ግን አቶ ዮናስ ደስታ ይህችን ምድር ሲገናኙ ስንት ጊዜ ይሆን እልል የተባለላቸው ... ?


እንኳን ደህና መጡልኝ

የጠ/ሚር አብይ አህመድ
           ሦስተኛው …
መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ።

„ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤

--- ምን ታደርጋለህ? አልኩት።“

መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪

ከሥርጉተ©ሥላሴ።
Seregute©Selassie
22.04.2019
ከእመ ብዙኃን ሲዊዚሻ።
የዘመን ጀግና! የሃቅ እጬጌ!


   እፍታ።

HelloTube

"የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዮናስ ደስታ ከስራቸው ተባረሩ።
ላለፉት ስምንት አመታት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር
ጀነራል የነበሩት አቶ ዮናስ ደስታ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ትእዛዝ 
ከስልጣናቸው ተነስተዋል። አቶ ዮናስ ስለመሰናበታቸው ሲናገሩ
"ወደሚቀጥለው የህይወቴ ምእራፍ ስሸጋገር የተደበላለቀ ስሜት 
ቢኖረኝም የጠ/ሚር አብይን እርምጃ በፀጋ ተቀብያለሁ" ብለዋል
ለጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት። አቶ ዮናስ በኃላፊነት ቆይታቸው ፊቼ
ጨምበላላና የገዳ ሥርዓትን በዓለም ቅርስነት አስመዝግበዋል።"


·        ከፍል ሦስት

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ደህና ናችሁ ወይ? ክፍል ሁለትን በአቶ ዮናስ ደስታ መንፈስ
 ሥልጣን አለን ብሎ ለመረማመድ የተወሰደው ግፋዊ እርምጃን ያጠናቀቅኩት 
እንዲህ በማለት ነበር …

„ዛሬ በሚኒሊክ ቤተመንግሥት እደሳት ባለሙሉ ሥልጣን ዳይሬክተር ሳይጠዬቅ፤ ሳይማከር ስለሆነው ነገር በአንድ ደብዳቤ ሲባረር ይህ የምሥራች ሆኖ መርዶውን
ተሸክሞ ከረባት እና ገበርዲንን አሳምሮ እንዲህ መሆን /ወደ አንቦ መጓዝ/ 
የሽንፈቶች ሁሉ ቁንጮ ነው ለእኔ። ብአዴን በዚህ ጉዞ ተዋርዷል፤ ማቅ ለብሶ ነው የሚመለሰው። ለነገሩ "ለሚኒሊክ ሰፋሪነት የተገባ ነው" እንዲህ በስል ገብቶ ጥቃትን ማሳታጠቅ ... 

አቶ ያሬድ አስራት በቲተር ገፃቸው እንዲህ ሲሉ ነው የገለጹት። የእኒያን የዘመን 
አርበኛ፤ ደፋር፤ ጀግና የ ኢትዮጵያ ባለውለታ …

„አቶ ዮናስ ደስታ፤ የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፤ "የሚኒሊክ ቤተ-መንግስት ታሪካዊ ቅርስነቱን ባልጠበቀ መልኩ መታደሱ ስህተት ነው" ብሎ 
አስተያየት በመስጠቱ በጠ/ አብይ ደብዳቤ ዛሬ ከስልጣን መነሳቱ ታውቋል። #StopDestroyingOurHeritage

ይህ የሁሉም ድምጽ መሆን ሲገባ፤ አብሶ „ለሚኒሊክ ሰፋሪዎች“ ለአዲሱ 
ሽብሸባ ደግሞ አዲስ የሞት ዋዜማ ላይ እንገኛለን … 

ቅኖቹ … 

ክፍል ሦስት ከመቀጠሌ በፊት ተንሳፋፊ የተደረጉት የብአዴኑ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ ጃንጥራር አባይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውም ተደምጧል። /ይህም ለጊዜያዊነት ነው/ ትቅማጥ እንደያዘው ሁሉ ወጣ ገባ የሚለው የሹመት ሰንጠረዥ በአፍ ጢም የሚደፋ አውሌ አለበት ... በትን በትን የሚለው ... መጥኔ... የጸና ወዳጅ አይሻም፤ የጸና መንፈስም በሽታውን ይቀስቅስበታል፤ በተለይ ሞጋች ከሆነ።  

ያው ቀደም ሲል የዶ.ር አንባቸው ዕጣ የገጠማቸው ናቸው አቶ ጃንጥራር አባይ ተንበርካኪነቱን እንደሳቸው ተቀብለው ልብ የተገጠመላቸው ዕለት የዶር አብይ አህመድ ማለቴ ነው ለህወሃቱ ኦህዴድ // ለኦነጉ ኦዴፓ ለሦስተኛ የማዕከላዊ ኮሜቴ አባልነት ይታጫሉ። አንደኛው እጬጌው ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሲሆኑ፤ የኦዴፓ ማዕከላዊ ምክር ቤት የክብር አባል ናቸው። ይህን ሁሉ ምስቅልልቅ የሚመሩት። አሁን ድል ላይ ነው የንጉሱ ጥላሁ አርሲኛ መንፈስ ባህርዳር ላይ።

ልክ አቶ ሳጅን በረከት ስምዖን ያደርጉት የነበረውን ኦርጅናሉ ነው በአማራ ህዝብ
ላይ እያስፈጸሙ የሚገኙት። ሁለተኛው የ ማዕከላዊ ምክር ቤት ተጠባባቂ አባል
ደግሞ የእግር ሚዜው ዶር አንባቸው መኮኑን ስለመሆናቸው አዬን፤ የሚገርመው
„የራሷ ሲያርባት የሰው ታምስላለች ነው የሆኑት“ እሳቸው ናቸው ስለ ኦነግ ዓላማ ስለሌንጮ ለታ ድንጋጌ የሚተጉት እንደነገሩን … ማፈሪያ! 

