ብልሃት የሌለው ቅላት በግራ ቀኙ ሲፈታተሽ።

ተገፊው ማህበረስብ ዛሬም
እንደ ትናንቱ ነገም…  
 „በሚያልፍ ቢዚህ ዓለም የምትኖሩ እናንተም መኳንንቱና ነገሥታቱን
በሚገባ ሥራ ጸንተው የኖሩ ከናንተ አስቀድሞ የነበሩ አባቶቻችሁ እንደዚሁ
መንግሥተ ሰማያትን እንደ ወረሱ ስማቸውም ለልጅ ልጅ ያማረ
 እንደሆነ አሰቧቸው።“ መጽሐፈ መቃብያ ካልዕ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፳፯ „ኃኋ
ከሥርጉተ©ሥላሴ
18.09.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።

ድሃን ስላስጠጋች ቅድስ ቤተ ክርስትያነችን ስትደፈር።

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94354#respond

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች በባህርዳር ከተማ ቤተክርስቲያን ደጃፍ በልዩ ሃይል ተደበደቡ

Ethiopia || የትግራይ ልዩ ሃይል አፍኖ እየውሰደ በደል እየፈጸመብን ነው
Published on Sep 18, 2018
  • ·      ለምን?

ዶር አብይ አህመድ እስቲ ይቆንጠጡ።

„ለምን“ ቃሉ ፍልስፍና፤ ለማወቅ መሻት፤ ለመመርምር መፈልግ፤ ለመፍጠር መነሳሳትን ያመለክታል ...

ቃሉ አቅም ይፈጥራል፤ ግርዶሽን ይገፋል፤ ጨለማን ያስወግዳል። „አይ“ ዕውነት ዕብለትን እንዲበቀለው አቅም ይለግሥሳል። ፍቅራዊነት መርሆ ጥላቻን ይበቀላል። ጥላቻን የሚበቀለው የትምህርት ዓይነት ቢኖር ፍቅራዊነት ብቻ ነው።

ሥርጉተ ሥላሴ ስታድግ አይደለም ወላጆቿን፤ ሊቀ - ሊቀውንት አያቶቿንም፤ የቀለም መምህራኖቿን „ለምን“ ብላ ትጠይቅ ስለ ነበረ እድገቷም ዕውነትን በመፈለግ ላይ ያተኮረ ነበር።

የንግግር ጥበብ መምህሬ ጋሼ አብነት ለምን መምህር ሆነህ ብላኮቦርድ እና ቾክ ትጠላለህ ብዬ ሞግቸዋለሁኝ። መጀመሪያ ደነገጠ ግን በይደር አስተካከለ።

ዶር አብይ አህመድም የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና አንባገነን የመሆን ወይንም የአማራን ሥነ- ልቦናውን የማጫጨት ሰውር ፍላጎት ከሌላቸው ሙግቴ ይደላቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። በስተቀር ግን ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ መንፈስ ለይቼ አላያቸውም።

እዬታዬ ነው ሞጋች የተፎካካሪ ድርጅት የሚባለው ከስሟል በራሱ ጊዜ። አገር ቤት ሲገቡ ሚዲያዎች፤ ጋዜጠኞች ሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶ ማዕከላቸው ሰው እንዲሆን እና እነሱም በዚህ ፍልስፋና እንዲሰክኑ ነበር። የሚታዬው ግን ግልብጥ ኩድኩድ ጉድ ነው። 

እኔ የማያቸው የኢህአዴግ ቅርንጫፍ ሆነው ነው እህት ፓርቲዎች ቢባሉ ይሻላል ተፎከካሪ ከሚባሉ። የሚያስር የምንም የማንፌስቶ ሎሌ ያልሆነው፤ በግል የምንታገለው ግን የተጫነብን የአሞሌ ቀንበር ስሌለ እንሞግታለን። እሳቸውም በምክንያት ሞግቱኝ ስላሉ ቀጣይ ነው ሙግቱ …

እኔ እማልሻው አብዮ ለጠ/ ሚር ቦታ አይመጥንም የሚሉትን፤ አብይ ልምድ የለውም የሚሉትን፤ የሽግግር መንግሥት የሚሉትን፤ የተጽዕኖ ፈጣሪ መንግሥት የሚሉትን፤ ሽብር ነዝተው፤ ህውከት፤ ፈጥረው በግርግር ህግ አጥሰው መንግሥትን ሊገለብጡ የሚያስቡትን ከህግ በላይ የሚታበዩትን ሃሳቦች ነው። 

ወደ ቀደመው እንደ አቦ፤ ቅድስት ተዋህዶ የዓለም ሃይማኖቶችን ሁሉ ብዕር ቀርጻ፤ ብራና ፍቃ፤ መጸሐፍ ጽፋ፤ እውቀት አቅዳ ብቻ ሳይሆን ልጆቿ ሁለገብ ዕውቀት እንዲማሩ ፈቃጅ ፍጽምት የሆነች የዴሚክራሲ ጽላት ናት።

አሁን እኔ ላቅ ያለ ምስጋና ሳቀርብ 10 ዕጣቶቼን አጣምሬ ነው። ሊቀ -ሊቃውነቱ መላክብርሃነት እሚታዬ ከነገረኝ መልካም ነገር አንዱ ስለሆነ። ሜዲቴሽን፤ ዮጋ ለመማር ፈቃዴም ከዛ አንጻር ነው። መጽሐፍም አለ ስለዚህ ሃይማኖት የሚያብራራ እርአሱ ጠፍቶብኛል።

ሃይማኖት የእውቀት ዘርፍ ነው። የማሰብም ልቅና ነው። የመመራመርም ልቅና ነው። ለምሳሌ ቁርዕን በዓለም አቀፈ ደረጃ ድንቅ ከሚበሉ የሥነ ጹሑፍ ጥበብ ልቅና ካላቸው ከ100ዎቹ አንዱ ነው።

ሰማይ እና መሬት የፈጠራቸው ክዋክብት፤ ፕላኔቶች በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዋንኛ የትምህርት የጥበብ ዘርፍ ነው። ለዚህ ነው ሃይማኖታችን የሥነ - ፈለግ የምርምር ማዕከል፤ ሳይንቲስትም ናት የምንለው። 

ፍልስፍና ላይም መጸሐፈ ሄኖክን መመርምር ነው። መጸሐፈ ሄኖክ ሞጋችም ነው። ዕውነት ፈላጊ፤ ደፋርም ነው።„ለምን?“ ብሎ መጠዬቅ ሃጢያትም ወንጀል አይደለምና። አቢ፤ ማሰብ ተፈቅዶልሻል፤ መናገርም ትችያለሽ፤ ማድነቅም ትችያለሽ አንቺ ዜጋ ነሽ ከሆነ መርሆው የአብይ ሌጋሲ  „ለምን“ ብዬ መጠዬቅም ግድ ይላል።

ግድም ባይሆን ሰው ሆኜ ስፈጠር፤ የተሰጠኝ ሰማያዊ ጸጋንም ማንም ሊነሳኝ አይችልም። መከባበሩ ይቅደም ካልተባለ። ስለሆነም ዛሬ እማናሳቸው ነጥቦች ብቻ ሳይሆን ህይወቴን ሙሉ የተጋሁበት፤ የነፃነት ትግል ፓርቲዬ ኢሠፓ ያስተማረኝ ፍልስፍና ርዕዮተ ዓለም ትንፋሹ ራሱ „ለምን“ ነው?

ትናንትም „ለምን“ እንደተባለው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዛሬም ለምን ይባላል ኦህዴድ። ይህ ተንጋሎ፤ ተጋድሞ መልስ ከተሰጠው ከነገ ወዲያ በኦሮሞ ዘመንም እንደ ወያኔ ነበር መባሉ አይቀሬ ነው። ጉዞው መምሰል ሳይሆን በመሆን ውስጥ እዬተሽከረከረ ስለሆነ ...

ኦህዴድ ወደ ብሄራዊ አቅም እንዲመጣ እንደ እኔም የጻፈም፤ እንደ እኔም የሞገት የለም። አሁን ድል ላይ ነው ኦህዴድ ግን ለድል ያበቃውን የአማራ ተጋድሎ እያገለለ ስለመሆኑ ደግሞ በድፍረት ሊነገረው ይገባል።

ታሪኩ የእሱ ብቻ እንዲሆን ማወጅ መደንገግ ነው የቀረው። ህግ ማውጣት እና በነጋሪት ጋዜጣ ለህትምት ማብቃት። ችግር ሲመጣበት ደግሞ „ማንነቱ ያልታወቁ ሰዎች ወንጀል ፈጸሙ“ ሆነ ጨዋታው። 

በይደር ተቀጥሮ ይሆን? ነገም ሌላም መከራ አለ ብለን እናስብ ይሆን? ያሰኛል። ገና በዕንቡጥነቱ ዕውነትን መደፈር ስላልተቻለ። ድሉን ቄሮ ካመጣ ቅልበሳ ሲጀምር፤ ወደ ጭካኔ፤ ወደ እንሰሳነት ሲያመራ ቄሮ ነው ብሎ መድፈር ግድ ይል ነበር። መቼም በጣም የምፈራው አብይ እውነትን እዬፈራ፤ እዬሸሸ ከሄደ ነው። ያን ያህል የጻፍኩለት፤ ያደንቅኩት ቄሮ እዬፈራሁት ነው፤ እኔ ጠና፣ አምኛ፤ ሮቤ አርሲ ስለሚናፍቀኝ በሃሳብ ለመጓዝም ማዕቀብ ጥሎብኛል - ቄሮ ወዮልሽ እያለ OMN ነፍጠኛን መንቀል እያለ። 

የሚዲያ ነፃነት ታዕቅቦ ከጎንደር ማግለል ተጀምሮ እንዳዬሁት አገር ምድሩን እያከለለ ነው ህግ የጣሱ የቄሮ አባላትን፤ እና አዘዦቻቸውን “በስተጀርባ ሌላ ተልዕኮ ያላቸው፤ በገንዘብ የተገዙ“ እዬተባለ ሽወዳ እዬታዬ ነው።፡ዛሬ ገና በጮርቃው ይህ የሚደያ ነፃነት መታፈን ከተጀመረ ነገ ወዮልህ ነው። የሻሸመኔው የታሪክ ዝግጠትም እንዲሁ ... 

