የአዲሲቱ አትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በዶር አብይ ዙሪያ መግለጫ አወጣ!
ዛሬ ትንሽ ቀለል አለኝ።
„እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጎም
የሚያውቅ ማን ነው?“
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
20.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
Action is everything!
Blessing!
ተመስገን ብዬ ልጀምር፤ ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ
የኢዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራች እና መሪ ዛሬ አንድ መግለጫ በዶር አብይ አህመድ ዙሪያ አውጥቷል። ከ እንግዲህ መተኛትም በወጉ መመገብም ይችላለሁኝ። አድራሻው ያልታወቀ መከረ የተሸከመው ተስፋ እጅግ አሳሳቢ ነበር።
ይህ መቼም ለእኔ እንደ ልዩ ሽልማት ያህል ነው ያዬሁት።
ምክንያቱም አቶ ኦባንግ አቅም ስላለው እሱ ከተጋ አንድ ጭብጥ ላይ ይደረሳል ብዬ አስባለሁኝ። አሁን ተስፋ ማድርግ ይቻላል። ከአግታው
ለማስወጣት። በጤንነታቸው ዙሪያም አቅም ያለው ጫና ለመፍጠር።
ያው የውጩን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በማስተባበር እረገድ
ሃላፊነት ከተሰጣቸው ሦስት ኢትዮጵውያን መካክል ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ አንዱ ነው። እሱ የእኔን አቋም ይዟል። ይህ መቼም ያልጠበቅኩት
ነገር ነው።
ምክንያቱም ፕ/ አለማርያም ባ፤ፈውም „አክ ወሬ“ የሚል አውጥተው ነበር ከሰሞናቱም ያንኑ የሚያጠናክርም ጽፈዋል። በእንግሊዘኛም
በአማርኛም ተተርጉሟል። የቀደመውን እንዲያውም ዓለምአቀፉ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ 100% እርግጠኛ አደረገኝ፤ ፌክ ወሬው በዜሮ ተባዛ
ብሎ በዛ በባለቀናው በነጎድጓዳማ ድምጹ ሁሉ አቀናብሮ አቅርቦታል።
- · የመጣላት ሱሰኛ ሆነናል።
የሚገርመኝ ግን በሁለቱም ጎራ ትርፍ ነገር መጻፉ
ነው። ፕ/ አለማርያም ቢሆኑ በቅንነት ፌክ ወሬዎች ከተደቀነው የሃላፊነት አንጻር እንዳያዘናጉ ነው፤ ዶር ኦባን ኢትዮጵያ ሜቶ ደግሞ
ተዘናጋተን ተስፋችችን እንዳናጣ አዌርነስ ይኑርን ነው።
ሁለቱም እኮ ጸረ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ታጋዮች ናቸው።
የፖለቲካ የአቋም ልዩነት አይደለም የአሁኑ የሁኔታዎችን ጭብጦች በመቀበል እና ባለመቀበል ብቻ ያለ የሃሳብ ልዩነት ነው። ሁለቱም
እኩል ናቸው።
ለእናት አገራቸው ኢትዮጵያ ሁለቱም ብርቅ ሊሂቃን ናቸው። ሁለቱም የሰባዕዊ
መብት ረገጣን ተቃዋሚዎች ናቸው። ዘመናቸው ሙሉም ለዚኸው የሰጡ ናቸው። ሁለቱም ለነፃነት ትግሉ ያስፍለጉናል፤ ሁለቱም በልባችን
ያላቸው ሥፍራ አኩል ነው። ሁለቱም ልናጣቸው የማንሻቸው ኢትዮጵያዊ ናቸው። ሁለቱም የሚታገሉት ለተስፋይቱ አገር እንጂ ለሥልጣን
