? ጎንደር ተገበሪ - ሰለምን ትመሪ?!
ጎንደር ተገበሪ - ሰለምን ትመሪ? ሙተሽ ተወረሪ ደግመሽ ተመርመሪ?
„የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፣---
እንሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን
በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤
በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል።“
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፮)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 30.07.2018
(ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ?
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርምሪ።
ጎንደር ምኞት ሁኚ ...
የዕንባሽን አንገረብ ታቀፈሽውም፤ ተኚ።
የዘመናት ማገዶ ስላንቺ መስታውት መንምኖ
ሥምሽን ተዘካሪ ዋይታሽን አዝንቦ
ኡኡታን አንግቦ!
በቁልቁለት መንገድ ፈትልሽ ቢገመድም
ዕንባሽ ዘመን በልቶት መብቀሉ አይቀርም።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ?
ጆንያሽ አፈር ነው በእሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርምሪ።
መደመርሽማ ጥንትም የነበረ
መቀነሰሽ ቢሆን ታሪክ ተረተረ።
ተጋድሎሽ ብዙ ነው አንቺው አሳርኛ
የመከራ እትብት የደመሯ ማኛ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ?
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትፈረፈሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
„ደመህም ደሜ ነው“ ብለሽ ሥትመሰከሪ
„ድምፃችን ይሰማ“ ብለሽ ብትገሪ
በሰኔል በቹቻ እንዲህ ትሰበሪ?
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ?
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ሰንደቄ ይከበር የነብያት ሥራ
ሉላዊት ይደነቅ የህብርነት ብራ
ደንበሬ ይከበር የማንነት ዓውራ!
ነበረ ነፃነት መከራሽ ሊገራ
ታዲያ ምን ይሆናል አንቺ የውንት ጎመራ
የቂም መወጣጫ የሩምታ ደመራ!
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ?
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ቀና ለማለትም ተስፋን ስትቆጠሪ
በሰኔል በቹቻ እንዲህ ስታበሪ
ዝክረ ታሪክሽም የቹቻ ተመሪ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ስለምን ይመሰከር አንቺ ማተበኛ?
ስለምን ይነገር አንቺ ታሪከኛ?
አፈሩን ቢያለበሱሽ አንቺው ነሽ ሁነኛ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ምን አለ? ምን አለ? በጥቅል በዋጁ ከካርታ ቢያወጡሽ
ምን አለ? ምን አለ? ሜርኩሪ ቢልኩሽ፤
ምኸዋሩ ከሆን የጥንት ነው በኩርሽ።
ሥህነ - ፈጠራ፤ ሥህነ - ውበቱ
መቼ ተሸምቶ እንዲህ በሟተቱ
የደም ሥንኝ ግሡ ቀምር ነው እትብቱ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ቃል ኪዳን አትበይኝ ላንቺ አልተፈጠረም?
አደራ ከፈይም ለአንችው አምልታደለም
ውለታንም ስጡኝ ብለሽ አታማሪ፤ ላንቺ አይሆንሽም
ወጪት መሰበሩ፤ ይኸው ነው ሥጦታሽ ልጓሙ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ
ደግመሽ ተመርመሪ።
መቼ አለሽ በኩሉ አንቺ አለሁኝ ብትይ፤
መቼ ኑረሽ አውቀሽ በህገ - ህሊና
መቼ ተደምመሽ በመንፈስ ዘበና
መቅጃ አይሉሽ ድልድይ የወይታ ቤተኛ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ሰላማችን አጥተን ከንቺ ስንፈጠር
ኑሯችን ተነስተን ከደምሽ በከንፈር፤
መክሊታችን ሆኖ የሴረኞች መክሰስ
መፈጠረ ሆኖብን በመቃብር መክሰል።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
ደግመሽ ተመርመሪ።
ስለምን ባይሆንም፤ ባይሆን ምንአለበት፤
ባይሆንም ስለምን፤ ኧረ ምንአለበት
በምንአለባት ሲሆን ኑሯችን ለአመድ
ደመ መራራ ነን የለንም ገድ መንገድ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ሆዴን እዬባሰው ስለንቺ ሳነሳ
ስሜትን ሲገርፈው መገለል ላይከሳ
ስመኛው ሳይበቅል አፈሩን አገሳ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
አሰንገላ ሆኖ ቤቴ በድርድሩ
እንቆቆው በሸማ ሲጣራ ማደሩ
ሃሙስ ዕልፈት ሆነ መስቀል ተደምሮ
በጠራራ ጸሀይ ሰንበት ተዘርሮ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
ደግመሽ ተመርመሪ።
ልረሳሽ እልና ሥነ - ቅርስ አለና
ልተውሽ እልና ሥነ - ደም አለና
ላልፍቅሽ ምዬ፤ አይሆንም እልና
ስመለስ እምለስ በዕንባ ጎዳና።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ሳይውቅሽ ለኖረው ማክሰኝት እንፍራዝ
ሳያይሽ ባጅቶ ቀኑ ሲደበዝዝ
ሚደያው ጎበኘሽ ለግዞቱ መዘዝ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
ደገመሽ ተመርመሪ።
አታስፈልጉንም፤ ብንባል ምንአለ ዕብለት ተዘልሎ ?
አንይችሁማ ኑረንበት የለ የመኖር አለሎ፤
ዕለታት ታትመው ዘመንም ለግሞ፤
አዬነው መሰቀል ላይ እኛነት ተግሎ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
እንዲህ በመባቻው ሁሉ ሰናይ ለቅሞ፤
በደሙ ገብሮ መባቻን አለምልሞ፤
አሁንም እሱ ነው ቀራንዮ ቀልሞ።
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
ነገም ተገበሪ የነገ ተረኛ
ጅልንት ብልሃቱ ጎንደር ተረበኛ፤
ጥበቡ ተረክቦት የድንኳን ሁነኛ
ርቱ ትንታጉ ከአፈር ይተኛ!
ጎንደር ተገበሪ
ስለምን ትመሪ
ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ
በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ...
ደግመሽ ተመርመሪ።
· መታሰቢያነቱ ለግፍ መመኮሪያ ለሆነው ለሊቀ ሊቃውነቱ ለኢንጂነር ስመኛው በቀለ ይሁንልኝ። 30.07.2018 ሲዊዘርላንድ።
ጌታ ሆይ! እባክህን በቃችሁ በለን! ለኢትዮጵያ ህፃናት ስትል እንኳን።
ነፍስ ይማር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