የሰው ልጅ ለሌንጮ ለታ መንፈስ ያደረ ዕለት ሱሪውም ቀበቶውም በቁሙ ወልቋለኝ
 ማለት ነው። መቼ ይሆን ዶር አንባቸው መኮነን ወደ አቶ ሌንጮ ሆቴል ካባ እና 
ተክሊል ይዘው ጎራ የሚሉት፤ እና የጸጋ ስግደቱን ሲያስነኩት የምናዬው ...?

ለመከላከያ ሚኒሰትርነት ቦታ ልዑልነት ሲባል የህሊና ዲሞሽን የደረሰባቸው ኢትዮጵያን የመንፈሳቸው ልዕልት ያደረጉት ቅኔያዊት  ወ/ሮ አይሻ መሃመድ ወደ ነበሩበት ሲመለሱ፤ በቀጥታ ሌላ የሥነ - ልቦና ስቃዛት የተዳረጉት ባጣ ቆዬኙ የብአዴኑ ጃንጥራር አባይ ነበሩ። ድክመታቸውም፤ ውድቀታቸው ሳይነገር ከቦታቸው መነሳታቸውን አደመጥን አሁን አዲስ ሹመት ሰምተናል፤ ለተንሳፈፊ ብአዴን ተሰጥቶ የነበረው ቦታ ተችሯቸወል፤ የሙከራው ጣቢያ የሚከወነው በብአዴን ነው። ምን አለ ሌሌ ሲገኝ ... ስለምን ገቢዎች ሚ/ር ላይ ይህ አልተሞከረም ነበር? 

ይልቅ ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን አንድ የመንፈስ እህት አግኝተዋል 
… ወ/ሮ ጠይባ ሃሰን … ይህ ራሱ ለሚኒሊክ ቤተ መንግሥት ትልቅ ቀይ 
መስመር ነው። „ለሰፋሪዎች፤ ለስደተኞች፤ ለመጤዎች“ ማለቴ ነው …

… ግን ተንበርካኪነቱ ከቶ ተመችቷቸው ወይንስ ሲያባንናቸው አድሮ ይሆን
 ዶር አንባቸው መኮነንን? ? ምን ምን ምንስ አላቸው ይሆን? ገዳገዳ፤ ቀን
 ሲከፋ እንዲህ ያንከረፍፋል ይከረፋልም።  

እንዲህ መርህአልቦሽ ይሆናሉ ብዬ አላስብም ነበር ዶር አንባቸው መኮነን።
አንቦ ውልቅልቃቸውን አውጥቶ ሸኝቷቸዋል። ጋይንቴ መሆናቸው ራሱ 
አጠራጠረኝ። ጋይንትን አሳምሬ ነው የማውቀው እያንዳንዱን የገበሬ መንደር።
መንደር ምስረታ ከዛ ነበር የሠራሁት፤ ታች ጋይንት፤ ላይ ጋንት የስይቴውን አንባ 
ስማዳን። … የ አንቦ ጉዞ ዋንኛ ዓላማ ብአዴንን ልክ እንደ ግንቦት 7 ከሁለት 
መተርተር ነበር። ጋይንት እኮ የቅኔ ባዕትም ነበር ...ስንት ሊቀ ሊቃውንት የፈሩበት እንዲህ ቁልቁል አወረዱት እንጂ ...

 ይህም ተሳክቷል ውርዴቱ ማለቴ ነው ። ኦዴፓ ላይ የነበረውን መከራ በዚህ መልክ
 ሽግግሩን ፈጽመዋል የተከበሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ብአዴን በመንፈስ ደረጃ
 በክልሉ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ስላማይረብሹት፤ ፍጸም ሰላማዊ ስለነበሩ የ አማራ ድርጅቶች የውስጥ ሰላም ነበረው አሁን ግን አዲስ ያፈነገጠ መከራ ተሸክሞ ነው የተመለሰው። መንፈሱን በ አዲስ ፋስ ከሁለት ነው የተረተሩት። 

የኢትዮጵውያን ተስፋ ሁሉ ነበር ብአዴን። ይህን የሠራው ደግሞ የአሁን አላስፈላጊ ግንኙነት ነበር። ቀድሞ ነገር አገር እዬመሩ እኮ ዞግን ማሳደድ ተፈላጊም አልነበረም።
ያው ሲጦዝ ማሰተንፈሻ መጫሪያ ገል ፈላጊው የወገሚቱ መንግሥታዊ አስተዳደር ሰነፉ ይተባህል ነው። 

ጣና ኬኛ ለኦነግ መፈንቅለ መንግሥት ዋና ሞተር ሆኖ አገልግሏል። ኦነግ በህወሃት ላይ የቋጠረውን የ27 ዐማት ቂም ያወራርድ ዘንድ ግርባው ብአዴን አስደረገ … ድሉም
የእኛ ነው እኛሞተን ሌሎችን ከሞት አስቀረነ የተባለው በአደባባይ ነው … የሚሊኒዬም የመጋቢት እስከ መጋቢት በዓል አከባበረም ይኸው ነው። የአቶ ለማ የዴሞግራፊ 
የመፈተኛ ንግግርን እርገትም የሰጠ … ን ይኸው ነው። 

እነሱ ከራሳቸው ዞግ ውጪ ስለሌላው የነፃነት ትግል ጨንቋቸው፤ ጠቧቸው። እኛ ብንለው ያምራል ... ለ አንድ ኦሮሞ እንታገላለን አሉ እሱን በህብራዊ ቨርዥን እያሳዩን ነው ... ሰው ገድሎ ሰቅሎ፤ ሰው ገደሎ አቃጥሎ እስከመተወን ... 17 ባንክ ተዘርፎ እሰከማዬት ... 