ለነገሩ ኦህዴድ እንደ ቀደመው በቅንነት ወስጥ ነውን? ምክንያቱም እያጎላ አራጊ ፈጣሪ የልብ ልብ የተሰጠው መንፈስ የት ላይ እንዳለ እያስተዋልን ነው።

ኦህዴድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ኦቦ አባ ዱላ ገመዳ 27 ዓመት ያልተናገሩትን ሃቅ አወጡ። ኦህዴድ ነፍሱ የሰከነችው በአማራ መሬት ላይ ነው ብለውናል። ተግባር ላይ ተገፍቶ የተሄደበት ግን አልታየዬም። ማለት ብቻ ደግሞ ባዶ ድርቆሽ ነው።  

የሆነ ሆኖ ለ ዐውነት ጥበቅናም እስከዚህ ዘመን ድርስ ግን ይህቺ ትንፍሽ አልተባለችም። አማራ በግራ በቀኝ ሲነቀል፤ ዘሩ ሲጠፋ፤ ሲንገለታ። ባለውለታችን አልተባለም።

ቁም ነገሩ የጣን ኬኛን ሞገድ ለማስቀጠል፤ የአማራን ህዝብ ድጋፍ ለመሸመት ይህ መርህ ነበር። ከሥልጣን ማግስት ደግሞ ለውጡ "ቄሮ እና የኢትዮጵያ ህዝብ" ያመጠቱ ለውጥ ተብሎ በሚሊዬንም አዳራሽ ታወጀ። ጥሎ ማለፍ ማለት ይህ ነው።
  • ·      ሌላም ይታከል።

የቄሮን ጄኒራል አቶ ጃዋር መሃመድን በሚሊዬንም አዳራሽ ባለው የመንግሥት ሚዲያ ሙሉ ሌት እና ቀን ራሱ በልዩ ክብር ሲያስነግሱ አዳምጫለሁ። የደከመ ወጣት ነው። የለፋ ወጣት ነው። ይህ ቢደረግለት ብዙም አይደንቅም። ታስሮ ተንገላቶ ወጥቶ ወርዶ ሳይሆን በማህበራዊ ሚዲያ ነው። ሚዲያ ራሱን ሲሰራ ያዬሁት በ እሱ ነው። ፈጠረው ብል ይሻላል - ለልብ ቅንነት ቢያውለው፤ በሰዋዊነት ቢያውለው ኢትዮጵያዊነት አይገደድም። 

በሌላ በኩል በማህበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኛ እና  የአማራ አክቲቢስት ሙሉቀን ተስፋው ደግሞ ሂድ ክልልህ ይቀበልህ ተብሎ የሆነውን አይተናል። ኢትዮጵያ ለጋዜጠኛ ለጸሐፊ ለአማራ አክቲቢስት ባዕዱ ናትን? ወይንስ አዲስ አባባ የተወሱኑ ዜጎች ብቻ ናትን?

ጋዜጠኛ ሙሉ ቀን እስከ አሁን ድረስ የመንግሥት ሚዲያ ይሁን የአብይ ካቢኔ ዕውቅና ሲሰጡት አልተመለከትንም። ብአዴን እራሱም። ወረቅ ካባ የደረበላቸውን ተመልክተናል። ወርቅ የሸለመላቸውንም። ዕድሜ¡ለአቶ ንጉሱ ጥላሁን ካቤኔ። እን ሙሌ ለዚህ አሁን ለተገኘው ለውጥ ፈርጥ¡ከነበሩ ታሪክ ይፈረደው።

ስለምን? የአማራ ተጋድሎ ከቄሮ ተጋድሎ ጋር እኩል የታሪክ ድርሻ እንዳይኖረው ስለተፈለገ ብቻ ነው። ለነገሩ ዘመነ ኦሮሞ ስለመሆኑም ሌላው ማመሳከሪያም ነው። በውጥኑ ይህን ያህል የሰፋ ልዩነት ከተጀመረ ነገስ ማለት አይቀሬ ነው።

ከዚህ ባለፈ ልባሙ የአብይ መንፈስ ያደረገው ትልቅ ነገር ግንቦት 7 እና ኢሳትን ልዕለ ተወዳደሪ አድርጎ አማራ መሬት ላይ ማምጣት ነው። የአማራ ተጋድሎ የህልውና ትግልን አፈር ድሜ አስግጦ ታሪክ አልባ ማድረግ። 

መቼም የግንቦት 7 ሊሂቃን አማራ ቢሆኑ ይህን አብይ አይደፈረውም ነበር። የግንቦት 7 አብዛኛው አማራር ጉራጌ ነው። አቶ ንጉሱም እንዲህ ሲባሉ አዳምጫለሁኝ። ስለዚህ የወርቅ ካባ ሲያንስ ነው። አንደበት ለሆነም። ይህ ድርጊት ሌላ ክልል ላይ አይደፈሬ ነው። 

እስኪ ባሌ፤ አርሲ፤ ወለጋ ላይ ያሉ ወጣቶችን አቶ ታማኝ በዬነ የግንቦት 7 ልሳኑ፤ ግንቦት 7 ሊሂቃኑ እንዲያወያዩ ይደፈር።  ትግራይ ላይም እንዲሁ።

መወዳጄ፤ መያዣ፤ መመኳሻ አማራ ላይ ግን ያስተዛዝባል። ቤት ለ እንግዳ እዛው ቤቤት ነበር መሆን የነበረበት። ብቻ አማራ ቀና እናዳይል የሚካሄደው ጭነት ድንቅ ፍልስፍና ነው¡

ህም! ትክክለኛው የአማራ ታጋድሎ ስለመጣ ሳይሆን ፔኑን የሚያውቁት ዶር አፈወርቅ ተሾመ ኢትዮጵያ ናቸው። እሳቸውን እማውቀው ዛሬ አይደለም። 

ልክ ዶር አረጋይ በርሄን፤ ዶር ነገዴ ጎበዜን፤ አቶ አብርሃም ያይህን፤ አቶ እያሱ አለማዬሁን፤ አቶ ዮሴፍ መርሻን፤ ረ/ፕ እጅጉን የመድህኑን ወዘተ እንደማውቀው ማለት ነው። በመአህድ ዘመን ነው እኔ ዶር አፈወርቅ ተሾመን እማውቃቸው።

ከዛ በኋላ እንደ ሌላው ለሥልጣን፤ ለማይክ እና ለዝና ጃኬታቸውን ሲቀያይሩ እንደ ሽንብራ ቂጣ ሲገላበጡ አልታዩም። እጅግ ቁጥብ የተሰበሰቡ ናቸው። ይህ ጽናታቸው እኔ አውድላቸዋለሁኝ። ኢትዮጵያ የሚስፈልጓት እንዲህ ዓይነት ሰዎች እንጂ ጃኬት በመቀዬር ፓርቲ ተፈጠረ ሲባል የሚጣዱትን የሥልጣን ጥመኞች አይደለም። ወይንም የማይክ አክሮባቲስቶችን አይደለም። 

ለረጅም ጊዜ ወደ 17/ 18 ዓመት በተደሞ ቆይተው ሞረሽ ሲመጣ ትግሉን ቀጠሉት። አሁን እግዚአብሄር ይመስገን የመአህድ ሊቀመንበር ናቸው። የረጉ ናቸው። ቂመኛም፤ ህግ ተላላፊም አይደሉም። ግጭት ላይ ተሰልፈው አዳምጬ አላውቅም። የሰከኑ ናቸው። የራሳቸውን ሥራ ብቻ የሚታኩሩ ልበ ብርሃንም ናቸው።

አማራም መሪ አለኝ ብሎ በእርግጠኝነት ከጎናች ሊሰለፍ የሚገባ ዳግማዊ ፕ/ አስራት ወ/ደዬስ/ ዳግሚያ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ናቸው።

ለሳቸው ብጣቂ አክብሮትም፤ አትኩሮትም በአብይ መንፈስ ውስጥ የለም። አዝናለሁኝ። አዘኔታዬ ከቁስለት ጋርም ነው። አብዩን እንዲህ አስቤው ስለማላውቅ። አዲስ ዓመት ላይ ሥም ሲዘረዘር ሲዘለሉ አመመኝ።

ጎንደር ባሕርዳር በአደባባይ ሆነ በአዳራሽ የክብር አቀባበል ሊያደርገላቸው የሚገቡ ዕውነተኛው ልጁ እና ክብሩም ናቸው - ለአማራው። አያሳፍሯቸውም። በሌላ በኩል ተብተነው ላሉ አማራዎችም ህይወቱን ስለኖሩት፤ እንዲሁም ስደት ላለነውም ህይወቱን ስለኖሩት መፍቻ ናቸው - የሐረር ልጅ ይመስሉኛል።

