የመከራ ዚታ ተሸካሚዋ ስደተኛ እናት።

አላዛሯ ኢትዮጵያ እና ልጆቿ።
„ምህረት እና ዕውነት ከአንተ አይራቁ“
ከሥርጉተ© ሥላሴ 09.10.2018
ከጭምቷ ሰዊዊዘርላንድ።


  • ·       መነሻ።

Ethiopia:"ከስደት መልስ የምስኪኗ የመኪና ውስጥ ጎጆ"፡ሁለት ልጆችዋን ይዛ
በመኪና ዉስጥ ኑሮዋን ካደረገችዉ ከወ/ ዘሪቱ ጋር የተደረገ ቆይታ
ስልክ ቁጥር 011-893-2975 ወይንም 0920 -0196 -34

የመከራ ቁልል የዕለት ኑራቸው ቤተኛ የሆነባቸው ሁለት ህፃናት እናት ናቸው ወ/ሮ ዘሪቱ። ኡጋንዳም ሱዳንም በስደት ቆይተዋል። ስደት ለሁሉ አይደላም ለሁሉም አይከፋም። ዕድል ለቀናቸው ይቀናል ዕድል ፊቱን ለነፈገችው ደግሞ መከራ ይቆልላል። ስደት በልክ ያልተሰፋ ሽብሽቦ ወይንም እጀ ጠባብ ነው።

ስደት እና ህይወቱ የፈተና ማሰልጠኛ ተቋም ነው። እርግጥ ነው በሰላ ሁኔታ የሰላ ገጠምኝ ባለቤቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ግን የሰላውም የሚባለው የማትቀበሉትን ዕድል መቀበል ከተቻለ ነው። ያ ካልሆነ ዘላቂ መከራ መሸከም አይቀሬ ነው። 

ስደት ውስጥ ብዙ አቅጣጫ ያለው ተራራዊ ገጠመኞች ነው ያሉት። ይህን እንደ ተጠቀለለ ትቼ የእነዚህን ምንዱባን ህፃናት ዕጣ ፈንታ እና የነገ አገር ገንቢ ታሪካዊ ድርሻቸው በምን ሁኔታ ሊሰላ እንደሚችል ያለኝን ዕይታ መጥኜ ላንሳ።
ለነገሩ በርዕሰ መዲናዋ በአዲስ አባባ ቀደም ባለው ጊዜ በሺሕ የሚቆጠሩ ወገኖች ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ እንደ ነበሩ ይታዋቃል። 

አሁን በብዙ እጥፍ አድጓል። ከዚህም አልፎ ከትግራይ በስተቀር ሁሉም ክልል በዬቀኑ ኗሪው ይፈናቀላል በገፍ። ስለዚህ ኢትዮጵያ በዓለም በአገር ወስጥ የኗሪ መፈናቀል አንደኛ ደረጃነቱን ይዛለች። ራሱ ወገኑ ለወገኑ አንጀት ስላልሰራለት መከራ ኖፍቆት፤ ዕንባ ናፍቆት 50 ሺህ የ አማራ እና የ ኦሮሞ ወጣቶች ወጣቶች ለካቴና ተገብረው የመጣውን ለውጥም በ =አግባቡ መያዝ አቅቶ የነገ ትውልድ ተራካቢ ህፃናትን መከራ በእጥፍ ድርብ ሲጨመር እና ሲያስጨመር ይታያል።

የአላዛሯ ኢትዮጵያ ሊሂቃኑ የአባት የእናት የእህት የወንድም ልጆቻቸው ደህንነታቸው የተረጋገጠ ነው። የዘመድ አዝማዳቸው ኑሮም የተደላደለ ነው። አብዛኞቹ ቤተሰቦቻቸው ውጭ አገር ነው የሚኖሩት። የመከራ መሞከሪያው ያው ባለቤት የሌለው ህዝብ ነው። የጭንቁ ጉሮሮ ደግሞ እናት። 