የህወሃተቱ ብአዴን/ የ ኦነጉ አዴፓ ቆፍጠን ብለህ ወደ ሆላ ተወርውረህ መጠቃጠቂያ የተደረክበትን የፖለቲካ ብልት በስክነት በለተህ ቢያንስ ክብርህን ማስጠበቅ ሲገባህ ሄዶ መንበርከክ ሞት ይሻላል …

ይልቅ ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከቤተዘመዶቻቸው ከወ/ሮ ጠይባ ሃሳን 
ጋር ሰርግና መልስ ሆኖላቸዋል። 

መጨረሻውን ያዬ ሰው ይህን የአንድ ሰው አሻጋሪነትን ፍልስፍና … ሥም የለሹ፤
ይፋዊ የሆነ ቅርጽ የለሹ - ፎርም የለሹ አቶ ሂደት በ4ኪሎ … መፈንቅል መፈንቅል አይሸታችሁም ወይ? በስል ገብቶ እኮ ኦነግ መፈንቀለ መንግሥት አድርጓል ብዬ አስባለሁኝ፤ የ80ዎቹን ድል አግኝቷል። ያልተገለጠው ድንብልብል ገመና ይኸው ነው። ፍኖተ ካርታ ምንሶ ቅብጥሮስ እያላችሁ እባካችሁን ልቡን አታፍስሱት ... 

ከብረቶቼ ... ይህን ለማያያዣ ካነሳሁ ዘንድ ... አሁን ዘመን ስለሰጠን የመርህ የእውነት አንጡራ የአባት የእናቶቹ ልጅ እንቁወጣት የእውነት አርበኛ ስለ አቶ ዮናስ
ደስታ በጠራራ ጸሐይ የዜግነት ገፋፋ የጀመርኩትን ልቀጥል።  

ግን ግን ወላጅ እናታቸው ክብርቷ፤ እመት በዜናሽ ጀግና ዮናስ ደስታን ሲወልዱ ከቶ
 ስንት ጊዜ ይሆን እልል ያሉላቸው? የውነት የምዕት ቅኔ ወልደዋልና ደስ ይበላቸው።
ካለ ብርጌድ ካለ ክፈለ ጦር፤ ከለ አዬር መቃዋሚያ ተራራን የደረመሰ የወዶች ቁና ... ወልደዋል ...የድል አንብርት ... ዮናስ ደስታ! 

·       መሪነት እና ላንቁነት።

መሪነት ለሁሉም ሙያ ባለሙያ ስላለው የባለሙያን በነፃነት የመጠበቅ ብቻ 
ሳይሆን አክብሮ የመቀበል፤ ዝቅ ብሎ ምክር የማግኘት ነው። አጤ ፋሲል እጅግ
ደግ መሪ ስለነበሩ በቅደስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በካራ እና በቅባት መሃል ተፈጥሮ
የነበረውን የመቋሚያ መቀጣቀጥ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሁለቱን ወገኖች ቁጭ
አድርገው የሊቀ ሊቃውንት ጉባኤ ተሰይሞ በሃይማኖታዊ ዶግማ ሙግት ነው ፍትህ እያዲያገኝ ያደረጉት ይላል ስለሳቸው የተጻፈው ገድለ ታሪክ።

የንጉሦስ ንጉሥ አጤ ሚኒሊክም ቢሆኑ የአንቀጽ 17 የሸፍጥ ውል እንዲደረመስ ያደረገው ባለቤታቸውን ዘብርሃናተ ኢትዮጵያ የእቴጌ ጣይቱተን ምክር በማድመጥ አቅማቸው ሆኖ ግድል የጻፋላቸውን የጥቁር ታምር የተፈጠመው  በአድማጭነታቸው
 ነው።

የንጉሶች ንጉስ አጤ ቴወድሮስም ብስጩ የሆኑት የቅርብ አማካሪያቸው ባለቤታቸው
እቴጌ ምንትዋብ በሥጋ ሲለዮዋች ነበር ይላል ታሪከ ገድላቸው። ከዛ በፊት ግን ደግ
እና ሩህሩህ እንደነበሩ ሰፊ ዓላማ እና ንድፍ እንደ ነበራቸው ሲሆን አብሶ ብጥቅጥቅ 
ያለውን መንፈስ አዋህዶ ኢትዮጵያን ገናና አገር የማድረግ ህልመኛ ነበሩ።  

ይህ የሚያሳዬው አድማጭነት ሲጠፋ አድማጭነት ሲኖር ያለው ርጋ መንግሥት 
ልዩነት አለው። እንኳንስ ዛሬ በዚህ ባልጸናው ኢትዮጵያዊው ወገሜት አልጋው።
ብዙም ጠላት ማብዛትም መልካም አይደለም።

ስክነት እርጋታ ብሎ ያልፈጠረለት የኢትዮጵያ መንግስት ወገሚት መንግሥት 
ብለው ይሻላል። የበታች መሪዎችን ማድመጠን የተው ዕለት ለመሪነት እዮር 
የፈቀደው ምርቃት ይበረግግና ይሸሻል ምክንያቱም መሪነት ለአሉታዊውም
ሆነ ለአዎንታዊነት እዮራዊ ቅብዕ ነው።