በሁኔታዎች አስገዳጅነት ሳይሆን አምነውበት ነው አማራ ነኝ የሚሉት። ይህ ደግሞ ተፈላጊው እና መከራችን ከጫንቃችን የምናወርድበት አውራው አመክንዮ ነው። አማራ መሆን በዕውነት ውስጥ ሲሆን ሽልማት ነው። እኔ ኮ/ ደመቀ ዘውዱን ስፍስፍ ብዬ የምወዳቸው እንዲህ  ለአመኑበት ጽኑ በመሆናቸው ብቻ ነው። እኔ በ አማራ ሊሂቃን ላይ ወጥቼ መስከሬ አላውቅም ነበር። አሁን መገለላቸው ጎርብጦኝ እንጂ። 

አሁን ዶር ለማ መገርሳ ለኦሮሞነታቸው እንዲሁ ናቸው። ጽኑ ናቸው። የ ኦሮሞ ብሄርተኛም ናቸው ዶር ለማ መግርሳ። ንግግራቸው ቶኑ እንዴት እንደሚቀዬር ቶኑ ይናገራል። ኦዶዬነሱ አሮሞ ሲሆን እና ሌላ ቦታ ላይ።

የሆነ ሆኖ አማራነት ምኑ ይጠላል? ምኑስ ይሸሻል? ለወጀብ ጭብጨባ ለከንቱ ውዳሴ ተብሎ? ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ እኮ ኦሮሞ ድርጅት ኦህዴድ የፈጠራቸው ናቸው። ከዬት የመጡ ባለከንፍ ናቸው?

የሆነ ሆኖ ዶር አፈወርቅ ተሾመ አገር ሲገቡ አቀባበላቸው እራሱ የሚዲያ ሽፋን አልነበረውም። የውሽማ ሞት ዓይነት ነው። ሂድ ወደ አማራ መሬት ነው የተባሉት። 

በሌላ በኩል የትኛውም የኦነግ ቅርንጫፍ አገር ቤት ሲገባ በይፋ በአደባባይ መንግሥታዊ አቀባበል መደረጉ ብቻ ሳይሆን ኦሆዴድ ክብር ሰጥቶ አካሎቹን አወያይቷል። ኦህዴድ ሁልጊዜም በተነሳበት ዓለማው ውስጥ የሰከነ ነው። ከ ኦሮሞ በመለስ ነው ሌላው ነገር የሚያሰበው። የ ኦሮሞ ልጆች ስለሚመሩት። 

ኦህዴድ ላይ ይህ ሆኖ ዶር አብይ አህመድ ዲ/ዳንኤል ክብረትን አሰልፈው አማራው የራሱን ልጆች እንዳያወጣ ከፍ ያለ ጫና እዬፈጠሩ ነው። 21ኛው ምዕተ ዓመት ላይ ልክ እንደ 13ኛው ክ/ ዘመን እሰቡ እዬተባለ ነው። እሱም ቢሆን አገር ስላበጀ አማራ ተወቀሰበት፤ ተገደለበት፤ ተገለለበት እንጂ ያተረፈበት ነገር የለም። የማይገናኝ አምክንዮ ነው። 

እስኪ ያሳዩን አዳማ ላይ እንደ ብአዴን የሁሉ ነገር አላፊ አራጊ ፈጣሪ አድርገው ኦሮምያ ላይ የአማራ ሊሂቃን  ያውጡ። ለውጭ ጉዳይ ሚኒሰተርም እጩ ያድርጉ፤ አቶ ደመቀ መኮነን እኮ በአማራ ውክልና ም/ጠሚ ደረጃ የደረሱ የኦሮሞ ልጅ ናቸው፤ ፌድራል ላይ ለጠረን እንኳን የአማራ ውክልና የነጠፈ ነው።  

የሰሞኑን የኦነግ አቀባበል እና ክብርም በብሄራዊ ደረጃ ተመልክተናል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ግን ባህርዳር ተቀመጥ ነው የተባለው። አማራ ናቸዋ መሪዎቹ።

ስለምን ለዶር አብይ አህመድ የፕ/ብርሃኑ ነጋ መንፈስ አቀረበው? ለሚለው ይህ የፋክት ጉዳይ ነው። ካባ አልብሱ ተብሎም ካባ ለብሳዋል፤ ባይሆን የባህርዳር ስታዲዮም ጉድ ሰራ እንጂ። አብይም ነገ ዕድሉ ይህ እንዳይሆን እሰጋለሁኝ። ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር መሰደዱ አይቀሬ ነውና።  

ኦሮምያ ላይ ሆነ ትግራይ ላይ ያለውን ተቀባይነት ያውቀዋል አብዩ …። ግንቦት 7 በሰፊ የመንግሥት ፕሮፖጋንዳ አማራ መሬት ላይ ያን ያህል ሲንቦላካ እነ ዶር አፈወርቅ ተሾመ ደግሞ ብትን አፈር ለማኝ ናቸው። ይህ ለውጥ አሁን ዛሬ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጅማ ላይ እንደ ነገሩን ለውጡ ብሩህ ተስፋነቱ ለአማራ ነውን? እኔ ድርብ ካቴና እየታዬኝ ነው።  

ብአዴን እኮ የአማራ ድርጅት አይደለም ትናንት፤ ዛሬም እዬታዬ ነው። መሪዎቹ አማራ ባለመሆናቸው አማራውን እንዲዋረድ እንጂ እንዲከበር እዬሠሩ አይደለም። በስሙ በአማራው ድርጅት የተቋቋመው ብአዴን ተግባሩ ጸረ አማራ ሊሂቃን ስለመሆኑ ከዚህ ዘመን በላይ ማሳያ ምስክር የለውም። ቢያንስ እኩል ከሌሎቹ ጋራ ለማዬት አለመታደሉ ከንቱነቱን አስመስክሯል - ብአዴን። እንደለመደበት ግርድናውን ለዬዘመኑ ገዢዎቹ ተንበርክኮ ያገልግል - የ"ለምን" ፈሪው ብአዴን 

ነገ የአብይ ካቤኔ እራሱን ያላስከበረውን ሎሌውን ብአዴንን የፖለቲካ ድርጅት ዛሬ ቴስት እዬሰጠ ስለፈተነው እንደ እንዝርት ያሾረዋል። ለነገሩ ጤነ ጥበቃ ሚኒስተር ወክለህ ተጋሩን ላክ ተባለ አደረገው፤ ሌላውንም እንዲሁ ተጋሩን ወከለ በሥሙ በአማራ ሥም ፌድራል ላይ ይንጎባላሉ።  የ አማራ ሊሂቃን ተገፍትረው የሌሎች ሊሂቃን ቁልፍ ቦታ እንዲይዙ ይደረጋል።

ብአዴን አሳፋሪ ድርጅትነቱ ከቀድሞው ይልቅ የዛሬው ጋሬነቱ ይብሳል። እሱ እራሱ በፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ስለመኖሩ ለአማራ ድርጅቶች በትጥቅ ይሁን በሰላማዊ መንገድ ለታገሉት አንድም ቅንጣቢ መንፈስ የለውም። 

የኢትዮጵያ መንግሥት ይታወቃል አማራን በሚመለከት የሄሮድስ መለስ ዜናዊን ፖሊስ አስፈጻሚ ነው የሆነው። የአድማ እስኪመሰል ድረስ።

የትም ቦታ የሚኖሩ፤ ጥቃትን አሻም የሚሉ የአማራ ሊሂቃን ይህን በማስተዋል ሊመረምሩት ይገባል። የ27 ዓመቱ ላይባቃ አሁንም አማራ ለቀጣዩ ኦሮማዊ ዘመን ጋሬ ሁኑ ነው ዓዋጁ። 20 ሺህ የአማራ ወጣት ለሞተለት ተጋድሎ የተሰጠው መፍትሄ ይህው ነው። አሁን አሁን ጥሩነታቸውን ባዬውም አቶ ደመቀ መኮነን እራሱ ብሄሩን የሚወክሉ አይደሉም። 

በዚህ ስሌት ሲኬድ ፈድራል ምክር ቤቱም፤ የጠ/ ሚር ጽ/ቤት፤ የፓርላማው ቢሮ አንድም ቅንጣቢ አማራን የሚወክል የለውም።
ስልጤ ጉራጌ የተሻለ ወሳኝ እና ቁልፍ ቦታ አለው ከአማራ ይልቅ። ምክንያቱም ግንባሩ የዞግ ነውና። ይህ ቀልድ ይቀጥል ነው የሚለው የአብይ ሌጋሲ።
አሁንም እንሱን የ66 ፖለቲከኞች አሰልፎ ነው አዲሱን የ አማራ ወጣት ህሊና ፉዞ እንዲሆን እዬተጋ ያለው። ይህ ኦህዴድ፤ ይህ ህውሃት ላይ አይተሰብም። በጅሉ እና ዘመን በማያሰተምረው አማራ እንጂ።፡

ግን ኦህዴድ ለዚህ ድል ያበቃው ጣና ኬኛ ነው። አማራ ነው ለዚህ ድል ያበቃው። አሁን ትዝም አንላቸውም ለዛውም ፊርማው ሳይደርቅ። እንዲያውም ለመጬው ዘመን አማራ መንፈስ እንዳያቆጠቁጥ ተጫኝ መንፈሶችን በቅደም ተከተል አሰማርተው ቀዝቃዘው ጦርነት አስውጀውበታል።
  
በአማራ ተጋድሎ ፍልስፍና ላይ የአማራ አክቲቢስቶች፤ ጋዜጠኞች፤ ጸሐፊዎች፤ ሚዲያዎች ህዝቡ ራሱ ሰፊ ተጋድሎ አድርጓል። ዕውነት የሆነው ነገር በአብይ ሌጋሲ ሁሉም ተገለዋል። ስለምን?

