የዶር ለማ መገርሳ ንግግር እና ዕድምታ ...ው።

እንኳን ደህና መጡልኝ

„በሰማይ የሚኖሩ ረቂቃን መላእክት ማደሪያቸው በሰማይ ይሆናል
 በዚህ ዓለም የተወለዱ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ማደሪያቸው
በምድር ይሆናል።“ መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፹፫



ከሥርጉተ©ሥላሴ
Seregute©Selasssie
31.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።

ከሳተናው ድህረ ገጽ የተወሰደ። 
የኢትዮጵያዊነት ሱስ ትሩፋት ቅርስ እና ውርስ?
ምስጋናውን መወደሱን ስለባጀንበት ስለስህትት 
እምነት እና ክክህደት ብልጽግና እንዲህም እንላለን
ከአፍንጫ ላይ ስለሆነው መፈጠር መከራ!
አሳረኛው ለገጣፎ ለጋዳዲ!



·       መነሻ።

Ethiopia: ሰበር መረጃ - ለማ መገርሳ ለተወራባቸው ሁሉ ምላሽ ሰጡ | Lema Megersa's Speech


·       ሰላምታ በአክብሮት።

ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? እንደምን አላችሁልኝ። ዛሬ ቀኑም ቀሎታል እኔም ቀሎኛል። ትናንት ማምሻ ላይ በተለያዩ ርዕስ አሰጣጥ የተዥጎረጎሩ የዶር ለማ መገርሳ ንግግር አዳምጥኩኝ። ሰው እፎይታ ተስምቶታል። የሚገርም ነው። ለተወራባቸው ምላሽ ሰጡ ይላል ዘሀበሻ ምን ይወራባቸዋል የፖሊሲ ጉዳይ ነው። ምህንድስናቸው ወገቤን ስለማለቱ ቢባል መልካም ነው። ወሬ ሳይሆን ትልም፤ ዓላማ፤ እቅድ ስልት ጥበብ ተብሎ የተያዘው መንገድ ሙግት ገጠመው።

ወሬ አይደለም። ይህ  ኦነግ የዘመናት ዓላማን ዘመናዊ አድርጎ የማስፈጸም ልዩ የተልዕኮ ፍጥጫ ነው። ልክ እነ ጥላሁን ግዛው አባቶቻችን ጨቁነውችሁዋል እናበጨቋኙ አማራ ሰፍ ምዘዙ እንደተባለው አሁን ደግሞ የስሜን ፖለቲካን ለመንቀል እራሰችሁን ገብሩ ነው። በጅ የሚል ከተገኜ … ግርባው ብአዴን ይሰለፍ ወፊቱ ሳትቀድመው … ቆፍጣናዎቹማ እማ ወድረው ይዘዋል …  

በሌላ በኩል የአማርኟ ቋንቋ፤ የነፍስም የሰው ልጅ እና ተፈጥሮ የመኖር አለመኖር፤ የብትን አፈር የመነፈግ ግራጫም ጉዳይ የህልውና ተጋድሎ ስለሆነ ወሬ አልነበረም እና። ይህ የአማራ የህልውና ታገድሎ ጉደኛ ነው። ተደፍሮ መነገር አልችል ያለበት ዘመን በራሱ ዘመን ጠበቃ አቆመለት። አሁን የዜጋ የህልውና ታገድሎ ወደ መሆን አድጓል ጉዳዩ። ተመስገን! አዲስ አባባ የመላ ኢትዮጵያ የአፍሪካም መናህሪያ እንጂ የአንድ ብሄር አይደለችም። በሌላ በኩል አዲስ አባባም የሉሲ በመሆኗ የሉላዊም መንፈስ የረበበባት ከተማ ናት። 

የሆነ ሆኖ ካላቸገረኝ በስተቀር እኔ እማምነው ዘሃበሻ ስለሆነ ብሎጌ እሱን ስለሚያከብር ሁሉጊዜ የእሱን ሊንክ ነው እመጠቀመው። ጥረቱን ስላመደንቅም።   
·       እዝሌ ንግግር… እና ዕድምታው።

ደግሜም አዳምጥኩት ንግግሩን - ዛሬም። መታበይ ብናኝ የለበትም። ይህ መልካም ነገር ነው። ጭብጡን ሳዳምጠው ግን ግርም እያለኝ ነው። ምዕራፍ አንድ „የጣና ኬኛ“ የጅዋ ጅዊት ግዳጅ ተጠናቋል፤ ህወሃትን ማስወገድ፤ „የአንቦ ኬኛ“ የምዕራፍ ሁለት ጅማሮ ይመስላል የዛ አንከሊስ „የኦሮማራ ቅንጅት ዳግሚያ ደመነፍሳዊ ትንሳኤ ደግሞ ቀስቅሶ የእስክንድር ንቅናቄ መቅኖ አባክኖ ለማስቀርት ይመስላል፤ ሌላም አዲስ ሹመት ጋርም ዝምድና እንዳለው ቢታሰብም።

የሆነ ሆኖ ንጉሥ እስከ ዙፋኑ በቤተመንግሥት ጉባኤ በተከታታይ ሲያካሄድ ባልደረስ ደግሞ ብዕርን ጨብጦ ያን ሲጋፈጥ እዮር በአደባባይ ፈረደና ሉላዊ ዕድምታውን አጎላው። ኢትዮጵያዊነት ሰምዕትነቱም ሉላዊ ነው። ኮርያ፤ ኮንጎ፤ ሱማሌ፤ ሩዋንዳ ወዘተ…

ምን አለ ለባለጊዜዎች ለእነሱ ይፈቀዳል ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠትም ሆነ ስብሰባ አካሂዶ ህዝብ ማነጋገር። እነሱ የክት ልጆች ናቸው ሌላው ደግሞ ስደተኛ።
የሆነ ሆኖ ከእስክንድር ንቅናቄ ከዚያ በኋዋላ ግንቦት 7 መግለጫ በመግለጫ፤ ቃለ ምልልስ በቃለ ምልልስ ማሸበርቁ ብቻ ሳይሆን… አለን ለማለት አንድ ስብሰባም ሰሞኑን አካሂደዋል፤ ያው አማራ ክልልም እንዲሁ …

የሞገርመው ነገር ዲያስፐራውን መንፈስ ለመግዛት የጸሐፊው የአቶ አንዳርጋቸው አቋም ጀባ ተብለናል በልዩነት አቋም። ይህም አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መደባቸው በ አዲሱ ፓርቲ የዲያስፐራውን የድጋፍ አካል በመምራት ይሆናል። ለዚያ መላሾ ነው ይህ ታቅዶ የተከወነው። የፕ/ ብርሃኑን ነጋ ተቃውሞ የሚወጣ ነፍስ በ ኢሳት ጉደይ ሆኖ በ አጀንዳ ውይይት ፈጽሞ አይደረገብተም። ለ አቶ ነ አምን ዘለቀም፤ ለመጀመሪያ ወታደራቸውም ለ አቶ ዘመነ ካሴም አልተሆነምና።

በሌላ በኩል ነገረ እስክንድ ንቅናቄን ቅስም ለመስበር ደግሞ አብይወለማ እንዳይከፋቸው ደግሞ ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ተሰልፈውበታል በተደራቢነት ማጫ ለማማታት። የጫጉላው ጊዜ ለ ማአካሪነት ክፍያ በዶላር ስለመሆኑም አዳምጠናል። ስለ ሃቁ ወፊቱ ትጠዬቅ… ግን ሃሳብ አቅራቢዎች እንዳሉ በሂልተኑ ጉባኤ ጠ/ ሚሩ ነግረውናል። የመጀመሪያ ከተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ ድርጅቶች አገር በነበራቸው ቆይታም የመረጡት ጋር አብሮ የመሥራት መብት እንዳላቸው ተነግሮናል። ያው ግርባው ብአዴን አፍንኮሎነትን እግረ መንገድም አዳምጠናል። ወዮልህ አማራ አልን ከቤታችን ሁነን … የሚስጢሩ አስኳል ይኸው ነውና።  
·       የልሳን ቡፌ በዓይነት።