ሰው ስለፈለገ መሪ መሆን አይችልም። ስላልፈለገም መሪ ሳይሆን አይቀርም። 
መሪነት አብሶ የአገር መሪነት እና ሃይማኖታዊ ሥልጣን የፈጣሪ ቅብዕ ነው። 
ዕድሜ ልካቸውን የአገር መሪ ለመሆን እንዳለሙ የሚያልፉ ብዙ ሰዎችን 
ዓለማችንም አገራችንም አስተናግዳለች። ይህ የሚሆንበት ምክንያት መሪነት
ቅብዕ ስለሆነ ነው።

አንድ ሰው መሪነትን ጸጋ ሲያገኝ ዕድሉን፤ ዘመኑን በምርቃት ለማሳለፍ ራሱን
ዝቅ ማድረግ ይኖርበታል፤ በስተቀር ይወድቃል። መንጠራራት፤ ማበጥ፤ አይደለም
ለመሪነት ለተመነትም አይሆንም። ቢያንስ ከእኔ በላይ አንድ ፈጣሪ አለኝ 
የፈጠረኝ ብሎ ማሰብ ይገባል።

አንድ መሪ የበዛ ታጋሽ መሆን ይኖርበታል። አይቶ እንዳለዬ፤ ሰምቶ እንዳልሰማም፤ እንኳንስ ራሱ ለፈጠረው ችግር ሌላው በፈጠረው ችግር ሳቢያ አጥፊ ነህ ቢባል 
እንኳን ስቆ ደስ ብሎት በአክብሮት ማሰረዳት ይገባዋል እንጂ እኔ ቃለ ወንጌል
ወይንም ቁራአን ነኝ ማለት አይገባውም። መታበይ መጨረሻው መሰበር ስለሆነ።

እውነት ለመናገር ጥያቄው እኮ እውነት ነው። የ እኔም ጥያቄ ነው አንደ ዜጋ 
ወይንም የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ቢሮውን መዝጋት ወይንም እሳቸው
እንደ ለመደባቸው ደርበው መስራት እንደ ሰላም ሚነስተር፤ እንደ ገቢዎች ሚ/ር
ይህ የሉሲ የሰላም ጉዞ ፕሮጀክት የሳቸው ነው፤ "መብቴን እጠይቃለሁ ግዴታዬንም እወጣለሁ" የሳቸው ፕሮጀክት ነው። እሳቸው ብዙ ናቸው። 

ስለሆነም ሁሉንም ሚ/ር መስሪያ ቤት ጨፈላልቀው መዝጋት ወይንም ባለሙያዎችን ማማከር ግድ ይላል። ሳቸው እኮ ብዙ ነው የሆኑት። ሌላ ሰው አገር ያልፈጠረች ይመስል። አንድ ጊዜ "የወጣልኝ ለማኝ ነኝ" ሲሉን፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከእኔ ወዲያ ላሳር ሲሉን ...ኧረ በህግ …! 

ስንት ጉድ ነው የሚታዬው። የራስ ቀለም ገመናቸውን ከሰብዕና በታች ድቅቅ 
አድርገው እንደ ሰው አልተፈጠርክም ያሉት እራሰቸውን፤ እነሱ እንኳን ክብር
አግኝተው ጠባቂ ተመድቧላቸው ስንት ጉድ አይተናል። ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ
ሲሰበር፤አዲስ አባባ ላይ ቡራዬ የሆነው የአረመኔነት ድርጊት …

የሆነ ሆኖ እስኪ ይሄ በአደብ ይደመጥ። ከዚህ መንፈስ ጋር ትቅቅፉን ብቻ ሳይሆን የሚሊዬንም አዳራሽ አቀባበል ራሱ ምስከር ነው። ከዛም በዬሚዲያው የሚደረገው
ቃለ ምልልስአቅም የለም፤ መሪው እኔ ነኝ ነውመባልን ሁሉ አዳምጠናል፤ 
ያዘዘውም ጠብ አይልም እዬተፈጸመ ነው። እነሱ ተከብረው አቶ ዮናስ ደስታ 
መባረር ... ህም! ከቶ ስንት ጊዜ ይማጥ? ማን አላቸው ለ ኢትዮጵውያን
ንጹህ መንፈሶች? ማንም የላቸውም። ለነገሩ ቀናተኛ ናቸው አቅም አለው 
ስለሚበለው መንፈስ። ለዛውም እያላቸው ... የማይካድ ብዙ ነገር አላቸው። 

ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት  ለምን አልፈለገችውም – 

ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል


ለነገሩ ዬዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ሊቀመናብርት ችግር ይህ ነው። ዬትኛውም
ተጽዕኖ ፈጣሪ ነፍስ መከራም ይኸው ነው። እነሱ ካሉት ውጭ አይቀበሉም። እንደ
ሰውም እንሳሳተልን ብለው አያምኑም፤ አያዳምጡም። የሚያዳምጡት ከወደቁ 
በሆዋላ ነው። 

ባለው ላይ አቅምን አሰባስቦ ማጠናከር ሲገባ እነሱ ጎልተው፤ ጎምርተው መውጣት 
ካልቻሉበት አዳዲስ ውጥኖች መክነው እንዲቀሩ መትጋት፤ የራሳቸውን ያፈነገጠ
ደጋፊ ነገር መፍጠር መጨረሻ ላይ እንሱም ሳይበረክቱ፤ መንፈስን ነፍስን መበተን ነው። ትውልድን ማባከን። የተደራጀ መንፈስ ከ እነሱ ውጭ ከሆነ አይፈልጉትም። 
ጣውንቱ ነው የሚሆኑት። አሁን ከ አብን አገር ያለው እሰጣ ገባ እነሱ የሌላቸውን
 ሌላው ሲያደርገው ያን ማውረስ ካልቻለ ያ ባለ መንፈስ በቃ ጦር ይመዘዝበታል። 

