የሥንኛት ማጫ። (የወግ ቅኔቤት)


እንኳን ደህና መጡልኝ
የሥንኛት ማጫ። (የወግ ቅኔቤት)
 „አቤቱ እርሱን ታውቀው ዘንድ
 ሰው ምንድር ነው?
መዝሙር ፻፵፫ ቁጥር ፫“

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21.05.2019
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ውዴቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ተሰናዳችሁን? የወግ ቅኔቤትን ለመታደም … እንሆ ….

 በድምጽ።

የሥንኛት ማጫ (የቅኔ ቤት ወግ 24.05.2019)


እዬራቅከኝ ስትቀርበኝ፤ እዬሸሸህ ስትመጣብኝ፤ እዬቆዬህ ስታቆዬኝ፤ እዬመለሰክ ስትነኝ፤ እያፈቀርክ ስትምገኝ፤ እዬዳበስክ ስትናኝ፤ እያዋዛህ ስትኩለኝ፤ እዬምከኝ ስታዳጉስ አንተ ለእኔ ለህይወቴ የተቀናህ ነህ።

ነፍስ ሰጥተህ ነፍስ ሆነህ፤ ነፍስ ዘርትህ አቅል ሆነህ፤ ትንፋሽ ሰጥተህ መንፈስ ሆነህ፤ ጠረን ሆነህ መኖር ሆንከኝ።

ጸዳል ሆነህ ሥህ ብልህ፤ ጸደይ ሆነህ ቀለብ ሆነህ፤ በልግም ሆነህ ሰቅ ሸልመህ፤ አይ ሆነህ በህብርነት አቀለምከኝ
አንተ ለእኔ ሩቅ ሆነህ፤ አንተ ለእኔ ምኞት ሆነህ፤ አንተ ለእኔ መሆን ሆነህ ብርቱ ጽላት አንጓ ሆንከኝ።

ሆነህ በተምታ ተመስጥረህ፤ ስንዴ ሆነህ በሥንኝታ ተገስሰኽ፤ ቅኔም ሆነህ በቅኝትህ አስድመህ፤ ነቁጥም ሆነህ በተደሞ አሟሻሽተህ፤ ተስፋን በገፍ አንሰራፍተህ፤ እሱ በእሱ በድር ማጉ ሸማን ሰርትህ፤ ተኘኸው ሩኽ ሆነኽ፣ ብጽናትህ ህሊና አንር አሰርተኽ።

ንጡህ ደጉ አንተ የዋሁ መሰላሌን ዘርግተኸው፤ ሳታጣፋ መገናኛ ድልድይ ሆነህ ማጣፊያውን አረዘምከው። በአጭር ልቆጭ ስሰናዳ፣ ድልድይ ሰርትህ አመሳጠርክ።


መኖር ብይን አዋደድከው፤ ቀኑን ባርከህ አከበርከው፤ አንተ ለእኔ የሰጠኸው፣ ሁለመና ሁንትናን አሰብልከው።

ቢሆንልኝ ቢሳካልኝ ለወልድዬ ለትንሳኤው ውልኛውን ባለዋንጫ ባለማጫ ባለማተብ ከአሱ ጋራ ውል እንሰር፤ ኪዳን ገብተን ጽዋ ላዳር።

ማስተዋል የህሊና ጸጋ ነው!

ቅኖቹ የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።