ልክ ኢህአፓ ቋራ ላይ ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ በዞጉ መደራጀት ይችላል ከአማራ በስተቀር እንዳለው በትክክል አሁን እዬታዬ ያለውም ይሄው ነው። 

ይህ የኦህዴድ መንገድ ግን አያዋጣውም። ሊመከር ይገባል። ጠቅልለን ከተነሳን ፈጣሪም ይረዳናል። የአማራ ሊሂቃን በፖለቲካው መድረክ ተፎካከሪ ሆነው እንዲወጡ አልተፈቀደም። ለዛሬ ብቻ አይደለም 27 ዓመት በዛ መልክ ተኑሮ አሁን ያ ጭቆና፤ መገለል፤ መገፍተር እንዲቀጥል ነው የሚገፋው።

 በመቼውም ዘመን አማራ መንግሥትን የመምራት አቅሙ ተሰብሮ ደቆ ከስሎ ባክኖ እንደቀር ነው ጥረት እዬተደረገ ያለው። እገነጠላለሁ እያለ የሚፎክረውን የራሱን ወገን ዙፋን ላይ አውጥተህ፤ አማራ ነኝ ያለውን እጫናለሁ ከሆነ የሚታይ ይሆናል። በዝምታ ውስጥ ያሉት ቦንቦች እጅግ የከፉ ናቸውና። 

የቄሮ ምክር ቤት ለማቋቋም እዬተሰራበት፤ የኦሮሞ ተማሪዎች ማህበር አቋቁመህ፤ ከዱከም እሰከ አዳማ የ ኢንደስትሪ ከተማ ለማድረግ አገር ምድር የሚያካልል ፕሮጀክት ነድፈህ አማራ መሬት ላይ ግን ከኢትዮጵያዊነት ውጪ አማራ በመንፈሱ እንዲራቆት ባልተጻፈ ህግ ግለት ላይ ነው። 

ሌላው ቀርቶ ዕንባቸውን ለማድመጥ ፈቃዱ የለም - በመንግሥት ደረጃ። ዛሬ እንኳን አቶ ንጉሦ ጥላሁን ንግግር ሲያደርጉ የራያ ወጣቶች የአማራዎችን ዕንባ ማንሳት አልተፈቀደላቸውም። ስለምን? ትግራይ ከተነሳ ኦሆዴድ መከራውን አይችለውምእና። እንደ ሰው እንኳን መሆን አልተቻለም። ስለምን? አማራ በወገኖቹ አይደለም የሚመራው እና።  

አቶ ጃዋር መሃመድ ግን እንደ መልካም አድራጊ በክብር ያውም ከአባ ገዳዎች ጋር ጉብ ብሏል። ማን ከልካይ አለበት። ዘመነኛነት እንዲህ ሲታወቅበት፤ የራያ ወጣቶች ዕንባ ግን ባለቤት የለውም። 

እማዬው ነገር ለእኔ Discrmnation ነው። ትግራይ ላይ፤ አፋር ላይ፤ ቤንሻንጉል ላይ፤ ኢትዮ ሱማሌ ላይ፤ ኦሮምያ ላይ የማትሰራውን ሥራ አማራ ላይ ትጭናለህ። ስለምን? አማራ ተቀብሮ እንዲቀር።

ሥነ - ልቦናው እንኩት እንዲል። አንድ ቀን ኦህዴድ ቀን ጥሎት ቢሠበር ደግሞ ልክ እንደ አሁኑ እንደ ግንቦት 7 እንደሚያደርገው ኦህዴድም በኦቦ አባ ዱላ ገመዳ እንደ ተደረገው የወያኔ ሃርነትን ለማስወገድ በጣና ኬኛ፤ በአባይ ኬኛ እረድታችሁ ነፍሳችን አሰንብታችሁ ነበር፤ ባለውለታችን ናችሁ እና እርዱኝ አይቀሬ ነው። 

ባጣ ቆዬኝ፤ ለጋሻ ጃግሬነት ወይንም ለግርድና እና ለሎሌነት ለእቃ አጣቢነት … ብቻ ነው አማራ የሚፈለገው እንጂ ለ አገር መሪነት፤ ለተፎካካሪነት አይደለም። ከልብ ማሰብ ይገባል። ለማሟያነት ሳይሆን ኢትዮጵያ አገሩ ከሆነች ይህ ሁሉ ሴራ መልክ ሊይዝ ይገባዋል። 
  • ሸፍጥ። 

   
ግንቦት 7 በአውሮፓ ህብረት እና በምዕራብውያን ድጋፍ ኦነግን ታቅፎ፤ ኤርትራን ምርኩዝ አድርጎ ሥልጣን እጨብጣለሁ ባለበት ሰዓት አማራ አለስፈለገውም ነበር፤ የየአማራ መንፈስ ሞገድ ግን የእኔ ነው ብሎ „የነጻነት ሃይል“ እያለ ነጮችን አታለለበት። 

ለዚህ ደግሞ አቤቶ ታማኝ በዬነ ዋንኛውን ተልዕኮ ፈጽሞላቸዋል።
አሁን ዶር አብይ አህመድ አተሙበት። ዕውነቱ ይህ ነው። ስለምን የግንቦት 7 እና የኢሳት አንደበት ሆኑ ለሚለው ማህተሙ አማራ በተጋድሎ የዚህ ለውጥ ባለቤት አይደለም የጉራጌ ሊሂቃን ያመጡት ነው ሚስጢሩ።

ይህም ብቻ አይደለም አማራ የታሠረው፤ ጥፍሩ የተነቀለው፤ የተሸለተው ለፖለቲካ ድርጀቱ ለግንቦት 7 ሲል ስለነበር ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያደረገው ትክክል ነው። ተጠያቂም አይደለም ነው። 

ይህም ብቻ አይደለም የአማራ የማንነት ጥያቄ ሳይሆን የግንቦት 7 ዓላማ ለማሳካት ነው የነበረው ተጋድሎ የዴሞክራሲ ምህዳሩ ይህው ተከፈተ ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ መነካት የለበትም። ራሱን ያሰከበረ ድርጅት ስለሆነ። የቄሮ ትግልም የኦነግ እንዲሆን የተደረገበትም ይህው ነው።

በዚህ ውስጥ የእትጌ ኤርትራ የማድረግ አቅም ማዬት ይቻላል። ታሪኩን የሠራው የኤርትራ መንግሥት እንጂ ኢትዮጵያ ያሉ  የኦሮሞ እና የአማራ አንበሶች አይደሉም ነው ሚስጢሩ።

 ከውስጣችሁ ሆናችሁ መርምሩት። አቶ ዳውድ ኢብሳ አገር ሲገቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ለውጡ "ቄሮ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ያመጣው ነው "ሲሉ የአቶ ሞላ አስገዶም የተጋሩ ድርጅት ደግሞ የ ኢትዮጵያ ህዝብ እና የ እኛ መስዋዕትነት ጭምር ነው ሲል አላግጧል። ስለመኖሩም የታወቀው ዕድሜ ለግንቦት 7 እና ለኢሳት ... ውጪ የሚገኙ የተጋሩ ሰዎች እንኳን የድጋፍ ድርጅት አልፈጠሩለትም ነበር። እንደ ሀውልት እንደተጎለተ ኖሮ አሁን አገር ሊገባ ነው ሲባል ሰምቻለሁኝ። 

ብቻ የድርድሩ ፍሬ ነገር ይህው ነው። ትንሽ ነገር አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍንጭ ሰጥተዋል። የሳቸው ከዶር አብይ አህመድ ጋር ያደረጉት ዝግ ስብሰባ ይህው ነው ሚስጢሩ። 

ስለዚህ ለአማራ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ እንደቆምላቸው፤ ካድሬዎቻቸው የልብሳ ሞዴል ትርኢት ሲሳዩ እኛ ጥቁር እንደለበስንላቸው፤ ፊት ለፊት ወጥተን እንደሞገትንላቸው ቃል ኪዳናችን አክብረዋልን? ወይንስ አንጋሎ አርዶናል?ያ ዝግ ስብሰባ የተደሎተው በአማራ ላይ ስለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለኝም።

 አብይ በዬትኛውም የሃላፊነት ቦታ እንዲህ አማራን አግላይ አለነበርም። ከአኖሌ ጋር የሚነሱ ነገሮች ቢኖርበትም፤ አማራን ፈቅዶ ማግባቱ ራሱን ያሸነፈ ፍጡር ስለመሆኑ በቂ ማሳረጃ ነው። የአማራ ልጅ እንዲኖረው መፍቅዱ ሌላ አብዮት ነው። የ50 ዓመቱን ፍልስፍና ንዶታል። ነገር ግን ማንን ካገኘ በኋላ ተለወጠ የሚለው መመርምር ግን ብልህነት ይመስለኛል። አብዩ ሰው ነው መላዕክ አይደለም። 

ዘመናቸውን ሁሉ አማራን በሚጭኑ፤ በሚያገሉ ፖለቲካዎች አቅማቸውን ያፋሰሱት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቢለቁን፤ ቢተውን ፈቃዴ ነው። „ብንከባባር“ እስር ቤትም ካልጠፋ ሊሂቅ አማራ ሊሂቃን ሥም ነበር በዝርዝር የሰጡት። አሁን ስለተፈቱ አምቄ ያቆዬሁትንም መግለጥ እሻለሁኝ።

ዶር አስፋ ነጋሽን፤ ዶር ነገዴ ጎበዜን፤ አመራሩ የግንቦት 7 ላይ ማን እንዳለ ይታወቃል፤ ነገር ግን አመራር ውስጥ የሌለውን ሳይንቲስት ሙሉ አለም አዳምን መርጠው ነበር ለበለሃሰብ አጋልጠው የሰጡት።

የተቆራረጠ ሰልነበር የቀረ ሊኖር እንደሚችል ባስብም …  
ሦስቱም አማራዎችን ሥም ዝርዝር ለዛ ጨካኝ እና አረመኔ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አሳልፎ መስጠት ስለምን አስፈለገ? ቤተሰባቸው ምን እንዲሆን ታስቦ? 