ቀደመው ባለው ጊዜ በደርግ ማለት ነው የመንግሥትን አቅም ጋር ተወዳደሪ የሆነ ሁሉ ነገር የነበረው፤ ጥበቡም፤ ክህሎቱም የኢኮኖሚ አቅሙም፤ ዕውቀቱም የተሟላ የእርዳታ ማስተባባሪ ኮሚሽን የሚባል ትልቅ አካል ነበር።

እንደዚህ ዓይነት ካሳስትሮፍ የሆነ የህዝብ የመፈናቀል ሱናሜ ሲደርስ ዜጋው የእኔ የሚለው ባለቤት ነበረው። ዛሬ ዜጋ የሚለው ራሱ የለም። ያለው ዞግ ነው።  ለእሱም እንደ ሊሂቃኑ መልካም ፈቃድ የሚፈጸም ነው የሚሆነው። ባለፈው ጊዜ አቶ ጃዋር መሃመድን ሰጥ ለጥ ብሎ የተቀበለው ብአዴን/ አዴፓ ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉትን ወገኖቹን ደግሞ በጸጥታ አስከባሪ ቤተ እግዚአብሄር ተጥሶ ዱላ ሁሉ ነበረባቸው። 



ደጀሰላምም መጠጋት ተነፍጓቸው ማለት ነው። በዞግም ቢባል ልብ ላላቸው እንደ ትግራይ ሊሂቃን እንጂ ልባቸውን ለሌላ እንዲያስረክቡ ለተገደዱት ያው ነው ባለቤት አልባ ናቸው። ልዩነት የለውም። የዞጉም ቢሆን እንደ ዜግነት እዳሪ አዳሪ ነው።

አዲስ አባባ አዬሯን ተጠልለው የሚኖሩ ሺሆች ናቸው ይህ ለዛሬ ነው። ለነገ ደግሞ አያድርገው እንጂ እንደ አሁን የእነ ም/ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ሥልጣን በምርጫ ከተረጋገጠ፤  እና እንደ አቶ በቀለ ገርባ ዓይነት መንፈስ ያላቸው ከነገሱ ለእዳሪው አዬርም የሚፈቀድ አይሆንም። ነፍስ በ እነሱ ቸርነት ነው የምትተነፍስው።

በምስሉ ላይ የሚታዩት እነዚህ ሦስት ነፍሶች መኪና ውስጥ ኑሯቸው የከተመ ሲሆን ዛሬ ባለው ሁኔታ ከነገው ከታቀደው የ ኦሮሞ ድርጅቶች ኦነጋውያን መንፈስ መከራ አንጻር ሲሳላ መኖር ከተባለ ተብሏል፤ የነገው ሲታሰብ ግን ጨለማ ነው ብቻ ያን ዘመን አያምጣብን ፈጣሪ አምላክ።

ለነገሩ መኪናውን የፈቀደውም ባለጋራዥ የተባረኩ ናቸው። ይህንም ለማግኘት መቻሉ ራሱ ዛሬ ላይ ነው ነገ ኦነጋውያኑ ከተሳካቸው ግን ይህም አይቻልም። ዘንድሮ ምን ያህል የአዲስ አበቤዎች እንስቶች ነፍሰጡር እንደሆኑ ባለውቅም ከኦሮሞ ውጪ ያሉ ነፍሰጡር ሴቶች የልጃቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ የተጋረጠበት ስለመሆኑ እዬታወጀላቻው ነው። እነሱም የ እርግዝና ወቅታቸውን በሥጋት እንዲያሳልፉ ተፈርዶባቸዋል። 

እናት እና ልጅ በጋራ በእትብት ሃዲዲ ጫናውን ይጋራሉ ማለት ነው ጽንሱ ሳይቀር። ይህን የሚያስበው የለም። በዚህ በ5 የኦሮሞ ድርጅቶች ውሳኔ በመንፈስ ኦህዴድ/ ኦዴፓም አለበት ይህን አቶ አዲሱ አረጋ ቀደም ብለው ገልጸውልናል፤ የሆነ ሆኖ ላለመውለድ የሚወስኑ የአዲስ አበቤዎች ጥንዶችም ሊኖሩ ይችላሉ ብዬም አሰብባለሁኝ። ነጋሪቱ እኮ ልክም መጠንም ደንበርም አልተሰራለትም። የበደለ ቀርቶ የተበደለ ነው የካቴና እራት ሆኖም እዬታዬ ያለው። ቁም ነገሩስ ነገስ ነው? 