ለምንትሶ ለቅብጥርሶ አይደለም …
ስለሆነም አንዱን አቅርበን ሌላውን የምንገፋበት፤
አንዱን ገፍተን ሌላውን የምናቀርብበት አንጀት ሊኖርን አይገባም። ብቻ ጠብ መፍጠር ሱስ ሆኖብናል። እጅግም ስስ ሆን።
ፕ/ አለማርያም የሚሉት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ደህና
ናቸው ሥራ በዝቶታባቸው ነው ማለታቸው እና ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ደግሞ ደህና አይደለም ሁኔታው አላማረኝም ማለቱ ሁለቱም ያቀረቡት
ሃሳብን በቅንነት ማዬት ይገባል።
እኔ ስለምን ከእናት አገራችን ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመማር
እንደማንፈቅድ ነው ግራ የሚገባኝ። አሁን ኢትዮ ሱማሌ ላይ ከ9 ያላነሱ አብያተ ቤተ ክርስትያናት ተቃጠሉ፤ የሃይማኖት አባቶች ታረዱ
ግን የኢትዮጵያ ህዝብ አመራሩ የፈጠረው እንጂ የእስልምና እምነት ሊቃውንታት የመሩት አይደለም በማለት በጸሎት ነው የተጋው።
በዬአካባቢው በሚነሱ ግጭቶችም ህዝባችን በመቻል እረገድ
ልክ የለውም፤ የሻሸመኔው ግፍን ማዬት ይቻላል። ተገድሎ እንደ ገና ቁልቁል ተዝቅዝቆ ያ ሁሉ ህዝብ ተመልካች ሲሆን አንድ ሰው ተው
ያለ የለም ይህም ሆኖ ህዝቡ ተንዶ ወጥቶ መሰሉን እርምጃ ለመውሰድ አልሞከረም። መቼም ሁሉም ዘመድ ቤተስብ አለው ቢያንስ።
ከ አንድ መርዶ ቀጥሎ ቃጠሎ አለ። ይህ ደግሞ ከሰኔ
16ቱ የፈንጅ ጥቃት ማግስት ጀምሮ ወይ የ እሳቱ ቀድሞ ቀጣዩ ግድያ በወል ወይንም በነፍስ ወከፍ፤ ወይንም ግድያው ቀድሞ እሳቱ
ተከታይ ስናዬው የባጀነው ነገር ነው።
አሁን ዛሬ አንድ ቃጠሎ አዲስ አባባ ላይ እንደነበር ሳተናው ላይ አንብቤያለሁ በቀጣይ ቀናት
ደግሞ ሌላ በነፍስ ወከፍ ወይንም በቡድን ሌላ መርዶ የሞት ይኖርል። ጠብቁት ነገ ወይ ከነገ ወዲያ ደግሞ ሞት ይጠብቃል … ይህ
አዲሱ የህገ ወጡ ሽፋት ቡድን ተግባር ነው። ይህንም ችሏል ህዝባችን ... በዬሳምንቱ ቃጠሎ ... ታቅዶ፤ በዬሳምቱ ጭፍጨፋ ታቅዶ፤ በዬሳምንቱ ግድያ ታቅዶ ...
በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ ሰባት ሱቆች በእሳት ወደሙ August
20, 2018
ሌላም የቆሞስ እንጅነር ስመኛው ህልፈት ወር ሊደፍን
ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት። በመንግሥት በኩል የውሽማ ሞት ሆኗል። ለቀብር እንኳን አልተፈቀደም። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም ችሏል።
ከዚህ ህዝብ አብራክ እና ማህጸን ወጥተን እኛ ትእግስት
ስለምን እንደሚነሳን አይገባኝም። ሁለቱም እኩላችን ናቸው። ሁለቱም የነፃነት ታገዮቻችን ናቸው። በሃሳብ ልዩነት በመጣ ቁጥር አንዱን
ስናቅፍ ሌላውን ስናገል እስከመቼ ድረስ? አሁን ባለፈው ጊዜ የዛሬ ዓመት ይሄን ጊዜ በክብር መንበር ላይ ያወጣነውን ጠቢቡ ቴወድሮስን
ዘንድሮ አውርደን ፈጠፈጥነው? ግን እኛ ምኖች ነን?