ወያኔ ሃርነት ትግራይ እኮ በቀለኛ ነው። ገራሚው ነገር አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁን ራሱ ጉዳዩን ሳያጠኑት ነው ዘው ያሉት። አማራ ተጋድሎ እና ግንቦት 7፤ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር እና ግንቦት 7፤ ደጋፊዎቹ እና ግንቦት 7 ምን ላይ እንዳሉ ሳያውቁ፤ ሳያጠኑ ነው ብዙ እላፊ ነው የሄዱት።

እኛን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ካሰደደን በላይ ግንቦት 7 አሳዶናል። የትም ቦታ እኔ ይህን እናገረዋለሁኝ። 

መቼም ሥርጉተ ሥላሴን ላይ የሠሩትን ደባ ግንቦት 7 ያውቁታል። ሙኒክን አይጨምርም። እነሱ ነፍሶቼ ናቸው።
  • ·      ከውልቀት በስተጀርባ። 

ጣና ኬኛ የፈጠረውን ሞገድ እና አብይን እንዴት በፍቅር መንበር ላይ እንዳወጣ ሲታወቀው፤ እሱም በመንፈስ ባዶውን ሲቀር ሁለት ነገር አደረገ ግንቦት 7፤ አንደኛው እኔ በ አብይ መንፈስ ሙግት ውስጥ ስጽፍ ወቅሼ „ህሊና“ በሚል ርዕሰ ጉዳይ በጻፍኩኝ ማግስት በቀጥታ በግንቦት 7 ፈቃድ ደጀን የጀርባ አጥንት ዛርማ የሚባል የወጣቶች ክንፍ ፈጠረ፤ ዝቅ ብሎ ዘረኝነት ላይ ወርዶ ህብረ ብሄሩ ድርጅት ይህን አደረገ - ለነገሩ እንዲህ በግላጭ መሄድ ጎሽ ነው። ኢትዮጵያዊነት ህብረ ብሄር ምንትሶ ቅብጥሮስ እያለ ከሚያባጭል ... 

በአማራ ወጣቶችም የጀመረው ነበር አልተሳከለትም እንጂ። የሆነ ሆኖ ለዛርማ የበላይነት ዶር አብይ አህመድ አንደበቱ ቢባሉ ማገነን አይሆንብኝ። ልክ ሁሉም ሊሂቃን የአማራን የህልውና ተጋድሎ ዘለው እንደሚያደርጉት ለቄሮ የባላይነት እንደታተሩት።  ይህ ዶር አረጋይ በርሄን አይመለከትም።  

የአማራ ተጋድሎ ለቄሮ ድል ጉዝጓዝ ሆነ። ቄሮ ዶር አብይ እን ዶር ለማን ሲፈጥር የ አማራ ተጋደሎ ደግሞ የገዱን መንፈስ አነጠረው፤ ይህ ተረሳ እና የ አማራ ተጋድሎ ባላይ አድርገው 'ዛርማ' ሲያወድሱ ሲቀደሱ ይደመጣሉ። ምን ያህል ሰው ታሰረበት፤ የት የት ቦታ ተጋለ፤ ምን ያህሉ ጥፍሩ ወለቀ? ምን ያህሉስ ተንኮላሸ? በውነቱ ዶር አብይ አህመድ መልስ የላቸውም። እሳቸው ስልጣን ከያዙ ማግስት እንደተፈጠረ ልባቸው ያውቀዋል።

 አሁን ዶር አብይ አህመድ የሚሰሩት የልጅ ልጁ ለማይሆን የድል አጥቢያ ላይ ለተፈጠረ ድርጀት የአማራ የህልውና ተጋድሎ ተንበርካኪ ይሆን ዘንድ ነው፤ አሁን አማራ መሬት ላይ ግንቦት 7 መድረክ ተሰጥቶት እንዲያወያይ እዬተደረገ ያለው። አማራነት ለዛርማ ስገድ ነው። አማራነት አሞሌነት ከሆነ ራሱን ይጠይቅ የአማራ ልጅ በሙሉ። 

በዬትኛውም ድርጀት ሊንኩ አማራ ነው። አማራ ይህን አደረኩ አትበል አገር አበጀሁ አትበል፤ ታሪክ ሠራሁ አትበል፤ መንፈስ ነኝ አትበል፤ ከተባል ለምን ይፈልጉናል? ንጥረ ነገራችን በመጠቃጠቂያነት፤ ለሎነት ከሆነ ስለምን እኛን ይሹናል። ለምን ሁሉችም አይተውኑም።  

ቁምነገሩ በአማራ አቅም ላይ፤ በአማራ መስዋዕትነት ላይ የሌሎች ብሄረሰብ ሊሂቃንን እንዲያወጣ እንጂ አማራነትን እንዲያፈልቅ አይፈለገም። ይህ ጎምዛዛ ዕውነት ነው። ስለሆነም አማራ ለባርነት፤ ለሎነት ወይንስ ራስህን ወክለህ በአቅምህ ልክ ተወዳድረህ ታሸንፈለህ ወይ? ይህ ወሳኙ ጥያቄ ነው።

አሁን ሳጅን በረከት የሉም። አሁን በተወሰነ ደረጃ ሳጅን አለምነህ መኮነን የሉም። አሁን ሳጅን አዲሱ ለገሰ የሉም፤ ያሉት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። እሳቸው ደግሞ የጭቃ እሾህ ናቸው  ለአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ነቀርሳው ናቸው። ሁለቱንም ያሟላሉ። አሪስኛውንም ግንቦታውያኑን መንፈሱንም ተክህነውበታል።

በደቦ አማራን መንፈሱን እዬቀበረቱ ነው ያሉት። ታሪክ አልባም እያደረጉት ነው። የብአዴን ሥ/አስፈጻሚ የሚባለው ለፌድራል ወክሎ የሚልከው እስከ አሁን ተጋሩን ነበር ነገ ደግሞ የሚታዬው ይታያል።

አማራ ለሞተለት፤ ለደማለት፤ ሁለመናውን ላጣለት፤ ከሥራ ለተፈናቀለበት፤ ትዳሩን ለበተነበት ተጋድሎ በኦህዴድ በይፋ  የተሸለመው መገለልን ብቻ ነው። 

በጥቁር ፊት መታዬት ነው እኔ እማዬው ይህን ነው፤ አማራ የህልውና ተጋድሎ ከተፈጠረ ጀምሮ ግለቱ ብልህነቱ፤ አዋቂነቱ፤ የማድረግ አቅሙ ተቀብሮ እንዲቀር ይፈለጋል፤ የዚህ የትናንት ግንባር ቀደም አውራ አርቲስት አቶ ታማኝ በዬነ ሲሆን፤ የዛሬው መንገድ ጠራጊም እሱው ነው። ለእኔ ጥላሁን ግዛው ባምሳያው ተፈጠረ ማለት እችላለሁኝ።  

ኢትዮጵያዊነትን እኔን ማስተማር ድፍረት ነው። ልማረው እምለው፤ ላጣጥመው ብል አማራነትን ነው። አሱን ደግሞ በመገፋቴ፤ በመገለሌ፤ በመጨቆኔ ዕድሜ ለግንቦት 7 አይቸዋለሁኝ። ኑሬበታለሁኝም። ግን ግንቦት 7 እሱን አሳጥቼ ለውጭ መንግሥታት ጽፌበት አላውቅም። ስለምን? ያዋጣኛል ካለ ይሞክረው በሚል … ብቻ … እንጂ አቅም ጠፍቶ አይደለም። በሌላ በኩል ሰብዕናቸውን የማከብርላቸው ወገኖቼም ስላሉበት። 

ግንቦት 7 ለእኔ የጭቆና ድምጽ እንጂ የነፃነት ድምጽ አይደለም። ጹሁፌን ውስጥ ለውስጥ ሲያሰግደኝ፤ በሁለመና ብለክ ሲያስደርገኝ የነረ ድርጅት ነው።

 እማዋይ እንግዲህ ለእኔ ጭቆና አብራ ትባክን። የእህቷን ሰብዕና እና መክሊት አብራ አፈር ምሳ ትቅበር። ዕውነቱ ይህ ነው። ቅንጣት ታክል እኔ ከግንቦት 7 የዕውነት፤ የግልጥነት፤ የመልካም ዜና ፍርፋሬ አልጠብቅም።

አሁን ደግሞ የአብይ ኬኛ ተጋድሎዬ እዬመረረኝ አብዩ ፊት ለፊት ውስጡን እያሳዬኝ ነው። ዶር ለማ መገርሳም እንዲሁ ድፍረት አንሷቸዋል ወይንም ታዳሚ ናቸው በድራማው። እንደ አብርሃም እና አጽብሃም አብረው እንደሚሠሩ ተነግሮናል። ከዚህ ቀደም አቤት ብዬ ነበር ለሁለቱም መልስ ግን የለም። 

በጊዜ ርዝመት የሚፈቱ ጉዳዮች እንደ ተጠበቁ ሆነው ቢያንስ ወልቃይት ጠገዴ ራያ ያሉ የአማራ እንባዎችን ለማደመጥ እንኳን ሁለቱም አቅም የላቸውም። የተገለበጠ ነገር ነው እማዬው። 

አገራዊ ጫና በሁሉ መስክ መኖሩን ባውቅም ከአያያዝ ይፈረዳል፤ ከአነጋጋር ይቀደዳል እንዲሉ አማራን በሚመለከት ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ከሞት የተነሱ ያህል እዬተሰማኝ ነው። ጨቆናችሁን! ተጫናችሁን!