ቤተ መንግሥቱ ደግሞ የአዲስ ወግ የጋዜጣዊ መግለጫ፤  ኦሮማማ ሊሂቃን የእርስ በርስ ድርድር በ8 አባላት የኮሜቴ ውቅር፤ የኮንዲኒዬም ውርክብ፤ የቄሮ ሰላማዊ ሰልፍ በሜንጫ ታጅቦ፤ አሁን ደግሞ የኦሮምያ ፕሬዘዳንት ንግግር በዓይነት የልሳን ቡፌ እያዬን ነው።

ሌላው ማጣፋጫ ጉዳይም ሚሊነዬም እና ውሎውም አለ … ዛሬ አንድ ነገር ሹክ ብሎናል።  በዚህም በዚያም አጋር የማሰባሰብ ቅኖችን በፌድራል ፖሊስ እያዋከቡ መሆኑ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፍዳ ቁልጭ ብሎ ይታዬናልን። ይህ ሁሉ ትዕይንት እነሱ በፈለጉት ልክ ስብሰባ፤ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የሃይማኖት ጉባኤ በሚሊዬንም አዳራሽ ይፈቀዳል ሌላው ደግሞ ባይታዋር ነው። የዜግነት ሲሶ እና እርቦ …

የሆነ ሆኖው የእስክንድር ንቅናቄ ኢትዮጵያዊነት ውስጡ ምን ያህል አቅም እና ጉልበት እንዳለው ከሊቅ እስከ ደቂቅ እዬአፍረከረከው ነው። ስለምን? በፈጣሪ ዘንድ የተባረከ ስለመሆኑ ካለው ግራ ቀኝ ቋያ ጋር ማስተዋል ይቻል ይመስለኛል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነት ያለው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋም ከዓመት በላይ በፍሬም ግድግዳ ላይ ለጌጥ ተንጠልጥሎ ተረስቶ አቧራ ሌት ዳንስ ሲፍነሸንሽበት የባጀው  „ኢትዮጵያዊ ሱስ ነውም“ ሲደግም እንሆ አዳመጥን። ተመስገን ለማለት ግን አንደበቴ አልደፈረውም። ኢትዮጵያዊነት እውነት ነውና።

ዛሬ ከዓመት በኋላ መነሳቱ ብዙም ባያስከፋም ተጻራሪው ተግባር መሬት ላይ ስላለ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም ለራሱ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው።“ ራሱ እዬፈተነ በፈተናው፤ በወጅቡ ውስጥ ትቢያ ስለመታጠቁ ራሱ እጬጌው ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ህሊና አለውና ልብ ስለሚለው ማለት ነው። ኢትዮጵያዊነት እኮ የሰዎች የመንፈስ ማህበር ነው። የተፈጥሮ ስምምነት ውል ነው። የፈጣሪ ምርቃትም።

እኔ ለቅኖቹ እማሳስበው ቁም ነገር ከእንግዲህ በወጀብ፤ በጎርፍ፤ በጦሮ፤ በጭብጨባ እና በቻቻታ እና በሁካታ፤ በመግለቢያ ትውልዳዊ ብክንትን ማስተናገድ ጠቃሚ መንገድ አድርጎ መከተል አስፈላጊ አይመስለኝም።  እንስከን። ስክነት ይጎድለናል። ማንዘርዘሪያ ይኑርን።

ቀድመው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውን“ የተቃወሙት አሸነፍን ይላሉ። ያ ግን መልካም መንገድ አይደለም። ቅን ሆኖ ሁሉንም ማዬት ውስጥን አጽድቶ መቀበል የተገባ ነገር ነው። ስለዚህ እንደ እኛ „ለኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ፊት ለፊት ሞግቶ፤ ፈተናውን ታገፍጦ ግን ፈትሾ አይቶ አዳምጦ፤ ተቀብሎ አንድቆ፤ ተንከባክቦ ቁርም ውርጭም እንዳይነካው ቁርጥ ውሳኔ መወሰን ግን የተገባ ነበር። ሌላው ቢቀር ፈጣሪም ይደስትበታል። በገሃዳዊው ዓለም ብዙ ነገር አጥተንበታል። በእዮራዊው ግን ያም ለምክንያት ስለነበር በረከት አለበት። ያለዬነውን ማዬት ጥሩ ነገር ነው።  ምርቃታችን አጽንትን ለመቀጠል ያስችለናል።

ብዙ ሰው በኦዴፓ ገዢነት ዘመን 3 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል ሲል አዳምጣለሁኝ። አንድ ሚሊዮኑ የቀደመ ስለሆነ እሱ መቀነስ እና መስተካከል ያለበት ይመስለኛል። ሁለት ሚሊዮን ቢባል መልካም ነው። ቁስሉ ግን ከዛም በላይ ነው ቁጥር ሊገልጸው አይችልም። በነፍስ ወከፍ ቆስለናል። ተጎድተናል። ቃል አባይ መሆን መከራ ነው። አዋርደውናል።

ለውጥ አለ ለውጥ አለ እንላለን፤ ለውጥ እኮ የኩሬ ውሃ ወይንም አሞሌ ሊሆን አይገባም። ማደግ፤ መጎልመስ፤ ተጨማሪ ውጤቶችን ማስመዝገብ ይኖርበታል። ለውጡ ደግሞ ብዙ መስዋዕትነት ተገብሮበታል። ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ ተገኜ ከሚባለው ትርፍ በላይ ናት። እናትን የሚተረጎም ምንም ነገር የለምና። በሌላ በኩል የሆነው ሁሉ ታጥቦ ጭቃ ነው የሆነው …

አቅም ያላችሁ የገዴኦ ሰቆቃን ለማገናዘብ የኦሾቲዝ ሚስጢርን መጸሐፉ እጅግ አጭር ነው ፈልጋችሁ አንብቡት። ምንም ልዩነት የለውም መንገዱ ወዳዛ ነውና  …

ሌላው ቀርቶ የተጎዱትን ለመርዳት እንኳን ቡራዩ እና የአዲስ አባባ ወጣቶችን መከራ አጢነን የግዲኦን መከራ መመርመር አለበን። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ከዚህ አንጻር ነው ሊታይ፤ ሊፈተሽ፤ ሊመረመር የሚገባው።

በድሃ አገር የ17 ባንክ ዘረፋ እና የጦርነት አዋጅ የሉዕላዊነት ቀናኢነት እና እርምጃም ከዚህ አንጻር መመዘን ይኖርበታል፤ ጉለሌ ላይ እኮ ነው ኢትዮጵያ ጦርነት የታወጀባት። ይህን መሰል ጥቃት ኢትዮጵያ በታሪኳ አስተናግዳ አታውቅም። በቪአይፔ በጥበቃ እዬተንፈለሰፈ እሷን የሚወጋ አካል ሲፈቀድለት፤ በትጥቅ ሲጠናከር፤ በፋይናንስ ሲደገፍ? ሞት ይሻላል …

 ጫናውን ደግሞ የሚፈለግ ነው። በግርግር ኦሮማይዝድን ለማጸደቅ። ይህንም አቶ በቀለ ገርባ ምን ያህል ለውጥ እንዳለ ከስልጣን ማግስት ጀምሮ አስሰው አስረድተውናል። ሌሎችም እንዲሁ … ምስክርነቱን እዬሰጡ ነው። ዶር ብርሃነመስቀል እረዳ „አብይ የኦነግ ወራሽ ነው“ ሲሉ እኔ ማህጸኔ ነው የተቀደደው፤ ስለ አብይ ስፋለም የኖርኩት ለአቶ ሌንጮ ለታ ለአቶ ዳውድ ኢብሳ መንፈስ አልነበረም እና … ማንነው ነጋ ጠባ የሚያታልሉት፤ ሊሂቃኑ የ ኦነግ መንፈስ በስል ተገብቶ እዬተከወነ መሆኑን አሳምረው ያውቁታል።

·       ሽሁራር ጭብጭባ

ሌላው እንደ እኔ አድርጓችሁ ከሆነ አላውቅም አብን ዒላማ አድርገው ሲወርፉ በዋሉበት ጠ/ሚር አብይ አህመድ የቃልኪዳን ፊርማ ንግግር ላይ ያ ቅጥ አንባሩ የጠፋበት ሽሁራር ጭብጭባ ገልምቶኝ ነበር። ጦርነት ያወጁ ዕለት በብዕርና በብራናም መሰሉን በአዲስ ወግ ንግግራቸው የነበረው ታዳሚ ነፍሴ ደሜ አዲስ አባባ ላይ ትፈሳለች ሲሉ ያ ጭብርቅ ጭበጭብ ነበር።

ያ እንደማህሌት አዬው የነበረው ድምጻቸው እራሱ ጉርና ጉርና እስኪለኝ ድረስ እያንገሸገሸኝ ነበር ያዳምጥኩት። አሁን ደግሞ ቀድመው የውጭ ጉዳይ ሚ/ርነታቸው ሚኒስተሩ እያለ በበላያቸው ላይ ተመድበው ሚኒሶታ ሄደው የቆንሲላ ጽ/ቤቱን ድልድሉን ያበሰሩት ዶር ለማ መገርሳ ጽድቁን ለመቀጠል የሚያስችላቸውን በተካኑበት የንግግር ጥበብ እና በፖለቲካ ሳይንቲስትነታቸው እያዋዙ የዝለት የአፍዝዝ የአደንዝዝ ዲስኩር ሲያደርጉ ደግሞ በዬማህሉ የነበረው ጭብጫባ ቋቅ እያለኝ ነበር ታደምኩበት። አሁን ለአውነት ቅብረት እንዴት ይጨበጨባል?  