አሁንም ቢሆን ደህና ነው አብይ እና መንፈሱ፤ ቤተሰቡም
ሰላም ነው የሚሉትም ቢሆኑም፤ አይ ችግር አለ ሊደረስለት ይባል መዘናጋት አይገባም፤ ነፃነቱን ተቀምቷል የምንለውም ብንሆን ያው
ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ከማሰብ ነው። ይህ የቅንነት መንፈስ እጥረት ካልሆነ በስተቀር አንዱ ቤተኛ ሌላው ውጪኛ የሚያደርግ አልነበረም፤
ወይንም አንዱ አሳቢ ሌላው ግዴለሽ የሚያደርግም አይደለም።
ስለምን? ቅኖች ከሆን በጎ ነገሮችን በአስተውሎት
ማዬት የተገባ ስለሆነ። አንድ ሰው „አይ“ ሲባልም ‚ይሁን“ ሲባልም እኩል ማስተናገድ ካልተቻለ ሚዛኑ የተዛባ ነው ማለት ነው።
ሰው ስብዕናው ሙሉ የሚሆነው ማስተዋልን ሲሆንበት ብቻ ነው።
የሆነ ሆኖ እኔ ሀምሌ 19 ቀን ሌሊት ባዬሁት ህልም
ድንጋጤ ስላለብኝ እና ነገሮችን ደግሞ ሰንሰለታቸውን በማያያዝ የራሴ መስመር ስላለኝ፤ እንግዲህ ሦስት ሳምንት ሊሆነኝ ነው በዚህ
ዙሪያ ራሱን አስችዬ ስጽፍ የባጀሁት።
አሁን ጭንቀቴ ቀሏል አንደ ድርጅት አዲሰቱ ኢትዮጵያ
የጋራ ንቅናቄ ይህን ሃላፊነት ስለሚወጣው ብዙ ነገሮች ቀሎልኛል። ስለሆነም ጹሁፌን በተመስገን ልከውን። መግለጫውን ከሥር አያይዠዋለሁኝ
ከእነ ሊንኩ።
በመጨረሻም የኢዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ላወጣው መግለጫ እና ለንጹህ አቋሙ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ።
ተባረኩ!
ነፃነት ለአብይ መንፈስ እና ለቤተሰቡ!
የኔዎቹ ኑሩልኝ
ቸር ወሬ ያሰማን።
v
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አስቸኳይ መግለጫ
- · ምንጭ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሕዝባቸው ጋር ሊገናኙ ይገባል!
ወደ
ሥልጣን
ከመጡ
ጀምሮ
በተደጋጋሚ
ከሕዝብ
ጋር
ቀጥተኛ
ሲያደርጉ
የነበሩት
ጠቅላይ
ሚኒስትር
ዐቢይ
አሕመድ
ከሕዝባቸው
ጋር
ግንኙነት
ሳያደርጉ
ሁለት
ሳምንታት
አልፈዋል።
ጉዳዩን
በቅርብ
የሚከታተለው
ለአዲሲቷ
ኢትዮጵያ
የጋራ
ንቅናቄ
(አኢጋን)
የጠ/ሚ/ሩ ደጋፊዎችና መላው ሕዝባችን ሁኔታውን እንዲያውቅና አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲወስድ ይፋ ለማድረግ ተገድዷል።
በእርግጥ
ዶ/ር ዐቢይ በተቀነባበረ በሚመስል ስልት ሁለት ሦስት ጊዜ ያህል ለሕዝብ ዕይታ ቀርበዋል። ሆኖም ከወትሮው በተለየ መልኩ ለውጡን አጥብቀው የሚቃወሙና ለማክሸፍ የሚፈልጉ ኃይሎች ያቀነባበሩት በሚመስል የተከናወነው ከሚዲያ ፍጆታ የማያልፍና በጥያቄ ውስጥ ያለውን ሕዝብ ለማርገብ የተሰራ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ሆኖ ነው ያገኘነው። ስለዚህ ሕዝባችን መሪውን የማግኘትና የማነጋገር መብቱ ሊነፈግ አይገባም፤ ይህም ባጭር ጊዜ ውስጥ በጋዜጣዊ መግለጫም ሆነ በፊት ሲደረግ እንደነበረው ዓይነት የውይይት መድረክ መገለጽ ይገባዋል በማለት አኢጋን አቋሙን በግልጽ ያስታውቃል።
ከዚህ
በፊት
“የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ በየሰዓቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መገለጽ አለበት፤ ከእንግዲህ በኋላ በኢትዮጵያ የድብቅ ፖለቲካ አበቃ፤ …. የእኔ ሥራ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት … ማስፈጸም ብቻ ነው” የሚል ቃል የገቡልን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሁም የመደበቅ እና የመሸረብ ፖለቲካ ማብቃቱን ያበሰሩልን መሪያችን ሕዝብ እንዲህ ተጨንቆና ባገሩ ላይ የመኖር ኅልውናው አደጋ ላይ ወድቆ ባለበት ወቅት ከሕዝባቸው ጋር እንደበፊቱ እንዳይነጋገሩ የገደባቸው ኃይል ምንድነው?