ሌላው በዶር አብይ አህመድ ደጋፊና ተቃዋሚ መሃከል ያለው ጉግስ ይገርመኛል። 
እኔ ፅኑ ደጋፊያቸው ነው ነበርኩኝ። ይህ ብሎግን የጀመርኩት ለ አብይ አክቲቢዝም ነው። የዛሬው የድል አጥቢያ አርበኛ ሁሉ ሳይሰለፍ፤ እንደ ዛሬ ሁሉም የእኔ ሳይላቸው
ኢትዮጵያ በቃሽ አላት ብዬ ከ2017 ጀምሮ ተግቻለሁኝ፤ ግን ያን ጊዜ የደገፍኩበት 
ሰብዕና ካጣሁኝ መቃወም ደግሞ መብቴ ነው። እንደሳቸው ጦርነት እገባለሁኝ ባልልም፤ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ግን እሞግታቸዋለሁኝ። 

ይልቅ አሁን ልማታዊ ካድሬ ነው አገር እያመሰ ያለው እንደ አቶ ስዮም ተሾመ ዓይነቱ። 
እሳቸው የሚያደርጉት ሥምን በወረቅ ቀለም ቀባቀባ፤ ወይንም አንድ ቦታ ሸጎጥ፤ 
ወይንም ምክር ስጠኝ ብለው የበለጠ ያቀረቡ መምሰል፤ ወይንም በብሄራዊ ጉባኤ
ተናጋሪ አድርጎ መመደብ ከዛ ያ አንቱ የተባለ የፋክት ባለራዕይ ሰው ሙሽሽ ብሎ
ቁጭ ይላል። ልሳኑን ይዘጋል። ወድቆም ይከሰከሳል። እሳች 4ኪሎ ፎቅ ሆነው
 አዘቅዝቀው እዬተመለኩቱ ይስቁበታል። ሰሞኑን አንቤን አንከረባብሰዋቸዋል። 

ይህ ርቁቅ አቅዶ የሚሰራ መንፈስ አንቱ የተባለውን ውቃቤውም ያስርቅና አቅለ ቀላል ሽላሽሊውት አድርጎ ቁጭ ያደርገዋል። በቃ ከዕሴት ውጭ አድርገው ቁጭ ነው የሚያደርጉት። ኤክስፓይርድ ያደረገ መንፈስ። ይህ ዋና ብርጌዳቸው ነው 
የተካኑበት …

አሁን በቅርበት ያሉት ሁሉ ነገ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ ነው። ራሱ ብአዴን ጥምረቱ ከተፈጠረላቸው /ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባ እሱ ነው የሚሆነው፤ ልክ ደርግ መኢሶንን እንዳደረገው ሁሉ፤ ወይንም ህወሃት 
በኢህአፓ እና በኦነግ እንደ ፈጸመው ክህደት ማለት ነው። አሁን አሁን ሳዬቸው 
እኔ ሄሮድስ መለስ ዜናውን ሁሉ እዬመሰሉኝ ነው።


ቀጣዩ ተጠቂ አብን የፊት ረድፈኛ ነው። ግሯቸው ይመጥናል ይበልጣል፤ ልኬታ
ይሆናል የሚባል አቅምን ማሳደድ ዋንኛ አላማቸው ነው፤ በማሰር አይደለም 
ለጊዜው ሰብዕናውን ፈትለው በመደቆስ እንጂ። ከፍ አድርገው ዘጭ ነው። 

እሳቸውን የሚገዳደር አቅም ከዬትኛውም ማህበረሰብ አይሹም። የት ገቡ እነ 
ዶር ኮንቴ ሙሳ? አንድም ቀን ስማቸው ተጠርቶ፤ መድረክ ተሰጥቷቸው አላዬንም? ስለምን? በዛ በዝምታቸው ልክ የተከደነ አቅም እንዳላቸው ጠረኑን አጥንተዋል 
ጠ/ሚር አብይ አህመድ። እነ ዶር አፈወርቅስ የት ናቸው ያሉት?

እሳቸው የአገር አለት ጽኑ የሚባለውን ሁሉ በስልት ፋስ ነው ትርትር ያደረጉት
እራሱ የሃይል አሰላለፉ ተዘበራርቋል ... ብትን ነው ያደረጉን፤ ስልብ ነው 
ያደረጉት አንቱ የተባለውን ጽኑ መንፈስ ሁሉ ...በቃ አቅምየለሽ ሽባ አድርገው አልፈስፍሰው መንፈሱን እግር ከወረች አስረው የቅምጥ ነው ያስኬዱት።  

ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ከሰሩት ከደከሙት በላይ  ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአጭር
ጊዜ ቅቤ አቅርበው መርዝ እያስጨለጡ ብዙ የመንፈስ ድል አነባብረዋል። 
ለተነሰቡት ዓላማ ስኬት ባድልም ናቸው።