„ራያ የትግሬ ነውን?“ የዚህ ድል ፈጣሪው የቄሮ እና  የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነበርን? ይህንን ለመመለስ ኦህዴድ እንደ ገዢ ፓርቲነቱ አቅም የለውም። 

አማራ ኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ አለ የሚለውን ተረት ተረት መስማት እና መሞገት ልዩነት አላቸው። አማራነት ነጥሮ ወጥቶ ስለሞገተ ብቻ ነው ባጭር ጊዜ ውስጥ ለድል የተበቃው። ነገም …

ነገር ግን አይደለም ትናንት ዛሬ አማራ የመኖር ነፃነቱን እንኳን አልተሰጠውም። ምክንያቱም ተጋድሎው ዕውቅና መስጠት ስለልተፈለገ።

ሌላው ድንቅ ንግግር ደግሞ አትሰቡ የአይቲ ባለሙያዎች አሉን ሁሉንም ልክ እናስገባዋለን ሲል ግንቦት 7 ፉከራውን ሰምተናል። አንደኛ መታበይ ነው። ሲቀጥል ደግሞ … እሱ ያለውን ያህል አማራም አለው። ያ ወገን ለወገን መጨካከኑ ስለሚባል ብቻ ነው ብዙው እዬታዬ የሚታለፈው፤ ተነሱ ከተባለ እሳት የላሱ አሉን።፡
  • ·      ጅልነት።

እኛ በማህበራዊ ሚዲያ እናሸንፋለን? በስንት ፐርሰነት በ2%? ሌላው ይህ አገላለጽ ግሎባል ዓለም ላይ ተቀምጠህ እኛ ብቻ ነው የተማርነው ዓይነት ያስገምታል፤ የእኔ እንኳን ታናሽ ወንደሜ ከፍተኛ የአይቲ ባለሙያ ነው፤ የእህቴ ልጅ፤  የእህቴ የልጇ ባለቤት የአይቲ ባለሙያዎች ናቸው። አማራዎች ናቸው። ወጣቶች ናቸው። ሌላው ያለው አቅም አላቸው ማለት ነው። ከአንድ ቤት ነው አገር ቤትም እንዲሁ አሉ።

 በዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ድርጅቶችም ቢሆን ተደማጭነታቸው ጉልህ የሆኑ አንቱዎች አሉ ቤተሰቦቻችን። ቀላል ሃይል አይደለም አማራ ያለው። ያው እኛ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ የበዛ ትኩረት ስለምናድርግ ብቻ ነው እራሳችን እያስጠቃን ያለነው። አማራነትን ማስረጽ ከሆነ መገፋቱ ሲከረፋ በእጥፍ ይጨምራል። ስልቱ እንደሆን ከእጃችን ነው። ትውስት አንፈልግም። አገር መመራት አይደለም ማበጀቱንም እናውቅበታለን፤ የዕውቀት ቀረፃ ማህደርነቱ ታክሎበት። 

አማራነት አማራ በመሆን ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው። ያ ደግሞ ንጥረ ነገሩ በመፈጠሩ ውስጥ አለ።

  • ·       ብልሃት የሌለው ቅላት በግራ ቀኙ። 

„ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ ተጨማሪ ቋንቋ የማይችል የሥልጣን አካል አይሆንም፤ ያልተማረ ዜጋ አይደለም፤ ከትግራይ እና ከአማራ ሊሂቃን ውጭ ማንንም ኢትዮጵያን የመምራት ዕድል እንሰጣለን የግንቦት 7 ዶክተሪን ነው። ይህ እርቃናቸውን ስላስቀረው፤ አሳምሮ ስለጠቀማቸውም¡ በዛ መክፈል ይችላሉ።

አይቲን አውቀቱን  በሚመለከት ግን እሳት የላሱ የዬትኛውም ብሄር በሄረሰብ አባላት አሉ። ሥልጣኔው እኩል ስለሆነ። በ እናነት ስለማይገደብ ከ እናንተ ሥርም ለችሮታ ጥወራ ስለማይመጣ። 
በሌላ በኩል ዓለም እንደ ግንቦት 7 ጥብቆ ድርጅት አይደለችም። ዓለም ጥልቅ ናት። ዓለምን የሰራት ማሰብ ነው። 

ራሱን ችሎ ማሰብ … ይህን ምን ያህል አቅም እንዳለው ግንቦት 7 ያውቀዋል። አንድም ቀን በሃሳቡ ውስጥ አቅዶ የሆነውን ነገር አላዬነም። በቋሚ ሃሳቡ ውስጥ መንፈቅ የሞላ ቆይታ ታይቶበት አይታወቅም። አሁንም በአብይ መንፈስ ጥገኛ ነው። ሃቁ ይህው ነው። ፍቅሩ ግን ያሰንብትላችሁ ብለናል ... እፍ ብላችሁዋል። 

ግሎባል ላይ የተቀመጥ ድርጅት በማነስ ስሜት ራሱን አሳንሱ አሁን ልሳኑ መሬት ላይ ወድቆ እንዲለምን እሱም በአካል የዘላለም ውሸቱን ተሸክሞ፤ የማይችለውን ኪዳን ሲያስተጋባ ከማድመጥ ባለይ ጤዛነት የለም። የጠላኸውን መተው። በቃ።

ተሟጋች አይስፍለገንም። እኛ ኢትዮጵያ ስለምንል እንጂ እንዲህ እንድንታጠፍ ከተፈለገ ግድ ይላል ዋንኛ አጀንዳችን አማራነትን የማድረግ። ለዬዘመኑ አማራ ተንበርክኮ የሚገዛበት ምንም መንገድ የለም። 

ስላልተወለዱት ልጆች ከፖለቲካ ዓለም መገለል ነው የአብይ ሌጋሲ እዬሰራ ያለው፤ እኛ ደግሞ የቤት ሥራችን ሰርተን ኢትዮጵያ የሁሉ እንድትሆን እንተጋለን፤ አታስፈለጉንም  በአቅማችሁ ልክ ከተባለ ደግሞ … የሚሆነው ይሆናል። ሰላማችን ፍቅራችን እንጂ ጠባችን ለማንም አይበጅም።    

ሌላው ቀርቶ የዶር አብይ አህመድ ካቢኔ የራያን ወንዶች እንባ ማስቆም አልተቻለውም። ከቤንሻንጉል፤ ከራያ፤ ከኢትዮ ሱማሌ የተፈናቀሉት ወገኖች ባለቤት አልባ ናቸው። ይህ ዕውነት ነው።

 ሰሞኑን ለተፈናቀሉ ወገኖች የትምህርት መሳሪያ በት/ ሚር ደረጃ እዬታደለ ነው። ለአማራ ልጆች ግን መፈጠራቸው አልታወቅም፤ ዜናውን ተከታትዬዋለሁኝ። እንዲያውም ቤተክርስትያን ተጠለላችሁ ተብለው እዬተደበደቡ ነው። የት ይህድላችሁ አማራ?

በዚህ ተዛነፍ ጉዞ ነገ ሲመዘን የአማራ ሊሂቃን እስር እንግልት በቀጣይ በሆነ ባልሆነው እዬተሳበበ እንደሚገጥማቸው አስባለሁኝ። 

አሁን እማዬው ልክ ወያኔ ሃርነት ሲመጣ የሚዲያ ነፃነት እሰጣለሁ ብሎ ፎካክሮ ያ ሁሉ ፕሬስ ሲፈጠር ወገቤን ብሎ እስር ቤት እንዳስገባው አይነት ነው።

ለአማራ የመደራጅት፤ አገር የመግባት ጉዳይ „እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ አይነት ነው። ራሱ እኔ ለኮ/ ደመቀ ዘውዱ ጤንነት፤ በህይወት መኖር እራሱ እርግጠኛ አይደለሁም።

የሆነ ሆኖ „ህልም ተፈርቶ እንቅልፍ ሳይተኛ አይታደርም“ እና አማራ መከራው በወለደው መንፈሱ ውስጥ መዝለቅ በዛም ላይ ራሱን በጥራት እና በብቃት ማወቅ፤ በዛም ላይ ጸንቶ መታገል ይኖርበታል።

የመጣው ለውጥ ተመስጥሮ ይፋ ሳይሆን እንዲያዝ ቢደረግም የአማራ ተጋድሎ ለውጥ ስለመሆኑ ሁሉም ያውቀዋል። ከሊቅ አስከ ደቂቅ። ስለዚህም ለውጡ እንዳይቀለበስ ከማንም በላይ አማራ ተግቶ ዘብ ሊቆምለት ይገባል።

ይህ ማለት ግን መሠረታዊ ጥያቄ አማራ በሊሂቆቹ የመመራት፤ ሊሂቆቹ በአገራቸው ፖለቲካ ራሳቸውን ሆነው እኩል እንዲሳተፉ፤ አማራን በቁጥር፤ በመልካምድር፤ በሥነ - ልቦና የመጫን የማቀጨጭ ሳንኮችን መሞገት ያስፍልጋል።