የጉራጌና
የቀቤና
ሕዝብ
በተጋጨበት
ወቅት
በፍቅር
ተግሳጽ
ታረቁ
ብለው
መክረው
ወዲያው
ያስማሙ
ብልሃተኛ
ከሕዝባቸው
ጋር
እንዳይመክሩ
የኅሊና
እስረኛ
ያደረጋቸው
ማነው?
ተስፋ
በሚሰጠውና
የወደፊቱን
ብሩህ
አድርጎ
በሚያሳየው
አንደበተ
ርዕቱነታቸው
ሕዝባቸውን
እንዳያረጋጉ
አጣብቂኝ
ውስጥ
የከተታቸው
ጉዳይ
ምንድነው?
ይህንን
የሕዝብ
ጥያቄ
የጋራ
ንቅናቄያችን
ሕዝብ
እንዲያውቀው
ይፋ
ለማድረግ
ተገድዷል።
እጅግ
በርካታ
የሰቆቃና
የመከራ
ዓመታትን
ያሳለፈው
የአገራችን
ሕዝብ
በቅርቡ
በጠቅላይ
ሚኒስትር
ዐቢይ
አሕመድና
እርሳቸው
በሚመሩት
ቡድን
አማካኝነት
ያገኘው
ለውጥ
ጥቂት
ከሚባሉ
ቡድኖችና
ግለሰቦች
በስተቀር
በአገር
ውስጥና
በውጭ
የሚገኘውን
ኢትዮጵያዊ
ያልጠበቀውን
ተስፋ
ያጎናጸፈው
ነው።
በአገራችን
ታሪክ
ታይቶ
በማይታወቅ
አሠራር
እያስተዳደሩን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በየጊዜው ባለማቋረጥ ለሕዝባችን የሰጡት ተስፋና ባጭር ጊዜ ውስጥ የፈጸሟቸው ተግባራት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙትም አገራት ታስቦ የማታወቅ ለውጥ ያመጣ ነው።
ሆኖም
ግን
ዶ/ር ዐቢይ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ በኋላ ሁኔታዎች ተለዋውጠዋል፤ እርሳቸውም እንደቀድሞው ከሕዝባቸው ጋር የሚደርጉትን ግንኙነት በእጅጉ ቀንሰዋል።
በእርግጥ
ዕረፍት
ዐልባ
በነበረው
የአሜሪካው
ጉብኝታቸውና
ከዚያ
በፊት
በነበሯቸው
ጊዜያት
ያለበቂ
ዕረፍት
መሥራታቸው፤
በጤናቸው
ላይ
መቃወስ
ሊያስከትል
እንደሚችል
ማንም
መገመት
ይችላል።
ሆኖም
ዝምታቸውን
ተከትሎ
የወጡ
ሕዝብን
የሚረብሹና
የለውጡ
ተቃዋሚዎችን
የሚያበረታቱ
ዘገባዎች
ሊወገዙ
የሚገባቸው
ናቸው።
ጊዜያዊና
ኢኮኖሚያዊ
ጥቅምን
ከማሰብ
በፊት
እንደ
ሚዲያ
የአገርን
ኅልውና፣
የጠላትን
አካሄድ፣
የሕዝብን
ጥቅም
ማስቀደም
ተገቢ
ነውና
የጋራ
ንቅናቄያችን
በዚህ
ላይ
ትኩረት
እንዲደረግበት ያሳስባል፤ ሕዝባችንም ምርቱን ከግርዱ እየለየ መረጃ የመቀበል ባሕሉን በማዳበር ለእንደዚህ ዓይነት ዘገባዎች ዕውቅና መንፈግ ይገባዋል። ጸረለውጥ የሆኑ ዘገባዎችንም እንዲሁ ዓላማቸውን አውቆ በመልሶ ማጥቃት ሊቃወማቸው ይገባል።