ቀድሜ እሳቸውም አያድርጋባቸው እኛም አያድርግብን ብዬ የጻፍኩት፤ ያለኩትን አስተካክዬ እዬዬን ስለሆነ፤ ደርሶናል መልዕክቱና፤ እውን ሆኖ በርግጥም ጠ/ሚር
አብይ አህመድ ዶር ብርሃነመስቀል አበበ እንዳሉት "የኦነግ መንፈስ ወራሽ ናቸው" ስለዚህም ስለ አላዛሯ ኢትዮጵያ ድንኳናችን ጥለን አብረን እናልቅስ ... ወንዝ
ሙላት ሲወስድ እያሳሳቀ ነው ...ና... አቅሙን እማ ከሚዲያ ወዲያ ምን ተገኝቶ። ንፈስ ላይ ነበር አሁንም ንፋስ ላይ ማያዣ መገረዣ ጠፈቶ መንገዋለል ነው። 

የህወሃት ደርግን ጥሎ ሥልጣኑን በተቆጣጠረበት ጊዜ ኦነግ ዋና ተደራዳሪ ነበር። ነገር
ግን ሥልጣኑን ህወሃት ከተቆጣጠረ በሆዋላ ኦህዴድን አቅርቦ ኦነግን ባዶ እጁን ሸኜ።
የዚህ ጥቃት ድርብ፤ ንብርብር ደም መላሽ ናቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ማለት። 
በማን ትክሻ ስትሉ ደግሞ በግርባው ብአዴን ትክሻ  … ነገ ደግሞ እሱ ያገኛታል። 

እናልቀሰ አብረን በቄራ መለከት
በዥንጉርጉር አውታር መሳሳት መዘት
ድገሙት ሰልሱት የጥት አብነት።

ጭልጥ አድርጎ ጠጣው ድቅድቁን ጨለማ
ጭልጥ አርጎ ዋጠው ጥቁሩነን ዘንባባ
ግጥም አርጎ በላው የሽንቱን ጽዋ
ታጠው እሰዬው የስጋት ዳመና።

ያለወቀ ልኩን በጃጅ ለባጀ
ቀብር ላይ መዋልን ለታን ላ
ምስክር ነው እሱ ያሰተኛል ንፋሱን
ለሙጃው ለቁርሻው የእልፍኙ ድሱን።

ሊጋባው ባርነት የስንፈቱን ዝግን
ማዛጋት ጥንስሱ የጥቅርሻ ምሱን። 

  • ሥጦታ ለህሊና ስንፈት። 22.04.2019 ቪኒተ 12.42

·       መውጫ በር ለለት።

እውነት መወገን። እውነት ስትጠቀጠቅ አይ ማለት ይገባል። አሁን በሚታዩ የነጠሩ
ሃቆች ላይ ጎሽ አበጀህ፤ ቀጥል ከሆነ ከዚህ በባሰ ነገ አውሬ ሆነው ይመጣሉ፤ አንድ
ቀንጣ የተለዬ ሃሳብ የማስተናገድ አቅም ፈጽሞ የላቸውም /ሚር አብይ አህመድ። ለዴሞክራሲ ሥርዓት ቀርቶ ለዶሞክራሲ ጠረን ዝግጁ አይደሉም። ሥልጣን እንዲህ ያደርጋል። እሳቸውም ወንበሩ ሲሞቀኝ እምሆነውን አላውቀውም ብለውናል፤ አሁን መጋረጃው ተከፍቶ፤ ምዕራፍ አንዳያ፤ ሁለትያ፤ ሦስትያ ኮምኩመን ወደ አራትያ እዬተሸጋገር ነው ... እያማጥን በዳጥ ተድጠን በምጥ ተቁላልተን። 

እኔ የርግጫ እና የፍጥጫ ምርጫ መጥቶ አይቸው ብያለሁኝ። መኖሩ ከተገኜ። 
በርደኑን የሚችሉት አይመስለኝም፤ ከአሁኑ ነፍሳቸው ደንጋጣ- ርብትብት - ፈሪ
- ትጥቅ ፈቺ ሆኖ ነው የማዬው። የገቡት ቃል፤ የፈረሙበት ውል ያለ ነው የሚመስሉት … ለኦነጋቸው። ለነገሩ በመሰከረሙ የ ኦህዴድ ጉባኤ ላይ "ለ አንድ ኦሮሞ አንድነት እሰራለሁ" ብለው ስለመናገራቸው ከሰሞኑ የአማራ ወጣቶች ህብረት ምሥረታ ላይ
 ወጣቱ ውስጡ ማልቀሱን ገልፆልናል። ሙሉውን ማድመት ካልፈለጋችሁ ከ40.46 ሰከንድ ላይ አለ። ቁርጥን ማወቅ ከቁርጥ ውሳኔ ያደርሳል።  

እኛ ነን የእኛ የምንላቸው እንጂ እነሱ አያስቀርቡንም፤ ጠረናችንም አይፈልጉትም።
አንድ የስሜን ጎንደር የገበሬዎች ማህበር ሊቀመነበር የ ኢሰፓ ማዕካላዊ ኮሜቴ 
ተለዋጭ አባል ነበሩ " የምጠላው ሲወደኝ አልወድም" ይሉ ነበር። የሆነው 
የሚሆነው ይኸው ነው። እዚህ ላይ አለ ሃሞቱን አዳምጡት። 

የሚገርመው ቋንቋውን ሳንሰማው ስንት እንደተላገጠብን፤ ወደፊትም ይህ ልግጫ እንዲቀጥል ነው አሁን የሰመመን መርፌ እዬተወጋ ያለው ዜጋው ... ወደራሳችን እንመለስ። እንደነሱ ሰውን መጥላት ሳይሆን በድቡሽት ላይ ኢትዮጵያ ትገነባለች
ብሎ ከማሰቡ ጋር እንፋታ።  የሰሞኑ ወጣ ገብ ሽረት ሰላባንት እና ሹመትም ፈጣሪ ሚስጢሩን በጻድቃን ተገልጦ ስላሳዬን ነው ... ተመስገን! የ አቶ ዮናስ ደስታ
 መንፈስ የነገረን ሰማያዊ ሚስጢር እና ራሳቸውን የማገዱበት አምክንዮም ይኸው
 ነው። እዬሞትን እባካችሁ አንሳቅ ... 