በጣም ነው የሚመረኝ እኔ ባሰብኩት ልክ መሆን አንድ ነፍስ ሲሳነው … ግድ ስለሆነ ነበር ያዳምጥኩትኝ … በቅቶኛል የእነሱ አግድም የታዛ ጉዞ እና ፍልስፍና።።

እኔ ለቅንጣት ታህል መንፈሴን አቅሜን ለኦነግ ዓላማ ስኬታማነት ማፍሰስ አልሻም። ይህን ልዩ ንግሥና የሰጧቸው ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ይፈጽሞላቸው፤ ያስፈጽሙላቸው … እኔ ግን እናቴ በአራስ ቤቷ አላበደችም

… አማርኛ ቋንቋ እንዲጠፋ ተተግቶ በሚሰራበት መሰሪ ሥር ሰደደ ሴራ ራሴን እምደመርሰስ ሴት አይደለሁኝም። አማርኛ ቋንቋ የጥቁር ህዝቦች የቃኔ ቅኔ ነው። ቅኔነቱን ደግሞ ሉላዊ ዓለምም መስክሮለታል። እና ለራሴ ጥፋት ጭብጫባ መንገዴ አይደለም። አቶ በቀለ ገርባ ክንውኑ እንደመሰጣቸው ነገረውናል። ቀጣዩን ትልም ነግረውናል።   

በዚህ ዝልብ ጉዞ የገለማኝ ቢኖር የአጨብጫቢ ኦዲዬንስ ዕብንነት ነው። ኢትዮ „ለስደተኛም ውሃና መብራት ይገባባለታል፤ የሚዲያው ጫጫታ ከሁለት ክልል የመጡት ስለሆነ ነው“ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ ያሉት ነው፤ እነሱም የሚሉን በቋንቋ ፌድራሊዚም፤ በህገ መንግሥት፤ በአዲስ አባባ የባለቤትነት መብት፤ በኦሮሞ ቋንቋ የፌድራዘሊዝም በማድረግ አንደራደርም የሚል ድርጅትን ታቀፈው ነው „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን፤ ዴሞክራሲን ምንትሶ የሚሉን“ የሚነገሩን። ጋዳን ሰምተነው አልቀረም አዬነ። አማራ 27 ፍዳውን ከፍሏል።

በሁለተኛ ዜግነት እንኳን መብት አልነበረውም። ይህ መልክ ይይዛል ሲባል ሌሎች አማርኛ ተናገራችሁ ተብለው ጭፍጨፋ በ አደባባይ ነው የታወጀባቸው። አብሶ አማራ ሁለተኛ ቋንቋ የግድ ከሆነ ግዕዝ ይሻላዋል፤ ወይንም የደጉን ጋሞን ቋንቋ መቀበል … ከእንግዲህ እነሱ ታምነው ራስን ለማክሰል ምንም አይነት ድርድር ላይ ዘው ማለት የሚያስፈልግ አይመስለኝም።

ስለ አቶ በቀለ ገርባ የቋንቋ ፍልስፍና ትንሽ የምላት ቆራጣ ነገር በቀጣዩ ሳምንት ይኖረኛል … እንዴት ሬሳ ሃሳብ እንደሚያራምዱ። ለነሱ ትንሳኤ ሌላው ራሱን ለማክሰም መትጋት አይኖርበትም። ለነገሩ ሥልጣኑን የሚፈልጉት ለዚህ ነው፤ ከሰነበታላቸውስ? ምክንያቱም አሁን በኪነ ጥበቡ ነው መሽቶ የሚነጋው። ፈጣሪ ኢትዮጵያን ስላረሳት … ሁሉ ነገር ክፍትፍት ያለ ነው … አንድ እስክንድር ይህን ያህል አስበረገገ ሌላ አቅም አለው ከች ቢል ምን ሊኮን እንደሚችል ፈጣሪ ይወቀው።

360 ቀናት እኮ ተፈተኑ እሰከ ገዳ ሥርዓት። ጦርነት አስከፍተው እርቀ ሰላሙ በ አባ ጋዳ ተከወነ ማለት ምን ማለት ስለመሆኑ ልብ አለን። ምንም ለማንገሥ እንደሆነ።

በዬደቂቃቃው በዬሰከነዱ ፈተና አለ። ፈተናን አጣርቶ አልፎ ቢያንስ 50% ለማግኘት እንኳን አቅም የለም። ኢትዮጵያን ቁምነገር በማድረግ ፍልስፍና ውስጥ በጥራት እና በብቃት ማለፍን ይጠይቃል የብሄራዊ አገር መሪነት። ለዚያውም ኢትዮጵያን አህል የገናና አገር መሪነት።

የቁስ አይደለም ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ጉዳይ ነው። እስኪ በአንድ አመት ውስጥ በራሳቸው ክልል ስለ ኢትዮጵያዊነት ያዘጋጁትን፤ ኮንፈረስ፤ ፓናል ዲስከሽን፤ ውይይት፤ ሰሚናር፤ ሥነ ጥብበ ምሽት ይነገሩን። አማራ ክልል ነው የተባጀው።

ለአማራ ህዝብ ኢትዮጵያዊነትን ማስተማር ሰማይ ካለካስማ የማቆም ያህል ነው። ማን ደፋር ነው እኔን ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያስተምረኝ። ለ አንዲት የ7 ዓመት ታዳጊ ወጣት ዜግነቷን አማራ መሬት ሲኬድ ይጠዬቅ?

ለእነሱ የኦነግ ፍላጎት ስኬት የአማራ ብሄርተኝነት መደፍጠጥ ነበርበት። ለዚህ ነበር ጠ/ሚር አብይ አህመድ በጥዋቱ ያንገሸገሻቸው። ለዚህ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሰፊውን ድርሻ አብርክተዋል … ኦህዴድ ወደ ኦዴፓ ሲሸጋገር ጉባኤያቸው ላይ እኮ አንድ የህብረ ብሄር ፓርቲ ውክል አካል እንዲገኝ አላደረጉም። ሱሴ ከዚህ ላይ ለጠፍ ነው? ቁሮ ነው? ምን ሆኖ ነበር? ወይንስ ታሞ ሆስፒታል ገብቶ ነበርን? ቀልዱን ማቆም አለባቸው ዶር ለማ መገርሳ።

ብአዴን ላይ በጫኑት ሞቶ ይህን ያክል ላይ የወጣ ትምህክት የሚያስፍልግ አይመስለኝም። ምን እና ምን ሲኮን እንደተባጀ ስለምናውቅ። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የሚገልጸው ልሙጡ የቀደመው የጀግና ኮ/ አብዲሳ አጋ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማ ነው። የትኛው ስብሰባ፤ ዲሞ ላይ ይሆን ይህ የታዬው?  