የአዲስ አባቤዎችን ኑሯቸውን የሚፈቅዱት የኦሮሞ ድርጅቶች ናቸው። በኪራይ  ይሁን በመደባል ቀጣዩ የአቅም ሁኔታ የሚፊጽመው በእነሱ ይሁናል። ይህ ታቅዶ የተከወነ ይመስላል። ለነገሩ ተጨማሪ ጫና ለመፍጠር የተሄደበት መንገድ ራስንም እያሰጋ መሆኑ ይታያል። 

አደጉ በለጸጉ የሚባሉ አገሮች  አንድ አገር መንግሥት አልመቻቸው ሲል ጣልቃ ይገቡና በጎን ጎሸም የሚያደርግ ቡድን ያደራጃሉ፤ በሉጅስትክስ ይደግፋሉ ይህ የተለመደ ነገር ነው፤ አሁን ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ ለራሳቸውም አስጊ ሆኖ ዜጎቻቸውን በራሳቸው መዲና እያሳጣ ያለው መከራ ሲጀመር ለሌላ ተልዕኮ ተብሎ የተደራጀ ነበር።

 ሙሉው ባይሆንም ኦህዴድ / አዴፓ እንደ መፈተኛ የጀመረው የትርፍ መንገድ ዛሬ በውጥኑ ይህን ያህል መስዋዕትነት ካስከፈለው ነገን ያዬ ነው። ችግሩ ለሃጣን የመጣው ለፃድቃን መሆኑ ነው። 

ኦህዴድ/ አዴፓ እንዲፈጸምለት ለሚፈልገው አንኳር ጉዳይ በግንባሩ ውስጥ ባለው ልክ ስለሆነ ያን የሚያጎለብት ነገር የጎን አቅም ለመፍጠር የሄደበት መንገድ ነገን አምርሮ አክስሎ፤ አልፎ ተርፎም የመካከለኛው አፍሪካ ጠንቅ እንዳይሆን ከአሁኑ ባሊህ ሊባል ይገባል። ስድ የለቀቁት ነገር ለመግራት ከገረጀፈ በኋዋላ የሚቻል አይሆንም … 

ልጆቿን ለከፈን፤ ለመጠለያ፤ ለዕለት ጉርስ ያላበቃች አገር በሽርብ ሴራ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ መከራ መጥራት መቼም መታመም ነው። በንብርብር ችግር እዬተናጠች ያለችው አላዛሯ ኢትዮጵያ የቀደመውን በቦንዳ በቦንዳ የተጠቀለለውን ችግር ሳትፈታ በላይ በላይ ደግሞ እዬታከለባት ነው። 

አሁን ከኤርትራ የሚጎርፈው ህዝብ ራሱ መገደቢያው ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም። አዲስ አባባ የገቡት መመለስ አይፈለጉም ወደ ኤርትራ። በትግራይ በኩል የገቡት ወደ 15ሺህ አዲስ ስደተኞች ከቀደመው በአራት  እጥፍ እንደሚበልጥ ይነገራል፤ ወደ አገር ግቡን ተከትሎ በአራቱም ማዕዘን  የገባውም እንዲሁ ... ከስደት ተመላሹም እንዲሁ ...  