 የዲያቆን ዳንኤል የ13ኛው ምዕተ ዓመት ትርክትን ኦሮምያ ትግራይ ጂጂጋ ላይ ሄደው ይስበኩ፤ የሰሞኑ የ66ቱ አብዮት የአማራ ወጣት እና የሊሂቃኑ ገድላዊ ተስትፎን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለተፈጠሩበት የኦሮሞ ብሄረሰብ በተለያዬ ሁኔታ ለጋብቻው  ትስስር መንደርም ሄደው ያስተምሩ።

እኛ ስለደቀቅንበት፤ ስለሞትንበት፤ ስለተገፋንበት ያ ከንቱ ትውልድ የጫነብን መከራ ስለመሆኑ ጠንቅቀን እናውቃለን። ደግሞ የተጠቀመው አንዳችም ነገር የለም - አማራ።

ኦህዴድን ደገፍን፤ ከኦህዴድ የተሻለ አማራን የሚደግፍ በቀና የሚይ ድርጅት የለም አለን። ባለነው ልክ ቀርቶ  በአንደበቱ ለመመስከር አልተቻለውም። የአንድ እኔ ኢትዮጵያዊ የአማራ ሊሂቅ  ሥም ሲጠራ አልሰማነም።

በዘመን መለወጫ እንኳን አልሰማንም። አላዬንም። ነገም ከዚህ የበሳ መከራን ለመሸከም ሳይሆን ራስን ሆኖ ወጥቶ ሞግቶ ማሸነፍ የአማራ ትውልድ ብቸኛው አማራጩ ነው።

መደራጀት፤ መደረጃት፤ መደራጀት፤ መደረጀት፤ መደረጃት።
ማንም ሰው ከህግ በታች እንጂ ከህግ በላይ ስላልሆን ህግ ማከበር። አማራ ሥርዓት በማክብር እንጂ በአናርኪዝም ሰብዕና ውስጥ ተዘፍቆ እራስን በማጥፋት ወንጀለኛ መሆንን መፍቀድ አይኖርበትም። ለውጡ የራሱ ነው። ለውጡ ግዴታውን መወጣት የሚቸለው ሰላሙ ሳይታወክ ነው። 

ነገር ግን የአባቶቻችን/ የእናቶቻችን ሌጋሲ - ሥነ ልቦናቸውን አዋርደው ሳይሆን የሥነ -ልቦናቸውን ልቅና አስከብረው አገር አበጅተው ቆይተዋል። አሁን ግን ለውጡ አንተም አልነበርከበትም፤ አንተም አላመጣኸውም ስለዚህም መብት አይገባህም አናውቅህም ነው። ዕውነቱ ይህ ነው …
  • ክወና

መሞገት ሰማያዊ ሥጦታ ነው። ዕውነት እንጂ ማይክ አይደለም ሰውን ሰው የሚሰኘው። ሰብዕና ባልከው ልክ ሆነህ መገኝት ብቻ ነው፤ ሰው ነህ እንሳሳ አይደለህም የሚያሰኝህ። ሰው መሆን ደግሞ ከግልጽነት መነሳት ያስፈልጋል። 

እስኪ ኦሆዴድ አማራ መሬት ላይ የሚስበከውን ኢትዮጵያዊነት መሬቱ ላይ ያስፍን በአሁነ ምርጫ ደግሞ ኦሀድድ ውስጥ ከጽ/ቤት ሃላፊ ጀምሮ ባሉ ቁልፍ ቦታዎች በክልሉ የታወለዱነት አማራዎችን የሚመጥኑትን እስኪ ያሰመርጡ እና እንይ። ሰው ቁስል ይህን ያህል ሩቅ ከሚሄድ? ግንቦት 7 የክብር እንግዳ አድርጎ በቅድሚ መጥራት የነበረብት በጉባኤው ኦህዴድ ነው፤ እትዮጵያዊ ሆኛለሁ እያለ ስለሆነ። 

አቶ ነዕምን ዘለቀ ቄሮ ውስጥም እኛ አለን ሲሉ በቢቢሲ ሃርድ ቶክ ላይ ነግረውን ነበር፤ ዝምድናው ከዚህ ላይ ውል መዋሉን ያሳዬን እስቲ ...ሰፊ አዳራሽ ላይ ቄሮን ሰብስቦ ግንቦት 7 እንዲያወያይም ይፈቀድለት። እንዲወዳደርም።  

በ ኦህዴድ በ አማራ ክልል ብቻ ለይቶ አቅዶ እና አስልቶ እሱን የሚወዳደር አዲስ ትውልድ አማራ መሬት ላይ በ አማራነቱ ኮርቶ እንዳየውጣ ከሚጫን፤ ይህን ያህል ትንፋሽ የሚያሳጣ አሳር በላይ በላይ ከሚጭን። 

የአሁን ጉዞ ያዬሁት ሰላማዊ የሆን ግን አቶ አባይ ወልዱ በብሄራዊ የግዛት ንግሥና መብታቸው ጎንደርን ጥሰው ገብተው እንደ ደፈሩት ዓይነት ነው እኔ የሚሰማኝ ...

 ሁሉንም እንችላለን ዓይነት ... ይህ በራስ ላይ ነው መሞከር የነበረበት፤ ግንቦት 7 በራሳችሁ ሜዳ እንዲሞግታችሁ ፍቀዱ ኢትዮጵያዊነት፤ አንድነት ከዚህ ይጀምራል፤ ባለቀ ሰዓት "የኛው ወገን አብይ፤ አብያችን" እዬተባላችሁ አይደል?  

ሁሉን አስደስቶ የሚኖረው ማን እንደሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀዋል። የሰለጠነው ዓለም የጥበብ ሰው ግን ሥልጣን ያዙ ብሎ ሆ! ብሎ የጥበብ ሰው ፕ/ ትራንፕን አልደገፈም። ይልቁንም የቀድሞውን ፕ/ ባራክ ኦባማን የልቡ ጽላት አድርጓቸዋል።

እኛ ግን መልካም ሲሆኑ መልካምነታቸውን መግለጽ፤ ግድፈት ሲሰሩም ያንኑ በመዘነ ልክ መሞገት ተፈጥሯችን ሆኖ የማዬው ግን ግልብጥ ነው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ሃቅ ሲኖር ፊት ለፊት ወጥቼ የምማገደውን ያህል መሬት መውደቅ ግን እኔ የመይሳው ልጅ አላደርገውም።

በሠራው ልክ ቆርጦ በተገኘበት ውስጥ ሳከብረው በሽራፊ ልብ አይደለም፤ ተንበርክኬ ሻማ አብርቼ ጸልዬ ነው።  የዕውነት አድርጌ ነው።

  • የቤት ሥራ ለዶር አብይ አህመድ።

አሁን እምሞግታቸውን ጠ/ ሚር አብይ አህመድን፤ ዶር ለማ መገርሳን፤ ዶር አንባቸው መኮነን፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ሥርጉተ ሥላሴ ትቢያ ውስጥ ያለች ሴት ኢሳት እና ግንቦት 7 ሲያብጠለጥላቸው፤ ኦህዴድ አከርካሪው ተሰብሮ ሽባ እንዲሆን ሲፈርድባቸው፤ እናንተ አገር የመምራት አቅም የላችሁም ልጆቻችሁን እዛው ሆናችሁ ኢትዮጵያዊነት አስተምሩ ለእኛ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ግን ትጉ፤ ወያኔን ጣሉ እና እኛም አስቀምጡ፤ የዛን ጊዜ የታሪክ ጀግና እንላችሁለን እያለ ሲታገላችሁ፤ ፕሮዎቹ ፎቷቸውን ሊለጥፉ ሲጸይፉ በነበረበት በዛ የወካባ ሰሞናት ሥርጉትሻ  ምን ብላ ለCDU እና በቀጥታ  ለጀርመኗ መራሂተ መንግሥት ለመቻቻል እናት ካንስለር አንጌላ ሜርክል ጻፈች ብለው ይጠይቁ? በካንስለሯ ጀርመን ተጋብዘው የለ፤ በአካል ሊያገኟቸው አይደል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ስለ ድምጽ አልባዎቹ  የኢትዮጵያ ሴቶች ዕንባ ምን ላከችለዎት ብለውም አክለው ይጠይቁ? በታሪክ ያለነቡትን የሙግት ሚስጢር ይነግሮዎታል። 

ሌላም አለኝ አንድ ቀን በተባበሩት መንግሥታትም ጽ/ቤትም የቀድሞ ዋና ጸሐፊ Ban – ki – moon ጋር ካተገናኙ  ቀረብ ብለው እናንተ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር ትሠሩ በነበረበት ጊዜ ማለት ሙሉ መንፈሳችሁ፤ የዛሬው ያው ግንባሩ ውስጥ ቢኖረም አንጻራዊ ስለሆነ ሥርጉተ ሥላሴ የምትባል ሴት፤ ከሲዊዘርላንድ የሬቻን ጭፍጨፋ በሚመለከት ምን ላከችለዎት በርጀንት ብለው ይጠይቋቸው።

የሥርጉተ ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ነው የሚላከው እንጂ መሬት ላይ ጊዜ ሰጠህ ብላ በመነጠፈ ወይንም ግደፈት ስታይ መሃያ እና የክብር ቁርጥራጭ የሆቴል ቢል ይከፈልልኛልብላ ዕውነትን የምትገፋ ሴት አይደለችም። በመታምነው አውነት ልክ ወስጥ የበቀለች የጸደቀች እናም ያፈራች ናት።

