እስኪነጋ...
እስኪነጋ ... “ከአፌ ቃልም ቃል ፈቀቅ አትበል። አትተዋት ትደግፍህማለች፤ ውደዳት ትጠብቅህምአለች።” መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፮ ከጸሐፊ መስፍን © ማሞ ተሰማ ( M esfin © Mamo Tessema) ሠላም ለናንተ ይሁን! አዎን እናምናለን። አዎን እየነጋ ነው። የህ ው ሃትና ህውሃታውያን ዘመነ ፅልመት እየተገፈፈ ነው። በኢትዮጵያ ሠማይ ሥር የብሩህ ቀን አጥቢያ ፍካት ይታያል። ያለጥርጥር ይነጋል። አዲስም ቀን ይሆናል። ግን ገና አልነጋም። መቼ ይነጋል? ብላችሁ አትቸኩሉ። ንጋትም ተፈጥሯዊ ዑደቱን ያጠናቅቅ ዘንድ ግድ አለውና። ንጋቱ በህወሃትና ህወሃታውያን ፅልመት እንዳይጋረድ ግድ ነውና። ህወሃታውያን እነማን ናቸው? ህወሃታውያን ማለት እነ ጃዋራውያን እነ ፀጋዬ አራርሳውያን መሰሎቻቸውና ወዘተርፈዎች ሁሉ ናቸው፤ የበቀልና የቂም በቀል የጥላቻና የጎጠኝነት ታንቡረኞች። ህወሃትና ህወሃታውያንም የኢትዮጵያን ዘመነ ፅልመት ናፋቂዎች ናቸውና። እንዲነጋ፤ የህወሃትና ህውሃታውያን መጋዝ ጥርሳቸው ሊረግፍ ግድ ነው። እብሪተኛው ጉልበታቸው ሊፈስ ግድ ነው። ለ27 ዓመት እንደ መንግሥት የረጩት መርዛቸው ሁሉ ሊመክን ግድ ነው። የታበዬ ልባቸው ሊሟሽሽ ግድ ነው። በዝርፊያ የደለበው የባንክ ደብተራቸው ይቀደድ ዘንድ ግድ ነው። እንዲነጋ፤ መከላከያ ፖሊስና ደህንነት በለውጡ ህግ ሊገዙና ሊደራጁ ግድ ነው። የሀገር እንጂ የጎጥ አገልጋይና ታዛዥ አይሆኑ ዘንድ ግድ ነው። ፍርድ ቤቶችና የህግ ተቋማት በለውጡ ራዕይ በህግና ፍትህ አርማታ ላይ ብቻ ይታነፁ ዘንድ ግድ ነው። እንዲነጋ፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ በህግ ማዕቀፍ ይከበሩ በዜጎችም ያለ ስጋት ይተገበ...