https://www.youtube.com/watch?v=Sb3Km-ckwsQ&t=24s

የአማራ ወጣቶች ህብረት ያዘጋጀው ውይይት በባህር ዳር ሙሉ ዝግጅት


ኢትዮጵያን በልጽጋ ራሷን ችላ ማዬት ለማይሹት ቀደምት ጠላቶቿ ሁሉመርከብ
ሆነው እያዬኋዋቸው ነው። የሚያሳድዱት መንፈስ የትኛውን ስለመሆኑ ዛሬ ላይ 
ተርጓሚ አይስፈልገንም ... ለዚህ ኢላማቸው ደግሞ አማራውን ...ግርባ 
ማድረግ ነው ከቻሉ። ለዚህ ነው በጥዋቱ የ አማራ ብሄርተኝነትን እንደ ጦር የፈሩት።
ሌላ ሥራ አልነበራቸውም አመቱን ሙሉ። እነሱ የዴሞግራፊ ተግባራዊነት ላይ ሲተጉ
አማራ መሬት ግን በምን ሁኔታ ላይ እንደነበር ልብ ያለን እናውቀዋለን። ለዚህ እጁን ያልሰጠው ህወሃት ብቻ ነው። አክበረውም፤ አቆላምጠውም አዬት ፍንክች 
አላለላቸውም። 

አማራ መሬት ላይ ሊሂቃንም አሏቸው ፈላስማው ዶር ዳኛው አሰፋ፤ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና አሁን በአቶ ዮናስ ደስታ ቦታ ከተኩት በታች አድርገው የሾሟቸው ፕ/ አበባው አያሌው።

እነዚህ የተፈለጉት እዬፈተናቸው ያለውን የአማራ ብሄርተኝነት እንዲቀብርላቸው
ነው … ኦነግ ግን እሳቸው አሉለት። ይህ የእርግጫ ጨዋታ ያልገባው የአንባቸው 
ሌጋሲ ትጥቁን አውልቆ ተንበርካኪነቱን በአደባባይ አውጆላቸዋል። 

እኔ እምለው ሌላ ያላሰቡት አቅም ወጥቶ ደግሞ ቢያንጫጫ ምን ሊኮን እንደሚችል ፈጣሪ ይወቀው። ይህ እውነት ስለሆነ እውነትን ወግኜ እቆማለሁኝ። በፈለገ ቀመር  የኢትዮጵያዊነት ጽኑ ጠረን በውስጡ ከሚጸዬፍ መንፈስ ጎን አብሬ አልሰለፍም።  

ይህን ተቀብሎ ለሽ ብሎ የሚተኛ የአማራ ልጅ ቀብሩን ቢያውጅ ይሻለዋል ...
እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ግን ጤነኛ ስለሆንኩኝ አሻም፤ እምብኝ፤ አይ ብያለሁኝ ... 
መይሳው ነፍሴን የቃኘው ዛሬ ሳይሆን ስጸንስ ነው። 

ኢትዮጵያዊነት ከነገሮች በላይ ነው። ኢትዮጵያን ሰቅስቆሶ ከሚደፋ መንፈስ ጋር
አብሬ አልሰለፍም፤ እኔ የኦነግ ካድሬ አይደለሁም ዝልቡ ብአዴን ለኦነግ ካድሬነት
ጠቅልሎ ስለተሰላፈላቸው እንኳን ደስ አላቸው የዴሞግራፊ ፈላስፎች ... 

ደግሜ ደጋግሜ መግለጽ የምሻው ግን በተከደነ ስውር ደባ ኢትዮጵያ ራሷ ለመፈረስ
እንዲህ አሸሼ ገዳሜ ሲባልላት ይህ የመጀመሪያው ይሆናል። እኔ የአቶ ዮናስ ደስታን መነሳት፤ የባልደራስን ንቅናቄ የማዬው ከዚህ አንጻር ነው። አብንም የሚጠብቀው
ይህን መሰል ሞረድ መከራ  ነው። ጠብቁት።

ሲፈልጉ አሰልፈው ያሰቅላሉ፤ ሲፈልጉ አሰልፈው ያሳርዳሉ፤ ሲፈልጉ አሰለፈው
ያዋርዳሉ፤ ሲፈልጉ አሰልፈው ያዘልፋሉ፤  ሲፈልጉ አሰለፈው ቅስም ይሰብራሉ፤ 
ሲፈልጉ አሰልፈው ያፈናቅላሉ፤ ሲፈልጉ አሰልፈው ያደናቅፋሉ፤ ሲፈልጉ አሰልፈው
 አበባ ያስጣሉ ይህ ነው ድራማው …

ይህን ዘመን በዚህ መልክ አብሮ ዘመኑን ለማረድ መሰለፍ ሬሳነት ነው። ቢያንስ
ሴራውን፤ ደባውን፤ ስውሩን መከራ እያጋለጡ መንገዱ እንዲስተካክል ከማድረግ
የዛሬ ዓመት በ100 ቀናት ውስጥ የተከወኑት ብቻ በውዳሴ ከንቱ ለዛ እዬወረቡ
ዛሬን ማሳረድ የተገባ አይሆን፤ ነገ እንዲሰቀል አብሮ መተባበርም የተገባ አይደለም።