በኦነግ አርማ ባሸበረቅ አይደለም ወይ ሚሊዬነም አዳራሽ ላይ ፍልቅልቅ ብለው የተገኙት „ከ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ ማግስት። የስሜን አሜሪካ ጉዞ ያደረጉትን ንግግር እና የውስጥ ፍንደቃቸውን መንፈስ በምልሰት ይዩት … ልብ ያለን ሰዎች ስላልን። ከባእድ ጋር የቆዩ እንጂ ከወገኖቻቸው ጋር ዲስም ሎሳንጅለስም ላይ የቆዩ አይመስሉም ነበር።

በሰጠነው ምስክርነት ልክ ስለመገኘት ግድ ስለሚለን ቅንጣት ታክል ነገር አታልፈንም … ውስጣቸውን ሁሉ ነው የእኔ ብለን የምንከታታለው።  ቀድሞ ነገር እኛ በውስጣችሁ የለንም። ስለምትሉን ነገር በመሆን ውስጥ በብዙ መስፈርት ለክተናዋል። 
·       የሚቀጥለው … ደግሞ

የሆነ ሆኑ ይህ ከንግግራቸው ከሥር ዩቱብ ላይ የለጠፍኩት ከሥር የተጻፈው ነው  …
ሊንኩን ደግሞ ከሥር እጨመራለሁኝ። ለማመሳከሪያ። የተወሰነውን ብቻ። ቀድሞ ነገር ልብ ላለው ሰው የምንወዳት የምናከብራት ብዙወቻችን እበሶ እኔ የተማገድኩላት የተከሰስኩባትም ክብርት ዳኛ ብርቱካም ሜዲቅሳ ሥርጉተ ሥላሴ ብትሆን ይህን ዕድል ልታገኘው ትችላላች ቢባል አይደፈረም። ፈጽሞ አይታሰብም።  

ሌላም አማካሪ ሆና የተመደበቸው ወታት ምድባዋ ከውጭ ድርጅት ጋር ቢሆንም ይለፉን ሌላዋ በእሷ የዕድሜ ክልል ያለች በብቃት የምትመጥን የሌላ ብሄር ብሄረሰብ ወጣት ታገኘዋለች ቢባል አይታሰብም። እርግጥ ነው አቅሟን በተለዬ ሁኔታ እኔ ከዶር አበበ ፈቃደ ጋር በአንድ የብቃት ውርርስ ምስክርነት የሰጠኋዋት እምሳሳላት ወጣት ናት። ሂደቱን በአደብ በተደሞ ከልብ ሆኖ ሲመረምሩት „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የእውነት ርስተ ጉልት የለውም። የጫዋታ ሟሟያ ብቻ ነው።  

ሌላው ኢትዮጵያዊ ሱስ ነው ኦርኬሰተር እዬታደመ ሙያ በልብ ሲከውን እንሆ አንድ ዓመት ተቆጠረ። 50 ምክትል ሚኒስተር እንደተሾሙ ሰምተናል ዝርዝሩን ለማውጣት እንኳን አልተደፈረም። ስለምን? ሲባል የሚፈራ ነገር ስላለ ነው።

ሌላው ሚኒስተር ሌላ ቢሆን ምክትሉ ኦሮሞ የግድ ነው። ጎልቶ ደምቆ የሚዲያ ንጉሥ ሆኖ የሚወጣውም ይሄው መንፈስ ነው … ንጥረ ነገሩ በመደዴ ሊኬድበት አይገባም … እስኪ አንድ የአማራ አክቲቢስት በኦሮምያ ዞን ንግግር እንዲያደርግለት ይፈቀድ፤ ይህም ይቅር ሊሂቃን ሁሉ ሲወደሱ ሲደነቁ ተደምጧል። „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ አቅም ከኖረው እስኪ የታሪክ ሊቀ ሊቃውንቱ ፕ/ ሃይሌ ላሪቦን ሥም በክብር ተነስተው እናዳምጠው።

ሱስነት እኮ ብዙ ነገር አሸንፎ መውጣት አለበት … ከዚህም ጋር ሌላ አማነሳቸው ድንቅ ኢትዮ አፍሪካዊ ፤ ልክ እንደ ቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን፤ ልክ እንደ ድንቁ ይድነቃቸው ተሰማ እኩል ተርታ የሚሰለፍ አቅም ያላቸው ፕ/ ማሞ ሙጬ ጋር ምን ተከወነ? ምን ተነገረ? „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ እንዲሸከም የሚፈለገው ሌላው ነው በተለይም ብአዴን እና አማራ … ልክ እንደ ከብት አሞሌ እንደሚያስፈልገው ለ አማራ ይህ ብቻ ይበቃል ነበር። ሰርቷለኝም።

ይህ ድጥ እና ማጥ ነው። ትውልድም አያበረከትም። የጠፋውን ትውልድ መፈወስ ሲገባ ኦነግን አቅም ሰጥቶ ሲያስፏጩ ምን ማለት እንደሆን ህሊና ስላለን ይገባናል። ቄሮን ደጀን አድርጎ ከፍ አድርጎ ስሎ ላዕላይ አጤነቱን በማስከበር ልባችሁ የሚያውቅው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ለማኮስስ የተሄደበት መንገድ በራሱ ሌላ ታሪክ ነው ጥቁራት ነው።\/

·       እም በህም በህመም …
ወደ ሁለት ጊዜ አዳምጨዋለሁኝ በጣም በተመሰጠ ሁኔታ ጭብጭባው ባርጭቃ ቢበጠብጠኝም። ያው የውጭ ጉዳይ /ርነት አዲስ ስልጣን ስለጸደቀ መጪው ወጀብ ላይ መከራን ማስታገሻ ነው። ዶር ለማ መገርሳ ንግግር ስህተት ሊፈቀድልኝ ይገባል ሳይሆን ተሳስቻለሁ ልታረም ይቅርታ እጠይቃለሁኝ አንድ ነገር ነው። ዲሞግራፊ አልነበረም ደግሞ ይላሉ? ማን ይሆን ጡጦ ጠቢው?  

የኢትዮጵያ መሪ ሆነው ለኦሮሞ እዬሠራሁ ነው ወደፊትም እሰራሉኝ ነው የሚሉት። ሁለት /ሚር ኢትዮጵያ እንዳለት አሳምረን እናውቃለን። ሁለቱንም እኛ በነፍሳችን ላይ ያነገስናቸው ስለ ኢትዮጵያዊነት እንጂ ስለ ኦሮማይዝድ ኢትዮጵያን ስለማድረግ አይደለም።

የኦሮምያ መስተዳድር ፕሬዚዳንት ስህትት አይደለም ስላሉት ስህተት የሆነ ነገር ስህትት ሳይሆን አይቅርም። ስለምን ይሆን ብሮድ ካስት የቦርድ ሰብሳቢ ኦሮሞ ያደረጉት፤ ስለምን ይሆን አዬር መንገድን ሰብሳቢ ኦሮሞ ያደረጉት አቃቢ ህጉም የቦርድ አባል ናቸው፤ አቃቢ ህጉም እንዲሆኑ የተደረጉት ከዚሕው ድርጅት ነው … ይህም ብቻ አይደለም ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊ አሶሳ ባይወለዱ ይህን ዕድል አያገኙም ነበር ወይብ ብዬ ሳስብ አይመስለኝም ነው። አቶ ንጉሡ ጥላሁን ይህን ያህል የልብ ኦርታ /ጋን/ የሆኑበት አርሲኛ ዘዬ ስለመሆኑ አሳምረን እናውቃልን። ሥነ - ልቦና የምህንድስናው እንብርት ስለሆነ። ታቅዶ በተጠና አኳኋን ነው ቁልፍ ቦታ የተሰጠው።

ወደ ሌላው ስንሄድ ስለምንድን ይሆን አዬር ሃይልን በኦሮሞ ከፍተኛ መኮነን አንዲመራ ያደረጉት፤ ስለምን ይሆን የገንዘብ / ከቁንጮ ጀምሮ ታህታይ መዋቅር በኦሮሞ የተጥለቀለቀው? የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ገዢስ እና መንፈሱስ? ንግድ ባንክ ለአማራ ክልል የመደበው ትራፊስ ቅርፊቱስ ምን የሚሉት ነው አማራ ትርፍራፊ ለቃሚ ስለማለት ይሆን? ለነገሩ ሽፍታ፤ አሽሸኛ፤ ጫተኛ፤ ዘራፊ፤  ወዘተ ..ተሰዳጅ፤ መጤ ምን ያልተባለው አለ አማራ። ይገባዋልም።