በዚህ ሁሉ ነው ደግሞ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ሴራ እና ደባ ፍንጂ ቦንብ አዬር መቃወሚያ አብረው ታድመው ሌላ መከራ አጭተው የሚያጋቡት ያንኑ ለእለት ከፍን ያልበቃውን ዜጋ ነው። የመከራው የመሸከሚያ ዚታው ደግሞ እናት ናት።

በጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሹመት ላይ ለእናት በሰጡት ክብር ብዙ ትችትን አስተናግደዋል። ያን ጊዜ ሳተናው ድህረ ገጽ ወደ 15 ቀን ተስተጓጉሎ ስለነበር አልጸፋኩበትም እንጂ የዘመናት ችግር ተሸካሚዎች የኢትዮጵያ እናቶች ስለመሆናቸው አንድ ጠንከር ያለ ጹሑፍ መጻፍ ፈልጌም ነበር። 

ምክንያቱም ዶር አብይ አህመድ ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ዘመነ ህማማት ተጋድሎ እና ውጤቱ / ስኬቱ ዕወቅና መሰጠታቸው የሚያስወቅስ ቅንጣት እንከን ስላልነበረው። እሳቸው የሰጡት ዕወቅና እውነት ነበር። የኢትዮጵያ ፍዳ ተሸካሚዎች የኢትዮጵያ እናቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ እናቶች የኢትዮጵያን መከራ ተሸክመው ቀን ያወጡ ቅዱሳን ናቸው። ትወልድ የሚባለውን ሁሉ ለታሰበው ግብ የሚያደርሱ እነሱ ናቸው አረረ መረረም። ጫን ተደል መከራ፤ አሳር፤ ፍዳ ዕንባቸው ተሸክሞ ነው ትውልድ ከትውልድ የሚሸጋገረው። የኢትዮጵያ እናቶች ተፈጥሮ ከብረት ቁርጥራጭ የተሠራ ነው። 

የኢትዮጵያ እናቶች ፈተናቸው ዝልቅ ትእግስታቸው ደግሞ ድንቅ ነው። አሁን ይህች እናት ስደትን አዬችው፤ አገሬ ብላ ተመለሰች ግን ይኸው ሁለት ልጆቹን ይዛ መኪና ውስጥ ትኖራለች። አሁን እንኝህ ልጆች አንዳቸው የአገር መሪ ቢሆኑ እናቴ ሙሴዬ፤ እናቴ ቅድስተ ቅዱሳኔ፤ እናቴ መንፈሴ ቢሉ ስለምን ሊወቀሱበት ይችላሉ? 

እኔ እንዲያውም ቀን ቢወጣ ቀን ቢያልፍለት የኢትዮጵያ እናቶች የምስጋና ቀን ሁሉ ቢዘጋጅ ፈቃዴ ነው። የምስጋና ቀኑ እንዲህ ሜዳ ላይ የወደቁ እናቶች የሚነሱበት፤ የሚወደሱበት፤ የሚመሰገኑበት አለናችሁ አይዟችሁ የሚባልበት ቀን ማለት ነው።

ዓለም ደስታ ፍሰሃ ሰናይ ሐሴት ፍቅር ተስፋ የሚባለው ነገር ሁሉ እኮ በእናት ወስጥ ብቻ ነው የሚገኙት። አብሶ የኢትዮጵያ እናቶች ከዘመን ዘመን ለእንባቸው ተቆርቋሪ ባለቤት ያላገኙ መከረኞች ናቸው። 

ሁሉንም የመከራ ዓይነት የሚያስተናግዱ በመከራ ወስጥ ሙሉ ሃላፊነትን የሚወጡ ብቁ ዜጎች ናቸው እናቶች። መከራቸውን ቻል አድረገው፤ ፍዳቸውን ዋጥ አድርገው፤ የእናት አገር ገመናን ክድን ሽክፍ አድረገው ለቀን የሚያድርሱ ናቸው የኢትዮጵያ እናቶች። አሁን ጦርነት አቶ ዳውድ ኢብሳ የሚያዙት የእነሱ ሳቅ  የእነሱ የተስፋ ቀን ቀንተውበት ነው። 