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ወደአገር ከተመለሱ ሁለተኛ ሳምንት አልፏቸዋል። በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ በርካታ የሚረብሹና የሚያስጨንቁ ሁነቶች ተከስተዋል። ለአብነት ያህል፤ እርሳቸው በወጡ በማግስቱ በግፍ ከተገደሉት ስመኘው በቀለ (ኢንጂነር) በኋላ በርካታ አለመረጋጋቶች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ታይተዋል። አሁን እየተረጋጋ ነው በሚባልበት የሶማሊ ክልል በርካታዎች ከመገደላቸውና ከቀያቸው ከመፈናቀላቸው ባሻገር እጅግ ባልተለመደ ሁኔታ እስከ 10 የሚደርሱ አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል፤ ካህናት ተገድለዋል፤ ሻሸመኔ ላይ በሐሰት በተሰራጨ ወሬ አንድ ወገናችን ላይ በቃላት ለመግለጽ የማይቻል አሰቃቂ ተግባር ተፈጽሞበታል፤
በምስራቅ
ኢትዮጵያ
አካባቢ
ከሶማሊ
ክልል
ከተከሰተው
አለመረጋጋት
ጋር
በተያያዘና
በሌሎች
ሰበቦች
በርካታ
ወገኖች
ከቤታቸው
እየተፈናቀሉ
ነው፤
ቤት
ንብረታቸው
እየወደመ
ነው፤
ሕይወታቻውን
ለማዳን
የለበሱትንና
ልጆቻቸውን
ብቻ
ይዘው
እየሸሹ
ነው፤
ከጅጅጋ
አካባቢ
ተፈናቅለው
ሕይወታቸውን
አትርፈው
አዳማ
(ናዝሬት)
የደረሱ
ወገኖች
እዚያም
እየተገደሉና
መግቢያ
እንዲያጡ
እየተደረጉ
ነው፤
የኢትዮጵያ
ሶማሊ
ተወላጅ
ያልሆኑ
በድሬዳዋና
አካባቢው
የሚገኙና
ከጅጅጋ
ተሰደው
የመጡ
በሶማሊ
ልዩ
ፖሊስና
በሄጎዎች
ጥቃት
ተሰንዝሮባቸው ህጻናት ሳይቀሩ ተገድለዋል፤
ቤ/ክ የተጠለሉ እርጉዞችንና እመጫቶችን ጨምሮ በርካታዎች ከዚያ እንዳይወጡ ተደርገው ምግብና ውሃ በማጣት ስቃይ ተዳርገው ከቆዩ በኋላ ስቃዩ በዝቶባቸው ለልጆቻቸው ውሃ ለማጠጣት የወጡ እናቶች ተገድለዋል፤ የተጠለሉበትም ቤ/ክንም ተቃጥሏል፤ በጅጅጋ የነበረው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም ጥቃት ደርሶበት መረጃዎችና ሰነዶቹ ከነኮምፒውተሮቹ ተዘርፈዋል፤ ጽ/ቤቱም ወድሟል፤
በጅቡቲ
በሰላም
ይኖሩ
የነበሩ
ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ሆነው 30ሺህ የሚሆኑ ወገኖቻችን ከጅቡቲ ለቅቀው ወጥተው በውሃ ጥምና በምግብ ማጣት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቴፒ ከተማ በተፈጠረ ሁከትና እስካሁን ባላቆመ ጥቃት ወገኖች እየተገደሉ ነው፤ የጌዲኦን ተፈናቃዮች ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ውስጥ በተፈጠረ አለመረጋጋት በሰላም ከሚኖሩበት ቀዬ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን በላይ ደርሷል።