ቀደም ባለው ጊዜ የህወሃት እቃ እቃ ጨዋታ ለአብአዴን ኮታ አሜሪካን ሰጠሁ ብሎ ያው ታገሩን መድቦ ይኖር ነበር። ብአዴን የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ልብ ስለተገጠመለት። እና በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ባለሙሉሥልጣን አንባሳደር ሹመት እራሱ እኮ ግርም የሚል ነው አቶ ፍጹም አረጋ ናቸው።ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውእንዲህ ነው ሊመዘን ሊለካ የሚችለው።

ስለምን ይሆን መከላከያ እንደዛ የሆነው … ዋና አዛዡ ተቀምጠውስ ስለምን ይሆን ምክትሉ ያን ያህል የሚዲያ አድባር ሆነው እንዲወጡ የተፈለገው …? ያን ይህለስ ደንበር ጥሰው አንድን ህዝብ የሚወርፉት በዬትናው የዜግነት ልህቅናቸው ነው? ለነገሩ ቀጥሎም ተቀጥቷል። 90 ሺህ ህዝብ … ተፈናቀለ? 44ሺህ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቀሉ … ምን ያልሆነ ነገር አለና።

የቡራዩ፤ የለገዳዲ ለገጣፎ፤ የገዲኦ ነፍስ የውሻ ነበርን ነው ወይንስ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው መጥቆ ጁቢተር ላይ ስለተቀመጠ? በዚህ ሥልጣን መቀራመት ሁሉን አይቀረኝ ኮንደሚኒዬም ሳይቀር፤ በዚህ ደግሞ የሥነ - ልቦና የበላይነት ተግቶ መስራት፤  በሌላ በኩል የዘር ማጥራት እና ብወዛአማርኛ ቋንቋ ገዲኦ ላይ፤ ቡራዩ ላይ መገደያ እና መቀጣጫ አስደርጓል። እና „የአቶ ለማ ኢትዮጵያዊነት ሱስ“ ነው ከመቃብር በታች ነበር ወይ ቹቻ እና ሰኔልን የሙጥኝ ብሎ? ከዩንቨርስቲ የሚፈናቀሉትስ አማራዎች ብቻ አይደሉንም? የት ላይ ነው የጣና ኬኛ ትርፍ? አቦ ሌንጮ ለታን አማካሪ ስለማድረግ ነበርን ታገድሎው?  

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያዊነት ተድጦ ኦሮማዊነት በተሟላ መሰረት ለዛውም በጥድፊያ እዬተሰራበት ስለመሆኑ አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶር አብይ አህመድ፤ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሌት እና ቀን እየሠሩ ስለመሆኑ እኮ ተነግሮናል።

ሦስቱ ምን እየሠሩ እንዳሉ አቶ አዲሱ አረጋም ስላተሙበት ማለት ነው። እኔ የሦስቱ የሲኦል መንገድ ነው የምለው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ አምላክም ስላላት።  ማረጋገጫው ተስጥቶናል። ግን ፈጣሪ አለ። ስለ አዲስ አባባ የባለቤትነት ጉዳይ እዬሰራን ነው ተብሎ ተነግሮናል። እሱስ ኢትዮጵያን ሱሴ ማድረግ ይሆን? ከእናት አገር የተለዬ ጥቅም ለማግኘት መስራትስ እሱስ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ይሆን?

በሌሎች ከተማ ማስፈር ይቻል እንደነበረ ተገልፆል እነዛም እኮ የነፍጠኛ ከቶሞች ናቸው። ነፍጠኞች የከተሟቸው ስመሆናቸው በርቀት ታሪክን ማገላበጥ ነው። ከተማ መመሰረት ጸጋው የሆነ ማህበረሰብ አለ። ንግድ ጸጋው የሆነ ማህበረሰብ አለ። ጥበብ መክሊቱ የሆነ ማህበረሰብ አለ። እርባታ ጸጋው የሆነ ማህበረሰብ አለ። እርሻም መክሊቱ የሆነ ማህበረሰብ አለ። ሁሉን አጣምሮ የተፈጠረ ደግሞ ማህበረሰብ አለ።
 
·       መሳቂያው ገመና።

አገር እዬተመራ ኮንደሚኒዮም ሥር የሚዋደቅ ድርጅት ሊያፍር ይገባል። አቅዶ መሳሳት እና ዕቅድ አፈጻጸም ስህተት መፈጸም ሁለቱ የተለያዩ ናቸው። በህዝብ የአሰፋፈር ስብጥር ላይ እንዲሳሳቱ ደግሞ አይፈቀድላቸውም አቶ ለማ መገርሳ። የህለውና ጉዳይ ስለሆነ። ትርጉሙ ሙሉው ተተርጉሟል። ከተከበሩ  የኢትዮጵያዊነት ሰማእት ዶር አብርሃም አለሙ ፌስ ቡክ ማግኘት ይቻላል። ፈጽሞ ማስተባበልም አይቻልም። ሰው በለበጣ ቀልቡ ሊገዛ ይቻልል ነገር ግን ፈጣሪ ንጹህ ልብን ብቻ ነው የሚሻው።

„ኢትዮጵያዊንተ ሱስ ነው“ ማድረግ የነበረበትን የተፈናቀሉት ወደ ቀያቸው ነው መመለስ ነበር። ስህተቱ የተለዬ በመሆኑ። በዚህ ውስጥ ዲስክርምኔሽን በግራቀኙ ህዝብ ላይም አለበት። ይህ ደግሞ በአደባባይ ነው የተሰራው።

አዲስ አባባ ላይ እኮ የአደባባይ ጭፍጫፋ ተካሂዷል … አዲስ አባባ ሚሊዮኖች በራሳቸው ወጪ ቲሸርት አሰርተው የፈንጅ ስንቅ ሆነው ግን ጭፍጨፋ እና ካቴና ነው ያስተናገዱት። እነ አቶ ታዬ ደንኣ እነ አቶ አዲሱ አረጋ ምን እና ምን ሲሉ ነበር? የመደቧቸውን እነ ዝልዝል የፖሊስ አዛዥ ወገኖቻቸውን መጠዬቅ ነው።
·       ኡኡ የመርህ አለህ?

በዬትኛው አገር ዴሞክራሲ ይሆን ከንቲባ አዲስ ህግ ተሻሽሎለት ከሌላ ቦታ መጥቶ አንድ ካድሬ ተመድቦ የሚወያውቀው? የት አንድ አገር ይጠራልኝ። ፖሊስ አዛዦቻቸው የአዲስ አባባ ተጠሪነቱ ለማን ነው? ለዛውም ከመከላከያ የተዛወረ ለዚኸው አዲስ አባባን ኦሮማይዝድ ለማድረግ ተልዕኮ? የወሰን እና የማንነት ኮሜቴው ተደራዳሪው እሳቸው እና አቶ ታከለ ኡማ አይደሉንም ሁለት ሰው ከራሱ ድርጅት ዓለማ ጋር ለድርድር ኦፊሻል ሆኖ ሲቀርብ በኦዴፓ የመጀመሪያ ነው?

ይህም በፐለቲካዊ አቅሙ የሚያስፍር ነው። ለዛውም ኮሜቴ 8 ሆኖ አያውቅም። ጎደሎ ቁጥር ነው ደንቡ ህጉ። የማንነት እና የወሰን ኮሚሽን በህግ ጸድቆ፤ ሹመት ተሰጥቶ ነው ይህ ተለጣፊ ኮሜቴ የተፈጠረው። እነ ቁጭ በሉም፤ ይህን አሜን ብላችሁ ተቀበሉም ራሱ ሰው ሆነህ አልተፈጠርከም ዓይነት ነው። የተቃለ መንገድ።   

ለመሆኑ አቶ ታከለ ኡማ ተጠሪነታቸው ለማነው? ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ሳይሆን ለኦዴፓ ማዕከላዊ ምክር ቤት ነው ለአዳማ /ለናዝሬት/ አይደለም ወይ ሹመታቸው ከዛ እንጂ በምርጫ የአዲስ አባባ ምክር ቤት አባል አይደሉም እና። ተጠያቂነትም የለባቸውም በመርህ ደረጃ። መርህ በንግግር አይታረቅም። መርህ መርህ ነው። መርህ ህግ ነው። ህግ ደግሞ በዲስኩር ሳይሆን በድንጋጌው አቅም ነው ሊብራራ ሊተረጎም የሚገባው።