የሴረኛው የፖለቲካ ሊሂቃን ማህበራዊ አድማ ሁሉም በመከረኞቹ የኢትዮጵያ ሴቶች ፍዳ ቀጣይነት እርካታ ስለሚያገኙበት ነው። ምን ሲጨንቃቸው የሰው ብርንዶ በዬዘሙኑ ያቀርቡላቸዋል የ ኢትዮጵያ እናቶች - ለእነሱ የወርቅ የድግስት --- የውቂ ደብልቂው ክብር ጭብጨባ እና ልዕልና።

እጅግ የሚገርመኝ አንድ ተረብ አለው ኢህአዴግ የህጻናት እና የሴቶች ሚር፤ የዕንባ ጠባቂ፤ አይታፈርም የሰብዕዊ መብት ኮሚሽን? ? ? ፌዝ ይባል፤ ቧልት ይባል? ተረብ ይባል? የማላገጥ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ፕሮግራም ይባል ምን ሥም ይውጣለት ይሆን? ትውልድ አውላላ ሜዳ ላይ ዜግነቱን ተቀምቶ እንዲህ እዬኖረ …

ከቶ የመኖር ዋስተና የሌለው ዜጋ እንዴት ዜጋ ሊባል ይችላል? አንድ አገርስ ዜጋ አለኝ፤ እዬመራሁት ነው ይህን ዜጋ እንዴት ልትል ትችላለች? ይህ የኖረውን የ50 ዓመት ችግር ቅኑ ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው ቱመታ ይፍታው እያልኩኝ አይደለም። ቁልሉን ችግር የአብይ ሌጋሲ የፈጠረው ነው እያልኩኝ አይደለም።

 ለሳቸው ርህርህና ደረጃውን የመጠነ ዕውቅና አይደለም ሌላው የወጡበት ድርጅት ኦህዴድ/ ኦዴፓ ያለውን የድንግልና አቅም እዮር ይመርምረው እንኳንስ ሌላው። እንዲያውም ከወጡበት ማህበረሰብ ይልቅ አማራ ክልል የልባቸውን አድራሽ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ወስጣቸው አድርጓቸዋል። ከአሜሪካ ወደ ጎንደር ያቀናቸው አንዲት ዘመዴ  እንደምትለው ከሆነ አብይ ለጎንደር ልቡ ነፍሱ እስትንፋሱ  ሆኗል ነው የምትለው።

የዘመን መለወጫ ተከትሎ የታዬው በጎ ምግባር አሁን ዞግ መረጣ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ አቆሸሹት እንጂ መንፈሱ ነገን የሚያሳይ ራዲዮሎጂ ነበር በአዎንታዊነት። ቀደም ባለው ጊዜ መባጃውን መልካምነት፤ ደግነት፤ ርህርህና፤ ቅንነት፤ አቅራቢነት ራሱ ዞጋዊ ሆኗል። ዕውነቱ ይህ ነው። 

እነዚህ የመልካም ሰውነት መለያዎች ግን የነፍስ ጉዳዮች ነበሩ። አሁንም ለነፍሳቸው ያደሩ ነፍሶች የዚህችን እናት ዕንባ ይመለከቱ ዘንድ የቻሉም ያቻሉትን ያደርጉ ዘንድ ነው ማጠናከሪያ መጻፍ ያስፈለገኝ። ነገ ሲታሰብ እንዚህን ሁለት ህጻናት ታስበው ቢሆንም መልካም ነው። የአነኝህ ህፃናት ሥነ ልቦና ተቀጠቀጠ … ዕጣቸውን እኔ ብገልጸው የጨለማ ማደጎ ነው ልበለው። 

ልዑል እግዚአብሄር ጸሎታቸውን ሰምቶ ለቤት ያብቃቸው! አሜን!
ድንግለዬ የኑሮ ዋስትናቸውን ያገኙ ዘንድ በምልጃዋ ትታደጋቸው። አሜን!

የኔዎቹ ኑሩልኝ መልካም ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።