፍር፤ ወንድ ልጅ የዘር ማፍሪያ በሚከስምበት አገር፤ ሴት ልጅ ተዘቅዝቃ ተስቅላ ሌት እና ቀን በምተደበደብበት፤ ሴት ልጅ ደም በምትሸናበት አገር። ሌላም አለ „የህጻነት እና የሴቶች በሚ/ ር“ ማዕረግ። ምስል ይባል የተቃጠለ ካርቦን ይባል አይታወቅም። አላዛሯ ኢትዮጵያ የልጇቿ ተፈጥሯዊ ስብዕና አንደ ጥንችል የመሞከሪያ ጣቢያ ሆኗል። ግንቦት 20 ድሉ ይሄው ነው¡ሰው አልባ አገር፤ ህዝብ አልባ መንግሥት … የተኖረው እንዲህ ነው።
  • ·         ማጠቃለያ።

ዴሞክራሲ የተፈጥሮ መኖር ፍልስፍና ነው። የመኖር መሪው ደግሞ ሰው ነው። መሪው ሰው ፍጥረት ነው የፈጣሪው። በፍጥረቱ ውስጥም መፈጠረም ተፈጥሮም አለ። ተፈጥሮም እንዲኖር ተፈቅዶለታት የተፈጠረ ነውና። መቼም ዴሞክራሲ ለቀልሃ እና ለድንጋይ ወፍጮ ካልተፈጠረ ለሰው እና ለተፈጥሮ ከተፈጠረ በሰው ውስጥ ያለ ሰብዕና እንጂ በብረት ውስጥ ያለ ጨካኝ እና አረመኔ ሰብዕና ለዴሞክራሲን ግንባታ አይመጥነውም። ያነጥረዋል ወይ አውርዶ ይፈጠፍጠዋል። ሁለቱንም ከሞት የሚያድነው ህሊና ያለው የሀገር ብሄራዊ የቢሮው ተጠሪ ሲኖር ነው። የሰብዕዊነት ታታሪዎች ትንታጎች ሰርተው የማይደክሙ ዜጎችም ሰራተኞች ሲሆኑ ነው። ለገሃዱ ዓለም ሳይሆን ሰማያዊ ዓለምን የሚያልሙ ህይወታቸው የሚያስተምር የቸርነት አንበሎች ሲመደቡበት ነው። ከዚህ ውጪ ከሆነ ግን ልሙጥ ነው።

ክቡር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሆይ!

መልካም ብሩህ፤ ብሩክ የስኬት፤ የመደማመጥ ዘመን ለጠ/ ሚር ቢሮ እንዲሆን ከህሊናዬ እመኛለሁኝ። ለነበርን ዘንካታ የመደማመጥ ጊዜ እና ለሚሰጠኝ በቂ የልባዊነት ጊዜ ህሊናዊ ምስጋናዬን ዘለግ ባለ ትሁታዊ ቅንነት አቀርባለሁኝ። ድንግልዬ ጥላ ከለላ ትሁነዎት። ይኑሩልን።

         አልአዛሯን ኢትዮጵያን አማኑኤል ይጠብቅልን። አሜን!   
         ኑሯችን ካንፓሳችን እና ኮንፖሳችን ነው።
         ጊዜ ታሪክን ይሠራል!
         አብዩን ተስፋችን ይጠብቅልን አዶናይ! አሜን!
  „ዩቱብ።“
  „kenebete ቀንበጥ“ ብሎግ።
  እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
  ሥርጉተ© ሥላሴ

                                     

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።