ስብከት እና ዕውነት ደግሞ በእውነት ውስጥ፤ በቃል ውስጥ፤ በመታመን ውስጥ መኖርን ይጠይቃል። ይህቺ ቅንጫቢ ነገር ናት ያነሳሁዋት።
·       ልባም ብልህ ጉዳይ።

ሌላው ይህ መግለጫ እንዲሰጥ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት የአሁኑ ይህን ያህል የመግለጫ ውርክብ የጠ/ሚሩ ቢሮ ጨምሮ አቶ ገዱ ከተነሱበት ጋርም በቅርብ ይያዛል። የአስክድር ንቅናቄን ከደን አድርጌ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በፈቃዳቸው አይደለም የተነሱት ብዬ ሞግቻለሁኝ።

ምክንያቱም የአቶ ለማ መገርሳ የብአዴንን ጉባኤ የመምራት ተልዕኮ ነበረው። ያን የማላገጥ ስሙን እንዳወረሰው ማለት ነው። የጎንደር ሊቃውንት እንኳንስ ለብአዴን ለሌላም የሚተርፍ ልቅና ቅድስናም አላች። ሊሂቃኑ ሌጋሲ ተጥሶ ነው ኢትዮጵያን ያበጃት እንደገና የሥም ተጠዋሪ የሆነው ለዛውም ከኦነግ መንፈስ። ነገም ወጥ ፓርቲ ሲኮን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ ነው የሚኮነው … ኦሮማማ እንዲህ እያተለለ ይጫንሃል። ለዛውም ህወሃት በጅ ካለ ነው።  

·        የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጉምጉም።

የሆነው እንዲህ ነውከመስከረም እስከ መጋቢት ተንሳፈው የቆዩት ዶር አንባቸው መኮነን ለውጭ ጉዳይ / ስለሚመጥኑ ይህ ጥያቄ እንዳይነሳ / ዳግማዊት ሞገስን ከአዲስ አባባ ምክር ምክል ከንቲባነት ለአቶ ታከለ ኡማ ሲባል ገሸሽ ለማድረግ የትራንስፖርት ሚኒስተር እንደተደረጉ ሁሉ ዶር አንባቸው መኮነን ወደ ክልል መስተዳደር ወስዶ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ውጭ ጉዳይ ስለማይመጡኑ ሌላ የሚ/ /ቤት በመስጠት አቶ ለማ መገርሳን ውጪ ጉዳይ ለማድረግ ነው። በቃ ይኸው ነው ትልሙ።

ዶር አንባቸው መኮነን አማካሪነት በጠ/ሚር ቢሮ ያ የግብር ይውጣ ድራማ ቢቀጥል ኖሮ ይህ ቦታ ፍጥጫ ያስነሳ ነበር … የሚኒሶታ ጉዞውም ይኽው ነው። በስውር ተመድበዋል ዶር ለማ መገርሳ። የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ለማ መገርሳ ናቸው። ያው የጠ/ሚር ቦታውም እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። ሰው ጠፍቶ ነው እንዲህ እና እንዲህ እዬተሆነ ያለው።

ለእጩነት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቀረቡ ተብሎበሹክሹክታየተደመጠው የተደረደሩት ሥሞች የማምታቻ እና ግብረ ምላሽ ለመሰብሰብሰብ ብቻ ነው። አቅርበን ነበር ለማለት። የሰርቤ ስራ ነው፤ አሁን ባለው ወጀብ ዶር ለማ መገርሳን ወደ ውጭ ጉዳይ ለማምጣት የግድ ውጥሩቱን የሚያረግብ ንግግር መደረግ ነበረበት። እንደ ማሟሻ ነገር እንጎቻ … ለቁንጥጫ …

 የሆነው ይኸው ነው። ዶር አንባቸው መኮነን አስቀድመው ተሸኝተዋል። ዶር ወርቅነህ ገበዬሁንም አሽቀንጠረው ተጥለዋል። የተመድ ምንትሶ የአቶ ለማ መገርሳ የምህንድስና ጥበብ ነው … እንጂ አሁን ሰብዕዊ መብት ቅንጣቢ ምስክርነት ለማይሰጠው ሰው እንዴት ተመድ ይመደባል? ነገርዬው ጉራማይሌም ነው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ። ኢትዮጵያውያን በዚህ ወጀብ ተጠምድው ሌላ ግዳጅ እንዲወጡ ነበር የታሰበው። ብዙም ግድ አልሰጠንም እንደ አጀንዳም አላዬነውም … ልክ እንደ ኢንጀነር ታከለ የባህርዳር ጉዞ …

ቀጣዩ ደግሞ የኦሮምኛ ቋንቋን የፌድራል ቋንቋ ማስደረግ ነው። ለዚህ ደግሞ የአሁኑ ወጀብ ጥሶ ለማድረግ ያው ሌላ ጣጣ ስላለበት ነው ይህ የአፍዝዝ አደንዝዝ እጸበለስ ለኢትዮጵያውያን የተቀናው። ለዚህ ደግሞ የታወከውን አዬር ማጠብ ያስፈልግ ስለነበር ….

የጠ/ሚሩ ጋዜጣዊ መግለጫም የተለያዬ ሁኔታ በመፍጠር እያደራጁ የሚሰጡት ስብከት ይኸው ነው፤ ሚዛን ከሚደፋው የማይደፋው ቢያመዝንምአፍ እላፊው እንደተጠበቀ ሆኖየጦርነት ዓዋጁም እንዳለ ሆኖእንዴት እንደገለማኝለእኔ ለማውያን ነኝ ብዬ ለወጣሁት ይህን ያህል ቃር የሆነ … ለሌላውማ ምን ያህል ይሆን እላለሁኝሳስበው

በመጣጣፍ የሚሆን ነገር የለም። ልባም ተግባር እዬተከወነ ነው። አዎን እሳቸው ጎንደርን ማዘዝ ይችላሉ ወለጋን ግን አይደለም ገዱ እሳቸው እራሳቸው ማዘዝ አይችሉም። ዕውነቱ ይኸው ነው

ሌላው በመሆን ውስጥ ያለ ተጨባጭ እውነቶች ስላሉ ያን አቅርቦ ማሟገት ነው። መስዋዕትነት በሚመለከት ጸሐፍት ሊወቀሱ አይገባም። ምነው ያን ያህል ስንታገልላቸው ስማችን አንስታችሁ አላሞገሳችሁንም? ጎንደርን ሽፍታ ከማለት ጎንደር እና ወሎ ዘራፊ ሀሺሸኛ ከማስባል „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ ያለውን ህዝብ ያከበረ አንዳችም ነገር አላዬንም። „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ አማራ ምድር ነፍስና ሥጋው ስለሆነ ሆኖበታል።

በዬትኛውም ቁልፍ ቦታ የኦሮሞ ደም ከሌለ እኮ ምደባ የለምከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ገብተው ከተሾሙት ማለቴ ነውእውቅናውም ሙገሳው ከአማራ ውጭ የሆነ በነቂስ ተፈልጎ ነው።

እሳቸው እራሳቸው ቄሮ እንደሚሉት የአማራ የህልውና የማንንት ተጋድሎ ጀግና ነው ይላሉን? ይላሉ ወይ? እንዲያውም ስልጣንን አትሰቡት እያሉን  ነው ጠ/ሚሩ … የአሻግራችኋለሁ ፖለቲካ „አሞራው በረረ ቅሉ ተሰበረ“ በቃልኪዳኑ ፍርፍም እለት ተረጋግጧል። በነገረ እስክንድርም ሚሰጢር ምርመራ ሲደረግበት መጪው ምርጫ ለ እርግጫ ስለመሆኑ ጠንቆይ ቤት መሄድ አያስፈልግም።

ሁሉንም ልብ አለን እናስተውላልን። ብዙ እጅግ ብዙ ፈተናው እያንዳንዱ የነፃነት ታጋይ አሳልፏል። የእነሱን ያህል ክብር እና ሞገስ ያገኜ ግን የለም። ማነው የተጋላላቸው ዛሬ የሚያብጠለጥሉት፤ የሚአሳድዱት የአማራ ልጅ ነበር። ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን። እምናፍርበት የታሪክ ሆነ የተጋድሎ ጥቅርሻ ስለሌብን። ዓለምም ያውቀናል አሳምሮ። ድምጻችን ሲሰማ እንጂ እንዲህ ሲያበሻቅጠን የሰማንበትገጠመኝም የለንም።
·       የለማው ሰብዕና።  