ስለዚህ ለእኔ ኢትዮጵያዊነትን አዬሁት፤ ኖርኩበት የምለው በራስ ውስጥ መኖርን ነው። እንደ እስስት አለመገለባባጥን ነው እንጂ ለመጣው ሁሉ በዬዘመኑ የአንድ ድርጅት ልሳን እና መንገድ ጠራጊ መሆንን አይደለም። ምንግዜም ሰው እና ተፈጥሮን ማዕከል ማድርግ እንጂ የፖለቲካ ትርፍ እና ኪሳራ የዝናን አጀብ አይደለም። 

ስለሆነም ዛሬ አማራን እንዲህ ሲገለል፤ ካመጣው ለውጥ ተጠቃሚ እንዳይሆን የተጋድሎው ታሪኩ ሲሰረዝ ደግሞ ለምን ብዬ መጠዬቅ ግድ ይለኛል። አማራም ባልሆንም ይህን አደረገዋለሁኝ። ሰውኛው ተፈጥሮዬ ይህን እንዳደርግ ያስገድገደኛልና።
  • ·      ኢትዮጵያዊነት በክትር የተሠራ የደንገል ቤት አይደለም።

ሌላው የሚገርመኝ የግንቦት 7 ኢትዮጵያዊነት ነው።  የኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ፍልስፍና ፕላኔት እኮ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ነው፤ ስለምን ድርጅቱ አኔን አሳደደኝ? ለዚህም ነው ግንቦት 7 የብሄራዊ ሰንደቅዓላማውን ክብርም፤ የኢትዮጵያዊነት ፍልስፍናም የመሸከም አቅም፤ ሞራልም የለውም የምለው። እንዲያውም ለእኔ ያልተተረጎመ የፖለቲካ ድርጅት ነው ባይ ነኝም።

እርግጥ ነው በሎጂክ ደረጃ ለአማራ መብት ለመታገል አማራ መሆን አያስፈልግም። ልክ የኦሮሞ ፕሮቴስት ሲመጣ ብረስልስ ላይ የኦሮሞ ልጆች በተገኙት እኔ ቢሸፍቱ ተውልጄ ቋንቋውንም ባልችልም ኦሮሞ ዘርም አለበኝ እንዳሉት ጨዋታ ነው አሁን ፕ/ ብርሃኑ ነጋ እዬተጫወቱ ያሉት። "ለአማራ መብት መታገል አማራ መሆን አያስፈልገም" የሚሉን። እስኪ የእስከ ዛሬውን ንግግረዎትን ይመርምሩት አማራ አለ የሚል አለውን? ከ አዳራሹ ውስጪ ቃሉን እራሱ በመጠቀመዎት ሲቀፈዎት ውሎ ያድራል።

አማራ አይደለም አካሉ በመንፈሳቸው ውስጥ አለን? ቀዩን ጃኖ ሲለብሱ አዘንኩላቸው። ጫኗቸው ይበላል። ሌላው ፍልስፍናው እንደዛ ነበር። ግን ጨቋኝ ተብሎ የተሳለን ማህብረሰብ ሰብዕዊ መብቱ ተረገጠ ብሎ የጮኽ አንድም የሌላ የፖለቲካ ድርጅት  ሊሂቅ አላዬንም፤ ለዛውም ከግንቦት 7 ውስጥ። ሰማይ ላይ መርከብ ክንፍ አውጥቶ መርከብ ይሄዳል ነው። 

እንዲያውም በይፋ እና በአደባባይ ጭቆናው የሁሉም ነው ነው ስናዳምጥ የኖርነው። ከዚህም አልፎ አሁንም እዬገዛ ያለው አማራ እና ትግሬ ነው አለበት። ይህን የአማራ ሊሂቃን ደክመው ነው እንዲጠራ ያደረጉት።

ለዛውም ከዛም በፊት አውሮፓ ህብረት የወያኔ ሃርነት ትግራይ የፈጸመውን ግፍ ያጋለጠው ውብ ዶክመንትሪ ፊልም እንዲገለበጥ ተደርጎ ነው ድራማ የተሰራው። መረጃው አለን። 

እንግዳ ነን ተቀበሉን መባሉ ግን ከፖለቲካዊ ትርፍ እና ኪሳራ ውጪ ወላጅ እናቴ አንጥፋ ጎዝጉዛ ብድግ ቁጭ ብላ ግንቦት 7 እንደ ተፈጥሮዋ ብታስተናገድ ደስታውን አልችለውም። ጎንደርም አገሩ ነው። እናቴ ሰው ወዳጅ ናት። ኤርትራ ሠራዊታቸውን ሲፈናቅል 10 የሰራዊቱ አባላት ከእናቴ ቤት ነበሩ ያረፉት።  ለግንቦት 7 አባላትም የአማራ ወገናቸው ነው። ሸፍጡ፤ ሴራው ነውን የምጸዬፈው። በሌለቡት አመክንዮ አለን በዚህ ዕድሜ? ለዬትኛው ዕድሜ? 

ከዚህ ባለፈ ለፖለቲካ ንግድ ግን ስለ ቅንጀት ብትጠይቋት እናቴን የቅንጅት ደጋፊ ስለነበረች አቅመ ቢሶች የተሰጣቸውን ክብር በወጉ ለመጠቀም ከሰፈር ፖለቲካ ያለውጡ ብላ ነው ለእኔ የነገረችኝ። እንዴት ስንት ሚሊዮን ህዝብ ሊመሩ እንዴት አንድ  የአቶ ልደቱን ባህሬ መቻል ያቅታቸዋል ነበር ያለችኝ።  

ስለዚህ ስለ ግንቦት 7 ባታውቅም አሁን ስለማላገኛት ግን ስለ ቅንጅት መነኩሴዋ እናቴ ትሞግተዎት ነበር።

ግንቦት 7 የሚታገለው አቅሙን ስለሚያውቀው ተፎካካሪ ሆኖ እስከ ዘላለሙ በአማራ ሊሂቂ ትክሻ፤ በአማራ ህዝብ ድልድይነት እራሱን ማውጣት ነው። 

አማራ በሊሂቁ እንዳይመራ የሚፈልግ አማራ መንፈሱ እንዲሰመጥ የሚፈልግ ድርጅት ነው ግንቦት 7። ለነጮቹ ህሊና መርዝ ሲመግብ እንደኖረ እሱም ያውቀዋል እኛም እናውቃዋለን። ሰብዕና ማለት ለእኔ መማር አይደለም። እውነትን መድፈር እንጂ።

ሰሞኑ የክብርት አና ጉምዝ የቢቢሲ ቃለ ምልልስ በቂ ነው ግንቦት 7 በማን ላይ ምን ዓይነት ምልከታ እንዳለው። የአማራ ታገድሎ ገኖ ሲዎጣም እንዳሻው ቀኑን በሚያሰወስንበት ጉባኤ አንድ የአማራ ሊሂቅ ስለምን እንዲገኝ አልተደረገም?
                   የአማራ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ።

ጀግናው የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ሊሊሳ ፈይሳ ከአትላንታው ጉባኤ እንዳይገኝ ቀኑ ተሰልቶ ማህበረሰቡንም መንፈሱን ከሁለት ለመክፈል የተሠራ ትዕይንት ነበር። 

ይልቅ መሰሉን ዶር አብይ አህመድም የአርቲስት አቶ ታማኝ በዬን የሠራላችሁ በዚህ ስሌት ነው። ከሁለት ነው መንፈሱን የተረተረው። እኩል እድርጎ ተወዳዳሪ አድርጎ አወጣላችሁ። አሁን እሱ የትኛው ይመረጥልኝ እንደሚል ያዬው ሰው።

መንፈሱን እኮ ረስታችሁት ነበር እሱም ከማህበረሰቡ ፍቅር እዬራቀ ነበር። ዳግሚያ ትንሳኤው አብይ ነው … እናንተ ተጠቀማችሁ ከመነገድ ጠረጋው በኋዋላ የራሳችሁን ሰዎች አነገሳችሁ፤ አቆመሳችሁ፤

ሥርዓትስ? የአማራ ጸሐፍት ጋዜጠኞች ጠፍተው? የአማራ ሰቆቃን ያጡኑ ወጣቶች ጠፍተው?



     ሌላው የህይወት እና የትንሳኤ ሰነድ ዝግጅትም ይህ ነበር። 


ሌላው ቀርቶ የ2016 የዘመን ማጠናቀቂያ እና የ2017 ዘመን ተግባር ንድፍ አውሮፓ ህብረት በዛጋጀው ዘገባ ላይ 2 ጊዜ ስለ ኦጋዴን፤ 5 ጊዜ ስለ ኦሮሞ ሲተነተን አንዲት ቦታ አማራ የምትል እንዳትገባ ተብሎ በጥንቃቄ ነበር የተሠራው ዕድሜ ለሳተናው አትሞልኝም ነበር። ፈልጌም እለጥፈዋለሁኝ እዚህ ካራሴ ብሎግ ላይም።

ለኮሮጀ ማሙያ ብቻ እንጂ አማራ በመንፈሳችሁ ውስጥ ኑሮ አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖርም። ያው ጋብቻውንም ስለምናውቀው ማለት ነው። ሆድዕቃችሁን አጥንተነዋል።


ዕውነት ደፋሪ ጀግና እስክታገኝ ድረስ እንተጋለን!

ውዶቼ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ። ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።