በምስራቁ
የአገራችን
ክፍል
እየደረሰ
ያለውን
በተመለከተ
መንግሥት
ሁኔታዎች
እየረገቡ
ነው
ቢልም
ዋንኛ
የጥፋት
ኃይል
የሆነውን
የሶማሊ
ልዩ
ፖሊስን
ትጥቅ
ስለማስፈታት
የሚነገር
አለመኖሩ
“ለምን?” የሚል ጥያቄ እንድናነሳ የሚያደርገን ሆኗል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ይህ ሁሉ ሲሆን የእናቶችን እንባ በተግባር ሲጠርጉና ለወገናቸው ደም ሲለግሱ በገሃድ የታዩት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ዝምታ መምረጣቸው የእርሳቸው ባህርይ እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
“ልሞትልህ የተዘጋጀሁ ነኝ” ያሉት ሕዝባቸው “ወዴት እየሄድን ነው? አገራችንስ ወዴት እየሄደች ነው?” የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ተወጥሮ ባለበት ሁኔታ (ለሁሉም ነገር እርሳቸው እየተጠየቁ መልስ መስጠት አለባቸው ባንልም) በአስገዳጅ አጣብቂኝ ውስጥ ካልገቡ በስተቀር ሕዝባቸውን ዝም ሊሉት እንደማይችሉ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ያምናል። ለጋራ ንቅናቄያችን ከሚደርሱን መረጃዎች በመነሳት ይህንን እምነት ሕዝባችንም ይጋራል ብለን እናምናለን።
ስለዚህ
እነዚህንና
ከላይ
ያነሳናቸውን
ጥያቄዎች
ምላሽ
ለመስጠት
ቀላሉ
መንገድ
ጠቅላይ
ሚኒስትር
ዐቢይ
አሕመድ
የአገራችንን
ወቅታዊ
ሁኔታ
አስመልክተው
የአገር
ውስጥና
የውጪ
ጋዜጠኞችን
ሰብስበው
ያልተገደበ
ነጻ
መገለጫ
መስጠት
ይገባቸዋል
እንላለን።
ከሕዝቡ
ጋር
አንዳንድ
ጊዜ
በቀን
ከሁለት
ጊዜ
በላይ
ሲገናኝ
የቆየ
መሪ
ኮሪደር
ላይ
በማነጋገርና
ቪዲዮ
በመልቀቅ ወይም ሕዝብ መግቢያ መውጫ አጥቶ በተጨነቀበት ጊዜ ከቡና ላኪዎች ጋር ተገናኘ ብሎ ዜና በመሥራት “ደኅንነቱን”
ማሳየት
የዶ/ር ዐቢይን ባህርይ የሚገልጽ አይደለም፤ ማንም ሊቀበለው የማይችል ጊዜ መግዣ ነው።
ስለዚህ
ይህንን
የሕዝብ
ጭንቀት
ከላይ
በጠቀስነውና
ባልተገደበ
መልኩ
በቀጣይ
ጥቂት
ቀናት
ውስጥ
ለሕዝብ
ይፋ
እንዲደረግ፤
ሕዝብና
መሪው
እንደቀድሞው
እንዲገናኝ
ለአዲሲቷ
ኢትዮጵያ
የጋራ
ንቅናቄ
ያሳስባል።
ፈጣሪ
የአገራችንን
ሰላም
ያጽናልን፤
ሕዝቧንም
ይባርክ።
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