ክብር ልዕልና መሻት አሉታዊ ኢጎ የእርሰዎ ሰብዕና አይመስለኝም። ጠ/ሚር ለመሆን ያለመቻል ግን መርህም የሚያግደው አለው። የተወካዮች ምክር ቤት የመሆን ጉዳይ ነበር ሚስጢሩ። ያም ቢሆን ቅንነቱን አንግሰናዋል። ሌላ ቢሆን አቅም ያለውን ያስገልላል። ‚ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል“ ይላል ከሥር ሆኖ ለመታዬት አይፈቅድም ነበር - ለላው ሊሂቅ። ይህን ባለማዬታችን ነው እኛ ያመሰገነው እንጂ ልወዳደር ቢባል ለጠ/ሚር እጩነት መርህ አይፈቅድም የፖለቲካ ሹመት ምደባ የተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ጋር ስለማያስኬድ።

በሌላ በኩል ከሌሎች የኦሮሞ የፖለቲካ ሊሂቃን የሌለ የዶር ለማ መገርሳ በኩል ጥልቅ የሆነ ሰፊ ረቂቅ ዓላማ አለዎት ኦሮማማን የአህጉሩ ገዢ አድርጎ የማውጣት። እድሉን በበቃ ምህንድስና ተወጥተውታል።

ሌላው ቢሆን ለእኔ ካልሆነ የፈለገ ይቀመጥበት ይል ነበር። ይወዳደር ነበር ከዛ መርሁ ስላማይፈቅድ አንዱ ይመረጥ ነበር። ወይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወይ ደግሞ አቶ ደመቀ መኮነን። አሁን ያለው ዕድል የተገኘውም የጠ/ሚር ቦታውን ስለተጨበጠ ነው። በዛው ልክ መቃውሩን ሁሉ የመቆጠጠር አቅም ተገኝቷል።

በዬቀዬው ዜጋ ጊዜው የእኛ ነው ተብሎ ፍዳውን እዬከፈለ ነው የሚገኘው። ለሚዲያ ያልበቁ ስንት መከራዎች ህዝባችን እያስተናገድ እንዳለ መንፈሳችን ይነግረናል። ኢትዮጵያዊነት መሬት ላይ ቢሰራበት ኖሮ ግን ይህ ሁሉ ትርምስ አይፈጠርም ነበር። አትፈልጉትም ፈጽሞ። ጉዳዩ በምልዕቱ የፍቅር ጥገት በ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው በሞቶው ውስጥ የውሃ ልክ ሰርቶ ኦሮማማን ማንገስ ነው ፍልስፍናው። ኢትዮጵያዊነት ደግሞ በተጠጋው ልክ ነው ለፍሬ የሚበቃው። በስተቀር እንዲህ ማህል ላይ ያስቀራል። አንዲት ቃል በደሜ ውስጥ ሊገባ አልቻለም። ያ እንደ የፆም ውሃ የሚናፍቀኝ ድምጸዎት። እኔ ፍጹም ደጋፊያችሁ … ነበርኵኝ።

ለዚህም እኛው እራሳችን ተግተን በሰራነው የድጋፍ እርካብ ላይ ለኦነግ የኩሬ ውሃ ፍላጎት ስኬት እንደገና የመስፋፋት አቅም የመፈጥር ፍልስፍና ሆኖ ስናይ መሞጎት ግዴታችን ነው። በፈለጋችሁ ሁኔታ ብትመጡ መተማማን ከእንግዲህ የለም። ረስታችሁናል። እኛም ረስተናችሁዋል። ለመሆኑ አቤቱታ እቀርቤ ነበር ከዬት አደረሱት? አንዲት ቅንጣት አትኩሮት ሳይኖሮውት ስለምን አልጠዬቃችሁንም አይበሉን? እባክወትን? ከአገር በፊት ዜግነት ያለ መስሎኝ „አብይ ሆይ“ የሚል ረጅም አቤቱታ አቅርቤ ነበር። አሁን አሁን ሳስበው ከኦነግ ፍርፋሪ የመለመን ያህል ስለሚሰማኝ ይቀፈኛል … ስለ ጀግና ሃይለምድህን አበራም እንዲሁ ቢሯችሁን የጠዬቀ ነገር አቅርቤ ነበር።

ያው ራስ እግሩ እናንተው ስለሆናችሁ የውጭ ግንኙነት ለትንፋሽም ክፍት ቦታ አትገኝም … ይህን ፎቶውን መመልከት ነው። የኦዴፓ ቢሮ ነው የሚመስለው ጠ/ሚሩ ቢሮ …

ቢገርመዎት እንዲያውም ተጋድሎውን አልጀመርነውም እንጀምረውና እንተጋበታልን። ለኦነግ ዓላማ እና ዓርማ አልተገልነምና ጽፌዋለሁኝ ይህ ከሆነ ጥቁር እምለብስበት እኔ ስለመሆኔ። እኔ ብቻ ነበርኩኝ በመላ ዓለም ሁሉ ተለይቼ እኔ ለማውያን ብዬ የወጣሁት።“ ደፋር እርምጃ ነበር። የታግለኩትም ወደ 300 ጹሑፎች ጽፌዋለሁኝ። ከተከደነው ጥረቴ ባሻገር።

ለነገሩ ቀንበጥ ብሎግም ሥራ የጀመርኩበት ለዚህ ለውጥ የበኩሌን ድጋፍ አደርግ ዘንድ ነበር። ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያዊነት የበታችን ለማስደረግ፤ በኦነግ አርማ ሥር አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን አርማችን ለማስደረግ፤ አማራነትን ለማስደቆስ አልነበረም።
  
ቀድሞ ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰጠው ፍቅር በኦነግ ዓርማ ሥር መፈንደቅም ለርስዎ ሰብዕን የተገባ አልነበረም እውነቱ ይነገረኝ ካሉ። ሚሊዬነም አዳራሽ ያዬነው አይተናል። የታዘብነው ታዝበን።አመት በኋዋላ እራሱ በፍሬም ውስጥ የግድግዳ ጌጥ ሆኖ አቧራ ሲጠጣ የባጀውኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውተደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳምጠናል በራስዎት አንደበት።
·       ውዶቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች።

ዶር ለማ መገርሳ በዝምታቸው ውስጥ ምህንድስናቸውን ስለሚከውኑ የፈለገ የፈለገ ቢል ጉዳያቸው አይደለም፤ የልባቸውንም ስለሚያደርሱ ዝምታቸው እና መናገራቸው ልዩነት አለው። ለእኛ ደግሞ ጣና ኬኛን መልሶ ለማምጣት ሃይልና ጉልበት ከሆነ ብቻ ይሆናል እንጂ መንፈስ መንፈስን የሚገዛ በቃል ውስጥ መፅናት ብቻ ነው።

የአንድ ጋዜጠኛ መብት በአደባባይ መረገጥ ማለት የራስን ባለሜንጫ ተሸክሞ አያስኬድም፤ ሙግቱ በእውነት ላይ ነው። እላፊ ንግግርም በውነቱ ለዶር ለማ መገርሰ ሰብዕና አይመጥንም። በጣም እላፊ የሄደ አነጋገር አለበት።

ሌላው ስለ ዜግነት አንስተዋል። ማን ሰጪ ማን ነሺ ይሆናል? ይህንንስ ማን ቀማ። ባለሥልጣኖቹ፤ ገዢዎቹ ማማ ላይ ያለው የእናንተው መንፈስ ነው። እኛም ጊዜ የማያስተምረን ፈቅድን አነገስን፤ አጰጰስን፤ ታቦት ይቀረጽላቸው አለን፤ የምዕት ቅኔ አለን፤ ምን ያላደረገነው፤ ምንስ የቆጠብነው ነገር ነበርና?