የነፃነት ትግሉ ከአንድ ሰው አሻጋሪነት ወደ ብዙሃን አሻጋሪነት እስኪለወጥ ድረስ ሰፊ የመንፈስ አቅም ይጠይቃል … ለዚያ የእኔ የሚባል አንዳችም ነገር የለም የተደራጀን
አቅም የሚመራ።

ይህ በሌለበት ነው የዞግ ድርጅት በአዋጅ ይፈረስ እዬተባለ የሚታወጀው። ህፃን
ከማህጸን ሲወለድ እኮ እትብቱን ከእትብት የሚለይ ምላጭ ብቻ ሳይሆን 
እትብቱን የሚያስር ፈትል ያስፈልጋል፤ ያ ካልተዘጋጀ እናትም ልጅም ያልፋሉ
 … ጥበብ ያስፈልጋል።

ንደት ፍርሰት ስታስብ በእጅህ በመዳፍህ ያለውን ማወቅ ያስፈልጋል። ትናንት
ምንም ስላንበረን ነው በሰልፍ በጥድፊያ ያን ያህል አገር ለመግባት ርኩቻ የነበረው … ያለው እኮ አለው። ትናጋ ድርጅት አይደለም። ትናጋ እንኳንስ አገርን የእለት ኑሮ ለመምራት እንኳን አቅመ ቢስ ነው።

የነፃነት ትግላችን በረንዳ አዳሪ ከሆነ እኮ ቆዬ … ችግሩ ይህን ባለማወቅ ነው መኮፈሱም ጉራውም ሽብሸባውም … ይህን አሳምሮ ያውቀዋል የአብይ መንፈስ … ለዚህ ነው ጢባ ጢቦሽ የሚጫወተው። 
በዚህ ውስጥ በቅብ መልካም ነገሮች ንፋስ ላይ ተንጠልጥሎ አብሮ ኬክ ቆራሽ ከመሆን መሬት የያዙ የተቋማት ግንባታ ላይ በመተኮር፤ በሰብአዊ መብት ረገጣዎችን በማገለጥ ላይ አብሮ በመቆም ይህ ኦነጋዊ የጭካኔ ጉዞን ወደ ትክለኛው ኢትዮ ትውፊታዊ መንፈስ እንደሚለስ መትጋት ይገባል።

ራሱ ድምጻችን ይሰማ እኮ አንደበቱ ልሳኑ ተሰልቧል። አሁን የአቃቂውን ግፍ ስመለከት
የት ገቡ የነፃነት ኡስታዞች? አጅሬ የገቡበት መንፈስ እንዲህ ነው ትን ትን የሚለው … ትርታው የሁሉም ነው። ትንፋሽን ለመሰብሰብ እንትጋ … ቢያንስ አቅም ሆነው 
ለመውጣት የሚፈጨረጨሩትን አገር ቤት ያሉ ሁለት ጥንስሶችን የጉሮሮ አጥንት አንሁንባቸው።

ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ናት በሁሉም ዘርፍ። እና የቅንጦት ጥያቄዎችን ተግ ማድረግ ይጠይቃል። አማራጭ ሳትይዝ አማራጭ ይፍረስ ይናድ እያሉ ቅድመ ሁኔታ በመፍጠር መንፈስ ከመበተን መቆጠብ ይገባል።
አቅም ያለው ነፍስ ያለው ድርጅት ዲያስፖራ ላይ ያቋቁም። በቅኝ የማይያዝ ራሱን
የቻለ፤ ራዕይ ያለው። ቢያንስ የሎቢ ተግባር ይሰራል። የሌለውን አለ እያለ ኮማን ነፍስ ይዘራል ብሎ ከሚጠብቅ። ያላበቃ፤ ያልደቀቀ ነገር የለም። ስልብ ነው ያለው ሁሉ … ም።

አብዩ እንዲህ ነው በዝረራ ሁሉንም … የከነዳው፤ የለካው፤ የመዘነው እያሳቃቀ።
አሻም ያለው ጀግና ባለ ራዕይ አንበሳ ደግሞ ከሥራ ተባሯል እንደ አቶ ዮናስ ደስታ
አይነቱ። የአቶ አቶ ጃንጥራር አባይ ተመሳሳይ እርምጃ ነው፤ የት ይጣሏቸው? 
እንዲህ ነው ድመት ዓይጥ ገድላ እንደምትጫወተው በሥነ ልቦና ላይ ጢባ ጢቦሽ እዬተካሄደ ያለው …

አዬር ላይ ግልቢያውን አቁሞ አደብ ያለው ተግባር መከወን ይገባል። ለዛም በሩ
ዝግ ነው አገር ቤት። ቢያንስ ግን በዬሚዲያው እዬቀረቡ የ100 ቀኑን ተግባር
ድረስልን ማለቱን ማቆም የመጀመሪያው ቀዳማይ ተግባር መሆን ይገባዋል። 

3 ሚሊዮን ህዝብ አውላላ ሜዳ ላይ ተቀምጦ ነጋ ጠባ ድግሱም ይመረራችሁ 
… ትንሽ ይጎምዝዛችሁ የቤተ መንግሥት ባለሟልነት ለተነጣፋችሁትም … ጥቃት
ላይ ያለ መንፈስ ትጥቁን አጥብቆ ቢያንስ ሰቆቃን የእኔ ነህ ይበለው። ዜግነቱ 
የፖለቲካ አናት ከሆነ …


ውዶቼ ይቀጥላል …

(ከአቶ ያሬድ አስራት ቲተር ገጽ ላይ የተወሰደ።)


ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!


የኔዎቹ ኑሩልኝ

መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።