ይልቅ ዜግነቱን የተቀማው እኮ የጊዲኦ፤ የቡራዩ፤ የለጋዳዲ፤ የ አዲስ አባባ ህዝብ ነው። ብቻ ልስላሴ ያንደበት ሲሆን መልካም ቢሆንም ልብ ሲለስልስ ሲያዝን መልካም ነው በግሪደር ስለታረሱት የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ግድ የሚለን ዜጎች ስላለን ዝም አንልም ደግሜ እምገልጸው እላፊ ሄዶ መናገርም ለርሰውዎ ሰብዕና አይበጅም በጣም እላፊ ሄደው የወረፉት ስላለ። ፈጣሪንም መፍራት ያስፈልጋል። ሁሉም አላችሁ አሁን። ግን የፈጣሪን ቁጣ የሚያስቀር አቅም የላችሁም። ሃይል የእግዚአብሄር ነው።

መልካም የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነት … ሹመት ለዶር ለማ መገርሳ ይሁን ትግሉ ይቀጥላል ደግሜ ደጋግሜ እምለው … ቢያንስ እግዚአብሄርን ፍሩ። መዳህኒዓለም የመጋቢት አንድ ቀን ያሳዬው ታምር ለዚህም ነው ብላችሁ እሰቡት

ኢትዮጵያዊነት ሲያሸንፍ እንጂ ተሸንፎ አያውቅም። ኢትዮጵያዊነት ከውጭ የሚጫን ሸቀጥ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው። መንፈሱ ደግሞ ቅዱስ እና ተፈሪ ነው። ኢትዮጵያዊነት የረገጠውን የሚበቀልለት አምላክ አለው። ኢትዮጵያዊነት ተረግጧል።

ቅድሰናው ደግሞ ፈተናን አሸንፎ የመውጣት ሙሉ አቅም አለው። ሊዳፈር የሞከረውን ሁሉ እንቆቆ ሸልሞ እሱ ከመንበሩ ቁብ ማለቱን ያውቅበታል። ስለምን የራሱ ረድኤት፤ ጸጋ በረከት ስላለው። ቀደምትነቱ ደግሞ የሰው ልጅ መገኛነቱን አብስሯል። እግረ መንገዴን አዲስ አባባ የሉሲም ከተማ ናት።
·       መካች።
በተረፈ ትንሽ ምንጮችን ለማገናዘቢያነት መለጠፍ የሚያስለፈልግ ይመስለኛል። ታሪኩ ስለሆነ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ በፈተናው ውስጥ ምን እና ምን ሆኖ ሲለጋ እንደባጀ ያሳያል …

    ተጨማሪ ጥቂት የማነጻጻሪያ  መረጃ አባሪ። ሞራሉን አምጦ ለመውለድ እነዚህ ገመናዎች ይለፈ የሚሰጡ አይመስሉኝም። ማናቆ ናቸው እና። ህሊናም አለ ፈራጅምፈጣሪም አለ አዘቅዝቆ ይመለከታል።

Ethiopia: የአቶ ለማ መገርሳ ንግግር ያስነሳው አቧራ ሲፈተሽ | 108 አመቱ ወጣት ጋር የተደረገ ቆይታ

ርዕዮት ሚዲያ ከዶር አብርሃም አለሙ ጋር ባደረገው ቆይታ ምንም የትርጉም ግድፈት ያለነበረበት ስለመሆኑ በድጋሚ ተርጓሚው ያረጋገጡበት ቃለ ምልልስ።

ለማ መገርሳ በልዩ ሃይሉ ታግዞ፣ በጌድዮ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው፣ ዘግናኝ 
ግድያና ማፈናቀል አልጀዚራ አንደዘገበው።

የኦህዴድ/ኦዴፓ ሜዲያዉን የመቆጣጠር እርምጃ #ናኦሚን በጋሻው
ብአዴን(አዴፓለሌላ ዙር መከራ አሳልፎ እየሰጠን ነው፡፡አዲሶቹ ተረኞች በሁለት እግራቸው ሳይቆሙ በፊት መላ ሊባል ይገባል
March 10, 2019
ብአዴን(አዴፓለሌላ ዙር መከራ አሳልፎ እየሰጠን ነው፡፡አዲሶቹ ተረኞች በሁለት እግራቸው ሳይቆሙ በፊት መላ ሊባል ይገባል
March 10, 2019
ኦዴፓ የዘረጋው አመራር መዋቅር በአዲስ አበባ!
March 23, 2019
የተጀመርከው የብሽሽቅ ፖለቲካ እመነኝ የሚጎዳው ህዝባችንን አንድ ላይ ነው
March 7, 2019
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በሜኖሶታ “የኢትዮጵያ” (አካ ኦሮሚያቆንፅላ /ቤትን መርቀው ከፈቱ (አያሌው መንበር)March 2, 2019
ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው
February 26, 2019

ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ህጋዊ መስመር የማስያዝ ስራ ከመቼም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል” – ወይዘሮ ሎሚ በዶ (የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ)
February 22, 2019
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ከየካቲት 19 ቀን 2011 . ጀምሮ በሚያደርገው አራተኛ ዓመት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ወደ ህጋዊ መስመር የማስያዙ ስራ የሚቀጥል እንጂ ወደ ኋላ የሚመለስ ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
/ አብይ /ቤት “በኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም” – ግርማ ካሳ
February 20, 2019
የአቶ ለማ /ቤት
” 
አቶ ለማን ማናገር አትችሉም
የኦሮሞ ክልል መሬት አስተዳደር
ቤታችሁ ከመፍረስ አይድንም። ልንተባበራችሁ አንችልም
/ አብይ /ቤት
በኦሮሚያ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም
ይሄን ጊዜ የኦሮሞ ቡድኖች ቢሆኑ ኖሮ የመጡት …..እናንተው አረፍተነገሩን ጨርሱት …
ቢቢሲ ከዘገበው የተወሰደ
ክምታደርገው ይልቅ የምትናረው ብዙ ርቀት ይጓዛል (ይኄይስ አእምሮ)
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94303“
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ላሉት ክፍት ቦታዎች 350 ሠራተኞች ተመልምለው እንዲሰለጥኑና እንዲቀጠሩ የሚመለከተውን ክፍል ያዛል አሉ – ከሁነኛ ምንጮች የሰማሁት ነው፤ በሚዲያም ተገልፆ ከሆነ አላውቅም፡፡ ትዕዛዙ የደረሰው ክፍል በአጭር ጊዜ ውስጥ ምልመላውን አካሂዶ 350 ሰዎችን ስም ዝርዝር ያቀርባል – የሰውነት ደረጃችሁን ያልሳታችሁ ጤናማ ወገኖቼ እንዳትደነግጡ እነዚያ ሰዎች ሁሉም ኦሮሞ ናቸው፡፡ የበላይ ማኔጅመንቱ ውስጥ የሰው ሽታ ያላቸው ጥቂት ርዝራዥ አሳቢ ሰዎች ኖረው መሆን አለበት “አይ፣ በዚህ የለውጥ ጊዜ ይህማ እንዴት ሊሆን ይችላልአየር መንገዱ እኮ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው፤ ከሁሉም ዜጎች በአዲስ መልክ ምልመላው ይካሄድና ይምጣ” ተብሎ ይመለሳል፡፡ እንዲያም ሆኖ ተሻሽሎ በቀረበው ዝርዝርም 350 170 በላይ የሚሆኑት ኦሮሞዎች ናቸው፡፡ የገባንበትን አረንቋ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ ወያኔዎች ጥቁር ውሻ ይውለዱ፡፡“ አሜን ብለናል።
የሚኒስትሮች ሹመት – ሳይድበሰበስ! (ዮፍታሔ)
የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን አዲሱ መዋቅር የሹመት ዝርዝር:-
1. እናትአለም መለስ ዋና ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
2. ነጻነት አለሙ…………/ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
3. ሳሙኤል ከበደ ……../ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
4. ዮሚ ተመሰገን…….……../ዳይሬክተር (ኦሮሞ)
5. ካሳ /ሰንበት…….. አማካሪ (ኦሮሞ)
6. ውብሸት ወልዱ……..ልዩ ረዳት (ኦሮሞ)
Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡
ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን ቤንዚን አርክፍክፎ ያቃጠለው የኦዴፓ ጭንቅላት።
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019
ኦፌኮ ደግሞ ይህን ኮሶ ይዞ ብቅ ብሏል
የኦሮሚያና የፌደራሉ መንግስት ሊከሰሱ ይገባል - ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ | Ethiopia
Published on Mar 16, 2019
  
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!


የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።